የፓኪስታን የአገር ውስጥ ሚኒስትር ሞህሲን ናቂቭ በኢራን እና አሜሪካ መካከል የተቋረጠውን የሰላም ንግግር ለማስቀጠል ቴህራን መግባታቸው ተገለጸ። የጉዞው ዓላማ “ንግግሮች እንዲካሄዱ ለማመቻች እና ቀጣናዊ ሰላም ለማስፈን” መሆኑ ተገልጿል።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 3 ሰአት በፊትየኢራን እና አሜሪካ ድርድር እንዲቀጥል የቅድመ ሁኔታዎች ልውውጥ መደረጉ ተገለጸትራምፕየፎቶው ባለመብት,Bloomberg via Getty Imagesኢራን ላቀረበችው የሰላም ዕቅድ አሜሪካ ባለ አምስት ነጥብ ምላሽ መስጠቷን የቴህራን መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።ለወታደራዊ እና ደኅንነት ተቋማት ቅርብ የሆነው ፋርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው፤ አሜሪካ ካስቀመጠችው ቅድመ ሁኔታ መካከል ቴህራን አንድ የኒውክሌር ተቋም ብቻ እንዲኖራት የሚጠይቀው ይገኝበታል።የኢራን ጦርነት የሚቆመው ቅድመ ሁኔታዎች ተከብረው ድርድር ሲካሄድ መሆኑም ተመልክቷል።ኢራን ለጦርነቱ ካሳ እንዲሰጣት ብትጠይቅም አሜሪካ ጥያቄውን አልተቀበለችም።ሊባኖስን ጨምሮ በሁሉም ግንባሮች ጦርነትን ማቆም የኢራን ቅድመ ሁኔታ ነው።በተጨማሪም ማዕቀቦች እንዲነሱ ቴህራን ያቀረበችውን ጥያቄ ዋሽንግተን አልተቀበለችም።ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ሉዓላዊነቷ እንዲከበር መጠየቋም ተገልጿል።የፓኪስታንየአገር ውስጥ ሚኒስትር ሞህሲን ናቂቭ በኢራን እና አሜሪካ መካከል የተቋረጠውን የሰላም ንግግር ለማስቀጠል ቴህራን ገብተዋል።ያጋሩ, የኢራን እና አሜሪካ ድርድር እንዲቀጥል የቅድመ ሁኔታዎች ልውውጥ መደረጉ ተገለጸ
  2. ከ 4 ሰአት በፊትትራምፕ ማስጠንቀቂያ ቢሰጡም ታይዋን ነጻነቷን እንደምታውጅ ገለጸችየታይዋን ፕሬዝዳንት ላይ ቺንግ-ቲየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የታይዋን ፕሬዝዳንት ላይ ቺንግ-ቲየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማስጠንቀቂያ ቢሰጡም ታይዋን ነጻነቷን ከማወጅ ወደኋላ እንደማትል አስታወቀች።ትራምፕ ከቻይናው ፕሬዝዳንት ጋር በቤጂንግ ለሁለት ቀናት ከተወያዩ በኋላ የታይዋንን ነጻነት በተመለከተ “ምንም ማረጋገጫ” እንዳልሰጡ ተናግረዋል።ቻይና ታይዋንን የግዛቷ አካል አድርጋ ትቆጥራለች። ታይዋንን በኃይል ልትጠቀልል የምትችልበት ዕድል እንዳለም ይታመናል።የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ከትራምፕ ጋር ቢወያዩም ለታይዋን የ11 ቢሊዮን ዶላር መሣሪያ የመሸጥ ጉዳይ ውሳኔ አላገኘም።ታይዋን እራሷን እንድትከላከል አሜሪካ መሣሪያ መስጠት ብትሻም ከቻይና ጋር የሚያጋጫት እርምጃ ከመውሰድ መቆጠብ ትፈልጋለች።የታይዋን ፕሬዝዳንት ላይ ቺንግ-ቲ፤ ታይዋን “አሁንም ነጻ እና ዴሞክራሲያዊ አገር ስለሆነች ነጻነቷን ማወጅ አያስፈልጋትም” ብለዋል።ያጋሩ, ትራምፕ ማስጠንቀቂያ ቢሰጡም ታይዋን ነጻነቷን እንደምታውጅ ገለጸች
  3. ከ 6 ሰአት በፊትበጣሊያን በደረሰ የመኪና ጥቃት ስምንት ሰዎች ተጎዱመኪናውን ካቆመ በኋላ ስለት ይዞ በመውጣት አንድ ሰው ላይ ጥቃት ፈጽሟል።የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,አሽከርካሪው መኪናውን ካቆመ በኋላ ስለት ይዞ በመውጣት አንድ ሰው ላይ ጥቃት ፈጽሟልበሰሜን ጣልያን በመንገደኞች ላይ በደረሰ የመኪና ጥቃት ስምንት ሰዎች መጎዳታቸው ተገለጸ።አንድ ግለሰብ ሰዎች በተሰበሰቡበት ጎዳና ላይ መኪና በመንዳት ባደረሰው ጥቃት ከተጎዱት አንዷ እጇም እግሯም እንደተጨፈለቀ ተገልጿል።በመኪና ከተገጩት አራቱ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ጥቃቱን የፈጸመው ተጠርጣሪ የ31 ዓመት ሞሮኳዊ ጣልያናዊ መሆኑ ተገልጿል።መኪናውን ካቆመ በኋላ ስለት ይዞ በመውጣት አንድ ሰው ላይ ጥቃት ፈጽሟል። በዚያው አካባቢ እየሮጠ ሳለም ተይዟል።የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎሚ ጥቃቱ “እጅግ የከፋ ነው” ብለዋል።ተጠርጣሪው በአውሮፓውያኑ 2022 የአእምሮ ሕሙማን ሆስፒታል ገብቶ እንደነበር ተገልጿል።አንድ የዐይን እማኝ “መኪና ወደ መታጠፊያው ሲመጣ አይተነዋል። ድንገት ፍጥነቱን ጨመረ በሰዓት 100 ኪሎሜትር እየተጓዘ ነበር። ሰዎች ሲወድቁም ተመልክተናል። የተወሰኑ ሰዎችን ገጭቶ ሌሎችን መንገድ ላይ ሲያሳድድ ነበር” በማለት ጥቃቱን ገልጸዋል።የመኪና ጥቃትየፎቶው ባለመብት,EPAያጋሩ, በጣሊያን በደረሰ የመኪና ጥቃት ስምንት ሰዎች ተጎዱ
  4. ከ 6 ሰአት በፊትግዙፉ የአሜሪካ የጦር አውሮፕላን ጫኝ መርከብ ወደ ዋሽንግተን ተመለሰየአሜሪካ ግዙፉ የጦር አውሮፕላን ጫኝ መርከብየፎቶው ባለመብት,EPAየምስሉ መግለጫ,የአሜሪካ ግዙፉ የጦር አውሮፕላን ጫኝ መርከብ ዩኤስኤስ ጀራልድ አር ፎርድበመካከለኛው ምሥራቅ ለ326 ቀናት ተሰማርቶ የቆየው የአሜሪካ ግዙፉ የጦር አውሮፕላን ጫኝ መርከብ ወደ ዋሽንግተን መመለሱ ተገለጸ።የኢራን ጦርነት ሳይጀመር በፊት የተሰማራው ግዙፍ መርከብ ‘ዩኤስኤስ ጀራልድ አር ፎርድ’፤ አሜሪካ ከቬትናም ጦርነት በኋላ ለረዥም ጊዜ ተልዕኮ የሰጠችው የጦር መሣሪያ ነው።የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴት የጦር መርከቡን ለመቀበል ቨርጂኒያ ገብተዋል።የጦር መርከቡ በኢራን ጦርነት ከመሰማራቱ አስቀድሞ በካሪቢያን ባሕር አደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪ ጀልባዎች ላይ ጥቃት መፈጸም ከተልዕኮዎቹ አንዱ ነበር ተብሏል።የጦር መርከቡ በስምሪት ላይ ሳለ የልብስ ማጠቢያ ክፍሉ ውስጥ በተነሳ የእሳት አደጋ ሁለት ሠራተኞች ተጎድተዋል።ያጋሩ, ግዙፉ የአሜሪካ የጦር አውሮፕላን ጫኝ መርከብ ወደ ዋሽንግተን ተመለሰ
  5. ከ 8 ሰአት በፊትየፊፋ ዋና ጸሐፊ ከኢራን ጋር “ገንቢ” ውይይት ማድረጋቸውን ተናገሩየፊፋ ዋና ጸሐፊ ማቲያስ ግራፍስትሮም ከኢራን የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ኃላፊ መሕዲ ታጅ ጋርየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የፊፋ ዋና ጸሐፊ ማቲያስ ግራፍስትሮም ከኢራን የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ኃላፊ መሕዲ ታጅ ጋርየፊፋ ዋና ጸሐፊ ማቲያስ ግራፍስትሮም ከኢራን የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ኃላፊ መሕዲ ታጅ ጋር “ገንቢ እና አዎንታዊ” ውይይት ማድረጋቸውን ለሮይተርስ የዜና ወኪል ገለጹ።የኢራን ብሔራዊ ቡድን ሦስት የቡድን ማጣሪያ ጨዋታዎችን በዋሽንግተን እንዲያካሂድ መርሃ ግብር ወጥቷል።ሆኖም አሜሪካ እና እስራኤል በቴህራን ላይ የከፈቱት ጦርነት የእግር ኳስ ጨዋታውን መካሄድ አጠያያቂ አድርጓል።የፊፋው ዋና ጸሐፊ “ከኢራን የእግር ኳስ ፌደሬሽን ጋር ጥሩ እና ገንቢ ውይይት አድርገናል። በቅርበት እየሠራን ነው። በዓለም ዋንጫ ልናስተናግዳቸው ጓጉተናል” ብለዋል።የኢራን እግር ኳስ ተጫዋቾች ቪዛን በተመለከተ ዝርዝር ምላሽ ከመስጠጥ ቢቆጠቡም፤ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በሚመለከት ያደረጉት ውይይት አዎንታዊ ውጤት እንዳሳየ ጠቁመዋል።የኢራን የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ኃላፊ መሕዲ ታጅ፤ በካናዳ፣ ቫንኩቨር ለሚካሄደው የፊፋ የውይይት መድረክ ቪዛ ሳይሰጣቸው መቅረቱ ውጥረት ፈጥሯል።ኃላፊው ቪዛ ያልተሰጣቸው ከኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ጋር ባላቸው ትስስር መሆኑ ተገልጿል።ከሜክሲኮ ጋር በመጣመር የዓለም ዋንጫን የሚያስተናግዱት አሜሪካ እና ካናዳ የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብን አሸባሪ ቡድን ብለው ፈርጀዋል። ከአብዮታዊ ዘቡ ጋር ግንኙት ያላቸው ሰዎችን ወደ አገራቸው እንደማያስገቡም አስታውቀዋል።ኢራን ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾችየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesያጋሩ, የፊፋ ዋና ጸሐፊ ከኢራን ጋር “ገንቢ” ውይይት ማድረጋቸውን ተናገሩ
  6. ከ 9 ሰአት በፊትየኢራን እና አሜሪካን የሰላም ንግግርን ለማስቀጠል የፓኪስታን ባለሥልጣን ቴህራን ገቡቴህራንየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየፓኪስታን የአገር ውስጥ ሚኒስትር ሞህሲን ናቂቭ በኢራን እና አሜሪካ መካከል የተቋረጠውን የሰላም ንግግር ለማስቀጠል ቴህራን መግባታቸው ተገለጸ።ፓኪስታን፤ የሰላም ንግግሩን ለማስቀጠል ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ማድረጓን ቀጥላለች።የኢራኑ መገናኛ ብዙኃን ታስኒም እንደዘገበው የፓኪስታን የአገር ውስጥ ሚኒስትር ለሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ትናንት ቅዳሜ ቴህራን ገብተዋል።የጉዞው ዓላማ “ንግግሮች እንዲካሄዱ ማመቻቸት እና ቀጣናዊ ሰላም ማስፈን” መሆኑ ተገልጿል።ከዚህ ቀደም የኢራን የአገር ውስጥ ሚኒስትር ኢካንዳር ሞምኒ ፓኪስታን ሲሄዱ ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸው ኤኤፍፒ ዘግቧል።ባለፈው ወር የኢራን እና አሜሪካ ልዑካንን ያስተናገደችው ፓኪስታን ሰላም ለማውረድ ጥረቷን እንደቀጠለች ነው።በሁለቱ አገራት መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት “ቋፍ ላይ ነው” ቢባልም ግጭቱ እንዳይባባስ አስችሏል።ያጋሩ, የኢራን እና አሜሪካን የሰላም ንግግርን ለማስቀጠል የፓኪስታን ባለሥልጣን ቴህራን ገቡ
  7. ከ 9 ሰአት በፊትከሊባኖስ ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ቢራዘምም እስራኤል ጥቃት መፈጸም እንደቀጠለች ተገለጸበደቡብ ሊባኖስ የተፈጸመው ጥቃትየፎቶው ባለመብት,Reutersእስራኤል እና ሊባኖስ የተኩስ አቁም ስምምነታቸውን በ45 ቀናት ቢያራዝሙም በደቡብ ሊባኖስ የሚፈጸመው ጥቃት መቀጠሉ ተገለጸ።እስራኤል በደቡብ ሊባኖስ በተከታታይ የአየር ጥቃት የፈጸመች ሲሆን፤ ከሄዝቦላህ ጋር ግንኙነት ያላቸው ዒላማዎችን መምታቷን አስታውቃለች።በደቡብ ሊባኖስ ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት በዘጠኝ መንደሮች ለነዋሪዎች ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።በደቡብ ሊባኖስ በአሥር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል። እስራኤል ጥቃት መሰንዘር መቀጠሏ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ዘላቂነት ላይ ጥያቄ አስነስቷል።ትናንት ቅዳሜ ከሊባኖስ ድንበር በ50 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኙ ብዙ መንደሮች ዒላማ መደረጋቸውን የአገሪቱ ብሔራዊ ጣቢያ ዘግቧል። የነዋሪዎች መፈናቀልም እንደቀጠለ ተገልጿል።ያጋሩ, ከሊባኖስ ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ቢራዘምም እስራኤል ጥቃት መፈጸም እንደቀጠለች ተገለጸ
  8. 16 ግንቦት 2026የፊፋ ባለሥልጣናት ከኢራን የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ተገናኝተው ስለ ዓለም ዋንጫ ሊወየዩ ነውየዓለም ዋንጫየፎቶው ባለመብት,Reutersዓለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ ፊፋ ዋና ጸሃፊ ማቲያስ ግራፍስትሮም ከኢራን እግር ኳስ ፌደሬሽን ባለሥልጣናት ጋር ቅዳሜ ዕለት ኢስታንቡል ሊገናኙ መሆኑን ምንጮች ለሮይተርስ ተናገሩ።የፌፋ ባለሥልጣናት በዓለም ዋንጫ ላይ ባላት ተሳትፎ “ማረጋገጫ” መስጠታቸውን ምንጨቹ ጨምረው ገልጸዋል።ኢራን ሦስቱንም የዓለም ዋንጫ ግጥሚያዎች የምታካሄደው በአሜሪካ ውስጥ ቢሆንም እስራኤል እና አሜሪካ የካቲት 21 2018 ዓ.ም. ጦርነት ከከፈቱባት በኋላ ቡድኑ ሰኔ 4 እና ሐምሌ 12/2018 ዓ.ም. የሚያደርጋቸው ግጥሚያዎች ላይ እርግጠኛ መሆን አልተቻለም።የኢራን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የሆኑት ሜህዲ ታጅ በካናዳ ቫንኮቨር በተካሄደ የፊፋ ጉባዔ ላይ እንዳይገኙ ከኢራን አብዮታዊ ዘብ ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ቪዛ በመከልከላቸው የበለጠ የአገሪቱን ተሳትፎ ጥያቄ ውስጥ ትሎታል።የዓለም ዋንጫን በጥምረት የሚያዘጋጁት አሜሪካ እና ካናዳ አብዮታዊ ዘቡን “አሸባሪ” በማለት ፈርጀውታል። ሁለቱም አገራት ከቡድኑ ጋር ግንኙነት ያለውን ማንኛውም አካል ወደ አገራቸው እንደማያስገቡ ግልጽ አድርገዋል።የኢራን ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካዘም ጋሪባባዲ በማኅበራዊ ገጻቸው ላይ ፊፋ ሁሉም ቡድኖች እና ልዑካን ቡድናቸው የዓለም ዋንጫን ወደሚያዘጋጁት አገራት እንዲገቡ የማድረግ ኃላፊነት አለበት ሲሉ ተናግረዋል።”የኢራን ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን በፊፋ ሕግ መሠረት በጨዋታው የመሳተፍ መብቱን አግኝቷል” ሲሉ ጽፈዋል።”ተጫዋቾች፣ ቴክኒካል ቡድኑን፣ የፌዴሬሽኑ ባለሥልጣናት ወይም አስፈላጊ የኢራን ልዑካን አባላት እንዳይገቡ የሚከለክል ማንኛውም እርምጃ የዓለም ዋንጫን መንፈስ እና ዓላማ ይጥሳል።አዘጋጅ አካል ኢራንን ጨምሮ ብቁ የሆኑ ቡድኖች ያለ አድልዎ እና ገደብ ወደ አስተናጋጅ አገር ገብተው በእኩል ደረጃ እንዲወዳደሩ ማረጋገጥ ካልቻለ የዓለም ዋንጫው ተአማኒነት በራሱ ይጎዳል።ምንጮች ለሮይተርስ የዓለም ዋንጫ ተሳታፊዎች በአስተማማኝ እና ደህንነቱ በተጠበቀ አካባቢ እንዲወዳደሩ ፊፋ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ጦርነት ውስጥ ቢሆኑም ቴህራን በዓለም ዋንጫ ላይ ብትሳተፍ “ምንምችግር የለውም” ሲሉ ከሁለት ሳምንታት በፊት ተናግረው ነበር።ያጋሩ, የፊፋ ባለሥልጣናት ከኢራን የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ተገናኝተው ስለ ዓለም ዋንጫ ሊወየዩ ነው
  9. 16 ግንቦት 2026ሴራ ሊዮን ከአሜሪካ የተባረሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ምዕራብ አፍሪካውያንን ለመቀበል መስማማቷ ተነገረየሴራ ሊዮን ውች ጉዳይ ሚኒስትር ቲመቲ ካባየፎቶው ባለመብት,Reutersሴራ ሊዮን በአሜሪካ የሚባረሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ የምዕራብ አፍሪካ ስደተኞችን ለመቀበል መስማማቷን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ለሮይተርስ ተናገሩ።ስምምነቱ የትሩምፕ አስተዳደር ከአገር የሚያባርራቸውን ስደተኞች በፍጥነት ለማስወጣት ከወሰዳቸው በርካታ እርምጃዎች መካከል ይህ የቅርቡ ነው።“የሦስተኛ አገር” ተባራሪዎች የሚባሉት ስደተኞቹ የመጀመሪያ በረራ ግንቦት 12 ወደ ሴራሊዮን እንደሚደርስ ሚኒስትሩ ቲመቲካባ ተናግረዋል።ስደተኞቹ ከሴኔጋል፣ ጋና፣ ጊኒ እና ናይጄሪያ የመጡ 25 ዜጎች መሆናቸው ታውቋል።“ሴራ ሊዮን ከአሜሪካ በየዓመቱ 300 የኢኮዋስ [የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማኅበረሰብ] ዜጎችን ለመቀበል የሦስተኛ አገር ስምምነት ፈርማለች። በወር ከፍተኛው 25 ስደተኞች ይገባሉ” ሲሉ ካባ ተናግረዋል።አሜሪካ ከዚህ ቀደም “የሦስተኛ አገር” ስደተኞችን እንደ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ጋና፣ ካሜሩን፣ ኤኳቶሪያል ጊኒ እና እስዋቲኒ ወዳሉ የአፍሪካ አገራት አባርራለች።ይህም በሕጋዊ መሠረት እና በስደተኞች አያያዝ ላይ በሕግ ባለሙያዎች እና በመብት ቡድኖች ክርክር አስነስቷል። በተለይም ስደተኞቹ ዜግነት የሌላቸውበት አገር መላካቸው ትችት ያስተናገደ ጉዳይ ነው።ሴራ ሊዮን ከኢኮዋስ አገራት የሚመጡ ስደተኞችን ብቻ ለመቀበል ያደረገችው ስምምነት ከጋና ጋር ያለው ተመሳሳይ ነው።ሮይተርስ የዜና ወኪል ቀደም ሲል ወደ ጋና፣ ኤኳቶሪያል ጊኒ እና ሌሎች አፍሪካ አገራት የተላኩ ስደተኞች ምንም እንኳ በአሜሪካ ፍርድ ቤት ጥበቃ ቢሰጣቸውም ወደ ትውልድ አገራቸው እንዲመለሱ እንደተገደዱ ዘግቧል።ወደ ሴራ ሊዮን የሚላኩት ስደተኞች እዚያ እንዲኖሩ ይፈቀድላቸው እንደሆነ ግን ግልፅ አይደለም።የሴራ ሊዮን መንግሥት አንድ ቃል አቀባይ ሲጠየቁ ወዲያው ምላሽ አልሰጡም። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካባ ሴራሊዮን ስደተኞችን በመቀበሏ ምን እንደምታገኝ አልገለፁም።“የኢሚግሬሽን ፖሊሲዎቻቸውን መደገፍ ከአሜሪካ ጋር ያለን የሁለትዮሽ ግንኙነት አካል ነው” ብለዋል።ባለፈው የካቲት ወር በዲሞክራት የሴኔት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የታተመ ሪፖርት ወደ ሦስተኛ አገር ማባረር አጠቃላይ ወጪ ያልታወቀነው ቢልም፤ ከ32 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለአምስት አገራት መላኩ ግን ታውቋል። እነዚህ አገራት ኤኳቶሪያል ጊኒ፣ ሩዋንዳ፣ ኤልሳልቫዶር፣ እስዋቲኒ እና ፓላው ናቸው።አሜሪካ እና ሴራ ሊዮን ቀደም ሲልም ስደተኞችን በማባረር ጉዳይ አለመግባባት ውስጥ ነበሩ።እ.አ.አ በ2017 በመጀመሪያው የትራምፕ አስተዳደር ወቅት ዋሽንግተን በፍሪታውን ያለው የአሜሪካ ኤምባሲ ለሴራ ሊዮን የውጭ ጉዳይ እና የኢሚግሬሽን ኃላፊዎች የጉብኝት እና የንግድ ቪዛ መከልከሉን ገልጿል። ለዚህ የሰጠው ምክንያት መንግሥት የሴራ ሊዮን ስደተኞችን ለመቀበል በመቃወሙ ነው።ያጋሩ, ሴራ ሊዮን ከአሜሪካ የተባረሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ምዕራብ አፍሪካውያንን ለመቀበል መስማማቷ ተነገረ
  10. 16 ግንቦት 2026ኢራቅ በሚያዚያ ወር 10 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ብቻ በሆርሙዝ በኩል መላኳን አስታወቀችየኢራቅ የነዳጅ ሚኒስቴር ሚኒስትር ባሲም ሞሐመድየፎቶው ባለመብት,reutersየምስሉ መግለጫ,የኢራቅ የነዳጅ ሚኒስትር ባሲም ሞሐመድከኢራን ጦርነት በፊት በወር 93 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ትልክ የነበረችው ኢራቅ በሚያዚያ ወር 10 ሚሊዮን በርሜል ብቻ መላኳን የአገሪቱ የነዳጅ ሚኒስትር ባሲም ሞሐመድ አስታወቁ።የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት ሳዑዲ አረቢያ፣ ዩኤኢ፣ ኩዌት እና ኢራቅ የነዳጅ ምርታቸውን ወደ ውጭ እንዳይልኩ እንቅፋት ሆኗል።ኢራቅ በአሁኑ ወቅት በቀን 1.4 ሚሊዮን በርሜል የነዳጅ ዘይት ታመርታለች።ባግዳድ እና የኩርዲስታን ክልላዊ መንግሥት መስማማታቸውን ተከትሎ በመጋቢት ወር የአገሪቱ የድፍድፍ ነዳጅ ዘይት በኪርኩክ-ሴይሃን የነዳጅ ማስተላለፊያ በኩል መላክ ተጀምሯል።መሃመድ “200,000 በርሜል በ (ቱርክ) ሴይሃን ወደብ በኩል ልከናል። ወደ 500,000 በርሜል ለማሳደግ ዕቅድ አለን” ብለዋል።ባግዳድ ቀደም ሲል ከአንካራ ጋር ድፍድፍ ነዳጅ በመላክ ብቻ ተገድቦ የነበረውን ስምምነቷን ለማስፋት እየተነጋገረች መሆኑን ገልጸዋል።ኢራቅ የአገሪቱን የምርት እና የኤክስፖርት አቅም ለማሳደግ ከኦፔክ ጋር ለመነጋገር አቅዳለች ያሉት ሚኒስትሩ፣ ባግዳድ በዚህ ውይይት በቀን 5 ሚሊዮን በርሜል የማምረት አቅም ላይ ለመድረስ ማቀዷን ይፋ አድርገዋል።ኢራቅ ከኦፔክ የመውጣት ዕቅድ እንደሌላት ጨምረው ተናግረዋል።ያጋሩ, ኢራቅ በሚያዚያ ወር 10 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ብቻ በሆርሙዝ በኩል መላኳን አስታወቀች
  11. 16 ግንቦት 2026በምሥራቅ ዲሞክራቲክ ኮንጎ በኢቦላ ወረርሽኝ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 80 ደረሰመርፌ የያዘች የሕክምና ባለሙያየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየአፍሪካ በሽታ መቆጣጠር እና መከላከል (አፍሪካ ሲዲሲ) በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምሥራቃዊ ኢቱሪ ግዛት በተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 80 መድረሱን ገለጸ።እስካሁን ድረስ ወርቅ በሚወጣባቸው የሞንግዋሉ እና ርዋምፓራ ግዛቶች 246 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 80 ሰዎች ደግሞ መሞታቸውን የአፍሪካ ሲዲሲ አስታውቋል።የኡጋንዳ ባለሥልጣናት አርብ ዕለት ወደ አገራቸው ከኮንጎ ተሻግሮ የገባ አንድ በቫይረሱ የተያዘ ግለሰብ ማግኘታቸውን ይፋ አድርገዋል።የኡጋንዳ ጤና ሚኒስቴር የ59 ዓመቱ ግለሰብ ቫይረሱ እንዳለበት ከተረጋገጠ በኋላ ሐሙስ ዕለት መሞቱን አስታውቀዋል።ኢቦላ በቫይረስ ከተያዘው ሰው ከሰውነት በሚወጣ በጣም አነስተኛ መጠን ባለው ፈሳሽ ሳይቀር በመተላለፉና ያልተለመዱ ምልክቶች ስላሉት ችግሩን ከቁጥጥር ውጭ ያደርገዋል።ቫይረሱ ለመጀመሪያ ጊዜ በተመራማሪዎች የተገኘው እንደ አውሮፓውያኑ በ1976 አሁን ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በመባል በምትታወቀው የቀድሞው ዛየር ውስጥ በሚገኝ አንድ መንደር ነው።ለቫይረሱ ኢቦላ የሚል ስያሜ የሰጡት በአካባቢው ከሚገኘው ኢቦላ ከተባለው ወንዝ በመነሳት ነው።በ1970ዎቹ ውስጥ ብቻ ዛየር እና ሱዳን ውስጥ ቫይረሱ ለሦስት ጊዜያት ተቀስቅሷል። ሆኖም ከዚህ በኋላ ቫይረሱ እስከ እአአ 1994 ድረስ ሳይታይ ቆይቷል።ገዳዩ ኢቦላ ውስጣዊ ደም መፍሰስን የሚያስከትል ተላላፊ በሽታ ነው።በሽታው የሰውነት ፈሳሽና የአካል ንክኪን ምክንያት አድርጎ በፍጥነት ይሰራጫል፤ ጉንፋን መሳይ ቀዳሚ ምልክቶቹ አንዳንዴ ላይጤኑ ይችላሉ።የጡንቻ ሕመም፣ ራስ ምታት፣ የጉሮሮ መቁሰል፣ ትኩሳት የመጀመርያ ምልክቶቹ ሲሆኑ ማስመለስ፣ ተቅማጥ፣ ሽፍታ እና መድማት ተከትለው የሚመጡ መሆናቸውን ባለሙያዎች ይናገራሉ።የዓለም ጤና ድርጀት መረጃ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ግማሽ ያህሉ እንደሚሞቱ ያሳያል።ያጋሩ, በምሥራቅ ዲሞክራቲክ ኮንጎ በኢቦላ ወረርሽኝ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 80 ደረሰ
  12. 16 ግንቦት 2026ናይጄሪያ እና አሜሪካ በጋራ በወሰዱት እርምጃ የአይኤስ ከፍተኛ መሪ መገደሉ ተነገረየናይጄሪያ ጦርየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የናይጄሪያ ሠራዊት አባላትየናይጄሪያ ጦር ሠራዊት ከአሜሪካ ኃይሎች ጋር በጋራ ባካሄደው ዘመቻ በምዕራብ አፍሪካ ከፍተኛ ተጽእኖ አለው የተባለን የኢስላሚክ ስቴት (አይኤስ) የበላይ መሪን መግደሉን አስታወቀ።ጦር ሠራዊቱ ባወጣው መግለጫ ላይ በተካሄደው የተቀናጀ የፀረ ሽብር ዘመቻ “በዓለም ላይ ካሉ ዋነኛ የሽብር ቡድኞች መካከል አንዱ የሆነውን የአይሲስ ከፍተኛ መሪ የሆነውን አቡ ቢላል አል ሚኑኪ ተደምስሷል” በማለት አስታውቋል።የቡድኑን ከፍተኛ መሪ ዒላማ በማድረግ የተካሄደው ዘመቻ “በቅርቡ በአሜሪካ እና በናይጄሪያ መካከል በተፈጠረው የደኅንነት መረጃ የመጋራት ስምምነት ትበብር” አማካይነት መሆኑ ተገልጿል።የናይጄሪያ ጦር ከፍተኛ የአይኤስ አመራር የተገደለበት ዘመቻ የት እንደተካሄደ ያልገለጸ ሲሆን፣ ከአይኤስ ጋር ግንኙነት ያለው የትኛውም ቡድን ስለጥቃቱ አስካሁን ያለው ነገር የለም።ጦሩ እንዳለው አቡ ቢላል አል ሚኑኪ በቡድኑ የመገናኛ ብዙኃን እንቅስቃሴን፣ የጦር መሳሪያ እና የፈንጂዎች ምርትን እንዲሁም የድሮን አጠቃቀምን ጨምሮ ሌሎች ዘመቻዎችን ከናይጄሪያ ባሻገርም በማካሄድ ሚናው የጎላ ነው።ጨምሮም ግለሰቡ በቅርቡ “የመንግሥታት አጠቃላይ አመራር ክፍል ኃላፊ” በሚል ተሹሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ ካሉ የቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዱ ለመሆን እንደበቃ የደኅንነት መረጃዎች አመልክተዋል።ቀደም ሲልም ግለሰቡ ሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸሙ እና አናሳ ማኅበረሰቦችን ዒላማ ያደረጉ ጥቃቶችን ጨምሮ አይኤስ በሳህል እና በምዕራብ አፍሪካ አካባቢ የሚያካሂዳቸውን ዘመቻዎች ይመራ እንደነበር ባለሥልጣናት ይናገራሉ።የናይጄሪያ ሠራዊት በተጨማሪም ከስምንት ዓመት በፊት በሰሜን ምሥራቅ ናይጄሪያ ከሚገኝ የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት ከ100 በላይ ተማሪዎችን ተጠልፈው ከተወሰዱበት ድርጊት ጋር ግንኙነት እንዳለው ገልጿል።የቦኩ ሃራም ከፍተኛ አዛዥ የነበረው አቡ ቢላል አል ሚኑኪ በአውሮፓውያኑ 2015 ለአይኤስ ታማኝነቱን ከማረጋገጡ በፊት ድጋፍ ለመስጠት ተዋጊዎችን ወደ ሊቢያ አሰማርቶ እንደነበር የናይጄሪያ ጦር ቃል አቀባይ ተናግረዋል።የአይኤስ ከፍተኛ መሪ መገደል በምዕራብ አፍሪካ አካበቢዎች ባለው የቡድኑ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ይኖራዋል የተባለ ሲሆን፣ አሜሪካም ከናይጄሪያ ጋር በመተባበር በቀጣናው ዘመቻዎችን ለማካሄድ ከ200 በላይ ወታደሮቿን ወደ ናይጄሪያ አሰማርታለች።ያጋሩ, ናይጄሪያ እና አሜሪካ በጋራ በወሰዱት እርምጃ የአይኤስ ከፍተኛ መሪ መገደሉ ተነገረ
  13. 16 ግንቦት 2026የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ወደ ቻይና ለጉብኝት ሊጓዙ ነውቭላድሚር ፑቲንየፎቶው ባለመብት,Reutersፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ቻይና ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት እንደሚጓዙ ተገለጸ።ሳውዝ ቻይና ሞርኒንግ የተባለ ድረገጽ አርብ ዕለት ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ፕሬዚዳንት ፑቲን ቤይጂንግ ይደርሳሉ ተብሎ የሚጠበቀው ረቡዕ ዕለት ነው።የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ አርብ ዕለት ለፕሬዚዳንቱ ጉዞ ዝግጅቶች እየተካሄዱ መሆኑን አስታውቀው ለጋዜጠኞች ቀኑ “በጣም፤፤ በጣም በቅርቡ” ይፋ እንደሚሆን ተናግረዋል።“አጀንዳው ግልጽ ነው። በዋናነት በሁለትዮሽ ጉዳይ ይሆናል” በማለት ፔስኮቭ የሁለቱ ፕሬዚዳንቶች ውይይት በስልታዊ አጋርነት ላይ እንደሚያተኩር ተናግረዋል።ቃል አቀባዩ አክለውም ፑቲን እና ከቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ጋር በትራምፕ ጉብኝት ወቅት ስለተነሱ ጉዳዮች “እንደሚወያዩ” ተናግረዋል።“ቻይና በምንሄድበት ወቅት ራሳችን መረጃውን ለማግኘት ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል።ትራምፕ ለሁለት ቀናት በቤይጂንግ ያደረጉትን ይፋዊ ጉብኝት አጠናቅቀው ወደ ዋሺንግተን አርብ ዕለት ተመልሰዋል።ያጋሩ, የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ወደ ቻይና ለጉብኝት ሊጓዙ ነው
  14. 16 ግንቦት 2026የኢራቅ ሚሊሻ አዛዥ አሜሪካ ውስጥ በአይሁዶች ላይ ጥቃት ለማድረስ በማሴር ክስ ተመሰረተበትሞሐማድ ባቀር ሳድ ዳውድ አል ሳዲን ከቀድሞው የአብዮታዊ ዘብ ቁድስ አዛዥ ቃሴም ሶሌይማኒ ጋርየፎቶው ባለመብት,US Attorney’s Officeየምስሉ መግለጫ,ሞሐማድ ባቀር ሳድ ዳውድ አል ሳዲን ከቀድሞው የአብዮታዊ ዘብ አዛዥ ቃሴም ሶሌይማኒ ጋርአሜሪካ አርብ ዕለት የሄዝቦላህ አባል የሆነ ኢራቃዊን በቁጥጥር ስር አዋለች።ሞሐማድ ባቀር ሳድ ዳውድ አል ሳዲን የተባለው ግለሰብ በኢራን ለሚደገፈው የሽብርተኛ ቡድን የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ የተወነጀለ ሲሆን በአሜሪካ ዜጎች እና ፍላጎቶች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ትዕዛዝ ሰጥቷል በሚል ተወንጅሏል።የአሜሪካ ፍትሕ ቢሮ ግንቦት 7 2018 ዓ.ም. “ሞሐማድ ባቀር ሳድ ዳውድ አል ሳዲ፣ ኢራቃዊ ዜግነት ያለው እና የሄዝቦላህ ካታይብ ከፍተኛ አባል በቁጥጥር ስር ውሏል” ብሏል።ቢሮው አክሎም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አል ሳዲ የካታይብ ሄዝቦላህ እና የኢራን አብዮታዊ ዘብ ግቦችን ለማስፈጸም በአሜሪካ እና እስራኤል ፍላጎቶች ላይ ጥቃቶች እንዲፈጸሙ እንዲሁም አሜሪካውያን እና አይሁዶች እንዲገደሉ ሲቀሰቅስ ነበር ሲል ወንጅሎታል።የግለሰቡ መያዝ አሜሪካ በቅርቡ በኢራን የሚደገፈው እና በኢራቅ ውስጥ በሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ቡድን ላይ ከወሰደችው እርምጃ መካከል አንዱ ነው።የአሜሪካ ፍትሕ ቢሮ የግለሰቡን ምስል ከቀድሞው የአብዮታዊ ዘብ ቁድስ አዛዥ ቃሴም ሶሌይማኒ ጋር አጋርቷል።አሜሪካ ሶሌይማኒን እአአ በ2020 በኢራቅ ውስጥ በፈጸመችው የድሮን ጥቃት ከካታይብ ሄዝቦላህ አዛዥ ጋር አቡ ማሃዲ አል ሙሃንዲስ ጋር ገድላቸዋለች።ያጋሩ, የኢራቅ ሚሊሻ አዛዥ አሜሪካ ውስጥ በአይሁዶች ላይ ጥቃት ለማድረስ በማሴር ክስ ተመሰረተበት
  15. 16 ግንቦት 2026አሜሪካ የተኩስ አቁሙ በ45 ቀን መራዘሙን ስታሳውቅ የእስራኤል ጦር ስድስት ሰዎችን መግደሉን ሊባኖስ ገለጸችየሊባኖስ ወታደሮች በቤይሩት በሚገኝ የፍተሻ ጣቢያየፎቶው ባለመብት,EPAየእስራኤል ጦር በደቡባዊ ሊባኖስ በፈጸመው የአየር ድብደባ ሦስት የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ ስድስት ሰዎች መግደሉን የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።ዋሺንግተን በበኩሏ በሁለቱ አገራት መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በ45 ቀን መራዘሙን ይፋ አድርጋለች።የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር በሃሮፍ ከተማ የሚገኘው የሲቪል መከላከያ ማዕከል ጥቃት ከደረሰበት በኋላ አራተኛው የሕክምና ባለሙያ “ከፍተኛ ጉዳት” እንዳጋጠመው አስታውቋል።አርብ ዕለት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እስራኤል እና ሊባኖስ ለሁለት ቀናት በዋሺንግተን ድርድር ካደረጉ በኋላ የተኩስ አቁሙን ለማራዘም መስማማታቸውን ገልጿል።የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሚያዚያ 8 2018 ዓ.ም. በሁለቱ አገራት መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት መደረሱን ይፋ ቢያደርጉም ከሄዝቦላህ ጋር የሚደረገው ውጊያ ግን ቀጥሏል።ረቡዕ ዕለት የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር በአገሪቱ ደቡባዊ ክፍል እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት ስምንት ሕጻናትን ጨምሮ 22 ሰዎች መገደላቸውን አስታውቋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ቶሚ ፒጎት “እነዚህ ንግግሮች በሁለቱ አገራት መካከል ዘላቂ ሰላም እንደሚያመጡ፣ ሁለቱም አንዳቸው የሌላኛቸውን ሉዓላዊነት እንዲሁም የግዛት አንድነት እንደሚያከብሩ፣ እንዲሁም በሚጋሯቸው ድንበሮች አካባቢ ትክክለኛ ደህንነትን እንደሚያሰፍኑ ተስፋ እናደርጋለን” ሲሉ ተናግረዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ በሰኔ ወር “የፖለቲካ ድርድሩን ለመቀጠል ዳግም እንገናኛለን” ሲል አስታውቋል።ፒጎት አክለውም “በተጨማሪም ግንቦት 21 2018 ዓ.ም. አዲስ የደህንነት እና መከላከያ ውይይቶች በፔንታጎን ይጀመራሉ” ብለዋል።በአሜሪካ የእስራኤል አምባሳደር ይቼል ሌይተር ውይይቱ “ግልጽ እና ገንቢ” ነበር ብለዋል።የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋፍ ሳላም ከእስራኤል ጋር በሚደረጉ “ድርድሮቹ ያለንን ስፍራ ከፍ ለማድረግ የሁሉም የአረብ እና ዓለም አቀፍ ድጋፍ ለማሰባሰብ” ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።እስራኤል እና ሄዝቦላህ የሚያካሄዱትን ውግያ ተከትሎ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሊባኖሳውያን ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል። አብዛኞቹ ተፈናቃዮች ሄዝቦላህ ከሚቆጣጠራቸው ከደቡባዊ የአገሪቱ ክፍል፣ ከምሥራቃዊ ቤካ ቫሊ እንዲሁም ከቤይሩት ደቡባዊ ክፍል ዳሄህ ናቸው።በእስራኤል እና በሄዝቦላህ መካከል ግጭት የተቀሰቀሰው የኢራን ጦርነት በተጀመረ በሁለተኛው ቀን የካቲት 23 2018 ዓ.ም. ነው።በወቅቱ ሄዝቦላህ ወደ እስራኤል ሮኬቶችን ያስወነጨፈ ሲሆን የእስራኤል ጦር በበኩሉ በደቡባዊ ሊባኖስ መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት እና የምድር ጦር ዘመቻ ከፍቷል።ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በግጭቱ በሊባኖስ ብቻ ቢያንስ 2,896 ሰዎች ሲገደሉ 18 የእስራኤል ወታደሮች እና ሰላማዊ ሰዎችም ሞተዋል።ያጋሩ, አሜሪካ የተኩስ አቁሙ በ45 ቀን መራዘሙን ስታሳውቅ የእስራኤል ጦር ስድስት ሰዎችን መግደሉን ሊባኖስ ገለጸች
  16. 15 ግንቦት 2026የብሪክስ አባላት የኢትዮጵያን የኮፕ ጉባኤ አዘጋጅነትን ደገፉ፤ መካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ላይ የጋራ አቋም ሳይዙ ቀሩየብሪክስ ሚኒስትሮችየፎቶው ባለመብት,Reutersለሁለት ቀናት በቆየው የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ የመካከለኛው ምሥራቅን ሁኔታ በተመለከተ “በተወሰኑ አባላት መካከል ባለው የተለያየ ምልከታ” የተነሳ የጋራ መግለጫ ሳያወጣ መጠናቀቁን አዘጋጇ ሕንድ አስታወቀችከሐሙስ ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው እና ኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጤሞቲዮስ የተወከለችበት ስብሰባ ዛሬ ተጠናቅቋል።የሕንድ መንግሥት ስብሰባውን አስመልክቶ ያወጣው መረጃ እንደሚያስረዳው፤ የኅብረቱ አባላት ኢትዮጵያ 2020 ዓ.ም. ላይ የሚካሄደው ዓለም አቀፉን የአየር ንብረት ለውጥ ስብሰባ “ኮፕ32” አዘጋጅ መሆኗን ደግፈዋል።ኢትዮጵያ ለጉባኤው ያዘጋጀችው የድርጊት መርሃ ግብር እና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች “ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራዎችን ይበልጥ እንደሚያጠናክሩ እንዲሁም የታዳጊ አገራትን ተሳትፎና መሪነት እንደሚያሳድጉም” ገልጸዋል።በአባል አገራቱ መካከል የተፈጠረ ውልዩነት ተጽዕኖውን ለማስፋት የሚፈልገው ብሪክስ አንድነትን ጠብቆ ማስቀረት ላይ የተጋረጠበትን ተግዳሮት ማሳየቱን የኦሺዬትድ ፕሬስ ዘግቧል።ሕንድ ባወጣቸው መግለጫ እንዳስታወቀችው አባል አገራት በተለያዩ ጉዳዮች “የየራሳቸውን ብሔራዊ አቋም እና ሰፊ የጋራ ምልከታዎችን” ገልጸዋል።ከተወያዩባቸው ጉዳዮች መካከል ሉዓላዊነት፣ የባሕር ትራንስፖርት ደኅንነት እንዲሁም በመካከለኛው ምሥራቅ የሲቪሊያን መሠረተ ልማቶችን እና የንጹኃን ሕይወትን ማስጠበቅ እንደሚገኙበት የዜና ወኪሉ ዘገባ ያሳያል።የብሪክስ አባል አገራት የጋዛ ጉዳይም እንዲሁም የቀይ ባሕር እና ባብ ኤል ማንደብ ወሽመጥ ደኅንነትን ማስጠበቅን በተመለከተ “አንድ አባል ያለውን የሃሳብ ብልዩነት” እንዳስመዘገበ በመግለጫው ተጠቅሷል።ልዩነት የተመዘገበበት ይህ ነጥብ፤ “ሚኒስትሮቹ፤ በቀይ ባሕር እና በባብ ኤል ማንደብ ወሽመጥ በማንኛውም አገር ስም የሚንቀሳቀሱ መርከቦች በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት የመርከብ ጉዞ መብቶቻቸው እና ነጻነቶቻቸው እንዲከበሩ የማድረጉን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተዋል” የሚል ነበር።የብሪክስ አባል አገራትን የሆኑት ኢራን እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በጥምረቱ ስብሰባ የመጀመሪያ ቀን ላይ ውዝግብ ውስጥ መግባታቸው ተዘግቦ ነበር።ከስብሰባው አስቀድሞ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በኢራን ጦርነት ወቅት ወደ ኤምሬቶች መጓዛቸውን ገልጸው ነበር። ኤምሬቶችን ይህንን ብታስተባብልም፤ ኢራን ግን አስቀድማ በስለላ መረጃዋ ያረጋገጠችው ጉዳይ መሆኑን ገልጻለች።ስብሰባው ላይም የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ “የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አገሬ ላይ በተፈጸመው ጥቃት ቀጥተኛ ተሳትፎ ነበራት። ጥቃቶቹ ሲጀመሩ የውግዘት [መግለጫ] እንኳ አላወጡም” ሲሉ ከስሰዋል።ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት ለኤምሬቶች ተወካይ ንግግር በሰጡት ምላሽ መሆኑን የዘገቡት መገናኛ ብዙኃን፤ የኤምሬቶች ተወካይ አስተያየት ምን እንደነበር አልጠቀሱም።ያጋሩ, የብሪክስ አባላት የኢትዮጵያን የኮፕ ጉባኤ አዘጋጅነትን ደገፉ፤ መካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ላይ የጋራ አቋም ሳይዙ ቀሩ
  17. 15 ግንቦት 2026በአሜሪካ ላይ እምነት እንደሌላት የገለጸችው ኢራን ድርድሩ መቀጠሉ አጠራጣሪ ነው አለችየኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺበአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚካሄደው ድርድር በእንጥልጥል ላይ ባለበት በአሁኑ ጊዜ፤ ኢራን በአሜሪካ ላይ እምነት እንደሌላት እና ዋሽንግተን ድርድሩን በሙሉ ልብ የማትይዘው እስከሆነ ድረስ የመሳትፈ ፍላጎት እንደሌላት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ተናገሩ።የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ዛሬ አርብ ሕንድ ውስጥ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፤ ከቴህራን ጋር ጦርነት ውስጥ ከሚገኙት አገራት መርከቦች ውጪ ሌሎች ከኢራን ባሕር ኃይል ጋር በመነጋገር በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ማለፍ እንደሚችሉ አሳውቀዋል።የብሪክስ አባል አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ የተገኙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጨምረውም ኢራን ለዲፕሎማሲያዊ ጥረት ዕድል ለመስጠት በአሁኑ ወቅት ያለው የተኩስ አቁም ባለበት እንዲቀጥል እየጣረች ነው ብለዋል።በሆርሙዝ ጉዳይ ያለው ሁኔታ ውስብስብ መሆኑን የጠቀሱት ባለሥልጣኑ በኤክስ ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት “ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን በመጠበቅ በኩል ዘወትር ታሪካዊ ግዴታዋን ትወጣለች” ብለዋል።አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱትን ጦርነት ተከትሎ የዓለም ከፍተኛ የነዳጅ ፍጆታ የሚተላለፍበት የሆርሙዝ ወሽመጥ በኢራን እርምጃ ምክንያት ከየካቲት ወር አንስቶ ተዘግቶ ይገኛል።ጦርነቱን ለማቆም እና የባሕር መተላለፊያው እንዲከፈት ለማድረግ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ድርድር እየተደረገ ቢቆይም አስካሁን መቋጫ ላይ አልደረሰም። ነገር ግን ሁለቱም ወገኖች ድርድር ቀጥለው ከስምምነት ላይ ለመድረስ ፍላጎት እንዳላቸው እየገለጹ ነው።ያጋሩ, በአሜሪካ ላይ እምነት እንደሌላት የገለጸችው ኢራን ድርድሩ መቀጠሉ አጠራጣሪ ነው አለች
  18. 15 ግንቦት 2026“እጅግ ውጤታማ” የተባለው የትራምፕ እና የዢ ጂንፒንግ ንግግር ተጠናቀቀ፤ ስምምነታቸው ግን ይፋ አልተደረገምፕሬዝዳንት ዢ ሺፒንግ እና ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Reutersወደ ቻይና የተጓዙት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሁለት ቀናት የቆየውን እንዲሁም “እጅግ ውጤታማ” እና “የማይረሳ” ሲሉ የገለጹትን ከፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ጋር የተደረገ ንግግር አጠናቅቀው ወደ ዋሽንግተን እየተመለሱ ነው።የቻይና መገናኛ ብዙኃንም የትራምፕን ጉብኝት “ታሪካዊ እና ታላቅ ምዕራፍ” ሲሉ ገልጸውታል። መሪዎቹ በሁለቱ አገራት መካከል “አዲስ ገንቢ ስትራቴጂክ እና የተረጋጋ ግንኙነት” እንዲኖር መሠረት መጣላቸውን በዘገባቸው ጠቅሰዋል።በዛሬው የጉብኝቱ መጨረሻ ቀን በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ መሪዎቹ ስለ ንግድ፣ ኢራን እና “ሌሎች በርካታ ነገሮች” የሁለትዮሽ ንግግር እንዳደረጉ ተገልጿል።ሁለቱም ወገኖች ስለ ንግግሮቻቸው ይዘት ዝርዝር መረጃ አልሰጡም። በተለይም የውጥረት ምንጭ ስለሆነው የታይዋን ጉዳይ አላነሱም።ምንም እንኳ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወደ ቻይና የተጓዙት በርካታ የአሜሪካ የቢዝነስ አመራሮችን አስከትለው ቢሆንም በጉልህ የሚጠቀስ አንድም የንግድ ወይም የፖሊሲ ስምምነት ላይ አልደረሱም።ቻይና ከጥቅምት ወር አንስቶ ከተለያዩ አገራት ጋር የንግድ ስምምነቶችን ስትፈጽም ነበር። ጥር ላይ ቻይና እና ደቡብ ኮሪያ የቴክኖሎጂ፣ ንግድ እንዲሁም የትራንስፖርት ትብብራቸውን የሚያጠናክሩ በርካታ የኤክስፖርት ኮንትራት እና ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።ታሪፍን በተመለከተ ከዋሽንግተን ጋር ውጥረት ውስጥ የገቡት ቻይና እና ካናዳም ከረጅም ጊዜ የሻከረ ግንኙነት በኋላ አንዳቸው የሌላኛቸው ምርት ላይ የሚጣል ቀረጥን ለመቀነስ ተስምተው ነበር።ከቀናት በፊትም ቻይና ከኢስዋቲኒ ውጪ በሁሉም የአፍሪካ አገራት ምርቶች ላይ የምትጥለውን ቀረጥ አንስታለች።ትራምፕ ሐሙስ ምሽት ጉብኝት ላይ እያሉ በተላለፈ የፎክስ ቲቪ ቃለ መጠይቃቸው፤ ቻይና የአሜሪካን ነዳጅ እና 200 የቦይንግ አውሮፕላኖችም ለመግዛት ቃል መግባቷን ተናግረዋል። እስካሁን ግን ከቻይና በኩል ስለዚህ ጉዳይ አስተያየት አልተሰጠም።ያጋሩ, “እጅግ ውጤታማ” የተባለው የትራምፕ እና የዢ ጂንፒንግ ንግግር ተጠናቀቀ፤ ስምምነታቸው ግን ይፋ አልተደረገም
  19. 15 ግንቦት 2026ዩኤኢ የሆርሙዝ ወሽመጥን ለማለፍ አዳዲስ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ግንባታን ልታፋጥን ነውዩናይትድ አረብ ኤሚሬትስየፎቶው ባለመብት,Reutersዩናይትድ አረብ ኤሚሬትስ (ዩኤኢ) ወደ ውጭ የምትልከውን የነዳጅ ዘይት መጠን እአአ በ2027 በእጥፍ ለማሳደግ የአዳዲስ የማስተላለፊያ መስመሮችን ግንባታ ልታፋጥን መሆኑን ሮይተርስ ዘገበ።አዳዲስ የማስተላለፊያ መስመሮቹ የሆርሙዝ ወሽመጥን ለማለፍ የሚያስችሉ መሆናቸው ተገልጿል።የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመሮቹ የሚገነቡት በፉጃይራህ በኩል መሆኑን የአቡ ዳቢ ሚዲያ ዘግቧል።ፕሮጀክቱ መቼ እንደሚጀመር እና እንደሚጠናቀቅ ይፋ የሆነ ዝርዝር መረጃ የለም።ዩኤኢ አሁን እየተጠቀመችበት ያለው የነዳጅ ማስተላለፊያ ሐብሻን ፉጃይራህ የሚባል ሲሆን በቀን 1.8 ሚሊዮን በርሜል የማስተላለፍ አቅም አለው።ዩኤኢ አዲስ የምትገነባው የማስተላለፊያ መስመር ከባህረ ሰላጤው ወደ ኦማን ወደብ ነዳጅ ለማጓጓዝ የሚደረገውን ፍጥነት በከፍተኛ መጠን ይጨምረዋል ተብሏል።ዩኤኢ እና ሳዑዲ አረቢያ ከሆርሙዝ ወሽመጥ ውጪ ነዳጅ በቧንቧ የሚያስተላልፉ ብቸኞቹ የባሕረ ሰላጤው አገራት ናቸው። ኦማን በባህረ ሰላጤ በኩል ረዥም የባህር ዳርቻ ስላላት ወሽመጡን ማቋረጥ አይጠበቅባትም።የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (ዩኤኢ) ከፔትሮሊየም ላኪ አገራት ድርጅት (ኦፔክ) እንደምትወጣ ያሳወቀችው ከሦስት ሳምንት በፊት ነው።ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ የነዳጅ ምርቷን በቀን ወደ 5 ሚሊዮን በርሜሎች እንድታሳድግ ይጠበቃል።ይህ ሊሆን የሚችለው ግን ዳግም ነዳጇን በባሕርም ሆነ በተዘረጋው የማስተላለፊያ መስመር ለውጭ ገበያ ማቅረብ ስትችል ብቻ ነው።የኤሚሬትስ ባለሥልጣናት አቡ ዳቢ ከሚገኘው የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የነዳጅ ማውጫዎች የሚነሱ አዳዲስ የማስተላለፊያ መስመሮች አደገኛ የሆነውን የሆርሙዝ ባሕረ ወሽመጥን በመተው ብዙም ጥቅም ላይ ወዳልዋለው ፉጃይራ ወደብ እንደሚያመሩ ተናግረዋል።ያጋሩ, ዩኤኢ የሆርሙዝ ወሽመጥን ለማለፍ አዳዲስ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ግንባታን ልታፋጥን ነው
  20. 15 ግንቦት 2026በምሥራቅ ኮንጎ በተከሰተ የኢቦላ ወረርሽን 65 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸበዲሞክራቲክ ኮንጎ እአአ ከ2018 እስከ 2020 ባለው ጊዜ ውስጥ የተቀሰቀሰው የኢቦላ ወረርሽኝ ወደ 2,300 የሚጠጉ ሰዎችን ገድሏልየፎቶው ባለመብት,Universal Images Group via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,በዲሞክራቲክ ኮንጎ እአአ ከ2018 እስከ 2020 ባለው ጊዜ ውስጥ የተቀሰቀሰው የኢቦላ ወረርሽኝ ወደ 2,300 የሚጠጉ ሰዎችን ገድሏልየአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ አፍሪካ) በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምሥራቃዊ ኢቱሪ ግዛት የኢቦላ ወረርሽኝ መከሰቱን አስታወቀ።ሲዲሲ አፍሪካ በዋናነት የወርቅ ማዕድን በሚወጣባቸው ሞንግዋሉ እና ሩዋምፓራ ከተሞች 246 ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን እና 65 ሰዎች ደግሞ መሞታቸውን ይፋ አድርጓል።ማዕከሉ አርብ ዕለት ባወጣው መግለጫ ከዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ ከኡጋንዳ፣ ከደቡብ ሱዳን እና ከሌሎች ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ስለሚወሰዱ እርምጃዎች እና መደረግ ያለበትን ድንበር ተሻጋሪ ክትትል ለመወያየት ስብሰባ መጥራቱን አስታውቋል።ኢቦላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው አሁን ዲሞክራቲክ ኮንጎ በመባል በምትታወቀው ግዛት ውስጥ እአአ በ1976 ነው።ኢቦላ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በሌሊት ወፎች አማካኝነት እንደሆነ ይታሰባል። ይህ በአገሪቱ ውስጥ ለ17ኛው ጊዜ የተከሰተ ወረርሽኝ ነው።ከሰውነት በሚወጣ ፈሳሽ ጋር በሚኖር ቀጥታ ግንኙነት የሚተላለፈው በሽታው ከባድ የደም መፍሰስ እና የአካል ክፍሎች ሥራ መቆምን ያስከትላል።ትኩሳት፣ የጡንቻ ሕመም፣ ድካም፣ ራስ ምታት እና የጉሮሮ ሕመም የበሽታው ምልክቶች ናቸው። በኢቦላ ለተያዘ ሰው የሚሰጥ ምንም ዓይነት መድኃኒት የለም።ከ65ቱ በበሽታው ተይዘው ከሞቱ ሰዎች መካከል የአራቱ የሞት መንስዔ በላብራቶሪ መረጋገጡን ሲዲሲ አፍሪካ አስታውቋል።የኢቱሪ ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው ቡኒያ ተጨማሪ በበሽታው መያዛቸው የተጠረጠሩ ግለሰቦች መኖራቸው የተገለጸ ሲሆን የምርመራ ውጤታቸው እየተጠበቀ ነው።የኮንጎ መንግሥት እስካሁን በይፋ ወረርሽኙ መከሰቱን አላወጀም።ባለፉት 50 ዓመታት በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ወደ 50,000 የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ ​​ተይዘው ሞተዋል።ወረርሽኙ በዲሞክራቲክ ኮንጎ የተከሰተው እአአ ከ2018 እስከ 2020 ባለው ጊዜ ውስጥ ሲሆን በዚህ ወቅት ወደ 2,300 የሚጠጉ ሰዎች ሞተዋል።ባለፈው ዓመት የኢቦላ ወረርሽኝ በማዕከላዊ ካሳይ ግዛት ተከስቶ 45 ሰዎች ሞተዋል።ያጋሩ, በምሥራቅ ኮንጎ በተከሰተ የኢቦላ ወረርሽን 65 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ