አዲሱ የሰላም ዕቅድ በሊባኖስ ውስጥ የሚካሄደውን ጨምሮ በሁሉም ግንባሮች የሚደረጉ ጦርነቶች እንዲቆሙ፣ በኢራን አቅራቢያ የሰፈሩ የአሜሪካ ወታደሮች እንዲወጡ እና በጦርነቱ ለደረሰባት ውድመት ካሳን እንዲከፈላት የሚጠይቅ መሆኑን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 53 ደቂቃዎች በፊትበኬንያ በነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ምክንያት የተጠራው አድማ ከመንግሥት ጋር ለመደራደር ተቋረጠአድመኞችየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየኬንያ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች በነዳጅ ዋጋ መጨመር ምክንያት በመላው አገሪቱ ለሁለት ቀናት ያካሄዱት የሥራ ማቆም አድማ ከመንግሥት ጋር ድርድር ካደረጉ በኋላ ለጊዜው እንዲቋረጥ አደረጉ።እስከሚቀጥለው ማክሰኞ ድረስ አድማው የቆመው የትራንስፖርት ማኅበራቱ ከመንግሥት ጋር ለሚያደርጉት ድርድር አመቺ ሁኔታን ለመፍጠር ነው ብለዋል።ሰኞ እና ማክሰኞ የተካሄደው የትራንስፖርት ማቆም አድማ ለጊዜው የተቋረጠው ዋና ከተማዋን እና ሌሎች የአገሪቱን ከተሞች እንቅስቃሴ ቀጥ እንዲል ካደረገ በኋላ ነው።የኬንያ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ኪፕቹምባ ሙርኮሜን እንዳሉት አድማውን ያስቆመው ስምምነት የተደረሰው ከሕዝብ ትራንስፖርት ሰጪ ተወካዮች ጋር ምክክር ከተደረገ በኋላ “በከፍተኛ ደረጃ” ንግግሩን ለመቀጠል በመግባባቸታው ነው።ሰኞ ዕለት ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ የአገሪቱ ኤነርጂ ሚኒስትር ከፍተኛ ጭማሪ ተደርጎበት በነበረው የናፍጣ ዋጋ ቅናሽ መደረጉን ቢገልጹም ተጨማሪ ቅናሽ በመጠየቅ አድማው ቀጥሎ ነበር።ከአድማው ጋር ተያይዞ በተከሰተ ጉዳት ቢያንስ አራት ሰዎች ሲገደሉ 30 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን እንዲሁም ከ700 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።ያጋሩ, በኬንያ በነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ምክንያት የተጠራው አድማ ከመንግሥት ጋር ለመደራደር ተቋረጠ
  2. ከ 4 ሰአት በፊትኢቦላ መጀመሪያ ከተገመተው በላይ በፍጥነት እየተሰራጨ ሊሆን እንደሚችል የዓለም የጤና ድርጅት ሐኪሞች አስጠነቀቁሕፃን አዝላ እጇን የምትታጠብ ሴትየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተቀስቅሶ የተገኘው ኢቦላ በጎረቤት ኡጋንዳም ተገኝቷልበዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዳግም የተቀሰቀሰው ኢቦላ 131 ሰዎችን ሲገድል፤ የዓለም የጤና ድርጅት ተወካዮች ከታሰበው በላይ በፍጥነት ሊሰራጭ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ሰጡ።ዶ/ር አን አኒሲያ ለቢቢሲ ድርጅቱ ምርመራውን ባጠናከረ ቁጥር በሽታው በሌሎች አካባቢዎች መዛመቱ ግልፅ ሆኗል ብለዋል።እስከ ማክሰኞ ድረስ 513 ሕሙማን መኖራቸው በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተመዘገበ ሲሆን በኡጋንዳ የአንድ ሰው ሕይወት አልፏል።ይሁን እንጂ መቀመጫውን ለንደን ያደረገ የተላላፊ በሽታዎች ማዕከል ሠኞ ዕለት ይፋ ባደረገው ትንታኔ አሁንም በኢቦላ መያዛቸው ያልታወቀ ሕሙማን መኖራቸውን እና ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው ሳይገኙ እንዳልቀረ ጠቁሟል።ባለፈው ሳምንት በሽታውን ዓለም አቀፍ ድንገተኛ አደጋ ሲሉ ያወጁት የዓለም የጤና ድርጅት ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም “መጠኑ እና የበሽታው ፍጥነት በጣም እንዳሳሰባቸው” ተናግረዋል።በሽታው በሚያዚያ መጨረሻ ከመገኘቱ በፊት ለሣምንታት ቆይቷል የሚል ስጋት አለ።አሁን የተቀሰቀሰው የኢቦላ ቫይረስ ዝርያ ክትባት የሌለው ሲሆን፤ የዓለም የጤና ድርጅት ሌሎች መድኃኒቶች መከላከያ ሊሆኑ የሚችሉ ከሆነ በሚል ምርመራ እያረገ ነው።ያጋሩ, ኢቦላ መጀመሪያ ከተገመተው በላይ በፍጥነት እየተሰራጨ ሊሆን እንደሚችል የዓለም የጤና ድርጅት ሐኪሞች አስጠነቀቁ
  3. ከ 6 ሰአት በፊትኢራን በጦርነቱ ለደረሰባት ውድመት ካሳ እንዲሁም የአሜሪካ ወታደሮች እንዲወጡ የሚጠይቅ ሃሳብ አቀረበችኢራናውያን ባንዲራ ይዘውየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesኢራን በሁሉም ግንባሮች የተከፈቱ ጦርነቶች እንዲቆሙ እና ለደረሰባት ጉዳት ካሳ እንዲከፈላት የሚጠይቅ የስምምነት ሃሳብ አቀረበች።አዲሱ የሰላም ዕቅድ በሊባኖስ ውስጥ የሚካሄደውን ጨምሮ በሁሉም ግንባሮች የሚደረጉ ጦርነቶች እንዲቆሙ፣ በኢራን አቅራቢያ የሰፈሩ የአሜሪካ ወታደሮች እንዲወጡ እና በጦርነቱ ለደረሰባት ውድመት ካሳን እንዲከፈላት የሚጠይቅ መሆኑን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።ቴህራን የሰላም ዕቅዱን በሚመለከት በሰጠችው የመጀመሪያ አስተያየት ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ካዘም ጋሪባባዲ ማዕቀቦች እንዲነሱ፣ እንዳይንቀሳቀሱ የታገዱ ንብረቶቿ እንዲለቀቁ አንዲሁም የአሜሪካ ባሕር ኃይል የጣለውን እገዳ እንዲያነሳ መጠየቃቸውን ኢርና የዜና ወኪል ዘግቧል።የኢራን መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ከሆነ የቴህራን አዲሱ ዕቅድ ከዚህ በፊት ካቀረበችው እና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ቆሻሻ” ሲሉ ውደቅ ካደረጉት ብዙም የተለየ አይደለም።ትራምፕ ሰኞ ዕለት አቅደውት የነበረውን ጥቃት ያቆሙት ቴህራን ለዋሺንግተን አዲስ ሰላም ዕቅድ መላኳን ተከትሎ መሆኑን ተናግረው፤ የኢራንን የኒውክሌር ፕሮግራም ለመገደብ እና ከስምምነት ላይ ለመድረስ “በጣም ጥሩ ዕድል አለ” ብለዋል።ትራምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ ልጥፋቸው ላይ ኳታር፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ “አሜሪካ እንዲሁም የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ሊቀበሉት የሚችሉት ስምምነት ላይ ሊደረስ ይችላል” በማለት ጥቃቱ እንዲዘገይ መጠየቃቸውን ተናግረዋል።ዶናልድ ትራምፕ ሰኞ ዕለት ቴህራን የኒውክሌር የጦር መሣሪያ እንዳታገኝ የሚያደርግ ስምምነት ላይ መድረስ ከተቻለ ደስተኛ እንደሚሆኑ ተናግረዋል።ያጋሩ, ኢራን በጦርነቱ ለደረሰባት ውድመት ካሳ እንዲሁም የአሜሪካ ወታደሮች እንዲወጡ የሚጠይቅ ሃሳብ አቀረበች
  4. ከ 6 ሰአት በፊትጋና ዜጎቿን ከደቡብ አፍሪካ የፊታችን ሐሙስ ልታስወጣ ነውበበርካታ የደቡብ አፍሪካ ከተሞች ጸረ ስደተኛ ሠልፎች ተካሄደዋልየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,በበርካታ የደቡብ አፍሪካ ከተሞች ጸረ ስደተኛ ሠልፎች ተካሄደዋልየጋና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሐሙስ ዕለት ዜጎቹን ከደቡብ አፍሪካ ሊያስወጣ መሆኑን አስታወቀ።የጋና መንግሥት ከዚህ በፊት 300 ዜጎቹን ከደቡብ አፍሪካ ለማስወጣት ምዝገባ ማከናወኑን ገልጾ የነበረ ሲሆን የመጓጓዣ ሙሉ ወጪያቸውንም እንደሚሸፍን ተናግሯል።የጋና ፕሬዚዳንት ጆን ማሃማ በደቡብ አፍሪካውያን የጸረ ስደተኞች ሰልፍ መካሄዱን ተከትሎ ዜጎቻቸውን በአስቸኳይ ለማስወጣት ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው ተነግሯል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሳሙኤል ኦኩድዜቶ አብላክዋ በኤክስ ገጻቸው ላይ የጋናውያን ደህንነት ያለምንም ድርድር ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን ጽፈዋል።የመጀመርያው ዙር መንገደኞች ሐሙስ ዕለት 5 ሰዓት ላይ ከኦ አር ታምቦ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደሚነሱ ተገልጿል።አንድ ጋናዊ በተቃዋሚዎች ተከብቦ ሲወዋከብ የሚያሳይ ቪዲዮ በስፋት ከተዘዋወረ በኋላ በጋና እና በደቡብ አፍሪካ መካከል ዲፕሎማሲየዊ ውጥረቱ ተባብሷል።ሁለቱ አገራት ውጥረቱን ለማርገብ በተደጋጋሚ ንግግሮች ቢያደርጉም የጋና መንግሥት ለዜጎቹ ደህንነት ቅድሚያ እንደሚሰጥ በመግለጽ እርምጃዎቹን መውሰዱን ቀጥሏል።ናይጄሪያም ፈቃደኛ የሆኑ ዜጎቿን ከደቡብ አፍሪካ ለማስወጣት ዝግጁ መሆኗን አስታውቃለች።በደቡብ አፍሪካ በተደጋጋሚ ጸረ ስደተኛ ሰልፎች የተካሄዱ ሲሆን አፍሪካውያን ስደተኞች ዒላማ ተደርገው ጥቃት ደርሶባቸዋል።ባለፈው ሳምንት የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ በስደተኞች ላይ ጥቃት የሚፈጽሙ ተቃዋሚ ሠልፈኞችን ኮንነው የአገሪቱን የስደተኛ ፖሊስ ለማሻሻል ቃል ገብተዋል።እንዲህ ዓይነት ተግባር ደቡብ አፍሪካንም ሆነ ፖሊሲዎቿን አይወክልም ያሉት ፕሬዚዳንቱ ሁሉም የአገሪቱን ሕግ እዲያከብር ጠይቀዋል።ያጋሩ, ጋና ዜጎቿን ከደቡብ አፍሪካ የፊታችን ሐሙስ ልታስወጣ ነው
  5. ከ 7 ሰአት በፊትዶናልድ ትራምፕ ኢራን ላይ ለመፈጸም ያሰቡትን ጥቃት ካዘገዩ በኋላ ከሥምምነት ላይ ለመድረስ “ጥሩ ዕድል” መኖሩን ተናገሩፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,EPAፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሰኞ ዕለት ኢራን የጦር መሣሪያ እንዳይኖራት ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ላይ ለመድረስ “በጣም ጥሩ ዕድል” መኖሩን ተናገሩ።ትራምፕ ይህንን የተናገሩት በኢራን ላይ ጥቃት ለመፈጸም ይዘውት የነበረውን ዕቅድ ካዘገዩ ከሰዓታት በኋላ ነው።ፕሬዚዳንቱ ቁልፍ የመካከለኛው ምሥራቅ አጋሮቻቸው ማክሰኞ ዕለት ለመፈጸም አቅደውት የነበረውን ዕቅድ ከቴህራን ጋር የሚደረገው ድርድር እንዲቀጥል በሚል እንዲያዘገዩት መጠየቃቸውን ተናግረዋል።ትራምፕ ሰኞ ዕለት ለጋዜጠኞች “አንድን ነገር ላይ ለመድረስ የሚያስችል በጣም ጥሩ ዕድል ያለ ይመስላል። በቦምብ ሳንደበድባቸው ያንን ማድረግ ከቻልን በጣም ደስተኛ እሆናለሁ” ብለዋል።የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ስምምነት ላይ ካልተደረሰ ጥቃት ለመፈጸም ዝግጁ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ጨምረው አስታውቀዋል።ዶናልድ ትራምፕ በባሕረ ሰላጤው አገራት ጥያቄ መሠረት ኢራን ላይ የሚፈጸምን አዲስ ጥቃት ማስቀረታቸውን ተናገሩያጋሩ, ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ላይ ለመፈጸም ያሰቡትን ጥቃት ካዘገዩ በኋላ ከሥምምነት ላይ ለመድረስ “ጥሩ ዕድል” መኖሩን ተናገሩ
  6. ከ 9 ሰአት በፊትበአሜሪካ መስኪድ ላይ በተከፈተ ተኩስ ሦስት ሰዎች መሞታቸው እና ተጠርጣሪዎቹ ራሳቸውን ማጥፋታቸው ተገለጸበሳንዲያጎ ታዳጊዎች ባደረሱት ጥቃት የሞቱ ሰዎች ማንነት ገና ይፋ አልሆነምየፎቶው ባለመብት,EPAሁለት ታዳጊዎች ራሳቸውን ከማጥፋታቸው በፊት በአሜሪካ ሳንዲያጎ በሚገኝ መስኪድ ላይ ጥቃት ከፍተው ሦስት ሰዎች መግደላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።ጥቃቱ የተፈጸመው ሰኞ ማለዳ ሲሆን ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።ፖሊስ በሳንዲያጎ በሚገኘው የሙስሊሞች ማዕከል ተኩስ መከፈቱን የሚገልጽ ጥቆማ አንደደረሰው ወደ ስፍራው ሲደርስ ሦስት ሰዎች በጥይት ተመትተው ማግኘቱን ገልጿል።ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በአቅራቢው ከሚገኝ መኪና ውስጥ ተኩስ መሰማቱን የሚገልጽ መረጃ ደርሶት ወደ ሥፍራው ሲያመራ የ17 እና የ18 ዓመት ታዳጊዎች ራሳቸውን አጥፍተው ማግኘቱን አስታውቋል።የከተማዋ ባለሥልጣናት ጥቃት ከደረሰባቸው እና ከሞቱት መካከል አንዱ በጥቃቱ የባሰ ጉዳት እንዳይደርስ “ወሳኝ ሚና የተጫወተ” የማዕከሉ ዘብ መሆኑን ተናግረዋል።የሳንዲያጎ ፖሊስ አዛዥ ስኮት ዋህል በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት “የጀግና ተግባር ነው የፈጸመው ማለት እንችላለን” ሲሉ አድንቀው “ያለምንም ጥርጥር ዛሬ ሕይወት አድኗል” ብለዋል።የከተማዋ ባለሥልጣናት የሟቾቹን ስም ይፋ አላደረጉም። ነገር ግን የማዕከሉ ዘብ የስምንት ልጆች አባት መሆኑን በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር የሆነው ሲቢኤስ ዘግቧል።መርማሪዎች ጥቃቱ የተፈጸመበት ምክንያት እንዳልተወቀ ተናግረዋል።ነገር ግን በሳንዲያጎ ግዙፍ በሆነው መስኪድ ላይ ጥላቻ ያላቸው ሊሆኑ አንደሚችሉ ተጠርጣሪው ከጻፈው በመነሳት ያላቸውን ጥርጣሬ ተናግረዋል።ያጋሩ, በአሜሪካ መስኪድ ላይ በተከፈተ ተኩስ ሦስት ሰዎች መሞታቸው እና ተጠርጣሪዎቹ ራሳቸውን ማጥፋታቸው ተገለጸ
  7. 19 ግንቦት 2026እስራኤል በሊባኖስ በፈጸመችው ድብደባ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ3,000 ማለፉን የአገሪቱ ባለሥልጣናት ተናገሩበእስረኤል ጥቃት የሞቱ ቤተሰቦቻቸውን የሚቀብሩ ሴቶችየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በእስራኤል እና በሊባኖስ መካከል የተኩስ አቁም ቢደረስም ከሄዝቦላህ ጋር የሚደረገው ውግያ እንደቀጠለ ነውየሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር በእስራኤል ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 3,000 ማለፉን አስታወቀ።እስራኤል እና ሄዝቦላህ ዳግም ወደ ግጭት የገቡት የኢራን ጦርነት በተጀመረ በሦስተኛው ቀን ነው።በሁለቱ አገራት መካከል በተደጋጋሚ የተኩስ አቁም ቢደረሰም አሁንም ውጊያዎች እየተካሄዱ ሲሆን ይህም ሰኞ ዕለት የሟቾችን ቁጥር 3,020 አድርሶታል።ሊባኖስ ዳግም ወደ ጦርነት ተጎትታ የገባችው በኢራን የሚደገፈው ሄዝቦላህ የቴህራኑ ጠቅላይ መሪ መገደላቸውን በመቃወም ወደ እስራኤል ሮኬቶችን በማስወንጨፉ ነው።አርብ ዕለት እስራኤል እና ሊባኖስ የተኩስ አቁማቸውን በ45 ቀናት ቢያራዝሙም የሟቾች ቁጥር እየጨመረ ነው።ሁለቱ አገራት ዳግም ድርድራቸውን በሰኔ ወር መጀመርያ ላይ ለመቀጠል ተስማምተዋል።የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር ከ400 በላይ ሰዎች የተገደሉት የተኩስ አቁም ስምምነቱ ሚያዚያ 9 2018 ዓ.ም. ከተደረሰ በኋላ ነው ሲል አስታውቋል።አሜሪካ ያደራደረችው ይህ የተኩስ አቁም ስምምነት እስራኤል የሄዝቦላህን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለመመከት ጥቃት እንድትፈጽም ይፈቅዳል።ሊባኖስ ጥቃቶቹን አውግዛ አገሪቱ ዳግም ታጣቂዎች የያዙትን መሣሪያ ለመቆጣጠር የምታደርገውን ጥረት ዝቅ የሚያደርግ ነው ብላለች።አርብ ዕለት ዳግመኛ የተኩስ አቁሙ ከተራዘመ በኋላ እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ የሚገኙ መንደሮችን በማጥቃት በርካቶችን ገድላለች።ቅዳሜ ዕለት በበርካታ መንደሮች ላይ ጥቃት ብትፈጽምም አካበቢውን ለቅቀው እንዲወጡ ቅድመ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ግን ዘጠኙ ብቻ ናቸው።የዚያኑ ዕለት ሄዝቦላህ በርካታ የድሮን ጥቃቶችን በእስራኤል ላይ መፈጸሙን አስታውቋል።የእስራኤል ጦር ቅዳሜ ዕለት አንድ ወታደሩ መገደሉን የገለጸ ሲሆን ይህም በዚህ ጦርነት የተገደሉ የእስራኤል ወታደሮችን ብዛት 20 አድርሶታል።ያጋሩ, እስራኤል በሊባኖስ በፈጸመችው ድብደባ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ3,000 ማለፉን የአገሪቱ ባለሥልጣናት ተናገሩ
  8. 18 ግንቦት 2026በኬንያ የነዳጅ ዋጋ መጨመርን በመቃወም አደባባይ የወጡ ከ200 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉየኬንያ ፖሊስየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየኬንያ ፖሊስ የነዳጅ ዋጋ መጨመርን በመቃወም አደባባይ ከወጡ መካከል ከ200 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስታወቀ።የናይሮቢ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኢሳ ሞሐሙድ በመላ አገሪቱ የተጠራን የትራንስፖርት ማቆም አድማን ተከትሎ ለተቃውሞ አደባባይ ከወጡ ሰዎች መካከል 225ቱ በቁጥጥር ሥር ውለዋል ብለዋል።በኬንያ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 10 2018 ዓ.ም. ከፍተኛ የነዳጅ ጭማሪን በመቃወም በመላ አገሪቱ የመጓጓዣ አገልግሎት ሰጪዎች ሥራ አቁመው ውለዋል።በናይሮቢ እና በዋና ዋና ከተማዎች የአውቶቡስ፣ የሞተር ሳይክል እና ሚኒባስ ትራንስፖርት አገልግሎት በመቋረጡ ተጠቃሚዎች ረዥም ርቀት በእግራቸው ለመጓዝ ተገድደዋል።በአንዳንድ አካባቢዎች ተቃዋሚ ሠልፈኞች መንገድ ዘግተው ጎማ ሲያቃጥሉ ታይተዋል።ፖሊስ መንገዶችን ለመክፈት በሚሞክርበት ወቅት ከተቃዋሚ ሠልፈኞቹ ጋር የተጋጨ ሲሆን ለመበተን አስለቃሽ ጋዝ ተጠቅሟል።የናይሮቢ ፖሊስ አዛዥ አምስት የፖሊስ እና አንድ የግለሰብ መኪኖች በሠልፈኞቹ መውደማቸውን አስታውቀዋል።እስካሁን ድረስ በተቃውሞ ሠልፉ ምክንያት የሞተ ሰው ስለመኖሩ የተባለ ነገር የለም።ባለፈው ሳምንት የኬንያ ኢነርጂ እና ፔትሮሊየም ቁጥጥር ባለሥልጣን በመካከለኛው ምሥራቅ ያለውን ውጥረት በመጥቀስ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ይፋ ካደረገ በኋላ ተቃውሞ ተቀስቅሷል።የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢዎች በተለይ ደግሞ የሕዝብ ማመላለሻ ባለንብረቶች እና አሽከርካሪዎች የዋጋ ጭማሪው ለመስራት አስቸጋሪ እንዳደረገባቸው ተናግረዋል።በተቃውሞ ምክንያት በርካታ የረዥም ርቀት ተጓዥ አውቶብሶች ጉዟቸውን በመሰረዛቸው የተነሳ መንገደኞች ተጉላልተዋል።ዛሬ በኬንያ በነበረው የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢዎች ተቃውሞ የተነሳ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም የንግድ ተቋማት ተዘግተው ውለዋል።የአገሪቱ ገንዘብ ሚኒስትር ጆን ምባዲ የዓለም አቀፍ ነዳጅ ዋጋ ንረት በመካከለኛው ምሥራቅ ካለው ጦርነት ጋር እንደሚያያዝ ጠቅሰው ይህም በአገሪቱ ለተከሰተው ጭማሪ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል።የዓለም የነዳጅ ዋጋ በዚሁ ከቀጠለ መንግሥት የታክስ እፎይታን ከግምት ሊያስገባ እንደሚችል ጨምረው አስታውቀዋል።የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢዎች እና የተሽከርካሪ ባለቤቶች መንግሥት የነዳጅ ዋጋ እንዲቀንስ ቢጠይቁም እስካሁን ድረስ ይህ ነው የሚባል መግባባት ላይ አልደረሱም።ያጋሩ, በኬንያ የነዳጅ ዋጋ መጨመርን በመቃወም አደባባይ የወጡ ከ200 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
  9. 18 ግንቦት 2026አሜሪካ ለወታደራዊ እርምጃ “ሐሰተኛ ምክንያቶችን” እያደራጀች ነው ስትል ኩባ ከሰሰችኩባውያን በከፍተኛ የነዳጅ እጥረት ምክንያት የኃይል መቆራረጥ አጋጥሟቸዋልየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ኩባውያን በከፍተኛ የነዳጅ እጥረት ምክንያት የኃይል መቆራረጥ አጋጥሟቸዋልየኩባ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አገራቸው የፍሎሪዳ ግዛትን ማጥቃት የሚችል ድሮን አግኝታለች የሚል ዘገባን ተከትሎ አሜሪካ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ “ሐሰተኛ ምክንያቶችን” እያደራጀች ነው ሲሉ ከሰሱ።ብሩኖ ሮድሪጌዝ የአሜሪካ የዜና ድረገጽ አክሲዮስ ዘገባን ተከትሎ ሃቫና “አትፈራም እንዲሁም ጦርነት አትፈልግም” ሲሉ ተናግረዋል።አክሲዮስ ምሥጢራዊ የደኅንነት መረጃዎችን ጠቅሶ ኩባ በአቅራቢያዋ የሚገኙ የአሜሪካ ዒላማዎችን ማጥቃት የሚችሉ 300 ድሮኖች ታጥቃለች ሲል ዘግቧል።አሜሪካ ኩባን “ለስምምነት እንድትቀመጥ” ለማስገደድ በሚል ወደ ግዛቷ የሚሄድን ነዳጅ ካገደች በኋላ አገሪቱ ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት ገጥሟታል።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የኩባ ኮሚኒስት አመራሮችን የቬንዙዌላ ፕሬዝዳንት ማዱሮን ለመያዝ የወሰዱትን ወታደራዊ እርምጃ ዓይነት እንደሚጠብቃቸው አስጠንቅቀዋል።ኩባ ድሮኖችን በመጠቀም በካሪቢያን ደሴት ላይ የሚገኘውን የአሜሪካ ወታደራዊ የጦር ሠፈር፣ ጓንታናሞ ቤይን እንዲሁም የባሕር ኃይል መርከቦችን እና ፍሎሪዳ ከተማን የማጥቃት ፍላጎት እንዳላት አክሲዮስ እሁድ ዕለት ዘግቧል።ዘገባው የአሜሪካ የደኅንነት ባለሥልጣንን ጠቅሶ የኢራን ወታደራዊ አማካሪዎች በሃቫና ይገኛሉ ያለ ሲሆን፣ ይህም ለአሜሪካ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ሰበብ ሊሆን ይችላል ተብሏል።ሮድሪጌዝ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ “ምንም ዓይነት ቅቡልነት የሌለው ማስረጃ፣ የአሜሪካ መንግሥት ከቀን ወደ ቀን በኩባ ሕዝብ ላይ እያካሄደ ላለው ከባድ የኢኮኖሚ ጦርነት እና ለሚከፍተው ወታደራዊ ጥቃት ሐሰተኛ ምክንያቶችን እያደራጀ ነው” ሲሉ ጽፈዋል።“የተለዩ የመገናኛ ብዙኃን የአሜሪካ መንግሥት ጎጂ ውንጀላዎችን በማሠራጨት ረገድ ድጋፍ እያደረጉ ነው።”አክለውም ኩባ ጦርነት የማትፈልግ ብትሆንም ራሷን “ከውጭ ወረራ” ለመከላከል እየተዘጋጀች ነው ብለዋል።ሃቫና ለበርካታ ወራት ከአሜሪካ ጋር ያላትን ልዩነት ለመፍታት ንግግሮችን እያደረገች ነው። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ከሩሲያ እንዲገባ የተደረገ ነዳጅ እያለቀ መሆኑ ተዘግቧል።ኩባውያን በከፍተኛ የነዳጅ እጥረት ምክንያት የኃይል መቆራረጥ ያጋጠማቸው ሲሆን፣ በዚህም የተነሳ የሕዝብ ትራንስፖርት፣ የውሃ ማሠራጫዎች፣ የቆሻሻ ማስወገጃዎች እንዲሁም ሆስፒታሎች ሥራቸውን ለማቋረጥ እየተገደዱ ነው።ያጋሩ, አሜሪካ ለወታደራዊ እርምጃ “ሐሰተኛ ምክንያቶችን” እያደራጀች ነው ስትል ኩባ ከሰሰች
  10. 18 ግንቦት 2026የሳዑዲ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኢትዮጵያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩየሳዑዲ አረቢያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሊድ አብዱልከሪም አል ካሪጅ ከኢትዮጵያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋርየፎቶው ባለመብት,Ministry of Foreign Affairs of Ethiopiaየምስሉ መግለጫ,የሳዑዲ አረቢያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሊድ አብዱልከሪም አል ካሪጅ ከኢትዮጵያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋርየኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ እና የሳዑዲ አረቢያ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአዲስ አበባ ተገናኝተው ተወያዩ።ሰኞ ዕለት ግንቦት 10 2018 ዓ.ም. ሁለቱ ሚኒስትሮች በሁለትዮሽ ጉዳዮች እና በቀጣናው ባላቸው የጋራ ፍላጎት ዙሪያ መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማኅበራዊ ድረገጹ ላይ አስታውቋል።በተጨማሪም ባለሥልጣናቱ ከፖለቲካ እና ከፀጥታ ጉዳዮች ባሻገር፣ በሁለቱ አገራት መካከል ባለው ግንኙነት፣ ሕጋዊ የሠራተኛ ስምሪት ላይ መወያየታቸው ተገልጿል።በቀጣናዊ ሰላም እና ደኅንነት ዙሪያ የተወያዩት ሁለቱ ሚኒስትሮች በአካባቢው ላሉ የተለያዩ ግጭቶች ብቸኛው መፍትሔ በውይይት ፖለቲካዊ መፍትሄ መፈለግ መሆኑን መነጋገራቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።ምክትል የሳዑዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢንጂነር ዋሊድ አብዱልከሪም አል ካሪጅ በየካቲት ወር አሥመራን ከጎበኙ በኋላ ወደ አዲስ አበባ መጥተው ነበር።ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በሦስተኛ ወራቸው ወደ አዲስ አበባ የተመለሱ ሲሆን፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ጋር በሁለቱ አገራት የረዥም ጊዜ ወዳጅነት እና የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ዙሪያ ተወያይተዋል።ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የአገራቱ ግንኙነትን በማጠናከር በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ደኅንነት መጠበቅ እንዲሁም ለኢትዮጵያውያን ሠራተኞች ሕጋዊ የሥራ ቅጥር እንዲመቻች መጠየቃቸው ተገልጿል።በሳዑዲ አረቢያ ከ200 የሚበልጡ ኢትዮጵያውያን በደቡባዊ የአገሪቱ ክፍል በሚገኝ እስር ቤት የሞት ቅጣት እንደተፈረደባቸው እና ሌሎች 65 የሚሆኑ ስደተኞችም ተመሳሳይ ፍርድ እንደሚጠብቃቸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አስታውቀዋል።ኢንጂነር ዋሊድ አብዱልከሪም አል ካሪጅ በበኩላቸው ለኢትዮጵያውያን ሠራተኞች ደኅንነቱ የተጠበቀ የሥራ ዕድል ለማረጋገጥ ሕጋዊ የሠራተኛ ቅጥር አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል።በተጨማሪም አገራቱ በጋራ ጉዳዮች ላይ ተመሳሳይ አመለካከት እንዳላቸው በመግለጽ፣ በመካከላቸው ያለውን ግንኙነት ለሁለቱ አገራት ጥቅም በሚያመጣ መልኩ መጠናከሩ አስፈላጊ መሆኑን አመልክተዋል።የሳዑዲ አረቢያው ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አገራቸው ከኢትዮጵያና ከሕዝቦቿ ጋር ያላትንታሪካዊ እና የረጅም ዘመን ግንኙነት እጅግ እንደምታከብር መግለጻቸውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያሠራጨው መረጃ አመልክቷል።የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞትዮስ እና የሳዑዲ አረቢያ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርየፎቶው ባለመብት,Ministry of Foreign Affairs of Ethiopiaያጋሩ, የሳዑዲ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኢትዮጵያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
  11. 18 ግንቦት 2026ቢያንስ 6 አሜሪካውያን በኮንጎ ለተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ መጋለጣቸውን ተዘገበየሙቀት መጠኗ የሚለካ ሴትየፎቶው ባለመብት,AFPበዴሞክራቲክ ኮንጎ በተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ስድስት አሜሪካውያን ለቫይረሱ ተጋልጠዋል ሲሉ ምንጮች በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር ለሆነው ሲቢኤስ ኒውስ ተናገሩ።የዓለም የጤና ድርጅት ወረርሽኙን አሳሳቢ ዓለም አቀፍ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ መሆኑን አውጇል።የዲሞክራቲክ ኮንጎ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር 350 የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው እንደተጠረጠረ እና 91 ሰዎች ደግሞ መሞታቸውን ዘግቧል።አንድ አሜሪካዊ የበሽታው ምልክቶች እንደታዩበት የተገለጸ ሲሆን፣ ሌሎች ሦስት ደግሞ ከፍተኛ ተጋላጭነት ወይም ንክኪ አላቸው ተብሏል።የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) “በቀጥታ የተጎዱ ጥቂት አሜሪካውያንን ደኅንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ለቅቀው እንዲወጡ” ለማድረግ ድጋፍ እንደሚያደርግ ቢገልጽም ምን ያህል አሜሪካውያን እንደሆኑ ግን አላረጋገጠም።የአሁኑ የኢቦላ ዝርያ የሚከሰተው በቡንዲቡግዮ ቫይረስ ሲሆን፣ ለዚህም ምንም ዓይነት የተረጋገጡ መድኃኒቶች ወይም ክትባቶች የለም።በኡጋንዳ ሁለት ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውሲረጋገጥ፣ አንድ ደግሞ መሞቱን የሲዲሲ አፍሪካ ዘገባ አመልክቷል።የአሜሪካ መንግሥት በዲሞክራቲክ ኮንጎ ለሚገኙት ዜጎቹ ደኅንነቱ ወደ ተጠበቀ የለይቶ ማቆያ ስፍራ ለማጓጓዝ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አንድ ምንጭ ለስታት የጤና ድረገጽ ተናግረዋል።በተጨማሪም አሜሪካውያኑ ጀርመን ወደሚገኝ የአሜሪካ ወታደራዊ ጣቢያ ሊወሰዱ እንደሚችል ድረ ገጹ ዘግቧል።የዓለም ጤና ድርጅት ዴሞክራቲክ ኮንጎ እና ኡጋንዳ ወረርሽኙን ለመከታተል፣ በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸውን ለመለየት እና የመከላከያ እርምጃዎችን ለመተግበር የሚያስችሉ የአስቸኳይ ጊዜ ማዕከላትን እንዲያቋቁሙ መክሯል።ሥርጭቱን ለመግታት እንዲቻል በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች፤ በ48 ሰዓታት ልዩነት በሚደረጉ ሁለት የቫይረሱ ምርመራዎች ነፃ መሆናቸው እስከሚረጋገጥ ድረስ ወዲያውኑ ለብቻ ሊለዩ እና ሕክምና ሊደረግላቸው እንደሚገባ ተቋሙ ገልጿል።በሽታው መከሰቱ የተረጋገጠባቸውን አገራት የሚያዋስኑ ጎረቤት መንግሥታት የቅኝት እና የጤና ሪፖርት ሥራቸውን እንዲያጠናክሩም ተነግሯቸዋል።ያጋሩ, ቢያንስ 6 አሜሪካውያን በኮንጎ ለተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ መጋለጣቸውን ተዘገበ
  12. 18 ግንቦት 2026ኢራን ለአሜሪካ አዲስ የሰላም ዕቅድ በፓኪስታን በኩል ማቅረቧ ተነገረፓኪስታንየፎቶው ባለመብት,Reutersበመካከለኛው ምሥራቅ የሚካሄደውን ጦርነት ያስቆማል የተባለ ኢራን ያቀረበችውን አዲስ ዕቅድ ፓኪስታን ለአሜሪካ መስጠቷን ምንጮች ለሮይተርስ ተናገሩ።በሁለቱ አገራት መካከል እየተካሄደ ያለው የሰላም ድርድር ውጤት ሳያስገኝ በእንጥልጥል ባለበት ወቅት ዛሬ ሰኞ ነው ፓኪስታን የኢራንን አዲስ ዕቅድ ለአሜሪካ ያቀረበችው።ምንጮች በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ልዩነት በዚህኛው የሰላም ዕቅድ ማጥበብ ይቻል እንደሆነ ተጠይቀው “ጊዜ የለንም” ብለዋል፤ አክለውም ሁለቱም አገራት “የሚፈልጉትን በየጊዜው ይቀያይራሉ” በማለት ከስምምነት ያልተደረሰበትን ምክንያት ጠቅሰዋል።የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አገራቸው ዩራኒየም የማበልጸግ መብቷ “ድርድር የሚደረግበት ወይም ከአቋም ፈቀቅ የሚባልበት ጉዳይ” እንዳልሆነ የተናገሩት ዛሬ ነበር።”በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው፤ ዩራኒየም የማበልጸግ መብት ለድርድር የሚቀርብ ወይም የሚለወጥ አይደለም። ኢራን ዩራኒየም ለማበልጸግ ያላት መብት የኒውክሌር መሣሪያዎች ላለማስፋፋት በተፈረመው ስምምነት መሠረት ዕውቅና የተሰጠው ነው” ብለዋል።የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው የኢራን ባለሥልጣናት ከስምምነት ለመድረስ መፍጠን እንዳለባቸው በመግለጽ “ጊዜው እየተገባደደ ነው” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።ትራምፕ ማስጠንቀቂያውን የሰጡት ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር ትናንት እሑድ በስልክ መነጋገራቸውን ተከትሎ ነው።ያጋሩ, ኢራን ለአሜሪካ አዲስ የሰላም ዕቅድ በፓኪስታን በኩል ማቅረቧ ተነገረ
  13. 18 ግንቦት 2026ኢራን ዩራኒየም የማበልጸግ መብቷ ላይ “እንደማትደራደር ወይም ከአቋሟ ፈቀቅ እንደማትል” ገለጸችየኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አቀባዩ ኢስማኢል ባቃኢየፎቶው ባለመብት,Reutersየኢራን ዩራኒየም የማበልጸግ መብት “ድርድር የሚደረግበት ወይም ከአቋም ፈቀቅ የሚባልበት ጉዳይ” እንዳልሆነ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ተናገሩ።ቃል አቀባዩ ኢስማኢል ባቃኢ ዛሬ ሰኞ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ጦርነቱን ለመቋጨት በፓኪስታን አማካኝነት የሚደረገው ንግግር መቀጠሉን ገልጸዋል።ኢራን ባለ 14 ነጥብ የስምምነት ዕቅድ ወደ አሜሪካ ልካ እንደነበር ያስታወሱት ቃል አቀባዩ፤ ዋሽንግተንም ሆነ ቴህራን በዕቅዱ ላይ የራሳቸውን ሐሳብ ማንሳታቸውን ተናግረዋል።“የአሜሪካው ወገን ይህ [ባለ 14 ነጥብ] ዕቅድ ውድቅ መደረጉን ባለፈው ሳምንት በይፋ ቢያስታውቅም፤ ያቀረቧቸው ነጥቦች እና የማስተካከያ አስተያየቶች ዝርዝር ግን በፓኪስታን አማካኝነት ደርሶናል” ብለዋል።“ዕቅዳችንን በላክን ማግስት ከሌላኛው ወገን የቀረቡ ተከታታይ ዕቅዶች ደርሰውናል። ዕቅዶቹ ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ የተገመገሙ ሲሆን የእኛ ምላሽም ቀርቧል። በፓኪስታን አማካኝነት የሚደረገው ድርድር ቀጥሏል” ሲሉም ንግግሩን የማስጀመር ሂደቱ ያለበትን አረስድተዋል።ይህም ቢሆን ግን ኢራን ዩራኒየም የማበልጸግ መብቷን ለድርድር እንደማታቀርብ ባቃኢ ተናግረዋል።”በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው፤ [ዩራኒየም የማበልጸግ] መብት ልንደራደርበት ወይም ከአቋም ፈቀቅ የምንልበት ጉዳይ አይደለም። ኢራን ዩራኒየም ለማበልጸግ ያላት መብት የኒውክሌር መሣሪያዎች ላለማስፋፋት በተፈረመው ስምምነት መሠረት እውቅና የተሰጠው ነው” ብለዋል።እንደ ቃል አቀባዩ ገለጻ ኢራን የምትፈልጋቸው የድርድር ነጥቦች በግልጽ ተቀምጠዋል። እንዳይንቀሳቀሱ የታገዱ የኢራን ሀብቶች መለቀቅን በማሳያነት ያነሱት ቃል አቀባዩ፤ “እናንተ እኛ [ለድርድር] ያስቀመጥነው ቅድመ ሁኔታ እንደሆነ ትናገራላችሁ፤ እኛ የመብት ጥያቄ እንደሆነ እንናገራለን” ብለዋል።ያጋሩ, ኢራን ዩራኒየም የማበልጸግ መብቷ ላይ “እንደማትደራደር ወይም ከአቋሟ ፈቀቅ እንደማትል” ገለጸች
  14. 18 ግንቦት 2026ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን ላይ ሊወሰዱ ስለሚችሉ ወታደራዊ አማራጮች ‘በሲቹዌሽን ሩም’ ሊሰበሰቡ መሆኑ ተዘገበፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ላይ ሊፈጸሙ ስለሚችሉ ወታደራዊ አማራጮች ለመወያየት ማክሰኞ ዕለት ከፍተኛ የብሔራዊ ደኅነት አመራሮቻቸውን ይሰበስባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አክሲዮስ ዘገበ።የአሜሪካው የዜና ምንጭ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮችን ጠቅሶ ባወጣው ዘገባ፤ የፕሬዝዳንቱ የብሔራዊ ደኅንነት ቡድን አባላት ስለ ኢራን ለመወያየት ቅዳሜ ዕለትም ተሰብስበው ነበር።ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫምስ፣ የዋይት ሃውስ መልዕክተኛ ስቲፍ ዊትኮፍ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ እና የሲአይኤ ዳይሬክተር ጆን ራትክሊፍ ከተሰብሳቢዎቹ መካከል ነበሩ ተብሏል።ትራምፕ ለአክሲዮስ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፤ ከኢራን ጋን ስምምነት ላይ ይደረሳል ብለው እንደሚያስቡ ተናግረዋል።የኢራን የድርድር ዕቅድ ላይ የሚደረገውን ማሻሻያ እየጠበቁ መሆኑን የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ፤ ከቀናት በፊት ከቀረበው የተሻለ ይሆናል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉም ጠቅሰዋል። ለድርድሩ ቀነ ገደብ ከማስቀመጥ ግን ተቆጥበዋል።“ስምምነት መፈጸም እንፈልጋለን። እንዲሆኑ የምንፈልገው ቦታ ላይ አይደሉም። እዚያ መረድስ አለባቸው ወይም ክፉኛ ይመታሉ፤ ያንን ደግሞ አይፈልጉም” ብለዋል።አሜሪካ እና ኢራን ከመጀመሪያው ዙር ድርድር በኋላ ንግግሩን ለማስቀጠል አልተገናኙም።አሸማጋይ ሆና እየተንቀሳቀሰች ያለቸው ፓኪስታን ቅዳሜ ዕለት የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሯን ወደ ቴህራን ልካ ነበር። ድርድሩን ለማስጀመር እሑድ ዕለትም ከኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ሲነጋገሩ ነበር።ያጋሩ, ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን ላይ ሊወሰዱ ስለሚችሉ ወታደራዊ አማራጮች ‘በሲቹዌሽን ሩም’ ሊሰበሰቡ መሆኑ ተዘገበ
  15. 18 ግንቦት 2026የእስራኤል ጦር ከኢራን ጋር ለሚኖር ሌላ ዙር ጦርነት እየተዘጋጀ መሆኑ ተዘገበጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁየፎቶው ባለመብት,AFPየምስሉ መግለጫ,ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ (ፎቶ ከፋይል)እስራኤል በቀጣይ በኢራን ላይ ሊፈጸም በሚችለው ጥቃት ውስጥ ሠራዊቷ ከአሜሪካ ጎን እንዲሳተፍ ለማድረግ እየተዘጋጀች መሆኑን የእስራኤል መገናኛ ብዙኃን ዘገበ።ካን የተባለው ቴሌቪዥን ጣቢያ ስማቸው ያልተጠቀሰ የእስራኤል የደኅንነት ባለሥልጣንን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው፤ አሜሪካ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት ከጀመረች እስራኤል በዘመቻው ውስጥ በመሳተፍ የኢራንን “የኃይል ማመንጫ መሠረተ ልማቶችን” ዒላማ ታደርጋለች ብለዋል።ይህ ዘገባ የተሰማው ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ እሑድ ዕለት በስልክ ከተወያዩ እንዲሁም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ኢራን ከስምምነት ለመድረስ ያላት ጊዜ ወደ ማብቂያው እየተቃረበ መሆኑን ከገለጹ በኋላ ነው።ካን ቴሌቪዥን እንደዘገበው በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር እና በአሜሪካው ፕሬዝዳንት መካከል የተደረገው የስልክ ውይይት ከግማሽ ሰዓት በላይ የቆየ ሲሆን፣ ከኢራን ጋር ሌላ ዙር ጦርነት ሊከሰት በሚችልበት ሁኔታ ላይ ተነገግረዋል።ሌላኛው የእስራኤል ቴሌቪዥን ቻናል 12 ደግሞ በሁለቱ መሪዎች መካከል የተደረገውን የስልክ ውይይት “ከኢራን ጋር ለሚደረግ አዲስ ጦርነት በሚደረግ ዝግጅት ጥላ ስር” መካሄዱን በመጥቀስ የእስራኤል ጦርም ለአዲስ ግጭት በሙሉ ተጠንቀቅ ላይ” መሆኑን ዘግቧል።በተጨማሪም ቻናል 13 የተባለው የእስራኤል ቴሌቪዥን ጣቢያ በርካታ የጭነት አውሮፕላኖች የጦር መሳሪያዎችን ይዘው ወደ እስራኤል መግባታቸውን ዘግቧል።ዘገባው ጨምሮም የጭነት አውሮፕላኖቹ ጀርመን ውስጥ ከሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች ተነስተው ባለፉት 24 ሰዓተት ቴል አቪቭ ውስጥ አርፈዋል።ያጋሩ, የእስራኤል ጦር ከኢራን ጋር ለሚኖር ሌላ ዙር ጦርነት እየተዘጋጀ መሆኑ ተዘገበ
  16. 18 ግንቦት 2026ኩዌት እና ኳታር በሳዑዲ አረቢያ ላይ የተፈጸመውን የድሮን ጥቃት አወገዙኩዌት እና ኳታር በተናጠል ባወጧቸው መግለጫዎች፤ ከኢራቅ የአየር ክልል በመነሳት ሳዑዲ አረቢያ ላይ የተሰነዘረውን የድሮን ጥቃት አወገዙ።ኩዌት፤ ይህ ድርጊት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በባሕረ ሰላጤው መሠረተ ልማቶች ለመጠበቅ ያሳለፈውን ውሳኔ የሚጥስ ነው ብላለች።ሳዑዲ አረቢያ ደኅንነቷን ለማስጠበቅ ለምትወስዳቸው እርምጃዎች ያላትን ድጋፍም ገልጻለች።ኳታር በበኩሏ ድርጊቱን “ተቀባይነት የሌለው ጥቃት” እና የሳዑዲን ሉዓላዊነት በግልጽ የጣሰ ስትል ገልጻዋለች።ሁለቱም አገራት ለሪያድ ያላቸውን ሙሉ አጋርነት የገለጹ ሲሆን፤ ሳዑዲ ግዛቷን እና ዜጎቿን ለመጠበቅ የምትወስዳቸውን ማናቸውንም እርምጃዎች እንደሚደግፉ አስታውቀዋል።ኳታር እና ኩዌት መግለጫ ያወጡት ሳዑዲ አረቢያ የአየር መከላከያ ሥርዓቶቿ ሦስት የጥቃት ድሮኖችን መትተው መጣላቸውን ካስታወቀች በኋላ ነው።ያጋሩ, ኩዌት እና ኳታር በሳዑዲ አረቢያ ላይ የተፈጸመውን የድሮን ጥቃት አወገዙ
  17. 18 ግንቦት 2026የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኒውክሌር ጣቢያ አቅራቢያ ጥቃት መፈጸሙ ተገለጸየተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኒውክሌር ኃይል ማመንጫየፎቶው ባለመብት,AFPየምስሉ መግለጫ,የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኒውክሌር ኃይል ማመንጫየተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እሑድ ዕለት የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዋ አቅራቢያ የተፈጸመው የድሮን ጥቃት እሳት እንዲነሳ ማድረጉን አስታወቀች።ክስተቱን “አደገኛ [የግጭት] መባባስ” ስትል የጠራችው ኤምሬቶች፤ ባለሥልጣናት ጥቃቱ ከየት እንደተፈጸመ እየመረመሩ መሆኑን ገልጻለች።የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር እንደገለጸው ድሮኖች ወደ ኤምሬቶች ግዛት የገቡት “በምዕራብ የድንበር አቅጣጫ” በኩል ነው።ሁለቱ ድሮኖች እንደተጠለፉ እና ሦስተኛው ግን በአቡ ዳቢ የሚገኘው የባራካህ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ “ከውስጣዊው ቅጥር ግቢ ይዞታ ውጭ” የሚገኝ የኤሌክትሪክ ጄነሬተርን እንደመታ ተገልጿል። እሳቱም የተነሳው በዚሁ ምክንያት ነው ተብሏል።በጥቃቱ ጉዳት አለመድረሱን የሚናገሩት ባለሥልጣናቱ፤ በአካባቢው የራዲዮሎጂካል ደኅንነት ደረጃ ላይም ተጽዕኖ አለማሳደሩን ገልጸዋል።የኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ክስተቱን “ተቀባይነት የሌለው የጥቃት ድርጊት” በማለት ጠርቶታል። የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ለማንኛውም ጠበኛ ድርጊት ምላሽ የመስጠት መብት እንዳላት አስታውቋል።ሚኒስቴሩ “ሰላማዊ የኒውክሌር ኃይል ተቋማትን ዒላማ ማድረግ ግልጽ የዓለም አቀፍ ሕግ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስምምነት እና የሰብአዊ ሕግ መርሆዎች ጥሰት ነው” ብሏል።የኤምሬቶች መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ “የአገሪቱን ደኅንነት ለማዳከም የሚደረጉ ማናቸውንም ሙከራዎች በጽናት እንደሚጋፈጥ” አስታውቋል።የአገሪቱ ባለሥልጣናት ድሮኑ ከየት እንደተተኮሰ እስካሁን አልገለጹም። ከዚህ ቀደም ግን ኤምሬቶች ከጦርነቱ መነሳት ወዲህ በነዳጅ እና በኢኮኖሚ መሠረተ ልማቶቿ ላይ ከተፈጸሙ ጥቃቶች ጀርባ ኢራን እንዳለች በመግለጽ በተደጋጋሚ ከስሳለች።የተባበሩት መንግሥታት የኒውክሌር ተቆጣጣሪ ተቋም ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ገልጿል። የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ራፋኤል ግሮሲ በክስተቱ “ከፍተኛ ስጋት” እንደገባቸው ተናግረዋል።ዋና ዳይሬክተሩ በዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ የኤክስ ገጽ በወጣው መግለጫቸው፤ “የኒውክሌር ደኅንነትን አደጋ ላይ የሚጥል ወታደራዊ እንቅስቃሴ ተቀባይነት የለውም” ብለዋል።ያጋሩ, የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኒውክሌር ጣቢያ አቅራቢያ ጥቃት መፈጸሙ ተገለጸ
  18. 18 ግንቦት 2026ትራምፕ “ጊዜው እየተገባደደ ነው” ሲሉ ኢራንን አስጠነቀቁየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Reutersየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ጊዜው እየተገባደደ ነው” ሲሉ ኢራንን አስጠነቀቁ።የሁለቱ አገራት የሰላም ንግግር እንደተቋረጠ ሲሆን፤ ትራምፕ “በአፋጣኝ እንቅስቃሴ ማድረግ አለባቸው፤ ካልሆነ አንዳች ነገራቸው እንኳ አይተርፍም” ብለው ዝተዋል። በትሩዝ ሶሻል ማኅበራዊ ሚዲያቸው ላይ “ዋናው ነገር ጊዜ ነው” ብለዋል።ትራምፕ ማስጠንቀቂያውን የሰጡት ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር ትናንት እሑድ በስልክ መነጋገራቸውን ተከትሎ ነው።ቴህራን ጦርነቱን ለማቆም ያቀረበችው የሰላም ዕቅድ ላይ አሜሪካ ከስምምነት መድረስ አለመቻሏን የኢራን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።ዋሽንግተን የሰላም ዕቅዱ ተቀባይነት እንዲኖረው ጥረት ካላደረገች ውጤት እንደማይገኝ የኢራኑ መህር የዜና ወኪል ዘግቧል።ያሳለፍነው ሳምንት ትራምፕ የሁለቱ አገራት የተኩስ አቁም “በቋፍ ላይ ነው” ሲሉ ዘላቂነቱ አጠራጣሪ መሆኑን ገልጸዋል።የኢራን የሰላም ዕቅድ “ተቀባይነት የሌለው ነው” ብለው ትራምፕ ቢያጣጥሉም፤ የኢራን የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ኢስማኤል ባጊ “ምክንያታዊ እና ለጋስ” ነጥቦች እንዳቀረቡ ተናግረዋል።ያጋሩ, ትራምፕ “ጊዜው እየተገባደደ ነው” ሲሉ ኢራንን አስጠነቀቁ