ዩናይትድ ኪንግደም በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ ላይ የሚደረጉ የመርከቦች እንቅስቃሴን ለመጠበቅ በተዘጋጀ የጋራ ተልዕኮ ላይ ድሮኖችን፣ ተዋጊ ጄቶችን እና የጦር መርከብ እንደምታዋጣ አስታወቀች። ይህ የዩኬ ባሕር ኃይል ስምሪት የባሕር ውስጥ ፈንጂዎችን ለመለየት የሚረዳ መሣሪያን፣ ድሮን ጀልባዎችን እና የአየር ቅኝቶችን ለማድረግ የሚያግዙ የጦር ጄቶችን ያካተተ ይሆናል ተብሏል።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 42 ደቂቃዎች በፊትዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የገቡበትን ጦርነት ለማስቆም ቻይና እንደማታስፈልጋቸው ተናገሩየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Reutersየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የገቡበትን ጦርነት ለማስቆም የቻይናን እርዳታ እንደማይፈልጉ ተናገሩ።ፕሬዚዳንቱ ይህንን ያሉት ለሁለት ቀን ይፋዊ ጉብኝት ወደ ቻይና ከማምራታቸው አስቀድሞ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ ወቅት ነው።ቴህራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የምታደርገውን ቁጥጥር እያጠበቀች የመጣች ሲሆን በሁለቱ አገራት መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም የመፍረስ አደጋ ተጋርጦበታል።ወደ ቤይጂንግ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት እየሄዱ የሚገኙት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የገቡበትን ጦርነት ለመፍታት የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ድጋፍ ያስፍጋል ብለው እንደማያምኑ ተናግረዋል።የሆርሙዝ ወሽመጥ በመዘጋቱ የዓለም ነዳጅ ዘይት አቅርቦት እና ንግድ ተስተጓጉሏል።“ከኢራን ጋር ምንም ዓይነት እርዳታ ያስፍለጋል ብዬ አላስብም። በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ፣ በሰላማዊ መንገድም ሆነ በሌላ እናሸንፋለን” ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢራን በወሽመጡ ላይ ያላትን ቁጥጥር ያጠበቀች ሲሆን ከኢራቅ እና ከፓኪስታን ጋር ከቀጣናው ነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ማጓጓዝ እንዲችሉ መስማማቷን ምንጮች ተናግረዋል።ሮይተርስ ያነጋገራቸው ምንጮች ሌሎች አገራትም ተመሳሳይ ስምምነት ከኢራን ጋር ለመድረስ እየሞከሩ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን ይህም ቴህራን በመተላለፊያው ላይ ያላትን ቁጥጥር የበለጠ ያጠናክራል ብለዋል።ማክሰኞ ዕለት የትራምፕ አስተዳደር የአሜሪካ እና የቻይና ከፍተኛ ባለሥልጣናት ወደ ቀጣናው በወሽመጡ በኩል በሚደረግ ጉዞ ወቅት ምንም ዓይነት ቀረጥ እንዳይከፈል መስማማታቸውን ተናግሮ ነበር።ከቴህራን ጋር የቅርብ ግንኙነት ያላት ቻይና ከኢራን ነዳጅ ከሚገዙ ዋነኛ አገራት መካከል አንዷ ናት።ያጋሩ, ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የገቡበትን ጦርነት ለማስቆም ቻይና እንደማታስፈልጋቸው ተናገሩ
  2. ከ 1 ሰአት በፊትፕሬዝዳንት ትራምፕ ቬንዙዌላን ለመጠቅለል እያሰቡ መሆኑን ከተናገሩ በኋላ አገሪቱን ‘51ኛ የአሜሪካ ግዛት’ አድርጎ የሚያሳይ ምስል አጋሩየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ ማኅበራዊ የትስስር ገፅ ቬንዙዌላ በአሜሪካ ሰንደቅ ዓላማ ተሸፍና የሚያሳይ እና “51ኛ ግዛት” የሚል ጽሑፍ የያዘ ምስል አጋርተዋል።ይህ የፕሬዝዳንቱ ልጥፍ የመጣው አገሪቱን ለመጠቅለል እያሰቡ እንደሆነ ከገለፁ እና የቬንዙዌላ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ዴልሲ ሮድሪገዝ ሃሳቡን ውድቅ ካደረጉ ከአንድ ቀን በኋላ ነው።ሮድሪገዝ “የአገራችንን አንድነት፣ ሉዓላዊነት፣ ነፃነት፣ የአገራችን ወንዶች እና ሴቶች ነፃ አገር እንጂ ቅኝ ተገዢ እንዳንሆን ሕይወታቸውን የከፈሉበትን የክብር ታሪካችንን መከላከላችንን እንቀጥላለን” ብለዋል።የጊዜያዊ ፕሬዝዳንቷ አስተያየት የተሰማው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከፎክስ ኒውስ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ ቬንዙዌላን የአሜሪካ 51ኛ ግዛት ለማድረግ እያሰቡ እንደሆነ ከተናገሩ በኋላ ነው።የቬንዙዌላን የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ከካራከስ መኖሪያቸው ተይዘው ባለፈው ታኅሳስ መጨረሻ ወደ አሜሪካ ለፍርድ እንዲቀርቡ መደረጋቸውን ተከትሎ ትራምፕ ከአገሪቱ ጋር እየተግባቡ መሆኑ ሲነገር ቆይቷል።ትራምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ያጋሩት ምስልየፎቶው ባለመብት,Trump / Truth Socialያጋሩ, ፕሬዝዳንት ትራምፕ ቬንዙዌላን ለመጠቅለል እያሰቡ መሆኑን ከተናገሩ በኋላ አገሪቱን ‘51ኛ የአሜሪካ ግዛት’ አድርጎ የሚያሳይ ምስል አጋሩ
  3. ከ 1 ሰአት በፊትፔንታጎን የኢራን ጦርነት ስያሜን ‘ኦፕሬሽን ስሌጅሐመር’ በሚል ለመቀየር እያሰበ መሆኑን ኤንቢሲ ዘገበቴህራንየፎቶው ባለመብት,Reutersየአሜሪካ ጦር ከኢራን ጋር የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ፈርሶ ዘመቻው የሚቀጥል ከሆነ ስያሜውን ለመቀየር እያሰበ መሆኑን ኤንቢሲ ዘገበ።የአሜሪካ ባለሥልጣናት ዶናልድ ትራምፕ ጦርነቱ በድጋሜ እንዲጀመር የሚፈቅዱ ከሆነ የዘመቻው ስያሜ “ኦፕሬሽን ስሌጅሐመር” ተብሎ ሊቀየር እንደሚችል ተናግረዋል።አሜሪካ ኢራን ላይ ወታደራዊ ዘመቻዋን የካቲት 21 2018 ዓ.ም. ከእስራኤል አጋር በመሆን ስትጀምር “ኦፕሬሽን ኢፒክ ፊውሪ” ስትል ሰይማው ነበር።ለዘመቻው ኮንግረስ በ60 ቀናት ወስጥ ይሁንታውን ሊሰጥ ስላልቻለ ፔንታጎን በአዲስ ስያሜ ዳግም ጦርነቱን ለመጀመር እያሰበ መሆኑ ተገልጿል።የትራምፕ አስተደደር ኦፕሬሽን ኢፒክ ፊውሪ በይፋ ማብቃቱን ያስታወቀ ሲሆን በኢዝላማባድ አደራዳሪነት ከኢራን ጋር የሰላም ስምምነት ላይ ለመድረስ ጥረት እያደረገ ነው።ፔንታጎን ስለ ኢራን ጦርነት መግለጫ በሚሰጥበት ወቅት ‘ኦፕሬሽን ኢፒክ ፊውሪ’ እያለ የሚጠቀም ሲሆን አንድ የመስሪያ ቤቱ ባለሥልጣን የተኩስ አቁሙ ዋና ዋና ማጥቃቶችን ማስቆሙን ብቻ በመናገር ዘመቻው ቀጥሏል ብለዋል።ፔንታጎን በጉዳዩ ላይ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ አልሰጠም።የኢራን ጦረነት ዳግም የሚጀመር ከሆነ በአዲስ ስያሜ እንደሚሆን ጉዳዩን የሚያውቁ አንድ የዋይት ሐውስ ባለሥልጣን ተናግረዋል።ያጋሩ, ፔንታጎን የኢራን ጦርነት ስያሜን ‘ኦፕሬሽን ስሌጅሐመር’ በሚል ለመቀየር እያሰበ መሆኑን ኤንቢሲ ዘገበ
  4. ከ 2 ሰአት በፊትሊባኖስ በእስራኤል ጥቃት ሁለቱ የሕክምና ባለሙያዎች ጨምሮ 13 ሰዎች መገደላቸውን አስታወቀችሊባኖስ ላይ ጥቃት ሲፈፀምየፎቶው ባለመብት,EPAበእስራኤል እና የሊባኖስ ታጣቂ ቡድን በሆነው ሄዝቦላህ መካከል ግጭትን ማቆም ያላስቻለው የሰላም ስምምነት መክሸፉን ተከትሎ በደቡባዊ ሊባኖስ በእስራኤል አየር ጥቃት 13 ሰዎች መገደላቸውን አገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገበ።እንደ ሊባኖስ ብሔራዊ መገናኛ ብዙኃን ከሆነ በምሽቱ በአንድ ቤት ውስጥ በተፈፀመ ጥቃት ስድስት ሰዎች ሲገደሉ ሰባት ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።ማክሰኞ እለት የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር በእስራኤል ጥቃት ሁለት የሕክምና ባለሙያዎች መገደላቸውን እና ሦስተኛ ባለሙያ ደግሞ መቁሰሉን አስታውቋል።የእስራኤል ጦር ሪፖርቶችን እየተመለከተ መሆኑን ተናግሯል።የሊባኖስ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አውን በሕክምና ባለሙያዎቹ ግድያ ሐዘን እንደተሰማቸው ገልፀው፤ በእስራኤል የቀጠለው ጥቃት መረጋጋትን ለመመለስ ያለውን ጥረት የሚያደናቅፍ ነው ብለዋል።የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር እስራኤል የሕክምና ባለሙያዎችን ሆን ብላ ዒላማ እያደረገች ነው ሲል ከስሷል።ሚኒስቴሩ በጦርነቱ 108 የሊባኖስ የድንገተኛ አደጋ አገልግሎት ሰጪዎች እና የጤና ባለሙያዎች መገደላቸውን እና 140 እስራኤል ጥቃቶች በአንቡላንሶች እና የጤና ተቋማት ላይ መፈፀማቸውን አስታውቋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ ሄዝቦላህ በደቡባዊ ሊባኖስ እና ሰሜናዊ እስራኤል ባሉ አካባቢዎች ላይ በድሮን ጥቃት መፈፀሙን ተናግሯል።ባለፉት ጥቂት ቀናት የእስራኤል ጦር በደቡባዊ ሊባኖስ የሚፈጸመውን ጥቃት ጨምሯል።የእስራኤል እና ሊባኖስ ባለሥልጣናት ጦርነቱን ለማቆም ሐሙስ በዋሽንግተን ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።ያጋሩ, ሊባኖስ በእስራኤል ጥቃት ሁለቱ የሕክምና ባለሙያዎች ጨምሮ 13 ሰዎች መገደላቸውን አስታወቀች
  5. ከ 2 ሰአት በፊትትራምፕ የኢራንን የኒውክሌር ፕሮግራም ማስቆም ከአሜሪካውን የኢኮኖሚ ፈተና ይበልጣል አሉየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Reutersየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማክሰኞ ዕለት የአሜሪካውያን የፋይናንስ ችግር የኢራንን ጦርነትን ለማስቆም በሚያደርጉት የድርድር ውሳኔ ላይ ምክንያት አለመሆኑን ተናገሩ።ትራምፕ ቴህራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ እንዳይኖራት ማድረግ ቅድሚያ የሚሰጡት ጉዳይ መሆኑን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።ጋዜጠኞች አሜሪካውያን ጦርነቱን ተከትሎ እየደረሰባቸው ያለው የኢኮኖሚ ጫና ምን ያህል ከስምምነት እንዲደርሱ ግፊት እንደሚያደርግ ሲጠየቁ “ትንሽ እንኳን ተጽዕኖ” አያደርግም ብለዋል።ዶናልድ ትራምፕ ቅድሚያ የሚሰጡት ኢራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ እንዳይኖራት ማድረግ መሆኑን ተናግረው የአሜሪካውያን የፋይናንስ ችግር ጦርነቱን ከማቆም በሚያሳልፉት ውሳኔ ላይ ተጽዕኖ እንደማይኖረው ተናግረዋል።የፕሬዚዳንቱን አስተያየት እንዲያብራሩ የተጠየቁት የዋይት ሐውስ ኮሙኑኬሽን ዳይሬክተር ስቲቭን ቺዩንግ ትራምፕ “ዋነኛ ኃላፊነታቸው የአሜሪካኖች ሰላም እና ደህንነት ነው። ኢራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ሊኖራት አይችልም፤ እርምጃ የማይወሰድ ከሆነ እስካሁን ይኖራቸው እና አሜሪካውያንን ያስፈራሩ ነበር” ብለዋል።አሜሪካ እና እስራኤል ቴህራን ላይ ጦርነት ከከፈቱ በኋላ በዩናይትድ ስቴትስ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ እና የዋጋ ግሽበት ታይቷል።ያጋሩ, ትራምፕ የኢራንን የኒውክሌር ፕሮግራም ማስቆም ከአሜሪካውን የኢኮኖሚ ፈተና ይበልጣል አሉ
  6. ከ 5 ሰአት በፊትሳዑዲ አረቢያ በኢራን ጦርነት ወቅት ምስጢራዊ ጥቃቶችን መፈጸሟን ሮይተርስ ዘገበየሳዑዲ አረቢያ ተዋጊ ጄትየፎቶው ባለመብት,Katsuhiko Tokunagaሳዑዲ አረቢያ በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ወቅት ይፋ ያልሆኑ በርካታ ጥቃቶችን ኢራን ላይ መፈጸሟን ሁለት ምዕራባውያን እና ሁለት የኢራን ባለሥልጣናትን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘገበ።ሳዑዲ አረቢያ የአየር ድብደባዎቹን የፈጸመችው ለኢራን ጥቃቶች ምላሽ ለመስጠት ነው ተብሏል።የሳዑዲ ወታደራዊ እርምጃ ከዚህ በፊት ያልተሰማ ሲሆን ኢራን ላይ በቀጥታ ጥቃት መፈጸሟ በይፋ የታወቀው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።የሳዑዲ አየር ኃይል ጥቃቱን የፈጸመው በመጋቢት ወር መጨረሻ አካባቢ መሆኑ ሁለት የምዕራባውያን ምንጮች ለሮይተርስ ተናግረዋል።ሳዑዲ ኢራን ለፈጸመቻቸው ጥቃቶች ምላሽ ለመስጠት ድብደባዎቹን ማካሄዷን ጨምረው ተናግረዋል።ሮይተርስ ሳዑዲ አረቢያ ዒላማ ያደረገቻቸው የኢራን ስፍራዎች የትኞቹ እንደሆኑ ማረጋገጥ አልቻለም።የሳዑዲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሥልጣን ስለጉዳዩ ተጠይቀው በቀጥታ አገራቸው ጥቃት ስለመፈጸሟ ከመናገር ተቆጥበዋል።ሮይተርስ የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ቢጠይቅም ምላሽ ማግኘት አልቻለም።ሳዑዲ አረቢያ ከአሜሪካ ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያላት ሲሆን ከዚህ ቀደም የዩኤስ ወታደራዊ ከለላ ላይ ትተማመን ነበር።ነገር ግን 10 ሳምንት በቆየው የኢራን ጦርነት ወቅት ለጥቃቶች የበለጠ ተጋላጭ መሆኗን አሳይቷል።የሳዑዲ ጥቃት በመካከለኛው ምሥራቅ ግጭት መስፋፋቱን አሳይቷል። አሜሪካ እና እስራኤል የካቲት 21 2018 ዓ.ም. የጀመሩት ጦርነቱ ለሕዝብ ይፋ ባይደረግም በርካታ አገራትን ማሳተፉን አመላክቷል።ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ኢራን ስድስት የባሕረ ሰላጤው አገራት ላይ የሚሳዔል እና የድሮኖች ጥቃት ፈጽማለች።በአሜሪካ ጦር ሠፈሮች፣ በአውሮፕላን ማረፊያዎች፣ በነዳጅ መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃቶችን ከመፈጸም አልፋ የሆርሙዝ ወሽመጥን በመዝጋት የዓለም ንግድ እንዲስተጓጎል አድርጋለች።ሰኞ ዕለት ዎል ስትሪት ጆርናል እንደዘገበው ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ ቴህራን ላይ ጥቃት ፈጽማለች። የሳዑዲ እና የኤሜሬትስ በጦርነቱ ውስጥ መሳተፍ የግጭቱ ትክክለኛ መልክ የተደበቀ መሆኑን አጋልጧል።ዩኤኢ ቴህራን ለድርጊቷ ተገቢውን ዋጋ እንድትከፍል የሚል ጠንካራ አቋም ያላት ሲሆን ውስን ዲፕሎማሲያዊ ውይይቶችን ከኢራን ጋር አካሄዳለች።አንድ የሳዑዲ ከፍተኛ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሥልጣን ከኢራን ጋር ጦርነቱን የማርገብ ስምምነት ተደርሶ እንደሆን ተጠይቀው ሳይመልሱ ቀርተዋል።ነገር ግን “ሳዑዲ አረቢያ ለቀጣናው መረጋጋት፣ ደህንነት፣ ብልጽግና እና ለሕዘብ ደህንንት በሚል ውጥረትን በመቀነስ ላይ ያለንን የማያቋረጥ አቋም ላረጋግጥ እችላለሁ” ብለዋል።ለሮይተርስ መረጃውን የሰጡ የኢራን እና ምዕራባውያን ባለሥልጣናት ሳዑዲ አረቢያ ጥቃት እንደምትፈጸም ቴህራን እንድታውቅ ተደርጓል ብለዋል።ያጋሩ, ሳዑዲ አረቢያ በኢራን ጦርነት ወቅት ምስጢራዊ ጥቃቶችን መፈጸሟን ሮይተርስ ዘገበ
  7. ከ 5 ሰአት በፊትዩኬ የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥን ለመከላከል ጄቶችን፣ ድሮኖችን እና የጦር መርከቦችን እንደምትልክ አስታወቀችወደ መካከለኛው ምሥራቅ እየሄደ ያለው የአየር መቃወሚያ የተገጠመለት ኤችኤምኤስ ድራጎን መርከብየፎቶው ባለመብት,PA Mediaየምስሉ መግለጫ,ወደ መካከለኛው ምሥራቅ እየሄደ ያለው የአየር መቃወሚያ የተገጠመለት ኤችኤምኤስ ድራጎን መርከብዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ ላይ የሚደረጉ የመርከቦች እንቅስቃሴን ለመጠበቅ በተዘጋጀ የጋራ ተልዕኮ ላይ ድሮኖችን፣ ተዋጊ ጄቶችን እና የጦር መርከብ እንደምታዋጣ አስታወቀች።የመከላከያ ሚኒስትሩ ጆን ሄሊ ማክሰኞ ዕለት በተካሄደው የመከላከያ ሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ዩኬ የምታደርገውን ድጋፍ ይፋ አድርገዋል።ይህ የዩኬ ባሕር ኃይል ስምሪት የባሕር ውስጥ ፈንጂዎችን ለመለየት የሚረዳ መሣሪያን፣ ድሮን ጀልባዎችን ​​እና የአየር ቅኝቶችን ለማድረግ የሚያግዙ የጦር ጄቶችን ያካተተ ይሆናል ተብሏል።ሁኔታዎች ሲፈቅዱ ይጀመራል በተባለው በዚህ የሆርሙዝ መተላለፊያን ለመጠበቅ በሚደረገው ተልዕኮ ውስጥ ከ40 በላይ አገራት ይሳተፋሉ።ኢራን ለአሜሪካ እና ለእስራኤል ጥቃቶች አጸፋ በዓለም ላይ ከፍተኛ የመርከቦች እንቅስቃሴ ከሚደረግባቸው መስመሮች አንዱ የሆነውን የሆርሙዝ ወሽመጥን ለወራት ዘግታ ቆይታለች።አሜሪካ በበኩሏ በቴህራን ላይ ምጣኔ ሀብታዊ ጫና በማሳደር ወደ ድርድር ጠረጴዛ እንድትመጣ ለማድረግ በሚል ወደ ኢራን ወደቦች የሚገቡም ሆነ የሚወጡ መርከቦችን ላይ ዕገዳ ጥላለች።በዓለም ላይ 20 በመቶ የሚሆነው የነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ መተላለፊያ የሆነው ይህ የባሕር መስመር በመዘጋቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ ጨምሯል።ከሚያዝያ ወር ጀምሮ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተኩስ አቁም የተደረሰ ቢሆንም ሁለቱ አገራት ጦርነቱን ሊያስቆም ወደሚችል የሰላም ስምምነት መድረስ ባለመቻላቸው ትራምፕ ስምምነቱ “በቋፍ ላይ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።በወሽመጡ ላይ አንዳቸው ሌላኛቸውን ጥቃት በመክፈት ይካስሳሉ።በአሁኑ ወቅት በመካከለኛው ምሥራቅ ከ1000 በላይ የዩኬ ወታደሮች የሚገኙ ሲሆን፣ ይህም የፀረ ድሮን እና የፈጣን የውጊያ ጄቶች ቡድኖችን አንደሚያካትት ሚኒስትሩ ተናግረዋል።የመከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ባለፈው ወር በዩኬ እና በፈረንሳይ ይፋ የተደረገው ዓለም አቀፍ ተልዕኮ በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ ላይ የንግድ መርከቦችን እንቅስቃሴን ወደነበረበት ለመመለስ ያለመ ነው።ይህ የአገራቱ ስምሪት ፈንጂ ለመለየት የሚያገለግሉ ድሮኖች እና ፀረ-ድሮን ሥርዓቶችን ለማዘጋጀት 115 ሚሊዮን ፓውንድ የገንዘብ ድጋፍ እንደተደረገለት አስታውቀዋል።”ከአጋሮቻችን ጋር፣ ይህ ዓለም አቀፍ ተልዕኮ የመከላከል፣ ገለልተኛ እና ተዓማኒነት ያለው ይሆናል” ሲሉ ሄሊ ተናግረዋል።በእቅዱ መሠረት ወደ መካከለኛው ምሥራቅ እየሄደ ያለው የአየር መቃወሚያ የተገጠመለት ኤችኤምኤስ ድራጎን መርከብ እንዲሁ የባሕር ወሽመጥን በመጠበቅ “ማንኛውም ተልዕኮ ዝግጁ ይሆናል” ሲል የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።በተጨማሪምሌላ የብሪታንያ መርከብ የሆነው አርኤፍኤ ላይም ቤይ በባሕረ ሰላጤው ውስጥ ለሚደረጉ ሥራዎች አስፈላጊ ከሆነ በአዲስ መሳሪያዎች ማሻሻያ ማድረጉን ቀጥሏል።ያጋሩ, ዩኬ የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥን ለመከላከል ጄቶችን፣ ድሮኖችን እና የጦር መርከቦችን እንደምትልክ አስታወቀች
  8. 12 ግንቦት 2026አሜሪካ በኢራን ጦርነት እስካሁን 29 ቢሊዮን ዶላር ማውጣቷን ፔንታጎን አስታወቀአሜሪካ እና እስራኤል በቴህራን በፈጸሙት የአየር ድብደባ የወደመ የንግድ ሕንጻየፎቶው ባለመብት,Reutersአሜሪካ በኢራን በምታካሄደው ጦርነት እስካሁን ድረስ 29 ቢሊዮን ዶላር ማውጣቷን አንድ ከፍተኛ የፔንታጎን ባለሥልጣን ማክሰኞ ዕለት አስታወቁ።ፔንታጎን አሁን ይፋ ያደረገው የገንዘብ መጠን ባለፈው ወር ከገመተው የ4 ቢሊዮን ብልጫ አሳይቷል።ዲሞክራቶች ከስድስት ወር በኋላ ለሚካሄደው ምርጫ ድጋፍ እያገኙ ሲሆን ጦርነቱ የኑሮ ውድነትን አንሯል ሲሉ ጣታቸውን በሪፐብሊካኑ ፕሬዚዳንት ላይ ቀስረዋል።ታዛቢዎች በምርጫው ሪፐብሊካኖች አብላጫውን የኮንግረስ ወንበር ሊያጡ ይችላሉ ሲሉ ተንብየዋል።ፔንታጎን ሚያዚያ 21 2018 ዓ.ም. በኢራን ጦርነት 25 ቢሊዮን ዶላር ማውጣቱን ይፋ አድርጎ ነበር።የበጀት ጉዳዮችን የሚከታተሉት ጁለስ ሀርስት ለሕግ አውጪዎቹ አዲሱ የገንዘብ መጠን ጥገናን እና የምትክ መሣሪያዎችን እንዲሁም የሥራ ማስኬጃ ወጪዎችን የሚያካትት መሆኑን ተናግረዋል።ከመከላከያ ሚኒስትሩ ፒት ሄግሴት እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ዳን ኬይን ጋር በመሆን ለምክር ቤት አባላት ሪፖርቱን ያቀረቡት ሃርስት “የበጀት እና የመከላከያ ቡድኖች በጋራ ጦርነቱ ምን ያህል እንደሚያስወጣ በቋሚነት ያሰላሉ” ብለዋል።ፔንታጎን በጀቱን 29 ቢሊዮን ዶላር አንዴት እንዳደረሰው ግልጽ አይደለም።በመጋቢት ወር ለሮይተርስ መረጃ የሰጡ አንድ ምንጭ የትራምፕ አስተዳደር በጦርነቱ የመጀመርያ ስድስት ቀናት ብቻ 11̄.3 ቢሊዮን ዶላር ማውጣቱን ገምቷል።ያጋሩ, አሜሪካ በኢራን ጦርነት እስካሁን 29 ቢሊዮን ዶላር ማውጣቷን ፔንታጎን አስታወቀ
  9. 12 ግንቦት 2026ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጋር ወደ ቻይና የ17 የአሜሪካ ግዙፍ ኩባንያ ኃላፊዎች እንደሚጓዙ ተገለጸከትራምፕ ጋር ወደ ቻይና ከሚሄዱት መካከል የቴስላ ባለቤት ኤለን መስክ እና የአፕል ኃላፊው ቲም ኩክ እንደሚገኙበት ታውቋልየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ከትራምፕ ጋር ወደ ቻይና ከሚሄዱት መካከል የቴስላ ባለቤት ኤለን መስክ እና የአፕል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቲም ኩክ እንደሚገኙበት ታውቋልየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ቻይና ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሲያመሩ የ17 የአሜሪካ ግዙፍ ኩባንያ ኃላፊዎች አብረዋቸው እንደሚሄዱ ዋይት ሐውስ አስታወቀ።ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር በጀመሩት ጦርነት ምክንያት አራዝመውት የነበረውን የቻይና ጉብኝታቸውን የፊታችን ሐሙስ እና አርብ ዕለት ያካሄዳሉ።ከትራምፕ ጋር ወደ ቻይና ከሚሄዱት መካከል የቴስላ ባለቤት ኤለን መስክ እና የአፕል ኃላፊው ቲም ኩክ እንደሚገኙበት ታውቋል።የአሜሪካው ፕሬዚዳንት በዚህ ሳምንት በቻይና በሚያደርጉት ጉብኝት ወቅት አብረዋቸው ከሚሄዱት ከፍተኛ የንግድ እና የቴክኖሎጂ ባለቤቶች መካከል የአፕሉ ሥራ አስፈጻሚ ቲም ኩክ እና የቴስላ እና ስፔስ ኤክስ ባለቤቱ ኤለን መስክ እንዲሁም የሜታ፣ ቪሳ፣ ጄፒ ሞርጋን፣ ቦይንግ፣ ካርጊል፣ ብላክ ሮክ ኃላፊዎች ይገኙበታል ብሏል።ፕሬዚዳንት ትራምፕ በዚህ ጉብኝታቸው ከቻይናው አቻቸው ዢ ጂንፒንግ ጋር በመገናኘት ኢራንን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።ከአስርት ዓመታት በኋላ አንድ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ወደ ቻይና ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሲያደርግ ትራምፕ የመጀመርያው ናቸው።ጉብኝት በሁለቱ አገራት መካከል እየተካሄደ ያለውን የንግድ ጦርነት ያረግባል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።ትራምፕ ወደ ቻእና ለማቅናት አቅደው የነበረው እአአ መጋቢት 31 ሲሆን፣ የካቲት 21 2018 ዓ.ም. አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ከፈፀሙ በኋላ ዘግይቷል።በምላሹም ኢራን በባህረ ሰላጤው ውስጥ የእስራኤልንና የአሜሪካ አጋር አገሮችን በማጥቃት ለዓለም የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ዝውውር ቁልፍ የሆነውን የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥን በመዝጋቷ ዓለም አቀፍ የነዳጅ ቀውስ ተፈጥሯል።ትራምፕ በኢራን ነዳጅ ዘይት ላይ ጥገኛ የሆነችው ቻይናን ጦርነቱን ለማስቆም የሚያስችል ስምምነት ላይ እንዲደረስ ጫና እንድታደርግ ይጠይቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።ቻይና በኢራን ጦርነት ምክንያት የምታስቀባው የነዳጅ አቅርቦት በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ ሲሆን ጦርነቱ እንዲያበቃ በብርቱ ትፈልጋለች።ቻይና ከፍተኛ የሆነ የነዳጅ ክምችት እና የተለያዩ የኤነርጂ አቅርቦት አማራጮች አሏት።ትራምፕ በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ ዢን ጂንፒንግን በዋሽንግተን ዲሲ ተቀብለው ለማስተናገድ ቀጠሮ ይዘዋል።ያጋሩ, ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጋር ወደ ቻይና የ17 የአሜሪካ ግዙፍ ኩባንያ ኃላፊዎች እንደሚጓዙ ተገለጸ
  10. 12 ግንቦት 2026በኢራን ጦርነት ወቅት እስራኤል ለዩኤኢ የመሣሪያ እና የባለሙያ ድጋፍ ማድረጓን የአሜሪካ አምባሳደር ተናገሩአይረን ዶም ሚሳኤል የተተኮሰ ሮኬትን ሲያከሽፍየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,አይረን ዶም ሚሳኤል የተተኮሰ ሮኬትን ሲያከሽፍበእስራኤል የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ማይክ ሃክቢ ማክሰኞ ዕለት በኢራን ጦርነት ወቅት እስራኤል ወደ ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ ሚሳዔሎችን ለመከላከል የሚያገለግለው ‘አይረንዶም’ ባትሪዎችን እና ባለሙያዎችን መላኳን ተናገሩ።ማይክ ሃክቢ ይህንን ያሉት በቴልአቪቭ በተዘጋጀ አንድ መድረክ ላይ መሆኑን ሲቢኤስ ዘግቧል።”ለመጀመሪያዋ የአብርሃም ስምምነት አባል ለተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ምስጋናዬን ማቅረብ እፈልጋለሁ” ያሉት ሃካቢ “ጥቅሙን ተመልከቱ። እስራኤል የአይረን ዶም ባትሪዎች እና ማንቀሳቀስ እንዲችሉ ባለሙያዎችን ልካላቸዋለች” ሲሉ ተናግረዋል።ማይክ ሃክቢ እስራኤል ላከች ስላሉት መሣሪያም ሆነ ባለሙያዎች እስካሁን ድረስ አቡ ዳቢ ማረጋገጫም ሆነ ማስተባበያ አልሰጠችም።እስራኤል በዓለም ላይ ውጤታማነታቸው የተፈተኑ ናቸው ተብለው የሚታመኑ የሚሳዔል ጥቃት የመከላከያ ሥርዓት ያላት አገር ናት።ከእስራኤል የሚሳኤል ጋሻዎች መካከል በጣም የሚታወቀው “አይረን ዶም” ሲሆን፣ የአጭር ርቀት ሮኬቶችን ለመከላከል የሚያስችል ነው። ይህ መሳሪያ ሞርታሮችን እና ከሚሳዔል ማስወንጨፊያ የሚተኮሱ ከአራት እስከ 70 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚጓዙትን ያከሽፋል።የኢራን ጦርነት በየካቲት ወር መጨረሻ ላይ ከተጀመረ በኋላ ቴህራን በባሕረ ሰላጤው በሚገኙ የእስራኤል እና የአሜሪካ አጋሮች ላይ ጥቃት ስትከፍት የሆርሙዝ ወሽመጥንም ዘግታለች።በጦርነቱ የተነሳ በኢራን ከ3300 በላይ ሰዎች ሲገደሉ በሺህዎች የመቆጠሩ ደግሞ ተፈናቅለዋል። ከዚህም በተጨማሪ 13 የአሜሪካ ወታደሮችም ሲገደሉ በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል።በፓኪስታን አደራዳሪነት በኢራን እና በአሜሪካ መካከል የተኩስ አቁም ቢደረስም ኢዝላማባድ እስካሁን ድረስ ዘላቂ ሰላም በሁለቱ አገራት መካከል እንዲደረስ ማድረግ አልቻለችም።ያጋሩ, በኢራን ጦርነት ወቅት እስራኤል ለዩኤኢ የመሣሪያ እና የባለሙያ ድጋፍ ማድረጓን የአሜሪካ አምባሳደር ተናገሩ
  11. 12 ግንቦት 2026የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆርሙዝን “እንደ ጦር መሣሪያ” መጠቀም እንደማይገባ አስጠነቀቁየቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳንየፎቶው ባለመብት,Anadoluየምስሉ መግለጫ,የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳንየቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን ማክሰኞ ዕለት ለቀጣናዊ መረጋጋትም ሆነ ለዓለም አቀፉ ምጣኔ ኃብት ሲባል ሆርሙዝን እንደ ጦር መሣሪያ መጠቀም እንደማይገባ አስጠነቀቁ።ፊዳን ከኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሀመድ ቢን አብዱራህማን ቢን ጃሲም አልታኒ ጋር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ “በባህረ ሰላጤው ላይ እያጋጠመን ያለው ችግር በምንም መልኩ የጋዛ ጉዳይ እንዲረሳ ሊያደርገው አይገባም” ብለዋል።ፊዳን የእስራኤል ተስፋፊነት በቀጣናው “መረጋጋት እና ደህንነት ላይ” ዋነኛ ስጋት ሆኗል ብለዋል።በኢራን ላይ የተካሄደው ጦርነት የዓለም የኢነርጂ እና የሸቀጦችን ገበያ አውኳል። አገሪቱ ለነዳጅ ጭነት ወሳኝ የሆነውን የሆርሙዝ ወሽመጥን መዝጋት ብቻ ሳይሆን ለማለፍ የሞከሩ ነዳጅ ጫን መርከቦች ላይ ጥቃት ፈጽማለች።ዶናልድ ትራምፕ በአውሮፓ የሚገኙ የአሜሪካ አጋሮች የባሕር ወሽመጡን እንዲጠብቁ ጫና ለማሳደር ቢሞክሩም እስካሁን ድረስ አልተሳካላቸውም።አሜሪካ የሆርሙዝ ወሽመጥን እንደገና ለመክፈት የምታደርገውን ጥረት ካልደገፉ “የኔቶ የወደፊት ዕጣ ፈንታ በጣም መጥፎ” እንደሚሆን አስጠንቅቀው ነበር።በባሕረ ሰላጤው የተፈጠረው የመርከብ ጉዞ መስተጓጎል የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ከፍ እንዲል አድርጓል።ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት አንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ከነበረበት ከ70 የአሜሪካ ዶላር አሁን ከ100 የአሜሪካ ዶላር በላይ እንዲደርስ አድርጓል።ያጋሩ, የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆርሙዝን “እንደ ጦር መሣሪያ” መጠቀም እንደማይገባ አስጠነቀቁ
  12. 12 ግንቦት 2026ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ሰፊ ወታደራዊ ቀጣና አድርጋ እንደምትመለከተው አብዮታዊ ዘቡ አስታወቀየባሕር ወሽመጡ ላይ የሚንቀሳቀሱ አነስተኛ ጀልባዎችየፎቶው ባለመብት,Reutersኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ከጦርነቱ በፊት ከነበረው በተለየ ሰፊ ወታደራዊ ቀጣና አድርጋ እንደምትመለከተው አስታወቀች።የአብዮታዊ ዘቡ ባሕር ኃይል ከፍተኛ ባለሥልጣን ወሽመጡን ከዚህ በፊት ከነበረው ጠባብ መተላላፊያ በተለየ “ሰፊ ወታደራዊ ቀጣና” አድርገው እንደሚመለከቱት ተናግረዋል።ከአሁን በኋላ ወሽመጡ በጥቂት ደሴቶች ብቻ የሚወሰን ሳይሆን ከወታደራዊ ጠቀሜታ አንጻር ሰፋ ተደርጎ እንደሚታይ የአብዮታዊ ዘቡ ባሕር ኃይል የፖለቲካ ምክትል ዳይሬክተር ሞሐማድ አክባርዛዴህ ለፋርስ የዜና ወኪል ተናግረዋል።ምክትል ዳይሬክተሩ ማክሰኞ ዕለት ለዜና ወኪሉ “ከዚህ ቀደም የሆርሙዝ ወሽመጥ በሆርሙዝ እና ሄንጋም ደሴቶች አካባቢ ያለ ጠባብ ስፍራ ተደርጎ ይታይ ነበር። አሁን ግን ይህ እይታ ተቀይሯል” ብለዋል።ሮይተርስ የኢራን ባለሥልጣናት በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ አልሰጡም።የዓለም አንድ አምስተኛ የነዳጅ ዘይት እና የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦት የሚተላለፍበት የሆርሙዝ ወሽመጥ ወደ ባሕረ ሰላጤው አገራት ለመግባት እንዲሁም ሳዑዲ አረቢያ፣ ኢራን እና ኳታር ምርቶቻቸውን ወደ ውጭ የሚልኩበት ዋነኛ መስመር ነው።አክባርዛዴህ ወሽመጡ አሁን ስትራቴጂካዊ ቀጣና ተብሎ የሚበየን መሆኑን ተናግረው በምሥራቅ በሲሪ ደሴት ከምትገኘው ጃስክ ከተማ እስከ ደሴቲቱ ደቡባዊ ክፍል ድረስ የሚሸፍን “ሰፊ ወታደራዊ አካባቢ” መሆኑን ተናግረዋል።አሜሪካ እና እስራኤል ጦርነት ካወጁ ወዲህ የሆርሙዝ ወሽመጥ ሰፊ አካባቢን አንደሚያካልል ሲገለጽ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው።ግንቦት አራት የአብዮታዊ ዘቡ ባጋራው ካርታ ወሽመጡ እስከ የኦማን ባሕረ ሰላጤ ድረስ እንደሚሰፋ ያሳያል።ፋርስ እና ታስኒም የዜና ወኪሎች ማክሰኞ ዕለት የወሽመጡ ስፋት ከዚህ ቀደም ከ20 እስከ 30 ማይል ይገመት እንደነበር ጠቅሰው አሁን ግን ወደ 200 እና 300 ማይልስ ማደጉን ዘግበዋል።ታስኒም አክሎም የተጨመረው ቀጣና “የግማሽ ጨረቃ ቅርጽ” ይፈጥራል ሲል ዘግቧል።ያጋሩ, ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ሰፊ ወታደራዊ ቀጣና አድርጋ እንደምትመለከተው አብዮታዊ ዘቡ አስታወቀ
  13. 12 ግንቦት 2026አሜሪካ እና ኢራን የሰላም ዕቅድ ላይ ስላልተስማሙ የነዳጅ ዋጋ ጨመረየነዳጅ ማውጫ መሣሪያየፎቶው ባለመብት,Reutersአሜሪካ እና ኢራን በሰላም ዕቅድ ላይ ባለመስማማታቸው የነዳጅ ዋጋ ሁለት በመቶ መጨመሩን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘገበ።ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ላይ የሁለት ዶላር ጭማሪ ተደርጎ ዋጋው 106.21 ዶላር ደርሷል። የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋቱን ተከትሎ የነዳጅ ሽያጭ ቀንሷል።ነዳጅን ለውጭ ገበያ የሚያቀርቡ አገራት ማኅበር እንዳለው፤ በሁለት አሥርት ዓመታት ባልታየ ሁኔታ ባለፈው ሚያዝያ ወር ከፍተኛ የምርት መቀነስ ተስተውሏል።የነዳጅ ገበያው እስከ አውሮፓውያኑ 2027 ድረስ መረጋጋት ሳይታይበት ሊቆይ እንደሚችል የሳዑዲው አራምኮ ፕሬዝዳንት አሚን ናስር አስጠንቅቀዋል።የነዳጅ ምርት በአንድ ሳምንት ውስጥ እስከ 100 ሚሊዮን በርሜል መቀነሱ ተገልጿል።በሌላ በኩል የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው አቻቸው ዢ ዢፒንግ ጋር የሚያደርጉትን ውይይት የነዳጅ ነጋዴዎች በንቃት እየተከታተሉ ነው።የአሜሪካ ግምጃ ቤት የኢራንን ነዳጅ ለቻይና የሸጡ ወይም ያዘዋወሩ ናቸው ባላቸው 12 ግለሰቦች እና ተቋማት ላይ ማዕቀብ መጣሉን አስታውቋል።ያጋሩ, አሜሪካ እና ኢራን የሰላም ዕቅድ ላይ ስላልተስማሙ የነዳጅ ዋጋ ጨመረ
  14. 12 ግንቦት 2026ትራምፕ በኢራን ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት በድጋሚ ለመክፈት ማሰባቸው ተዘገበዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት በድጋሚ ለመጀመር “አጥብቀው ማሰባቸውን” ሲኤንኤን ዘገበ።ሲኤንኤን ምንጮቹን ጠቅሶ ባወጣው ዘገባ መሠረት፤ ኢራናውያን ድርድሩን የያዙበት መንገድ አስቆጥቷቸዋል።ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሁለት ምንጮች እንደገለጹት ትራምፕ በሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት እና በኢራናውያን ባለሥልጣናት መከፋፈል “ትዕግስታቸው እየተሟጠጠ ነው።በኢራናውያን ባለሥልጣናት መካከል ያለው ክፍፍል ኒውክሌርን በተመለከተ የሚደረገው ንግግር ውጤታማ እንዳይሆን ማድረጉ ተጠቁሟል።ትራምፕ ኢራን የሰጠችውን ምላሽ “ፈጽሞ ተቀባነት የሌለው” ብለው አጣጥለዋል። አሜሪካ በቀጣይ የምትወስደውን እርምጃ በተመለከተ በዋሽንግተን ባለሥልጣናት ውስጥ የተለያየ አቋም መወሰዱን የሲኤንኤን ምንጮች ጠቁመዋል።የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ኢራን ላይ ጫና ለማሳደር ዒላማዎችን ለይቶ ጥቃት መሰንዘርን እንደ አማራጭ እንደሚወስድ ተገልጿል። በሌላ በኩል ለድርድር ዕድል የመስጠት ፍላጎት ያላቸውም እንዳሉ ተጠቅሷል።ያጋሩ, ትራምፕ በኢራን ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት በድጋሚ ለመክፈት ማሰባቸው ተዘገበ
  15. 12 ግንቦት 2026ኢራን ጥቃት ከደረሰባት መሣሪያ መገንባት በሚያስችል መጠን ዩራኒየም ለማበልጸግ ዛተችኢራን በድጋሚ ጥቃት የሚፈጸምባት ከሆነ መሣሪያ ለመገንባት በሚያስችል የጥራት መጠን ዩራኒየም ማበልጸግ እንደምትጀምር ማስታወቋን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘገበ።በኢራን ምክር ቤት ንግግር ያደረጉት የብሔራዊ ደኅንነት እና የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ቃል አቀባይ ኢብራሒም ራይዚ፤ ኢራን ጥቃት ከደረሰባት ዩራኒየም በ90 በመቶ ደረጃ እንደምታበለጽግ አስታውቀዋል።ቃል አቀባዩ በኤክስ ገጻቸው “ኢራን ሌላ ጥቃት ከተፈጸመባት እስከ 90 በመቶ ማበልጸግን አንድ አማራጭ አድርጋ ትወስዳለች። ጉዳዩን በምክር ቤት እንወያይበታለን” ብለዋል።ያጋሩ, ኢራን ጥቃት ከደረሰባት መሣሪያ መገንባት በሚያስችል መጠን ዩራኒየም ለማበልጸግ ዛተች
  16. 12 ግንቦት 2026የኢራንን ነዳጅ ለቻይና ሸጠዋል የተባሉ 12 ግለሰቦች እና ተቋማት በአሜሪካ ማዕቀብ ተጣለባቸውየአሜሪካ ግምጃ ቤት የኢራንን ነዳጅ ለቻይና የሸጡ ወይም ያዘዋወሩ ናቸው ባላቸው 12 ግለሰቦች እና ተቋማት ላይ ማዕቀብ መጣሉን አስታወቀ።የኢራን አብዮታዊ ዘብ በፈጠራቸው ወረቀት ላይ ብቻ የሚገኙ ኩባንያዎች (shell companies) አማካኝነት በድብቅ የነዳጅ ሽያጭ እንደሚያከናውን ተገልጿል።ብዙም ቁጥጥር በማይደረግባቸው ዘርፎች ውስጥ የሚፈጠሩት እነዚህ የይስሙላ ኩባንያዎች ነዳጅ እየሸጡ ለኢራን መንግሥት ገቢ እንደሚያስገኙ የአሜሪካ ግምጃ ቤት አስታውቋል።ከነዳጅ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ለጦር መሣሪያ ምርት እና ኢራንን በእጅ አዙር ለሚደግፉ የውጭ አገራት ቡድኖች እንደሚውል ገልጿል።የአሜሪካ የግምጃ ቤት ጸሐፊ ስኮት ቤሴት “የኢራን ወታደራዊ ኃይሎች አቅማቸውን ለመገንባት እየሞከሩ ነው። እኛም የምጣኔ ሃብት ጫና ማሳደር እንቀጥላለን” ሲሉ በኤክስ ገጻቸው ጽፈዋል።“የኢራን መንግሥት የፋይናንስ ምንጮችን እንዘጋለን። የሽብር ድርጊቶችን በመደገፍ ዓለም አቀፍ ምጣኔ ሃብትን የሚያናጉበትን ትስስርም እንበጣጥሳለን” ሲሉም አክለዋል።ያጋሩ, የኢራንን ነዳጅ ለቻይና ሸጠዋል የተባሉ 12 ግለሰቦች እና ተቋማት በአሜሪካ ማዕቀብ ተጣለባቸው
  17. 12 ግንቦት 2026“የኢራናውያንን መብት ከማክበር ውጪ አሜሪካ ሌላ አማራጭ የላትም” አፈ ጉባኤ ጋሊባፍሞሐመድ ባጊር ጋሊባፍየምስሉ መግለጫ,አፈ ጉባኤ ሞሐመድ ባጊር ጋሊባፍከስምምነት ላይ ለመድረስ አሜሪካ የኢራናውያንን መብት ከማክበር ውጪ ሌላ አማራጭ የላትም ሲሉ በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ተሰሚነት ያላቸው የኢራን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ገለጹ።አፈ ጉባኤው መሐመድ ባጊር ጋሊባፍ ለፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተያየት ምላሽ በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ እንዳሉት ኢራን ጦርነቱን ለማስቆም ባቀረበችው “ባለ14 ነጥብ ሃሳብ ላይ እንደተቀመጠው የኢራናውያንን መብቶች ከማክበር ውጪ ሌላ ምንም አማራጭ የለም” ብለዋል።ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጦርነቱን ለማስቆም ከኢራን በኩል በተሰጠው ምላሽ ደስተኛ አለመሆናቸውን በተመለከተ ሰኞ ዕለት የተኩስ አቁሙ “በቋፍ ላይ” መሆኑን ከተናገሩ በኋላ ነው አፈ ጉባኤው በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የአገራቸውን አቋም ያስታወቁት።ጋሊባፍ በኤክስ ገጻቸው ላይ በእንግሊዝኛ እንደጻፉት “ሌላ የትኛውም መንገድ ተከታታይ ውድቀትን ከማስከተል ውጪ ምንም ዓይነት ውጤትን አያስገኝም። ነገሩ እየተራዘመ ሲሄድ ከአሜሪካውያን ታክስ ከፋዮች ኪስ የሚወጣውን ወጪን ይጨምራል” በማለት አሳስበዋል።የኢራን ምክር ቤት አፈጉበኤ ጋሊባፍ ከዚህ ቀደም ብሎ ባሠራጩት የማኅበራዊ ሚዲያ መልዕክት ኢራን ለየትኘውም ሁኔታ ዝግጁ መሆኗን አስታውቀው ነበር።ያጋሩ, “የኢራናውያንን መብት ከማክበር ውጪ አሜሪካ ሌላ አማራጭ የላትም” አፈ ጉባኤ ጋሊባፍ
  18. 12 ግንቦት 2026የኢራን ተኩስ አቁም “በቋፍ ላይ” መሆኑን ትራምፕ ተናገሩፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Reutersየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራን የተኩስ አቁም ስምምነት “በቋፍ ላይ” እንደሚገኝ ተናገሩ። የተኩስ አቁሙ ዘላቂነት “በማይታመን ሁኔታ ደካማ” መሆኑንም ገልጸዋል።ፕሬዝዳንቱ ትናንት ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፤ አንድ ወር ያስቆጠረው የተኩስ አቁም ስምምነት “በሕይወት ለመቆየት እየተንገዳገደ” ይገኛል።የትራምፕን አስተያየት ተከትሎ የኢራን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ መሐማድ ጋሊባፍ “ለማንኛውም ወረራ ምላሽ ለመስጠት እና ትምህርት ለማስተማር ዝግጁ ነን” ብለው በኤክስ ገጻቸው ምላሽ ሰጥተዋል።አሜሪካ ለኢራን ላቀረበችው የሰላም ዕቅድ ቴህራን የሰጠችው ምላሽ በዋሽንግተን ውድቅ ተደርጓል።ያለፈው እሑድ ኢራን ጦርነቱን ለማስቆም እና የሆርሙዝ ወሽመጥን ለመክፈት ለአሜሪካ ያቀረበችው ዕቅድ ተቀባይነት አላገኘም። ፕሬዝዳንቱም “ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው” እና “ቆሻሻ” ሲሉ ዕቅዱን አጣጥለዋል።ትራምፕ ይህንን ካሉ በኋላ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢስማኤል ባጊ የቴህራን ዕቅድ “ኃላፊነት የተሞላው” እና “ቸር” መሆኑን ተናግረዋል።የኢራን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ “በ14ቱ ነጥቦች እንደተመለከተው የኢራናውያንን መብት ከማክበር ውጭ አማራጭ የለም። ሳይቀበሉት በዘገዩ ቁጥር የአሜሪካውያን ግብር ከፋዮች ገንዘብ ይባክናል” ብለዋል።በኢራን እና አሜሪካ መካከል የተወሰኑ ግጭቶች ቢኖሩም የተኩስ አቁም ስምምነቱ አንድ ወር አስቆጥሯል።ፕሬዝዳንት ትራምፕ፤ “የተኩስ አቁም ስምምነቱ በሕክምና እርዳታ እንደሚተነፍስ ታማሚ ነው። ሐኪሞች መጥተው ‘ጌታዬ የሚወዱት ሰው በሕይወት የመቆየት ዕድሉ 1 በመቶ ነው’ የሚሉት ዓይነት ነው” ብለዋል።ያጋሩ, የኢራን ተኩስ አቁም “በቋፍ ላይ” መሆኑን ትራምፕ ተናገሩ
  19. 11 ግንቦት 2026ሆርሙዝ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ካልተከፈተ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ለረሃብ ይጋለጣሉ ተባለማዳበሪያ የሚበትን ሰውየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,በሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት ተስተጓጉሏልየሆርሙዝ ወሽመጥ በቶሎ ተከፍቶ የማዳበሪያ ምርት በባሕረ ሰላጤው መተላለፍ ካልቻለ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የምግብ እጥረት እና ረሃብ እንደሚገጥማቸው አንድ የተበባሩት መንግሥታት ባለሥልጣን ተናገሩ።ባለሥልጣኑ ለፈረንሳይ የዜና ወኪል ኤኤፍፒ እንደተናገሩት ወራት ባስቆጠረው የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ምክንያት በሆርሙዝ በኩል የሚደረገው የመርከቦች እንቅስቃሴ መስተጓጎሉ ለእርሻ ምርት አስፈላጊ የሆነውን የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት አደናቅፎታል።ስለዚህም በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የሆርሙዝ ወሽመጥ ተከፍቶ የአፈር ማዳበሪያ ምርት እና ግብዓት እንዲያልፍ ካልተፈቀደ የምግብ ምርት መስተጓጎል እና ረሃብ ሊያስከትል እንደሚችል የመንግሥታቱ ድርጅት የፕሮጀክቶች ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት ዮርግ ዳ ሲልቫ ተናግረዋል።ባለሥልጣኑ “ከፍተኛ የሰብአዊ ቀውስ ሊሆን የሚችለውን ችግር ለመቀልበስ ያሉን ጥቂት ሳምንታት ብቻ ናቸው” ሲሉ ለዜና ወኪሉ ገልጸዋል።አክለውም በጦርነቱ ሰበብ የአፈር ማዳበሪያ ምርቱ አቅርቦት በመስተጓጎሉ “ተጨማሪ 45 ሚሊዮን የሚሆኑ ተጨማሪ ሰዎችን ለምግብ እጥረት እና ለረሃብ የሚዳርግ ቀውስ ሊገጥመን ይችላል” ብለዋል።ባለፈው የካቲት ወር ማብቂያ አካባቢ በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት ኢራን እና አሜሪካ በወሳኙ የባሕር መተለላፊያ የሆርሙዝ ወሽመጥ የጭነት መርከቦች እንዳይንቀሳቀሱ የሚያደርግ እገዳ ጥለዋል።ካርታያጋሩ, ሆርሙዝ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ካልተከፈተ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ለረሃብ ይጋለጣሉ ተባለ
  20. 11 ግንቦት 2026ስለ አሜሪካ የጦር መሣሪያ ክምችት የተናገሩት ሴናተር ምርመራ እንደሚደረግባቸው መከላከያ ሚኒስትሩ ገለጹዴሞክራቱ ሴናተር ማርክ ኬሊየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴት፣ መሥሪያ ቤታቸው ዴሞክራቱ ሴናተር ማርክ ኬሊ ስለ አገሪቱ የጦር መሣሪያ ክምችት የሰጡትን አስተያየት እንዲመረምር ጠየቁ።ሴናተሩ “ቴሌቪዥን ላይ” ቀርበው ምሥጢራዊ ስለሆነ የፔንታጎን መረጃ “ዘላብደዋል” ያሉት ሄግሴት፤ “በድጋሚ… መሐላውን ጥሷል?” ሲሉ ኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ ጠይቀዋል።ሴናተሩ ኬሪ ወቀሳ ያስነሳባቸውን ንግግር ያደረጉት ከሲቢኤስ ኒውስ ‘ፌስ ዘ ኔሽን’ ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው። ፕሮግራሙ ላይ ቀርበው በኢራን ጦርነት ምክንያት ስለ አሜሪካ የጦር መሣሪያ ክምችት የተሰማቸው ስጋት ገልጸው ነበር።የጦር መሣሪያዎችን የሚዘረዝር የፔንታጎን ማብራሪያም በማጣቀስ የመሣሪያ ክምችቱ ምን ጥቅም ላይ እንደዋለ መረዳታቸው “አስደንጋጭ” እንደሆነ ተናግረዋል።ኬሊ፤ ከዚህ ቃለ መጠይቅ በኋላ ከመከላከያ ሚኒስትሩ ለቀረበባቸው ክስ በሰጡት ምላሽ ምሥጢራዊ መረጃ አውጥተዋል መባሉን አስተባብለዋል። ስለዚህ ጉዳይ “ከሳምንት በፊት ይፋዊ ውይይት ላይ ተነጋግረናል” ሲሉ ጉዳዩ ምሥጢር እንዳልነበረ ተከራክረዋል።የአሪዞናው ሴናተር በኤክስ ገጻቸው በሰጡት ምላሽ፤ “ከእነዚህ ክምችቶች የተወሰኑትን ወደ ነበሩበት ለመመለስ ‘ዓመታት’ ተናግረሃል” ሲሉ መረጃው የመጣው ከመከላከያ ሚኒስትሩ ንግግር እንደሆነ ገልጸዋል። ባለፈው ወር የነበረውን የሴኔት ስብሰባ የሚያሳይ ቪዲዮም ለጥፈዋል።”ይህ ምሥጢራዊ መረጃ አይደለም፤ የአንተ ንግግር ነው። ይህ ጦርነት ከፍተኛ ዋጋ እያስወጣ ነው፤ አንተ እና ፕሬዝዳንቱ እስካሁን ድረስ [የጦርነቱ] ግብ ምን እንደሆነ ለአሜሪካ ሕዝብ አላብራራችሁም” ሲሉ ወቅሰዋል።የመከላከያ ሚኒስትሩ ሄግሴት ሴናተር ኬሊ ላይ ምርመራ እንዲደረግ የጠየቁት ከዚህ ቀደም ባደረጉት ንግግር ምክንያት የተነሳው ውዝግብ ባልተቋጨበት ወቅት ነው። ሴናተሩ ከዚህ ቀደም የአሜሪካ ወታደሮች ሕገ-ወጥ ትዕዛዞችን እንዳይቀበሉ ሲናገሩ ተደምጠው ነበር።መከላከያ መሥሪያ ቤቱ በዚህ ንግግራቸው ምክንያት ሕጋዊ እርምጃ ሊወስድባቸው ያቀደ ሲሆን፣ ከቀናት በፊት ግን የፌዴራል ይግባኝ ሰበር ችሎት የፔንታገንን እርምጃ ውድቅ ሊያደርግ እንደሚችል ተሰምቷል።ያጋሩ, ስለ አሜሪካ የጦር መሣሪያ ክምችት የተናገሩት ሴናተር ምርመራ እንደሚደረግባቸው መከላከያ ሚኒስትሩ ገለጹ