የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ፤ አሜሪካ በድጋሚ ጥቃት መሰንዘር ጀመረች “ብዙ አዳዲስ ነበር ይጠብቃታል” በማለት ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዛቻ ምላሽ ሰጡ። ትራምፕ ቴህራን ላይ በድጋሚ ጥቃት ለመክፈት መዛታቸውን ተከትሎ “ወደ ውጊያ አውድማ ከተመለሱ ብዙ አዳዲስ ነገር እንደሚጠብቃቸወ ላረጋግጥ እወዳለሁ” ሲሉ አራግቺ አስጠንቅቀዋል።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 1 ሰአት በፊትኢራን በድጋሚ ጥቃት ከተከፈተባት ግጭቱ “ቀጣናውን እንደሚሻገር” አስጠነቀቀችየኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ወታደሮችየፎቶው ባለመብት,EPAአሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ በድጋሚ ጥቃት ከሰነዘሩ ግጭቱ “ከቀጠናውም ያለፈ እንደሚሆን” የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ አስጠነቀቀ።ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና እስራኤል በድጋሚ ኢራን ላይ ጥቃት ለመጀመር እየዛቱ ይገኛሉ።የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ባወጣው መግለጫ “ኢራን ላይ በድጋሚ ወረራ ከተፈጸመ፤ ቀጣናውን ያዳርሳል የተባለው ጦርነት ከቀጣናውም ይሻገራል” ብሏል።“የምንወስደው ደምሳሽ እርምጃ አስባችሁ የማታውቁት ቦታ ሳይቀር ይደርሳል” ሲልም አብዮታዊ ዘቡ አስጠንቅቋል።የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ አሜሪካ በድጋሚ ጥቃት መሰንዘር ከጀመረች “ብዙ አዳዲስ ነገር ይጠብቃታል” በማለት ለትራምፕ ዛቻ ምላሽ ሰጥተዋል።ያጋሩ, ኢራን በድጋሚ ጥቃት ከተከፈተባት ግጭቱ “ቀጣናውን እንደሚሻገር” አስጠነቀቀች
  2. ከ 1 ሰአት በፊትአሜሪካ እና እስራኤል ማህሙድ አህመዲነጃድን ወደ ኢራን መሪነት ለማምጣት ዕቅድ እንደነበራቸው ተዘገበየኢራን የቀድሞ ፕሬዝዳንት ማህሙድ አህመዲነጃድየፎቶው ባለመብት,EPA-EFE/REX/Shutterstockየምስሉ መግለጫ,የኢራን የቀድሞ ፕሬዝዳንት ማህሙድ አህመዲነጃድአሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ በፈጸሙት የመጀመሪያ ጥቃት ወቅት በቁም እስር ላይ ናቸው የተባሉትን የኢራን የቀድሞ ፕሬዝዳንት ማህሙድ አህመዲነጃድን ለማስለቀቅ እና የመንግሥት ለውጥ ለማምጣት የተቃደ ዓላማ እንደነበረው የአሜሪካው ጋዜጣ ኒው ዮርክ ታይምስ ዘገበ።ጋዜጣው እንዳለው የእስራኤልን የመጀመሪያ ዙር ጥቃት ተከትሎ የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከተገደሉ በኋላ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በይፋ ሁኔታው የአገሪቱን አመራር ለመረከብ “አገር ውስጥ ላለ አንድ ሰው የተሻለ ነው” ሲሉ ተናግረው ነበር ሲል አስታውሷል።“ይህም አሜሪካ እና እስራኤል ወደ ጦርነቱ የገቡት ግልጽ የሆነ እና ያልተጠበቀ ዓላማን ይዘው እንደሆነ አሁን ግልጽ ሆኗል” በማለት “በፀረ እስራኤል እና አሜሪካ ጠንካራ አቋማቸው የሚታወቁት የቀድሞው የኢራን ፕሬዝዳንት መሐሙድ አህመዲነጃድ” ምርጫቸው እንደነበሩ ዘግቧል።ኒው ዮርክ ታይምስ “ስለ ዕቅዱ ገለጻ የተደረገላቸው የአሜሪካ ባለሥልጣናት ይህ ያልተጠበቀ ሐሳብ የተዘጋጀው በእስራኤል መሆኑን እና አህመዲነጃድም እንደሚያውቁት ተደርጎ የነበረ ቢሆንም በፍጥነት ከታሰበው ውጪ ሆኗል” በማለት ገልጿል።የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ከቁም እስር ለማስለቀቅ በመኖሪያ ቤታቸው ላይ ጥቃት የተፈጸመ ሲሆን ዜናውም በተነገረበት ጊዜ አህመዲነጃድ በጥቃቱ መገደላቸው ቢዘገብም በአጭር ጊዜ ውስጥ በሕይወት እንዳሉ የማስተባበያ ዜናዎች ወጥተዋል።ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ባለፉት ሦስት ወራት ማህሙድ አህመዲነጃድ በጥቃቱ ስለደረሰባቸው ጥቃትም ሆነ ስላሉበት ሁኔታ ምንም የተነገረ ነገር ካለመኖሩም በተጨማሪ በይፋ ታይተው አይታወቁም።ያጋሩ, አሜሪካ እና እስራኤል ማህሙድ አህመዲነጃድን ወደ ኢራን መሪነት ለማምጣት ዕቅድ እንደነበራቸው ተዘገበ
  3. ከ 2 ሰአት በፊትበእስራኤል ጥቃት ቢያንስ 19 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸበደቡብ ሊባኖስ የደረሰው ጥቃትየፎቶው ባለመብት,Reutersእስራኤል በደቡብ ሊባኖስ ባደረሰችው የአየር ጥቃት ቢያንስ 19 ሰዎች መገደላቸውን የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።ከተገደሉት መካከል ሦስት ሕጻናት እና ሦስት ሴቶች እንደሚገኙበት ተገልጿል።አሥር የሚደርሱት ሰዎች በዲር ቆኖን ከተማ አንድ ቤት ላይ በተፈጸመ ጥቃት መገደላቸው የጤና ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል።አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጦርነት መክፈታቸውን ተከትሎ የሊባኖስ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላህ የውጊያው አካል ሆኗል።እስራኤል እና ሊባኖስ የተኩስ አቁም ስምምነታቸውን በ45 ቀናት ማራዘማቸውን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ሳምንት ቢናገሩም፤ ጥቃቶች መቀጠላቸው ተገልጿል።አብዛኛው ጥቃት እየደረሰ ያለው በደቡብ ሊባኖስ ነው። እስራኤል ሄዝቦላህን ዒላማ ማድረጓን ብትገልጽም ሕጻናትን ጨምሮ ንጹኃን ዜጎችም መገደላቸውን ሊባኖስ አስታውቃለች።ያጋሩ, በእስራኤል ጥቃት ቢያንስ 19 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ
  4. ከ 4 ሰአት በፊትየቻይናው ፕሬዝዳንት የመካከለኛው ምሥራቅ ሁኔታ “ቁልፍ የሆነ ነጥብ ላይ” ደርሷል አሉየቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግየፎቶው ባለመብት,GETTY IMAGESየቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ የመካከለኛው ምሥራቅ ሁኔታ “ቁልፍ የሆነ ነጥብ ላይ” ደርሷል ማለታቸው ተገለጸ።የቻይና ብሔራዊ ጣቢያ እንደዘገበው አሁን ያለው ሁኔታ ከጦርነት ወደ ሰላም የሚደረግ ሽሽግር ላይ የሚገኝ ነው ብለዋል።የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን እያስተናገዱ የሚገኙት ጂንፒንግ “ግጭቱን በድጋሚ መጀመር ተቀባይነት የለውም” ሲሉም ተናግረዋል።በመካከለኛው ምሥራቅ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን ባለ አራት ነጥብ ምክረ ሐሳብ ማቅረባቸውን የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ “ዓላማዬ ዓለም አቀፍ ስምምነት መፍጠር እና ውጥረትን ማርገብ” ብለዋል።ባለፈው ወር ከአቡ ዳቢ ልዑል አልጋ ወራሽ ሼኽ ካሊድ ቢን መሐመድ ዛይን አል ናህያ ጋር በተገናኙበት ወቅት ባለ አራት ነጥብ ምክረ ሐሳብ አቅርበዋል።ምክረ ሐሳቡ ሰላም፣ ብሔራዊ ልዕልና፣ ዓለም አቀፍ ሕግ ማክበር እንዲሁም ለልማት እና ደኅንነት መተባበር ላይ የተመረኮዘ ነው ተብሏል።ያጋሩ, የቻይናው ፕሬዝዳንት የመካከለኛው ምሥራቅ ሁኔታ “ቁልፍ የሆነ ነጥብ ላይ” ደርሷል አሉ
  5. ከ 5 ሰአት በፊትአሜሪካ በድጋሚ ጥቃት ከከፈተች “ብዙ አዳዲስ ነገር ይጠብቃታል” ስትል ኢራን አስጠነቀቀችየኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺየፎቶው ባለመብት,EPA/Shutterstockየኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ አሜሪካ በድጋሚ ጥቃት መሰንዘር ጀመረች “ብዙ አዳዲስ ነገር ይጠብቃታል” በማለት ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዛቻ ምላሽ ሰጡ።ትራምፕ ቴህራን ላይ በድጋሚ ጥቃት ለመክፈት መዛታቸውን ተከትሎ “ወደ ውጊያ አውድማ ከተመለሱ ብዙ አዳዲስ ነገር እንደሚጠብቃቸወ ላረጋግጥ እወዳለሁ” ሲሉ አራግቺ አስጠንቅቀዋል።አራግቺ በኤክስ ገጻቸው “የኢራን ጦርነት ከተጀመረ ከወራት በኋላ በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር የጦር አውሮፕላን መውደሙን የአሜሪካ ምክር ቤት አምኗል” ብለዋል።“ኃያል የሆነው ጦራችን ኤፍ-35 ተዋጊ ጀትን መትቶ በመጣል የመጀመሪያው መሆኑ ተረጋግጧል” ሲሉም አክለዋል።ትራምፕ በበኩላቸው ኢራን ላይ ዳግመኛ ጦርነት ለመክፈት ሊወስኑ “አንድ ሰዓት ሲቀራቸው” ሐሳባቸውን መለወጣቸውን ገልጸዋል።የኢራን ባለሥልጣናት ከአሜሪካ ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ “እየለመኑ” እንደነበረ ተናግረዋል። ትራምፕ በድጋሚ ኢራን ላይ ጥቃት መሰንዘር ሊያስፈልግ ይችላል ማለታቸውም ተዘግቧል።የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለትራምፕ ዛቻ በሰጡት ምላሽ “ወደ ውጊያ አውድማው ከተመለሱ፤ ባገኘነውን ትምህርት እና ተሞክሮ አማካኝነት ብዙ አዳዲስ ነገሮች እናሳያቸዋለን” ብለዋል።ትራምፕ ኢራን ላይ ጥቃት ሊከፍቱ ይዘውት የነበረውን ዕቅድ በባሕረ ሰላጤው አገራት ጥያቄ መሠረት መሰረዛቸውን አስታውቀዋል።ሳዑዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና ኳታር ለድርድር ዕድል እንዲሰጥ እንደጠየቁ ተገልጿል።ያጋሩ, አሜሪካ በድጋሚ ጥቃት ከከፈተች “ብዙ አዳዲስ ነገር ይጠብቃታል” ስትል ኢራን አስጠነቀቀች
  6. 19 ግንቦት 2026ትራምፕ ኢራንን ዳግም ለማጥቃት ሊወስኑ “አንድ ሰዓት ሲቀራቸው” ሐሳባቸውን እንደለወጡ ተናገሩትራምፕየፎቶው ባለመብት,Bloomberg via Getty Imagesየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ላይ ዳግመኛ ጦርነት ለመክፈት ሊወስኑ “አንድ ሰዓት ሲቀራቸው” ሐሳባቸውን መለወጣቸውን ተናገሩ።የኢራን ባለሥልጣናት ከአሜሪካ ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ “እየለመኑ” እንደነበረም ገልጸዋል።ትራምፕ በድጋሚ ኢራን ላይ ጥቃት መሰንዘር ሊያስፈልግ ይችላል ማለታቸውም ተዘግቧል።ከኢራን ጋር በቀጣይ ቀናት ስምምነት ላይ ካልተደረሰ ጥቃት መፈጸም እንደሚቀጥሉ አስጠንቅቀዋል።“ሁለት ወይም ሦስት ቀን ያለው። አርብ፣ ቅዳሜ፣ እሑድ ወይም ቀጣይ ሳምንት። ውስን ዕድል አለ። የኒውክሌር መሣሪያ እንዲታጠቁ መፍቀድ የለብንም” ብለዋል።ትራምፕ ዛሬ ማክሰኞ ኢራን ላይ ጥቃት ሊከፍቱ ይዘውት የነበረውን ዕቅድ በባሕረ ሰላጤው አገራት ጥያቄ መሠረት መሰረዛቸውን አስታውቀዋል።ሳዑዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና ኳታር ለድርድር ዕድል እንዲሰጥ እንደጠየቁ ተገልጿል።ኢራን እና አሜሪካ “በጣም ተቀባይነት ያለው” ስምምነት ላይ እንደሚደርሱ ሦስቱ አገራት እንደገለጹላቸው ትራምፕ ጠቅሰዋል።ያጋሩ, ትራምፕ ኢራንን ዳግም ለማጥቃት ሊወስኑ “አንድ ሰዓት ሲቀራቸው” ሐሳባቸውን እንደለወጡ ተናገሩ
  7. 19 ግንቦት 2026በኬንያ በነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ምክንያት የተጠራው አድማ ከመንግሥት ጋር ለመደራደር ተቋረጠአድመኞችየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየኬንያ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች በነዳጅ ዋጋ መጨመር ምክንያት በመላው አገሪቱ ለሁለት ቀናት ያካሄዱት የሥራ ማቆም አድማ ከመንግሥት ጋር ድርድር ካደረጉ በኋላ ለጊዜው እንዲቋረጥ አደረጉ።እስከሚቀጥለው ማክሰኞ ድረስ አድማው የቆመው የትራንስፖርት ማኅበራቱ ከመንግሥት ጋር ለሚያደርጉት ድርድር አመቺ ሁኔታን ለመፍጠር ነው ብለዋል።ሰኞ እና ማክሰኞ የተካሄደው የትራንስፖርት ማቆም አድማ ለጊዜው የተቋረጠው ዋና ከተማዋን እና ሌሎች የአገሪቱን ከተሞች እንቅስቃሴ ቀጥ እንዲል ካደረገ በኋላ ነው።የኬንያ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ኪፕቹምባ ሙርኮሜን እንዳሉት አድማውን ያስቆመው ስምምነት የተደረሰው ከሕዝብ ትራንስፖርት ሰጪ ተወካዮች ጋር ምክክር ከተደረገ በኋላ “በከፍተኛ ደረጃ” ንግግሩን ለመቀጠል በመግባባቸታው ነው።ሰኞ ዕለት ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ የአገሪቱ ኤነርጂ ሚኒስትር ከፍተኛ ጭማሪ ተደርጎበት በነበረው የናፍጣ ዋጋ ቅናሽ መደረጉን ቢገልጹም ተጨማሪ ቅናሽ በመጠየቅ አድማው ቀጥሎ ነበር።ከአድማው ጋር ተያይዞ በተከሰተ ጉዳት ቢያንስ አራት ሰዎች ሲገደሉ 30 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን እንዲሁም ከ700 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።ያጋሩ, በኬንያ በነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ምክንያት የተጠራው አድማ ከመንግሥት ጋር ለመደራደር ተቋረጠ
  8. 19 ግንቦት 2026ኢቦላ መጀመሪያ ከተገመተው በላይ በፍጥነት እየተሰራጨ ሊሆን እንደሚችል የዓለም የጤና ድርጅት ሐኪሞች አስጠነቀቁሕፃን አዝላ እጇን የምትታጠብ ሴትየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተቀስቅሶ የተገኘው ኢቦላ በጎረቤት ኡጋንዳም ተገኝቷልበዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዳግም የተቀሰቀሰው ኢቦላ 131 ሰዎችን ሲገድል፤ የዓለም የጤና ድርጅት ተወካዮች ከታሰበው በላይ በፍጥነት ሊሰራጭ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ሰጡ።ዶ/ር አን አኒሲያ ለቢቢሲ ድርጅቱ ምርመራውን ባጠናከረ ቁጥር በሽታው በሌሎች አካባቢዎች መዛመቱ ግልፅ ሆኗል ብለዋል።እስከ ማክሰኞ ድረስ 513 ሕሙማን መኖራቸው በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተመዘገበ ሲሆን በኡጋንዳ የአንድ ሰው ሕይወት አልፏል።ይሁን እንጂ መቀመጫውን ለንደን ያደረገ የተላላፊ በሽታዎች ማዕከል ሠኞ ዕለት ይፋ ባደረገው ትንታኔ አሁንም በኢቦላ መያዛቸው ያልታወቀ ሕሙማን መኖራቸውን እና ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው ሳይገኙ እንዳልቀረ ጠቁሟል።ባለፈው ሳምንት በሽታውን ዓለም አቀፍ ድንገተኛ አደጋ ሲሉ ያወጁት የዓለም የጤና ድርጅት ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም “መጠኑ እና የበሽታው ፍጥነት በጣም እንዳሳሰባቸው” ተናግረዋል።በሽታው በሚያዚያ መጨረሻ ከመገኘቱ በፊት ለሣምንታት ቆይቷል የሚል ስጋት አለ።አሁን የተቀሰቀሰው የኢቦላ ቫይረስ ዝርያ ክትባት የሌለው ሲሆን፤ የዓለም የጤና ድርጅት ሌሎች መድኃኒቶች መከላከያ ሊሆኑ የሚችሉ ከሆነ በሚል ምርመራ እያረገ ነው።ያጋሩ, ኢቦላ መጀመሪያ ከተገመተው በላይ በፍጥነት እየተሰራጨ ሊሆን እንደሚችል የዓለም የጤና ድርጅት ሐኪሞች አስጠነቀቁ
  9. 19 ግንቦት 2026ኢራን በጦርነቱ ለደረሰባት ውድመት ካሳ እንዲሁም የአሜሪካ ወታደሮች እንዲወጡ የሚጠይቅ ሃሳብ አቀረበችኢራናውያን ባንዲራ ይዘውየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesኢራን በሁሉም ግንባሮች የተከፈቱ ጦርነቶች እንዲቆሙ እና ለደረሰባት ጉዳት ካሳ እንዲከፈላት የሚጠይቅ የስምምነት ሃሳብ አቀረበች።አዲሱ የሰላም ዕቅድ በሊባኖስ ውስጥ የሚካሄደውን ጨምሮ በሁሉም ግንባሮች የሚደረጉ ጦርነቶች እንዲቆሙ፣ በኢራን አቅራቢያ የሰፈሩ የአሜሪካ ወታደሮች እንዲወጡ እና በጦርነቱ ለደረሰባት ውድመት ካሳን እንዲከፈላት የሚጠይቅ መሆኑን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።ቴህራን የሰላም ዕቅዱን በሚመለከት በሰጠችው የመጀመሪያ አስተያየት ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ካዘም ጋሪባባዲ ማዕቀቦች እንዲነሱ፣ እንዳይንቀሳቀሱ የታገዱ ንብረቶቿ እንዲለቀቁ አንዲሁም የአሜሪካ ባሕር ኃይል የጣለውን እገዳ እንዲያነሳ መጠየቃቸውን ኢርና የዜና ወኪል ዘግቧል።የኢራን መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ከሆነ የቴህራን አዲሱ ዕቅድ ከዚህ በፊት ካቀረበችው እና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ቆሻሻ” ሲሉ ውደቅ ካደረጉት ብዙም የተለየ አይደለም።ትራምፕ ሰኞ ዕለት አቅደውት የነበረውን ጥቃት ያቆሙት ቴህራን ለዋሺንግተን አዲስ ሰላም ዕቅድ መላኳን ተከትሎ መሆኑን ተናግረው፤ የኢራንን የኒውክሌር ፕሮግራም ለመገደብ እና ከስምምነት ላይ ለመድረስ “በጣም ጥሩ ዕድል አለ” ብለዋል።ትራምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ ልጥፋቸው ላይ ኳታር፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ “አሜሪካ እንዲሁም የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ሊቀበሉት የሚችሉት ስምምነት ላይ ሊደረስ ይችላል” በማለት ጥቃቱ እንዲዘገይ መጠየቃቸውን ተናግረዋል።ዶናልድ ትራምፕ ሰኞ ዕለት ቴህራን የኒውክሌር የጦር መሣሪያ እንዳታገኝ የሚያደርግ ስምምነት ላይ መድረስ ከተቻለ ደስተኛ እንደሚሆኑ ተናግረዋል።ያጋሩ, ኢራን በጦርነቱ ለደረሰባት ውድመት ካሳ እንዲሁም የአሜሪካ ወታደሮች እንዲወጡ የሚጠይቅ ሃሳብ አቀረበች
  10. 19 ግንቦት 2026ጋና ዜጎቿን ከደቡብ አፍሪካ የፊታችን ሐሙስ ልታስወጣ ነውበበርካታ የደቡብ አፍሪካ ከተሞች ጸረ ስደተኛ ሠልፎች ተካሄደዋልየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,በበርካታ የደቡብ አፍሪካ ከተሞች ጸረ ስደተኛ ሠልፎች ተካሄደዋልየጋና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሐሙስ ዕለት ዜጎቹን ከደቡብ አፍሪካ ሊያስወጣ መሆኑን አስታወቀ።የጋና መንግሥት ከዚህ በፊት 300 ዜጎቹን ከደቡብ አፍሪካ ለማስወጣት ምዝገባ ማከናወኑን ገልጾ የነበረ ሲሆን የመጓጓዣ ሙሉ ወጪያቸውንም እንደሚሸፍን ተናግሯል።የጋና ፕሬዚዳንት ጆን ማሃማ በደቡብ አፍሪካውያን የጸረ ስደተኞች ሰልፍ መካሄዱን ተከትሎ ዜጎቻቸውን በአስቸኳይ ለማስወጣት ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው ተነግሯል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሳሙኤል ኦኩድዜቶ አብላክዋ በኤክስ ገጻቸው ላይ የጋናውያን ደህንነት ያለምንም ድርድር ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን ጽፈዋል።የመጀመርያው ዙር መንገደኞች ሐሙስ ዕለት 5 ሰዓት ላይ ከኦ አር ታምቦ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደሚነሱ ተገልጿል።አንድ ጋናዊ በተቃዋሚዎች ተከብቦ ሲወዋከብ የሚያሳይ ቪዲዮ በስፋት ከተዘዋወረ በኋላ በጋና እና በደቡብ አፍሪካ መካከል ዲፕሎማሲየዊ ውጥረቱ ተባብሷል።ሁለቱ አገራት ውጥረቱን ለማርገብ በተደጋጋሚ ንግግሮች ቢያደርጉም የጋና መንግሥት ለዜጎቹ ደህንነት ቅድሚያ እንደሚሰጥ በመግለጽ እርምጃዎቹን መውሰዱን ቀጥሏል።ናይጄሪያም ፈቃደኛ የሆኑ ዜጎቿን ከደቡብ አፍሪካ ለማስወጣት ዝግጁ መሆኗን አስታውቃለች።በደቡብ አፍሪካ በተደጋጋሚ ጸረ ስደተኛ ሰልፎች የተካሄዱ ሲሆን አፍሪካውያን ስደተኞች ዒላማ ተደርገው ጥቃት ደርሶባቸዋል።ባለፈው ሳምንት የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ በስደተኞች ላይ ጥቃት የሚፈጽሙ ተቃዋሚ ሠልፈኞችን ኮንነው የአገሪቱን የስደተኛ ፖሊስ ለማሻሻል ቃል ገብተዋል።እንዲህ ዓይነት ተግባር ደቡብ አፍሪካንም ሆነ ፖሊሲዎቿን አይወክልም ያሉት ፕሬዚዳንቱ ሁሉም የአገሪቱን ሕግ እዲያከብር ጠይቀዋል።ያጋሩ, ጋና ዜጎቿን ከደቡብ አፍሪካ የፊታችን ሐሙስ ልታስወጣ ነው
  11. 19 ግንቦት 2026ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ላይ ለመፈጸም ያሰቡትን ጥቃት ካዘገዩ በኋላ ከሥምምነት ላይ ለመድረስ “ጥሩ ዕድል” መኖሩን ተናገሩፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,EPAፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሰኞ ዕለት ኢራን የጦር መሣሪያ እንዳይኖራት ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ላይ ለመድረስ “በጣም ጥሩ ዕድል” መኖሩን ተናገሩ።ትራምፕ ይህንን የተናገሩት በኢራን ላይ ጥቃት ለመፈጸም ይዘውት የነበረውን ዕቅድ ካዘገዩ ከሰዓታት በኋላ ነው።ፕሬዚዳንቱ ቁልፍ የመካከለኛው ምሥራቅ አጋሮቻቸው ማክሰኞ ዕለት ለመፈጸም አቅደውት የነበረውን ዕቅድ ከቴህራን ጋር የሚደረገው ድርድር እንዲቀጥል በሚል እንዲያዘገዩት መጠየቃቸውን ተናግረዋል።ትራምፕ ሰኞ ዕለት ለጋዜጠኞች “አንድን ነገር ላይ ለመድረስ የሚያስችል በጣም ጥሩ ዕድል ያለ ይመስላል። በቦምብ ሳንደበድባቸው ያንን ማድረግ ከቻልን በጣም ደስተኛ እሆናለሁ” ብለዋል።የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ስምምነት ላይ ካልተደረሰ ጥቃት ለመፈጸም ዝግጁ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ጨምረው አስታውቀዋል።ዶናልድ ትራምፕ በባሕረ ሰላጤው አገራት ጥያቄ መሠረት ኢራን ላይ የሚፈጸምን አዲስ ጥቃት ማስቀረታቸውን ተናገሩያጋሩ, ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ላይ ለመፈጸም ያሰቡትን ጥቃት ካዘገዩ በኋላ ከሥምምነት ላይ ለመድረስ “ጥሩ ዕድል” መኖሩን ተናገሩ
  12. 19 ግንቦት 2026በአሜሪካ መስኪድ ላይ በተከፈተ ተኩስ ሦስት ሰዎች መሞታቸው እና ተጠርጣሪዎቹ ራሳቸውን ማጥፋታቸው ተገለጸበሳንዲያጎ ታዳጊዎች ባደረሱት ጥቃት የሞቱ ሰዎች ማንነት ገና ይፋ አልሆነምየፎቶው ባለመብት,EPAሁለት ታዳጊዎች ራሳቸውን ከማጥፋታቸው በፊት በአሜሪካ ሳንዲያጎ በሚገኝ መስኪድ ላይ ጥቃት ከፍተው ሦስት ሰዎች መግደላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።ጥቃቱ የተፈጸመው ሰኞ ማለዳ ሲሆን ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።ፖሊስ በሳንዲያጎ በሚገኘው የሙስሊሞች ማዕከል ተኩስ መከፈቱን የሚገልጽ ጥቆማ አንደደረሰው ወደ ስፍራው ሲደርስ ሦስት ሰዎች በጥይት ተመትተው ማግኘቱን ገልጿል።ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በአቅራቢው ከሚገኝ መኪና ውስጥ ተኩስ መሰማቱን የሚገልጽ መረጃ ደርሶት ወደ ሥፍራው ሲያመራ የ17 እና የ18 ዓመት ታዳጊዎች ራሳቸውን አጥፍተው ማግኘቱን አስታውቋል።የከተማዋ ባለሥልጣናት ጥቃት ከደረሰባቸው እና ከሞቱት መካከል አንዱ በጥቃቱ የባሰ ጉዳት እንዳይደርስ “ወሳኝ ሚና የተጫወተ” የማዕከሉ ዘብ መሆኑን ተናግረዋል።የሳንዲያጎ ፖሊስ አዛዥ ስኮት ዋህል በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት “የጀግና ተግባር ነው የፈጸመው ማለት እንችላለን” ሲሉ አድንቀው “ያለምንም ጥርጥር ዛሬ ሕይወት አድኗል” ብለዋል።የከተማዋ ባለሥልጣናት የሟቾቹን ስም ይፋ አላደረጉም። ነገር ግን የማዕከሉ ዘብ የስምንት ልጆች አባት መሆኑን በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር የሆነው ሲቢኤስ ዘግቧል።መርማሪዎች ጥቃቱ የተፈጸመበት ምክንያት እንዳልተወቀ ተናግረዋል።ነገር ግን በሳንዲያጎ ግዙፍ በሆነው መስኪድ ላይ ጥላቻ ያላቸው ሊሆኑ አንደሚችሉ ተጠርጣሪው ከጻፈው በመነሳት ያላቸውን ጥርጣሬ ተናግረዋል።ያጋሩ, በአሜሪካ መስኪድ ላይ በተከፈተ ተኩስ ሦስት ሰዎች መሞታቸው እና ተጠርጣሪዎቹ ራሳቸውን ማጥፋታቸው ተገለጸ
  13. 19 ግንቦት 2026እስራኤል በሊባኖስ በፈጸመችው ድብደባ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ3,000 ማለፉን የአገሪቱ ባለሥልጣናት ተናገሩበእስረኤል ጥቃት የሞቱ ቤተሰቦቻቸውን የሚቀብሩ ሴቶችየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በእስራኤል እና በሊባኖስ መካከል የተኩስ አቁም ቢደረስም ከሄዝቦላህ ጋር የሚደረገው ውግያ እንደቀጠለ ነውየሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር በእስራኤል ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 3,000 ማለፉን አስታወቀ።እስራኤል እና ሄዝቦላህ ዳግም ወደ ግጭት የገቡት የኢራን ጦርነት በተጀመረ በሦስተኛው ቀን ነው።በሁለቱ አገራት መካከል በተደጋጋሚ የተኩስ አቁም ቢደረሰም አሁንም ውጊያዎች እየተካሄዱ ሲሆን ይህም ሰኞ ዕለት የሟቾችን ቁጥር 3,020 አድርሶታል።ሊባኖስ ዳግም ወደ ጦርነት ተጎትታ የገባችው በኢራን የሚደገፈው ሄዝቦላህ የቴህራኑ ጠቅላይ መሪ መገደላቸውን በመቃወም ወደ እስራኤል ሮኬቶችን በማስወንጨፉ ነው።አርብ ዕለት እስራኤል እና ሊባኖስ የተኩስ አቁማቸውን በ45 ቀናት ቢያራዝሙም የሟቾች ቁጥር እየጨመረ ነው።ሁለቱ አገራት ዳግም ድርድራቸውን በሰኔ ወር መጀመርያ ላይ ለመቀጠል ተስማምተዋል።የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር ከ400 በላይ ሰዎች የተገደሉት የተኩስ አቁም ስምምነቱ ሚያዚያ 9 2018 ዓ.ም. ከተደረሰ በኋላ ነው ሲል አስታውቋል።አሜሪካ ያደራደረችው ይህ የተኩስ አቁም ስምምነት እስራኤል የሄዝቦላህን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለመመከት ጥቃት እንድትፈጽም ይፈቅዳል።ሊባኖስ ጥቃቶቹን አውግዛ አገሪቱ ዳግም ታጣቂዎች የያዙትን መሣሪያ ለመቆጣጠር የምታደርገውን ጥረት ዝቅ የሚያደርግ ነው ብላለች።አርብ ዕለት ዳግመኛ የተኩስ አቁሙ ከተራዘመ በኋላ እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ የሚገኙ መንደሮችን በማጥቃት በርካቶችን ገድላለች።ቅዳሜ ዕለት በበርካታ መንደሮች ላይ ጥቃት ብትፈጽምም አካበቢውን ለቅቀው እንዲወጡ ቅድመ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ግን ዘጠኙ ብቻ ናቸው።የዚያኑ ዕለት ሄዝቦላህ በርካታ የድሮን ጥቃቶችን በእስራኤል ላይ መፈጸሙን አስታውቋል።የእስራኤል ጦር ቅዳሜ ዕለት አንድ ወታደሩ መገደሉን የገለጸ ሲሆን ይህም በዚህ ጦርነት የተገደሉ የእስራኤል ወታደሮችን ብዛት 20 አድርሶታል።ያጋሩ, እስራኤል በሊባኖስ በፈጸመችው ድብደባ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ3,000 ማለፉን የአገሪቱ ባለሥልጣናት ተናገሩ
  14. 18 ግንቦት 2026በኬንያ የነዳጅ ዋጋ መጨመርን በመቃወም አደባባይ የወጡ ከ200 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉየኬንያ ፖሊስየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየኬንያ ፖሊስ የነዳጅ ዋጋ መጨመርን በመቃወም አደባባይ ከወጡ መካከል ከ200 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስታወቀ።የናይሮቢ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኢሳ ሞሐሙድ በመላ አገሪቱ የተጠራን የትራንስፖርት ማቆም አድማን ተከትሎ ለተቃውሞ አደባባይ ከወጡ ሰዎች መካከል 225ቱ በቁጥጥር ሥር ውለዋል ብለዋል።በኬንያ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 10 2018 ዓ.ም. ከፍተኛ የነዳጅ ጭማሪን በመቃወም በመላ አገሪቱ የመጓጓዣ አገልግሎት ሰጪዎች ሥራ አቁመው ውለዋል።በናይሮቢ እና በዋና ዋና ከተማዎች የአውቶቡስ፣ የሞተር ሳይክል እና ሚኒባስ ትራንስፖርት አገልግሎት በመቋረጡ ተጠቃሚዎች ረዥም ርቀት በእግራቸው ለመጓዝ ተገድደዋል።በአንዳንድ አካባቢዎች ተቃዋሚ ሠልፈኞች መንገድ ዘግተው ጎማ ሲያቃጥሉ ታይተዋል።ፖሊስ መንገዶችን ለመክፈት በሚሞክርበት ወቅት ከተቃዋሚ ሠልፈኞቹ ጋር የተጋጨ ሲሆን ለመበተን አስለቃሽ ጋዝ ተጠቅሟል።የናይሮቢ ፖሊስ አዛዥ አምስት የፖሊስ እና አንድ የግለሰብ መኪኖች በሠልፈኞቹ መውደማቸውን አስታውቀዋል።እስካሁን ድረስ በተቃውሞ ሠልፉ ምክንያት የሞተ ሰው ስለመኖሩ የተባለ ነገር የለም።ባለፈው ሳምንት የኬንያ ኢነርጂ እና ፔትሮሊየም ቁጥጥር ባለሥልጣን በመካከለኛው ምሥራቅ ያለውን ውጥረት በመጥቀስ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ይፋ ካደረገ በኋላ ተቃውሞ ተቀስቅሷል።የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢዎች በተለይ ደግሞ የሕዝብ ማመላለሻ ባለንብረቶች እና አሽከርካሪዎች የዋጋ ጭማሪው ለመስራት አስቸጋሪ እንዳደረገባቸው ተናግረዋል።በተቃውሞ ምክንያት በርካታ የረዥም ርቀት ተጓዥ አውቶብሶች ጉዟቸውን በመሰረዛቸው የተነሳ መንገደኞች ተጉላልተዋል።ዛሬ በኬንያ በነበረው የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢዎች ተቃውሞ የተነሳ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም የንግድ ተቋማት ተዘግተው ውለዋል።የአገሪቱ ገንዘብ ሚኒስትር ጆን ምባዲ የዓለም አቀፍ ነዳጅ ዋጋ ንረት በመካከለኛው ምሥራቅ ካለው ጦርነት ጋር እንደሚያያዝ ጠቅሰው ይህም በአገሪቱ ለተከሰተው ጭማሪ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል።የዓለም የነዳጅ ዋጋ በዚሁ ከቀጠለ መንግሥት የታክስ እፎይታን ከግምት ሊያስገባ እንደሚችል ጨምረው አስታውቀዋል።የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢዎች እና የተሽከርካሪ ባለቤቶች መንግሥት የነዳጅ ዋጋ እንዲቀንስ ቢጠይቁም እስካሁን ድረስ ይህ ነው የሚባል መግባባት ላይ አልደረሱም።ያጋሩ, በኬንያ የነዳጅ ዋጋ መጨመርን በመቃወም አደባባይ የወጡ ከ200 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
  15. 18 ግንቦት 2026አሜሪካ ለወታደራዊ እርምጃ “ሐሰተኛ ምክንያቶችን” እያደራጀች ነው ስትል ኩባ ከሰሰችኩባውያን በከፍተኛ የነዳጅ እጥረት ምክንያት የኃይል መቆራረጥ አጋጥሟቸዋልየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ኩባውያን በከፍተኛ የነዳጅ እጥረት ምክንያት የኃይል መቆራረጥ አጋጥሟቸዋልየኩባ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አገራቸው የፍሎሪዳ ግዛትን ማጥቃት የሚችል ድሮን አግኝታለች የሚል ዘገባን ተከትሎ አሜሪካ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ “ሐሰተኛ ምክንያቶችን” እያደራጀች ነው ሲሉ ከሰሱ።ብሩኖ ሮድሪጌዝ የአሜሪካ የዜና ድረገጽ አክሲዮስ ዘገባን ተከትሎ ሃቫና “አትፈራም እንዲሁም ጦርነት አትፈልግም” ሲሉ ተናግረዋል።አክሲዮስ ምሥጢራዊ የደኅንነት መረጃዎችን ጠቅሶ ኩባ በአቅራቢያዋ የሚገኙ የአሜሪካ ዒላማዎችን ማጥቃት የሚችሉ 300 ድሮኖች ታጥቃለች ሲል ዘግቧል።አሜሪካ ኩባን “ለስምምነት እንድትቀመጥ” ለማስገደድ በሚል ወደ ግዛቷ የሚሄድን ነዳጅ ካገደች በኋላ አገሪቱ ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት ገጥሟታል።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የኩባ ኮሚኒስት አመራሮችን የቬንዙዌላ ፕሬዝዳንት ማዱሮን ለመያዝ የወሰዱትን ወታደራዊ እርምጃ ዓይነት እንደሚጠብቃቸው አስጠንቅቀዋል።ኩባ ድሮኖችን በመጠቀም በካሪቢያን ደሴት ላይ የሚገኘውን የአሜሪካ ወታደራዊ የጦር ሠፈር፣ ጓንታናሞ ቤይን እንዲሁም የባሕር ኃይል መርከቦችን እና ፍሎሪዳ ከተማን የማጥቃት ፍላጎት እንዳላት አክሲዮስ እሁድ ዕለት ዘግቧል።ዘገባው የአሜሪካ የደኅንነት ባለሥልጣንን ጠቅሶ የኢራን ወታደራዊ አማካሪዎች በሃቫና ይገኛሉ ያለ ሲሆን፣ ይህም ለአሜሪካ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ሰበብ ሊሆን ይችላል ተብሏል።ሮድሪጌዝ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ “ምንም ዓይነት ቅቡልነት የሌለው ማስረጃ፣ የአሜሪካ መንግሥት ከቀን ወደ ቀን በኩባ ሕዝብ ላይ እያካሄደ ላለው ከባድ የኢኮኖሚ ጦርነት እና ለሚከፍተው ወታደራዊ ጥቃት ሐሰተኛ ምክንያቶችን እያደራጀ ነው” ሲሉ ጽፈዋል።“የተለዩ የመገናኛ ብዙኃን የአሜሪካ መንግሥት ጎጂ ውንጀላዎችን በማሠራጨት ረገድ ድጋፍ እያደረጉ ነው።”አክለውም ኩባ ጦርነት የማትፈልግ ብትሆንም ራሷን “ከውጭ ወረራ” ለመከላከል እየተዘጋጀች ነው ብለዋል።ሃቫና ለበርካታ ወራት ከአሜሪካ ጋር ያላትን ልዩነት ለመፍታት ንግግሮችን እያደረገች ነው። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ከሩሲያ እንዲገባ የተደረገ ነዳጅ እያለቀ መሆኑ ተዘግቧል።ኩባውያን በከፍተኛ የነዳጅ እጥረት ምክንያት የኃይል መቆራረጥ ያጋጠማቸው ሲሆን፣ በዚህም የተነሳ የሕዝብ ትራንስፖርት፣ የውሃ ማሠራጫዎች፣ የቆሻሻ ማስወገጃዎች እንዲሁም ሆስፒታሎች ሥራቸውን ለማቋረጥ እየተገደዱ ነው።ያጋሩ, አሜሪካ ለወታደራዊ እርምጃ “ሐሰተኛ ምክንያቶችን” እያደራጀች ነው ስትል ኩባ ከሰሰች
  16. 18 ግንቦት 2026የሳዑዲ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኢትዮጵያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩየሳዑዲ አረቢያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሊድ አብዱልከሪም አል ካሪጅ ከኢትዮጵያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋርየፎቶው ባለመብት,Ministry of Foreign Affairs of Ethiopiaየምስሉ መግለጫ,የሳዑዲ አረቢያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሊድ አብዱልከሪም አል ካሪጅ ከኢትዮጵያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋርየኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ እና የሳዑዲ አረቢያ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአዲስ አበባ ተገናኝተው ተወያዩ።ሰኞ ዕለት ግንቦት 10 2018 ዓ.ም. ሁለቱ ሚኒስትሮች በሁለትዮሽ ጉዳዮች እና በቀጣናው ባላቸው የጋራ ፍላጎት ዙሪያ መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማኅበራዊ ድረገጹ ላይ አስታውቋል።በተጨማሪም ባለሥልጣናቱ ከፖለቲካ እና ከፀጥታ ጉዳዮች ባሻገር፣ በሁለቱ አገራት መካከል ባለው ግንኙነት፣ ሕጋዊ የሠራተኛ ስምሪት ላይ መወያየታቸው ተገልጿል።በቀጣናዊ ሰላም እና ደኅንነት ዙሪያ የተወያዩት ሁለቱ ሚኒስትሮች በአካባቢው ላሉ የተለያዩ ግጭቶች ብቸኛው መፍትሔ በውይይት ፖለቲካዊ መፍትሄ መፈለግ መሆኑን መነጋገራቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።ምክትል የሳዑዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢንጂነር ዋሊድ አብዱልከሪም አል ካሪጅ በየካቲት ወር አሥመራን ከጎበኙ በኋላ ወደ አዲስ አበባ መጥተው ነበር።ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በሦስተኛ ወራቸው ወደ አዲስ አበባ የተመለሱ ሲሆን፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ጋር በሁለቱ አገራት የረዥም ጊዜ ወዳጅነት እና የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ዙሪያ ተወያይተዋል።ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የአገራቱ ግንኙነትን በማጠናከር በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ደኅንነት መጠበቅ እንዲሁም ለኢትዮጵያውያን ሠራተኞች ሕጋዊ የሥራ ቅጥር እንዲመቻች መጠየቃቸው ተገልጿል።በሳዑዲ አረቢያ ከ200 የሚበልጡ ኢትዮጵያውያን በደቡባዊ የአገሪቱ ክፍል በሚገኝ እስር ቤት የሞት ቅጣት እንደተፈረደባቸው እና ሌሎች 65 የሚሆኑ ስደተኞችም ተመሳሳይ ፍርድ እንደሚጠብቃቸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አስታውቀዋል።ኢንጂነር ዋሊድ አብዱልከሪም አል ካሪጅ በበኩላቸው ለኢትዮጵያውያን ሠራተኞች ደኅንነቱ የተጠበቀ የሥራ ዕድል ለማረጋገጥ ሕጋዊ የሠራተኛ ቅጥር አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል።በተጨማሪም አገራቱ በጋራ ጉዳዮች ላይ ተመሳሳይ አመለካከት እንዳላቸው በመግለጽ፣ በመካከላቸው ያለውን ግንኙነት ለሁለቱ አገራት ጥቅም በሚያመጣ መልኩ መጠናከሩ አስፈላጊ መሆኑን አመልክተዋል።የሳዑዲ አረቢያው ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አገራቸው ከኢትዮጵያና ከሕዝቦቿ ጋር ያላትንታሪካዊ እና የረጅም ዘመን ግንኙነት እጅግ እንደምታከብር መግለጻቸውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያሠራጨው መረጃ አመልክቷል።የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞትዮስ እና የሳዑዲ አረቢያ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርየፎቶው ባለመብት,Ministry of Foreign Affairs of Ethiopiaያጋሩ, የሳዑዲ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኢትዮጵያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
  17. 18 ግንቦት 2026ቢያንስ 6 አሜሪካውያን በኮንጎ ለተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ መጋለጣቸውን ተዘገበየሙቀት መጠኗ የሚለካ ሴትየፎቶው ባለመብት,AFPበዴሞክራቲክ ኮንጎ በተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ስድስት አሜሪካውያን ለቫይረሱ ተጋልጠዋል ሲሉ ምንጮች በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር ለሆነው ሲቢኤስ ኒውስ ተናገሩ።የዓለም የጤና ድርጅት ወረርሽኙን አሳሳቢ ዓለም አቀፍ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ መሆኑን አውጇል።የዲሞክራቲክ ኮንጎ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር 350 የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው እንደተጠረጠረ እና 91 ሰዎች ደግሞ መሞታቸውን ዘግቧል።አንድ አሜሪካዊ የበሽታው ምልክቶች እንደታዩበት የተገለጸ ሲሆን፣ ሌሎች ሦስት ደግሞ ከፍተኛ ተጋላጭነት ወይም ንክኪ አላቸው ተብሏል።የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) “በቀጥታ የተጎዱ ጥቂት አሜሪካውያንን ደኅንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ለቅቀው እንዲወጡ” ለማድረግ ድጋፍ እንደሚያደርግ ቢገልጽም ምን ያህል አሜሪካውያን እንደሆኑ ግን አላረጋገጠም።የአሁኑ የኢቦላ ዝርያ የሚከሰተው በቡንዲቡግዮ ቫይረስ ሲሆን፣ ለዚህም ምንም ዓይነት የተረጋገጡ መድኃኒቶች ወይም ክትባቶች የለም።በኡጋንዳ ሁለት ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውሲረጋገጥ፣ አንድ ደግሞ መሞቱን የሲዲሲ አፍሪካ ዘገባ አመልክቷል።የአሜሪካ መንግሥት በዲሞክራቲክ ኮንጎ ለሚገኙት ዜጎቹ ደኅንነቱ ወደ ተጠበቀ የለይቶ ማቆያ ስፍራ ለማጓጓዝ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አንድ ምንጭ ለስታት የጤና ድረገጽ ተናግረዋል።በተጨማሪም አሜሪካውያኑ ጀርመን ወደሚገኝ የአሜሪካ ወታደራዊ ጣቢያ ሊወሰዱ እንደሚችል ድረ ገጹ ዘግቧል።የዓለም ጤና ድርጅት ዴሞክራቲክ ኮንጎ እና ኡጋንዳ ወረርሽኙን ለመከታተል፣ በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸውን ለመለየት እና የመከላከያ እርምጃዎችን ለመተግበር የሚያስችሉ የአስቸኳይ ጊዜ ማዕከላትን እንዲያቋቁሙ መክሯል።ሥርጭቱን ለመግታት እንዲቻል በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች፤ በ48 ሰዓታት ልዩነት በሚደረጉ ሁለት የቫይረሱ ምርመራዎች ነፃ መሆናቸው እስከሚረጋገጥ ድረስ ወዲያውኑ ለብቻ ሊለዩ እና ሕክምና ሊደረግላቸው እንደሚገባ ተቋሙ ገልጿል።በሽታው መከሰቱ የተረጋገጠባቸውን አገራት የሚያዋስኑ ጎረቤት መንግሥታት የቅኝት እና የጤና ሪፖርት ሥራቸውን እንዲያጠናክሩም ተነግሯቸዋል።ያጋሩ, ቢያንስ 6 አሜሪካውያን በኮንጎ ለተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ መጋለጣቸውን ተዘገበ
  18. 18 ግንቦት 2026ኢራን ለአሜሪካ አዲስ የሰላም ዕቅድ በፓኪስታን በኩል ማቅረቧ ተነገረፓኪስታንየፎቶው ባለመብት,Reutersበመካከለኛው ምሥራቅ የሚካሄደውን ጦርነት ያስቆማል የተባለ ኢራን ያቀረበችውን አዲስ ዕቅድ ፓኪስታን ለአሜሪካ መስጠቷን ምንጮች ለሮይተርስ ተናገሩ።በሁለቱ አገራት መካከል እየተካሄደ ያለው የሰላም ድርድር ውጤት ሳያስገኝ በእንጥልጥል ባለበት ወቅት ዛሬ ሰኞ ነው ፓኪስታን የኢራንን አዲስ ዕቅድ ለአሜሪካ ያቀረበችው።ምንጮች በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ልዩነት በዚህኛው የሰላም ዕቅድ ማጥበብ ይቻል እንደሆነ ተጠይቀው “ጊዜ የለንም” ብለዋል፤ አክለውም ሁለቱም አገራት “የሚፈልጉትን በየጊዜው ይቀያይራሉ” በማለት ከስምምነት ያልተደረሰበትን ምክንያት ጠቅሰዋል።የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አገራቸው ዩራኒየም የማበልጸግ መብቷ “ድርድር የሚደረግበት ወይም ከአቋም ፈቀቅ የሚባልበት ጉዳይ” እንዳልሆነ የተናገሩት ዛሬ ነበር።”በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው፤ ዩራኒየም የማበልጸግ መብት ለድርድር የሚቀርብ ወይም የሚለወጥ አይደለም። ኢራን ዩራኒየም ለማበልጸግ ያላት መብት የኒውክሌር መሣሪያዎች ላለማስፋፋት በተፈረመው ስምምነት መሠረት ዕውቅና የተሰጠው ነው” ብለዋል።የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው የኢራን ባለሥልጣናት ከስምምነት ለመድረስ መፍጠን እንዳለባቸው በመግለጽ “ጊዜው እየተገባደደ ነው” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።ትራምፕ ማስጠንቀቂያውን የሰጡት ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር ትናንት እሑድ በስልክ መነጋገራቸውን ተከትሎ ነው።ያጋሩ, ኢራን ለአሜሪካ አዲስ የሰላም ዕቅድ በፓኪስታን በኩል ማቅረቧ ተነገረ
  19. 18 ግንቦት 2026ኢራን ዩራኒየም የማበልጸግ መብቷ ላይ “እንደማትደራደር ወይም ከአቋሟ ፈቀቅ እንደማትል” ገለጸችየኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አቀባዩ ኢስማኢል ባቃኢየፎቶው ባለመብት,Reutersየኢራን ዩራኒየም የማበልጸግ መብት “ድርድር የሚደረግበት ወይም ከአቋም ፈቀቅ የሚባልበት ጉዳይ” እንዳልሆነ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ተናገሩ።ቃል አቀባዩ ኢስማኢል ባቃኢ ዛሬ ሰኞ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ጦርነቱን ለመቋጨት በፓኪስታን አማካኝነት የሚደረገው ንግግር መቀጠሉን ገልጸዋል።ኢራን ባለ 14 ነጥብ የስምምነት ዕቅድ ወደ አሜሪካ ልካ እንደነበር ያስታወሱት ቃል አቀባዩ፤ ዋሽንግተንም ሆነ ቴህራን በዕቅዱ ላይ የራሳቸውን ሐሳብ ማንሳታቸውን ተናግረዋል።“የአሜሪካው ወገን ይህ [ባለ 14 ነጥብ] ዕቅድ ውድቅ መደረጉን ባለፈው ሳምንት በይፋ ቢያስታውቅም፤ ያቀረቧቸው ነጥቦች እና የማስተካከያ አስተያየቶች ዝርዝር ግን በፓኪስታን አማካኝነት ደርሶናል” ብለዋል።“ዕቅዳችንን በላክን ማግስት ከሌላኛው ወገን የቀረቡ ተከታታይ ዕቅዶች ደርሰውናል። ዕቅዶቹ ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ የተገመገሙ ሲሆን የእኛ ምላሽም ቀርቧል። በፓኪስታን አማካኝነት የሚደረገው ድርድር ቀጥሏል” ሲሉም ንግግሩን የማስጀመር ሂደቱ ያለበትን አረስድተዋል።ይህም ቢሆን ግን ኢራን ዩራኒየም የማበልጸግ መብቷን ለድርድር እንደማታቀርብ ባቃኢ ተናግረዋል።”በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው፤ [ዩራኒየም የማበልጸግ] መብት ልንደራደርበት ወይም ከአቋም ፈቀቅ የምንልበት ጉዳይ አይደለም። ኢራን ዩራኒየም ለማበልጸግ ያላት መብት የኒውክሌር መሣሪያዎች ላለማስፋፋት በተፈረመው ስምምነት መሠረት እውቅና የተሰጠው ነው” ብለዋል።እንደ ቃል አቀባዩ ገለጻ ኢራን የምትፈልጋቸው የድርድር ነጥቦች በግልጽ ተቀምጠዋል። እንዳይንቀሳቀሱ የታገዱ የኢራን ሀብቶች መለቀቅን በማሳያነት ያነሱት ቃል አቀባዩ፤ “እናንተ እኛ [ለድርድር] ያስቀመጥነው ቅድመ ሁኔታ እንደሆነ ትናገራላችሁ፤ እኛ የመብት ጥያቄ እንደሆነ እንናገራለን” ብለዋል።ያጋሩ, ኢራን ዩራኒየም የማበልጸግ መብቷ ላይ “እንደማትደራደር ወይም ከአቋሟ ፈቀቅ እንደማትል” ገለጸች
  20. 18 ግንቦት 2026ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን ላይ ሊወሰዱ ስለሚችሉ ወታደራዊ አማራጮች ‘በሲቹዌሽን ሩም’ ሊሰበሰቡ መሆኑ ተዘገበፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ላይ ሊፈጸሙ ስለሚችሉ ወታደራዊ አማራጮች ለመወያየት ማክሰኞ ዕለት ከፍተኛ የብሔራዊ ደኅነት አመራሮቻቸውን ይሰበስባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አክሲዮስ ዘገበ።የአሜሪካው የዜና ምንጭ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮችን ጠቅሶ ባወጣው ዘገባ፤ የፕሬዝዳንቱ የብሔራዊ ደኅንነት ቡድን አባላት ስለ ኢራን ለመወያየት ቅዳሜ ዕለትም ተሰብስበው ነበር።ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫምስ፣ የዋይት ሃውስ መልዕክተኛ ስቲፍ ዊትኮፍ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ እና የሲአይኤ ዳይሬክተር ጆን ራትክሊፍ ከተሰብሳቢዎቹ መካከል ነበሩ ተብሏል።ትራምፕ ለአክሲዮስ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፤ ከኢራን ጋን ስምምነት ላይ ይደረሳል ብለው እንደሚያስቡ ተናግረዋል።የኢራን የድርድር ዕቅድ ላይ የሚደረገውን ማሻሻያ እየጠበቁ መሆኑን የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ፤ ከቀናት በፊት ከቀረበው የተሻለ ይሆናል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉም ጠቅሰዋል። ለድርድሩ ቀነ ገደብ ከማስቀመጥ ግን ተቆጥበዋል።“ስምምነት መፈጸም እንፈልጋለን። እንዲሆኑ የምንፈልገው ቦታ ላይ አይደሉም። እዚያ መረድስ አለባቸው ወይም ክፉኛ ይመታሉ፤ ያንን ደግሞ አይፈልጉም” ብለዋል።አሜሪካ እና ኢራን ከመጀመሪያው ዙር ድርድር በኋላ ንግግሩን ለማስቀጠል አልተገናኙም።አሸማጋይ ሆና እየተንቀሳቀሰች ያለቸው ፓኪስታን ቅዳሜ ዕለት የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሯን ወደ ቴህራን ልካ ነበር። ድርድሩን ለማስጀመር እሑድ ዕለትም ከኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ሲነጋገሩ ነበር።ያጋሩ, ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን ላይ ሊወሰዱ ስለሚችሉ ወታደራዊ አማራጮች ‘በሲቹዌሽን ሩም’ ሊሰበሰቡ መሆኑ ተዘገበ