አሜሪካ እና ኢራን በዩራኒየም ክምችት እና በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ በሚኖር ቁጥጥር ላይ አለመግባባታቸውን የሚያሳዩ ዘገባዎች ሐሙስ ዕለት ቢወጡም የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በድርድሮቹ ላይ “ጥሩ ምልክቶች” መኖራቸውን ተናገሩ።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 23 ደቂቃዎች በፊትበሕንድ ሊደረግ የነበረው የአፍሪካ ጉባኤ በኢቦላ ስጋት ምክንያት ተራዘመእጇን የምትታጠብ ሴትየፎቶው ባለመብት,Reutersበሚቀጥለው ሳምንት ሊካሄድ የነበረው የሕንድ-አፍሪካ ጉባኤ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ኡጋንዳ በተቀሰቀሰው የኢቦላ ቫይረስ ቀውስ ምክንያት መራዘሙ ተገለፀ።አራተኛው የሆነው ጉባኤው በአፍሪካ አገራት እና በሕንድ መካከል ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ለማሳደግ ያለመ ነው።የዘንድሮው ጉባዔ ከአስር ዓመታት ቆይታ በኋላ ከግንቦት 20 እስከ ግንቦት 23 2018 ዓ.ም. ድረስ በዴሊ ሊካሄድ ቀን ተቆርጦለት የነበረ ነው።ሕንድ እና የአፍሪካ ኅብረት ሐሙስ ዕለት በጋራ ባወጡት መግለጫ ጉባዔው በአህጉሩ በተቀሰቀሰው የኅብረተሰብ ጤና ስጋት ምክንያት መራዘሙን እና ጉባኤው ሊሰናዳበት የሚችል አዲስ ቀን ይፋ እንደሚሆን ገልፀዋል።እርምጃው የዓለም የጤና ድርጅት ቫይረሱን “የዓለም የኅብረተሰብ ጤና አደጋ” ብሎ ካወጀ በኋላ የመጣ ነው።እንደ ድርጅቱ መረጃ በቫይረሱ ተይዘዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች 600 ሲሆኑ፤ እስካሁን 139 ሰዎች በቫይረሱ ሕይወታቸው ማለፉ ታውቋል።የቫይረሱ ምልክቶች እስኪታዩ ድረስ ከሁለት እስከ 21 ቀናት ይወስዳል።ያጋሩ, በሕንድ ሊደረግ የነበረው የአፍሪካ ጉባኤ በኢቦላ ስጋት ምክንያት ተራዘመ
  2. ከ 47 ደቂቃዎች በፊትየፓኪስታን ልዑክ ከኢራን ባለሥልጣናት ጋር ለመወያየት ዳግም ቴህራን ገቡየፓኪስታን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሳይድ ሞሺን ናቅቪ ከኢራኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋርየፎቶው ባለመብት,@s_a_araghchiየምስሉ መግለጫ,የፓኪስታን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሳይድ ሞሺን ናቅቪ ከኢራኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋርየኢራኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከፓኪስታን ልዑክ ጋር ዛሬ አርብ በቴህራን ተገናኝተው ከአሜሪካ ጋር የተጀመረውን ጦርነት ለማስቆም ባቀረቡት የሰላም ዕቅድ ላይ መወያየታቸውን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።ቴህራን እና ዋሺንግተን በሆርሙዝ ወሽመጥ እና በከፍተኛ ደረጃ ተብላልቶ በተከማቸው ዩራኒየም ላይ መግባባት ላይ መድረስ አልቻሉም።ታስኒም የዜና ወኪል ፓኪስታን የአሜሪካን መልዕክት ለኢራን ካቀረበች ከሁለት ቀናት በኋላ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሳይድ ሞሺን ናቅቪ በቴህራን ለተጨማሪ ውይይት መገኘታቸውን ዘግቧል።የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ እየተደረጉ ባሉ ንግግሮች ላይ“ጥሩ ምልክቶች አሉ” በማለት ቴህራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ቀረጥ የምትጥል ከሆነ ግን ፋይዳ አይኖረውም ብለዋል።በንግግሩ ላይ የተወሰኑ ለውጦች ስለመኖራቸው “ጥሩ ምልክቶች አሉ” ያሉት ሩቢዮ “በጣም ተስፈኛ መሆን አልፈልግም. . . በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ምን አንደሚሆን እናያለን” ብለዋል።አንድ ከፍተኛ የኢራን ባለሥልጣን ለሮይተርስ የዜና ወኪል ሐሙስ ዕለት እስካሁን ምንም ዓይነት ስምምነት ላይ ባይደርስም ልዩነቶች እየጠበቡ መምጣታቸውን ተናግረዋል።ያጋሩ, የፓኪስታን ልዑክ ከኢራን ባለሥልጣናት ጋር ለመወያየት ዳግም ቴህራን ገቡ
  3. ከ 1 ሰአት በፊትአሜሪካ ለታይዋን ልትሸጥ የነበረውን 14 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ የጦር መሣሪያ በኢራን ጦርነት ምክንያት አቋረጠችየአሜሪካ የባህር ኃይል ተጠባባቂ ኃላፊ ሁንግ ካኦየፎቶው ባለመብት,CQ-Roll Call, Inc via Getty Imagesአሜሪካ ለታይዋን ልትሸጥ የነበረውን 14 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ የጦር መሣሪያ ለኢራን ጦርነት በቂ ክምችት እንዳላት ለማረጋገጥ በሚል አቋረጠች።የአሜሪካ የባህር ኃይል ተጠባባቂ ኃላፊ ሁንግ ካኦ ሐሙስ ዕለት የመረጃውን ትክክለኛነት ለሴኔቱ አባላት አረጋግጠዋል።ይህ የአሜሪካ ውሳኔ የተሰማው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሽያጩን ለማጽደቅ ቁርጠኛ እንዳልሆኑ እና በጉዳዩ ላይ ከታይዋን ፕሬዝዳንት ጋር እንደሚነጋገሩ ከገለጹ ከቀናት በኋላ ነው።የታይዋን ፕሬዚዳንት ቢሮ ቃል አቀባይ አርብ ዕለት ለጋዜጠኞች “አሜሪካ በጦር መሳሪያ ሽያጭ ላይ ስላደረገችው ማስተካከያዎች” ምንም ዓይነት መረጃ እንዳልደረሳቸው ተናግረዋል።አሜሪካ ለታይዋን የምትሸጠው የጦር መሣሪያ ቤይጂንግን ለረዥም ጊዜ ሲያስቆጣት ነበር።ካኦ ሐሙስ ዕለት በሴኔት ፊት ቀርበው “አሁን ለኤፒክ ፊውሪ የሚያስፈልገንን መሣሪያ፣ ምንም እንኳ በቂ ቢኖረንም፣ ለማረጋገጥ ለተወሰነ ጊዜ አቁመነዋል” ሲሉ አስረድተዋል።ካኦ የጦር መሣሪያ ሽያጭን በተመለከተ “ከታይዋን ጋር አልተነጋገርኩም” ብለዋል።አክለውም “ሁሉም ነገር እንዳለን እያረጋገጥን ነው፣ ነገር ግን አስተዳደሩ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ለውጭ አገራት የሚደረገው የመሣሪያ ሽያጭ ይቀጥላል” ብለዋል።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለፎክስ ኒውስ ባለፈው ሳምንት “ከቻይና ጋር ለመደራደር ጥሩ ነጥብ ነው” ቢሉም የመሣሪያ ሽያጩ እንዲቆም መወሰናቸውን ግን እስካሁን አላረጋገጡም።በተጨማሪም ለጋዜጠኞች “በሚቀጥሉት አጭር ጊዜያት ውስጥ ውሳኔ ላይ እንደርሳለን” ሲሉ ተናግረዋል።እነዚህ አስተያየቶች የተሰጡት ፕሬዚዳንቱ ቤይጂንግ ደርሰው ከመጡ በኋላ ነው።ትራምፕ ከዢ ጂንፒንግ ጋር ባደረጉት ውይይት ታይዋን በአሜሪካ እና በቻይና መካከል በጣም ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነች ተናግረው ነበር።ትራምፕ በኋላ ላይ ለጋዜጠኞች ከዢ ጋር የአሜሪካ የጦር መሣሪያ ሽያጭን በሚመለከት “በዝርዝር” መወያየታቸውን ተናግረዋል።እንደ አውሮፓውያኑ በ1982 አሜሪካ ለታይዋን በጉዳዩ ላይ ቤይጂንግን ላለማማከር ቃል ገብታ ነበር።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስለ ጦር መሣሪያ ሽያጭ ከታይዋን ፕሬዝዳንት ላይ ቺንግ-ቲ ጋር ሊነጋገሩ መሆኑን ተናግረዋልዋሽንግተን ለቻይና መንግሥት እውቅና በመስጠት ከታይዋን ጋር ያላትን ይፋዊ ግንኙት ካቋረጠችበት የአውሮፓውያኑ 1979 ወዲህ የአሜሪካ እና ታይዋን መሪዎች በቀጥታ ተነጋግረው አያውቁም።ቻይና ታይዋንን የግዛቷ አካል አድርጋ የምታይ ሲሆን፤ ከአንድነትን ለማምጣት ልትከተል ከምትችላቸው አማራጮች መካከል አንዱም በኃይል መጠቅለል ነው።ያጋሩ, አሜሪካ ለታይዋን ልትሸጥ የነበረውን 14 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ የጦር መሣሪያ በኢራን ጦርነት ምክንያት አቋረጠች
  4. ከ 1 ሰአት በፊትአሜሪካ የታንዛኒያ ፖሊስ ሁለት አክቲቪስቶችን በማሰቃየታቸው ኃላፊው ላይ ማዕቀብ ጣለችኬንያዊው ተሟጋች ቦኒፌስ ምዋንጊየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ የታንዛኒያ ፖሊስ ባለሥልጣናት የምሥራቅ አፍሪካ አክቲቪስቶች ላይ “ስቅይት እና ጾታዊ ትንኮሳ” በማድረሳቸው ማዕቀብ ጣለች።የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በመግለጫቸው ላይ የታንዛኒኣ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር የሆኑት ፋውስቲን ጃከሰን ማፍዌሌን “በሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ መሳተፋቸው በተጨባጭ መረጃዎች” በመረጋገጡ ማዕቀብ መጣሉን ገልጸዋል።የታንዛኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሃሙድ ታቢት ኮምቦ ለቢቢሲ ማፍዌሌ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ የተጣለባቸው ማዕቀብ በይፋ እንዳልደረሳቸው ተናግረዋል።ማዕቀቡ የተጣለው የአሜሪካ ሕግ አውጪዎች ታንዛኒያ ያላት የሰብዓዊ መብት አያያዝን በሚመለከት ጠንከር ያለ ትችት ካቀረቡ በኋላ ነው።ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ ቦኒፌስ ምዋንጊ እና አጋተር አቱሃይሬ የተባሉት አክቲቪስቶች ወደ ታንዛኒያ ያመሩት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ቱንዱ ሊሱን የፍርድ ሒደት ለመከታተል ነበር።በርካቶች የኬንያ መንግሥትን እና ባለሥልጣናትን በመገዳደር በደፋርነቱ የሚያውቁት ኬንያዊው ተሟጋች ቦኒፌስ ምዋንጊ በታንዛኒያ ወሲባዊ ስቅይቶች እንደተፈጸሙበት በተናገረበት ወቅት “ለመኖር እየታገልኩ ነው” ሲል ለቢቢሲ ተናግሮ ነበር።ኬንያዊው ቦኒፌስ እና ኡጋንዳዊቷ አቱሃይሬ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ለበርካታ ቀናት ታስረዋል።የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ከታሰረ በኋላም እርቃኑን እንዲቀር ተደርጎ፣ እጁ እና እግሩን አስረው፣ ተገልብጦ (ወፌ ላላ) ውስጥ እግሩን እንደተገረፈ ተናግሯል።በመቀመጫው በኩል የተለያዩ ቁሶችን እንዲሁም አንደኛው እጁን በመጠቀም የተለያዩ ወሲባዊ ጥቃቶችን እንዳደረሰቡት ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ እና እያለቀሰ ለጋዜጠኞች አስረድቷል።አቱሃይሬ በበኩሏ በእስር ላይ እያለች እንደተደፈረች ተናግራለች።የታንዛኒያ ዋና ከተማ ዳሬሰላም የፖሊስ ኃላፊ ቦኒፌስ የሰጠውን ምስክርነት ያልተቀበሉት ሲሆን፣ ክሱ ከአክቲቪስቶች የሚመጣ “አስተያየቶች” እና “የሰሚ ሰሚ” ነው ሲሉ ለቢበሲ ተናግረዋል።”እዚህ ቢሆኑ ኖሮ፤ ምን እያሉ እንደሆነ እጠይቃቸው ነበር። በሕግ እነዚህ ነገሮች የሰሚ ሰሚ ወይም የሰሚ ሰሚ ማስረጃ ይባላሉ” ሲሉ ጁማኔ ሙሊሮ ለቢቢሲ ገልጸዋል።ሐሙስ ዕለት ሩቢዮ በመግለጫቸው ላይ የታንዛኒያ ፖሊስ አባላት ሁለቱን አክቲቪስቶች “አስረዋል፣ አሰቃይተዋል እና ወሲባዊ ትንኮሳ ፈጽመዋል” ብለዋል።መግለጫው ማፍዌሌ የነበራቸውን ሚና ባይጠቅስም ነገር ግን ሁለት የሰብዓዊ መበት ተሟጋቾች “ለዚህ አስነዋሪ ተግባር ተጠያቂነት መውሰድ አለበት” ብለዋል።የታንዛኒያ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር የሆኑት ማፍዌሌ በሳሚያ ሱሉሁ አስተዳደር ዘመን የአሜሪካ ማዕቀብ የተጣለባቸው የመጀመርያው የታንዘኒያ ከፍተኛ ባለሥልጣን ሆነዋል።ቢቢሲ የታንዛኒያን ፖሊስ አስተያት ቢጠይቀም ምላሽ አላገኘም።ያጋሩ, አሜሪካ የታንዛኒያ ፖሊስ ሁለት አክቲቪስቶችን በማሰቃየታቸው ኃላፊው ላይ ማዕቀብ ጣለች
  5. ከ 2 ሰአት በፊትአሜሪካ እና ኢራን በቁልፍ ጉዳዮች ላይ ባይግባቡም ድርድሩ ለውጥ እያሳየ መሆኑን ሁለቱም ተናገሩትራምፕ እና ሞጅታባአሜሪካ እና ኢራን በዩራኒየም ክምችት እና በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ በሚኖር ቁጥጥር ላይ አለመግባባታቸውን የሚያሳዩ ዘገባዎች ሐሙስ ዕለት ቢወጡም የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በድርድሮቹ ላይ “ጥሩ ምልክቶች” መኖራቸውን ተናገሩ።የአሜረካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው የኢራንን በከፍተኛ ደረጃ ተብላልቶ የተከማቸ ዩራኒየም ከአገሪቱ እንደሚያወጡ ተናግረዋል።አሜሪካ የኢራን ተብላልቶ የተከማቸ ዩራኒየም የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ለማምረት መቃረቡን ታምናለች።ቴህራን በበኩሏ ለሰላማዊ አገልግሎት ብቻ የሚውል መሆኑን በመግለጽ ትከራከራለቸ።“እናገኘዋለን፤ አንፈልገውም። አያስፈልገንም። ካገኘነው በኋላ እናወድመው ይሆናል፤ ነገር ግን እንዲኖራቸው ግን አንፈቀድም” ሲሉ በዋይት ሐውስ ለተገኙ ዘጋቢዎች ተናግረዋል።ሩቢዮ ለጋዜጠኞች ቴህራን በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚያልፉ መርከቦች ላይ ቀረጥ የምትጥል ከሆነ ዲፕሎማሲ ቦታ አንደማይኖረው ጨምረው ተናግረዋል።አክለውም በንግግሩ ላይ የተወሰኑ ለውጦች አሉ ሲሉ ተናግረዋል።“ጥሩ ምልክቶች አሉ” ያሉት ሩቢዮ “በጣም ተስፈኛ መሆን አልፈልግም. . . በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ምን እንደሚሆን እናያለን” ብለዋል።አንድ ከፍተኛ የኢራን ባለሥልጣን ለሮይተርስ የዜና ወኪል ሐሙስ ዕለት እስካሁን ምንም ዓይነት ስምምነት ላይ ባይደርስም ልዩነቶች እየጠበቡ መምጣታቸውን ተናግረዋል።አክለውም የኢራን የተብላላ ዩራኒየም እና በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ያላት ቁጥጥር አሁንም ያላግባቡ ነጥቦች መሆናቸውን ጨምረው ተናግረዋል።ሁለት ከፍተኛ የኢራን ባለሥልጣናት ከትራምፕ አስተያየት አስቀድመው ለሮይተርስ ጠቅላይ መሪው አያቶላህ ሞጅታባ ኻሜኒ በከፍተኛ ደረጃ የተብላላ ዩራኒየሙ ከአገር እንዳይወጣ ማዘዛቸውን ተናግረዋል።ያጋሩ, አሜሪካ እና ኢራን በቁልፍ ጉዳዮች ላይ ባይግባቡም ድርድሩ ለውጥ እያሳየ መሆኑን ሁለቱም ተናገሩ
  6. ከ 5 ሰአት በፊትአሜሪካ ከሄዝቦላህ ጋር በተያያዘ በሊባኖስ የኢራን አምባሳደርን ጨምሮ ዘጠኝ ሰዎች ላይ ማዕቀብ ጣለችሄዝቦላህ ሊባኖስ ውስጥ ሠፊ የድጋፍ መሠረት አለውየፎቶው ባለመብት,EPAአሜሪካ ሐሙስ ዕለት በሊባኖስ የኢራን አምባሳደርን ጨምሮ ዘጠኝ ሰዎች ላይ ከሄዝቦላህ ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ማዕቀብ ጣለች።ግለሰቦቹ ሄዝቦላህ ትጥቁን እንዳይፈታ በማድረግ በመካከለኛው ምሥራቅ ሰላምን አደናቅፈዋል በሚል ተወንጅለዋል።የአሜሪካ ግምጃ ቤት ባለሥልጣናቱ በሊባኖስ ፓርላማ፣ መከላከያ፣ እና የጸጥታ መዋቅሩ ውስጥ በመሆን ሄዝቦላህ ወሳኝ የሆኑ የሊባኖስ ተቋማት ላይ ተጽዕኖውን እንዲያሳርፍ አድርገዋል በማለት ወንጅሏል።የግምጃ ቤቱ ኃላፊ ስኮት ቤሴንት “ሄዝቦላህ ሽብርተኛ ድርጅት ነው እናም ሙሉ በሙሉ ትጥቅ መፍታት አለበት” ብለዋል።ሄዝቦላህ ከኢራን የትጥቅ እና ስንቅ ድጋፍ የሚያገኝ ሲሆን እንቅስቃሴውን የጀመረው ከአውሮፓውያኑ 1980ዎቹ መባቻ ጀምሮ ነው።አሜሪካ እና የባሕረ ሰላጤው አረብ አገራት ሳዑዲ አረቢያን ጨምሮ “ሽብርተኛ ቡድን” ሲሉ ፈርጀውታል።ሄዝቦላህ በ1983 (እአአ) በአሜሪካ ኤምባሲ እና በአሜሪካ ባሕር ኃይል ላይ ጥቃቶችን ፈጽሞ 258 አሜሪካውያን እና 58 ፈረንሳያውያን ሞተዋል።ከዚህም በተጨማሪ እአአ በ1983 በቤይሩት በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ ጥቃት በመፈጸምም ይወነጀላል።እስራኤል እና ሊባኖስ ባለፈው ሳምንት በመካከላቸው የተደረሰውን የተኩስ አቁም በ45 ቀን ለማራዘም ተስማምተዋል።ነገር ግን አሁንም እስረኤል በደቡብ ሊባኖስ በሄዝቦላህ ወታደራዊ ተቋማት ላይ የምትፈጽማቸውን ድብደባዎች ሄዝቦላህም ወደ እስራኤል ዒላማዎች ሮኬቶች እና ድሮኖች መተኮሱን አላቆመም።የአሜሪካ ግምጃ ቤት ቃል አቀባይ ቶሚ ፒጎት የታጣቂ ቡድኑን የገንዘብ ምንጭ ለማድረግ የሚረዳ መረጃ ለሰጠ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ 10 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት መወሰኑን ተናግረዋል።ፒጎት በመግለጫቸው ላይ “ይህ የመጀመርያው ነው። ማንኛውም ከአሸባሪ ድርጅቱ ጋር የሚተባበር ወይንም ያስጠለለ ወይም የሊባኖስን ሉዓላዊነት የሚገዳደር ተጠያቂ አንደሚሆን ማወቅ አለበት” ብለዋል።አክለውም “የተረጋጋች፣ አስተማማኝ እና ነጻ የሆነች ሊባኖስ እንድትኖር ሄዝቦላህ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ መፍታት እና የሊባኖስ መንግሥት በመላ አገሪቱ በጸጥታ ጉዳዮች ላይ ብቸኛ ሥልጣን እንዲኖረው ማድረግን ይጠይቃል” ሲሉ ተናግረዋል።ያጋሩ, አሜሪካ ከሄዝቦላህ ጋር በተያያዘ በሊባኖስ የኢራን አምባሳደርን ጨምሮ ዘጠኝ ሰዎች ላይ ማዕቀብ ጣለች
  7. 21 ግንቦት 2026“በሆርሙዝ በኩል ለማሳለፍ ገንዘብ መጠየቅ ተቀባይነት የለውም” – የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርማርኮ ሩቢዮየፎቶው ባለመብት,EPAየአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ በሚተላለፉ መርከቦች ላይ የክፍያ ሥርዓት ለመዘርጋት የምታደርገውን ጥረት “ተቀባይነት የለውም” ሲሉ አጣጣሉት።በማያሚ አውሮፕላን ማረፊያ ለጋዜጠኞች ባደረጉት ንግግር በሆርሙዝ ወሽመጥ ለማለፍ ክፍያ መጠየቅ ተቀባይነት እንደሌለው “እኛ ብቻ ሳንሆን ዓለም ይስማማበታል” ብለዋል።ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ያላትን ይዞታ እና ቁጥጥር በማስፋት በሆርሙዝ ለሚያልፉ መርከቦች የክፍያ ሥርዓት እንደምትዘረጋ አስታውቃለች።ይሄንን የተቃወሙት ማርኮ ሩቢዮ በጉዳዩ ላይ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት የውሳኔ ሐሳብ ማርቀቁን ገልጸዋል።በባህሬን የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ከ100 በላይ አገራት ደግፈዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩም “በፀጥታው ምክር ቤት ታሪክ ብዙ ደጋፊ ያገኘ የውሳኔ ሐሳብ ነው” ብለዋል።ጉዳዩን ቻይና ሳሉ እንዳነሱት ጠቅሰው “የትኛውም አገር ክፍያን አልደገፈም” ብለዋል።ይህ አካሄድ ዲፕሎማሲያው ንግግርን እንደሚያሰናክልም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። “እንደዚህ ካደረጉ ለዓለም ስጋት ነው። ፍጹም ሕገ ወጥም ነው” ሲሉ አክለዋል።ያጋሩ, “በሆርሙዝ በኩል ለማሳለፍ ገንዘብ መጠየቅ ተቀባይነት የለውም” – የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
  8. 21 ግንቦት 2026ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ያላትን ቁጥጥር የሚያሰፋ ካርታ ይፋ አደረገችካርታኢራን ወሳኝ በሆነው የሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ያላትን ቁጥጥር ለማጠናከር ባላት ዓላማ መሠረት የመተላላፊያ አካባቢውን ሰፊ ቦታ በይዞታዋ ስር የሚስገባ ካርታ በማውጣት የወታደራዊ ቁጥጥሯ ክልል መሆኑን አሳውቃለች።ኢራን ጦርነት ከተከፈተባት በኋላ ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ እና ጋዝ የሚተላለፍበትን ወሽመጥ ለመቆጣጠር ያስችለኛል ያላቸውን ሕግ በፓርላማዋ በኩል ማውጣቷ ይታወሳል።ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ አለኝ የምትለውን ሉዓላዊ ይዞታን ለማረጋገጥ በምታደርገው ጥረት ውስጥ መተላላፊያውን እንዲቆጣጠር “የፋርስ ባሕረ ሰላጤ ወሽመጥ ባለሥልጣን” የተባለ አካል አቋቁማለች።ባለሥልጣኑ ይፋ ባደረገው ካርታ የኢራን ይዞታ አስከ ኦማን እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውሃ ክልል ድረስ ዘልቆ የሚገባ ነው። ይህንንም አካባቢ የኢራን ጦር ኃይሎች የሚቆጣጠሩት መሆኑን አሳውቋል።ይህንንም ተከትሎ የተበባሩት አረብ ኤምሬቶች የውሃ ክልሏን ያካተተውን የኢራን ካርታ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን “ያልተጫበጠ ህልም” በማለት ውድቅ አድርጋዋለች።ነገር ግን ሆርሙዝን የሚቆጣጠረው የኢራን ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት እንዳለው በወሽመጡ በኩል የሚደረጉ ማንኛውም የመርከቦች እንቅስቃሴ “ከባለሥልጣኑ ጋር በመነጋገር እና ፈቃድ በማግኘት” ሊሆን እንደሚገባ አስታውቋል።አሜሪካ እና በባሕረ ሰላጤው የሚገኙ አጋሮቿ ግን ኢራን በሆርሙዝ ላይ ያላትን ቁጥጥር ለማረጋገጥ የምታደርገውን ሙከራ ውድቅ አድርገውታል።አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚያልፉ መርከቦች ኢራን ላወጣችው የቁጥጥር መመሪያ ተገዢ እንዳይሆኑ እየነገረች ነው።በተባበሩት መንግሥታት የባሕር ላይ እንቅስቃሴ ሕግ ስምምነት መርከቦች በሌላ አገር የውሃ ክልል ላይ ያለምንም ችግር እንዲተላለፉ የሚፈቅድ ሲሆን፣ ነገር ግን ኢራን ይህንን ስምምነት አልፈረመችም።ያጋሩ, ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ያላትን ቁጥጥር የሚያሰፋ ካርታ ይፋ አደረገች
  9. 21 ግንቦት 2026አሜሪካ ኩባን ‘ማስፈራራት’ እንድታቆም ቻይና አሳሰበችየቀድሞ የኩባ ፕሬዝዳንት ራውል ካስትሮየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የቀድሞ የኩባ ፕሬዝዳንት ራውል ካስትሮአሜሪካ ኩባን “ማስፈራራት” እንዲሁም “ጫና ለማሳደር መሞከር” እንድታቆም ቻይና አሳሰበች።የአሜሪካ ፍርድ ቤት የ94 ዓመቱ የቀድሞ የኩባ ፕሬዝዳንት ራውል ካስትሮ ላይ ክስ መመሥረቱን ተከትሎ ነው ቻይና ማሳሰቢያ የሰጠችው።ከ30 ዓመት በፊት በኩባ እና በፍሎሪዳ መካከል ተመትተው ከወደቁ ሁለት አውሮፕላኖች ጋር በተያያዘ የቀድሞው የኩባ መሪ ላይ የተመሠረተው ክስ የአሜሪካ ዜጎችን ለመግደል ማሴር እና ሌሎችንም የያዘ ነው።አራት ሰዎች የሞቱበት ክስተት የሁለቱን አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አሻክሯል።የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኩባን ኮሚኒስት መንግሥት መገርሰስ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጋዎ ጂያኩን “አሜሪካ በየአጋጣሚው ኩባን ማስፈራራት ማቆም አለባት” ብለዋል።ቻይና “በጽኑ ኩባን ትደግፋለች። በውጭ ኃይሎች በማንኛውም አውድ ኩባ ላይ የሚደርስ ጫናን ቤይጂንግ ትቃወማለች” ሲሉም ተናግረዋል።ቃል አቀባዩ “አሜሪካ ማዕቀብ እና የሕግ መዋቅርን በመጠቀም ኩባን ማስፈራራት እና ጫና ማሳደር ማቆም አለባት” በማለትም አክለዋል።የኩባን ሉዓላዊነት እና ክብር ቻይና እንደምትደግፍ እንዲሁም የውጭ ኃይሎችን ጣልቃ ገብነት እንደምትቃወም ገልጸዋል።ያጋሩ, አሜሪካ ኩባን ‘ማስፈራራት’ እንድታቆም ቻይና አሳሰበች
  10. 21 ግንቦት 2026የኢራኑ ጠቅላይ መሪ በከፍተኛ ሁኔታ የተብላላ ዩራንየም ከአገራቸው እንዳይወጣ ወሰኑየኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒየፎቶው ባለመብት,Tasnim News Agencyኢራን ጦርነቱን ለማስቆም የቀረበላትን በከፍተኛ ሁኔታ የተብላላ ዩራንየምን ወደ ውጭ ለመላክ የቀረበውን ሐሳብ ውድቅ ለማድረግ መወሰኗን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘገበ።ሮይተርስ ሁለት ምንጮችን ጠቅሶ ባወጣው ዘገባ የኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ በከፍተኛ ሁኔታ የተብላላ ዩራንየም ከአገር እንዳይወጣ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።አሜሪካ ለሰላም ድርድር ካቀረበቻቸው ነጥቦች መካከል አንዱ ይሄው ጉዳይ ነው።የጠቅላይ መሪው ውሳኔ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን አስተዳደር ሊያስቆጣ እና የድርድር ሒደቱን ሊያወሳስብ ይችላል።ሮይተርስ ያነጋገራቸው የእስራኤል ባለሥልጣናት እንደሚሉት፤ ኢራን ያከማቸችው የተብላላ ዩራንየም ከአገሪቱ እንደሚወጣ ለእስራኤል ማረጋገጫ ሰጥተዋል።የሰላም ስምምነት ላይ ኒውክሌር ጦር መሣሪያ የመሥራት ነጥብ ላይ የደረሰው የተብላላ ዩራንየም ከኢራን እንደሚወጣ መናገራቸው ተገልጿል።ስለ ጉዳዩ የኢራን መገናኛ ብዙኃን እስካሁን ድረስ ዘገባ አላወጡም።ኢራን ከአሜሪካ እና ከሌሎች ምዕራባውያን ጋር ለዘመናት ሲያወዛግብ የቆየው የኒውክሌር መርሃ ግብሯን ሙሉ ለሙሉ እንድታቆም እና ከጥቅም ውጪ እንድታደርግ የቀረበላትን ጥያቄ ባለመቀበሏ ነው።በአሜሪካ እና በእስራኤል የተከፈተባትን ጦርነት ለማቆም ከቀረበላት ቅድመ ሁኔታ መካከልም እንዱ የኒውክሌር መርሃ ግብሯ ቢሆንም፤ ኢራን አልተቀበለችውም።ያጋሩ, የኢራኑ ጠቅላይ መሪ በከፍተኛ ሁኔታ የተብላላ ዩራንየም ከአገራቸው እንዳይወጣ ወሰኑ
  11. 21 ግንቦት 2026ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኢቦላ ቫይረስ መቀስቀስ ምክንያት የዓለም ዋንጫ ልምምድን አቋረጠችየዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጨዋችየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እ.አ.አ ከ1974 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ለፊፋ ዓለም ዋንጫ አልፋለችዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በምሥራቁ የአገሪቱ ክፍል የተቀሰቀሰውን ኢቦላ ተከትሎ በዋና ከተማዋ ኪንሻሳ ሊካሄድ የነበረን የዓለም ዋንጫ ቅድመ ልምምድ መሰረዟን አስታወቀች።ከ130 በላይ ሰዎችን ስለመግደሉ የተነገረለት በሽታ ማገርሸቱን ተከትሎ ዝግጅቶች ወደ ቤልጂየም መዘዋወራቸው ታውቋል።የዓለም የጤና ድርጅት ኢቦላን “የኅብረተሰብ ጤና ስጋት” ሲል መድቦታል።አገሪቱ እ.አ.አ ከ1974 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ዋንጫ ለመሳተፍ እየተዘጋጀች ሲሆን፤ ቀድመው የተያዙ የሙከራ ጨዋታዎች በአውሮፓ እንደሚካሄዱ የብሔራዊ ቡድኑ ቃል አቀባይ ጄሪ ካሊሞ ለዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የወዳጅነት ጨዋታዎችን ከዴንማርክ፣ ቤልጂየም፣ ችሊ እና ስፔን ጋር ትጫወታለች።ቃል አቀባዩ እንዳሉት ልምምዱ የተሰረዘው ከሜክሲኮ እና ከካናዳ ጋር የዓለም ዋንጫን የምታዘጋጀው አሜሪካ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ላይ የጉዞ እግድ በመጣሏ ነው።ዋሽንግተን ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ጨምሮ በሦስት አገራት ባለፉት 21 ቀናት ጉዞ ያደረጉ እና አሜሪካዊ ያልሆኑ መንገደኞች ወደ ግዛቷ እንዳይገቡ ክልከላ ጥላለች።ሁሉም የአገሪቱ ተጨዋቾች እና ፈረንሳዊው የቡድኑ አሰልጣኝ ሰባስቲያን ድሳብሬ መቀመጫቸው ከማዕከላዊ አፍሪካዊት አገር ውጭ በመሆኑ እና ልምምድ በመሰረዙ እግዱ ተፅዕኖ አያሳድርባቸውም።ያጋሩ, ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኢቦላ ቫይረስ መቀስቀስ ምክንያት የዓለም ዋንጫ ልምምድን አቋረጠች
  12. 21 ግንቦት 2026ኢራን ከታሰበው በበለጠ ፍጥነት የወታደራዊ ኢንዱስትሪዋን መልሳ እየገነባች መሆኑን ሲኤንኤን ዘገበየኢራን ወታደርየፎቶው ባለመብት,NurPhoto via Getty Imagesአሜሪካ እና እስራኤል በከፈቱት ጥቃት ወታደራዊ አቅሟ የተመታባት ኢራን፤ የተኩስ አቁም ከተደረገ ወዲህ ወታደራዊ ኢንዱስትሪዋን በፍጥነት እየገነባች እንዲሁም የተወሰኑ ድሮኖችን እያመረተች መሆኑን ሲኤንኤን የአሜሪካ የስለላ መረጃን ጠቅሶ ዘገበ።የአሜሪካው ቴሌቪዥን ጣቢያ ያነጋገራቸው አራት ምንጮች እንደገለጹት የኢራን ጦር መጀመሪያ ላይ ሲጠበቅ ከነበረው ፍጥነት በበለጠ ሁኔታ አቅሙን እያጠናከረ መሆኑን የዋሽንግተን የስለላ መረጃ አመልክቷል።በአሁኑ ጦርነት ጥቃት የተፈጸመባቸው የሚሳዔል ስፍራዎች፣ ማስወንጨፊያዎች እና የመምረቻ አቅሞች እየተተተኩ መሆኑ፤ ኢራን በቀጣናው ለሚገኙ የአሜሪካ አጋሮች አሁንም ትልቅ ስጋት መሆኗን ያሳያል ተብሏል።እንደ ሲኤንኤን ዘገባ፤ የስለላ መረጃው ስለ ኢራን ጦር እዚህ ድምዳሜ ላይ መድረሱ አሜሪካ እና እስራኤል በፈጸሙት ጥቃት የሠራዊቱ አቅም ላይ የደረሰው ጉዳት ምን ያህል ነው የሚለውን ጥያቄ ውስጥ አስገብቶታል።የተለያዩ የጦር መሣሪያ ክፍሎችን ማምረት ለመጀመር የሚያስፈልገው ጊዜ የተለያየ ቢሆንም፤ ኢራን በድሮን ጥቃት የመፈጸም አቅሟን በስድስት ወር ውስጥ ሙሉ በሙሉ ወደ ነበረበት መመለስ እንደምትችል አንድ አሜሪካ ምንጭ መናገራቸውን ዘገባው ገልጿል።ሲኤንኤን ያነጋገራቸው ባለሥልጣን፤ “ኢራናውያን የስለላ ማኅበረሰቡ ለመልሶ ግንባታ ያስቀመጠውን የጊዜ ሰሌዳ በሙሉ አልፈዋል” ማለታቸው ተጠቅሷል።ዘገባው እንደሚያመለክተው፤ ኢራን ከታሰበው በበለጠ ፍጥነት መልሳ መገንባት የቻለችው በተለያዩ ምክንያቶች ነው።ከሩሲያ እና ቻይና ያገኘችው ድጋፍ እንዲሁም አሜሪካ እና እስራኤል ተስፋ ባደረጉት መጠን ከፍተኛ ጉዳት አለማድረሳቸው በምክንያትነት እንደሚጠቀሱ አንድ ምንጭ ተናግረዋል ተብሏል።አሜሪካ እና ኢራን የተኩስ አቁም ካደረጉ ሳምንታት ቢቆጠሩም እስካሁን ድረስ ጦርነቱን በዘላቂነት የሚያስቆም ስምምነት ላይ አልደረሱም። አሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ኢራን የሰላም ስምምነት የማትፈጽም ከሆነ ጥቃት እንደሚፈጽሙ አስጠንቅቀዋል።ያጋሩ, ኢራን ከታሰበው በበለጠ ፍጥነት የወታደራዊ ኢንዱስትሪዋን መልሳ እየገነባች መሆኑን ሲኤንኤን ዘገበ
  13. 21 ግንቦት 2026የፓኪስታን ሠራዊት አዛዥ ወደ ኢራን ሊጓዙ ነውየፓኪስታን ሠራዊት አዛዥ ፊልድ ማርሻል አሲምየፎቶው ባለመብት,Reutersየአሜሪካ እና ኢራን ዋና አሸማጋይ የሆነችው ፓኪስታን የሠራዊት አዛዥ ፊልድ ማርሻል አሲም ሙኒር ዛሬ ወደ ቴህራን እንደሚገቡ የኢራን መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።ዘገባዎቹ እንደሚያመለክቱት የወታደራዊ አዛዡ የቴህራን ጉዞ ከዚህ ቀደም ከኢራን ባለሥልጣናት ጋር ሲደረግ ከነበረው ንግግር እና ምክክር የቀጠለ ነው።የፓኪስታን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሰይድ ሞህሲንም በአንድ ሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ረቡዕ ዕለት ቴህራን መግባታቸውን ‘ኢስና’ የተባለው ኢራን መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል። ከኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን እና የአገር ውስጥ ሚኒስትሩ እስካንዳር ሞሜኒ ጋር ተገናኝተዋል።የፓኪስታን እና የኢራን ባለሥልጣናት በንግግራቸው ቀጣናዊ ሁኔታዎችን እንደገመገሙ ዘገባው ጠቅሷል። በኢራን እና አሜሪካ መካከል የሚካሄደው ቀጥተኛ ያልሆነ ድርድር ስላለበት ሁኔታ መነጋገራቸውም ተገልጿል።የፓኪስታኒ ሚኒስትር አገራቸው ድርድሩን በተመለከተ ያላትን ምልከታ ለኢራን ባለሥልጣናት እንዳስረዱ ዘገባው አስነብቧል።ከፓኪስታኑ ሚኒስትር ጋር የተነጋገሩት የኢራን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ከዚያ በኋላ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፤ ቴህራንን “በማስገደድ እጅ እንድትሰጥ” ለማድረግ የሚደረግ ጥረት “ቅዠት” ነው ብለዋል።“ኢራን ያለማቋረጥ ቃሏን ጠብቃለች፤ ጦርነትን ለመቀልበስም ሁሉንም ጎዳና አስሳለች” ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ “በእኛ በኩል ሁሉም መንገዶች ክፍት ናቸው” በማለት ጽፈዋል።“ኢራንን በማስገደድ እጅ እንድትሰጥ ማድረግ ቅዠት እንጂ ሌላ ነገር አይደለም። በዲፕሎማሲ ውስጥ የጋራ መከበባርን ማምጣት ከጦርነት እጅህ የላቀ ብልህ፣ አስተማማኝ እና ዘላቂነት ያለው መንገድ ነው” ብለዋል።ያጋሩ, የፓኪስታን ሠራዊት አዛዥ ወደ ኢራን ሊጓዙ ነው
  14. 21 ግንቦት 2026የአሜሪካ ጦር የሆርሙዝ እገዳን በመጣስ የተጠረጠረን በኢራን ባንዲራ የሚንቀሳቀስ መርከብ አቅጣጫ ማስቀየሩን አስታወቀየአሜሪካ ወታደሮች መርከቡ ላይ ሲያርፉየፎቶው ባለመብት,U.S. Central Commandየአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንትኮም) ዋሽንግተን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የጣለችውን እገዳ ለመጣስ ሞክሯል በሚል የተጠረጠረን በኢራን ባንዲራ የሚንቀሳቀስ ነዳጅ ጫኝ መርከብ በኦማን ባሕረ ሰላጤ ላይ በቁጥጥር ስር አውሎ አቅጣጫውን ማስቀየሩን አስታወቀ።ማዕከላዊ ዕዙ የአሜሪካ ኃይሎች ወደ መርከቡ ላይ ሲወጡ እና በቁጥጥር ስር ሲያውሉት የሚያሳይ ቪዲዮ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ አጋርቷል።“ኤም/ቲ ሴሌስቲያል ሲ የተባለው እና የኢራን ባንዲራን የሚያውለበልብ ነዳጅ ጫኝ የንግድ መርከብ” በባሕር ኃይሉ ወታደሮች የተያዘው “አሜሪካ የጣለችውን የባሕር ጉዞ እገዳ በመጣስ ወደ ኢራን ወደብ ለመጓዝ በመሞከር ተጠርጥሮ” እንደሆነ ገልጿል።“የአሜሪካ ኃይሎች መርከቡን ከፈተሹ እና የመርከቡ ሠራተኞች የጉዞ አቅጣጫቸውን እንዲቀይሩ ካደረጉ በኋላ መርከቡን ለቅቀውታል” ብሏል።የአሜሪካ ኃይሎች የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ወደ ኢራን ወደብ የሚደረጉ ጉዞዎች ላይ የጣለውን እገድ “ሙሉ በሙሉ እያስፈጸሙ” መሆኑን የገለጸው ዕዙ፤ “91 የንግድ መርከቦች” ለእርምጃው እንዲገዙ መደረጉን ገልጿል።የአሜሪካ ወታደሮች መርከቡ ላይ ሲያርፉየፎቶው ባለመብት,U.S. Central Commandየምስሉ መግለጫ,የአሜሪካ ወታደሮች መርከቡ ላይ ሲያርፉያጋሩ, የአሜሪካ ጦር የሆርሙዝ እገዳን በመጣስ የተጠረጠረን በኢራን ባንዲራ የሚንቀሳቀስ መርከብ አቅጣጫ ማስቀየሩን አስታወቀ
  15. 21 ግንቦት 2026ትራምፕ እና ኔታንያሁ ስለ ኢራን ድርድር አካሄድ “በውጥረት የተሞላ” ንግግር ማድረጋቸው ተዘገበፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ቤንጃሚን ኔታንያሁየፎቶው ባለመብት,EPAፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ቤንጃሚን ኔታንያሁ የኢራን ጉዳይን በተመለከተ ማክሰኞ ዕለት “ከፍተኛ ውጥረት” የነበረበት እንዲሁም የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር “እጅግ ያበሳጨ” የስልክ ንግግር ማድረጋቸውን የአሜሪካው የዜና ምንጭ አክሲዮስ ዘገበ።እንደ አክሲዮስ ዘገባ፤ ከኢራን ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ እየተከናወኑ ስላሉ አዲስ ጥረቶች የተነሳበት የሁለቱ መሪዎች ንግግር ረጅም እና “አስቸጋሪ” ነበር።አሜሪካ እና ኢራን ጦርነቱን በመደበኛነት ለማቆም እና በ30 ቀናት ውስጥ ድርድር እንዲካሄድ የሚያስችል “የፍላጎት መግለጫ” በአሸማጋዮች በኩል እየተዘጋጀ መሆኑን ትራምፕ ለእስራኤሉ መሪ ተናግረዋል ተብሏል።ዘገባው እንደሚያመለክተው በአንድ ወር ውስጥ የሚደረገው ድርድር እንደ የኢራን የኒውክሌር ፕሮግራም እና የሆርሙዝ ወሽመጥ መከፈት ያሉ ጉዳዮች ንግግር እንዲደረግባቸው የሚያስችል ነው።ዋሽንግተን እና ቴህራን እዚህ ሰነድ ላይ ፊርማቸው እንደሚያኖሩ የተነገራቸው ኔታንያሁ በአካሄዱ እንዳልተስማሙ ሁለት የእስራኤል ምንጮች ለአክሲዮን ተናግረዋል።ስለ ስልክ ንግግሩ ገለጻ የተደረገላቸው የአሜሪካ ምንጭ ደግሞ “ከስልክ ጥሪው በኋላ የቢቢ ጸጉር እሳት ለብሶ ነበር” ሲሉ የኔታንያሁን ስሜት መግለጻቸውን ዘገባው አስነብቧል።እንደ አክሲዮስ ዘገባ፤ ከኢራን ጋር የሚደረገው ድርድር ላይ ከፍተኛ ጥርጣሬ ያላቸው ኔታንያሁ፤ ጦርነቱ እንዲጀመር እና የኢራን ወታደራዊ አቅም ይበልጥ እንዲዳከም ፍላጎት አላቸው። ወሳኝ መሠረተ ልማቶችን በመምታት አገዛዙ እንዲዳከምም ይፈልጋሉ ተብሏል።ትራምፕ በበኩላቸው ለሚደረገው ንግግር ጥቂት ተጨማሪ ቀናትን ለመስጠት ፈቃደኛ ናቸው። ይሁን እንጂ “ትክክለኛውም ምላሽ ካላገኘን” ጦርነት “በጣም በፍጥነት” ሊጀመር ይችላል ማለታቸውን ዘገባው ጠቅሷል።ያጋሩ, ትራምፕ እና ኔታንያሁ ስለ ኢራን ድርድር አካሄድ “በውጥረት የተሞላ” ንግግር ማድረጋቸው ተዘገበ
  16. 20 ግንቦት 2026ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ በልጃቸው የሚመራ የፀረ ሙስና ዘመቻ በባለሥልጣናት ላይ ጀመሩፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ እና ልጃቸው ሙሁዚ ካይኔሩጋባየፎቶው ባለመብት,Xየምስሉ መግለጫ,ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ እና የጦሩ አዛዥ ልጃቸው ሙሁዚ ካይኔሩጋባፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ የኡጋንዳ ጦር ሠራዊት አዛዥ በሆነው በልጃቸው የሚመራ በአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ላይ የፀረ ሙስና ዘመቻ መጀመራቸው ተዘገበ።በዚህም የተነሳ ካምፓላ የሚገኘው የተሰናባቿ የአገሪቱ ፓርላማ አፈ ጉባዔ መኖሪያ ቤት በኡጋንዳ የደኅንነት ኃይሎች ተፈትሾ ሮልስ ሮይስ እና ሬንጅ ሮቨርን ጨምሮ ቅንጡ መኪኖች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል።የአገሪቱ ጦር አዛዥ እና የፕሬዝዳንቱ ልጅ የሆኑት ሙሁዚ ካይኔሩጋባ አባታቸው ኡጋንዳ ውስጥ የሚገኝ ማንኛውንም ሰው በቁጥጥር ስር የማዋል ሥልጣን እንደሰጧቸው ተናግረዋል።የፀረ ሙስና ዘመቻው ለአራት አስርት ዓመታት ኡጋንዳን እየመሩ ባሉት በፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ትዕዛዝ የሚካሄድ ሳይሆን እንደማይቀር ይታመናል።ቤታቸው የተፈተሸው አፈ ጉባዔዋ የፕሬዝዳንቱ የቅርብ ሰው ተደርገው ይታዩ የነበረ ሲሆን ለረዥም ጊዜ ስማቸው ከሙስና ጋር ሲነሳ ቆይቷል። በዚህም በብሪታኒያ እና በአሜሪካ ማዕቀቦች ተጥሎባቸዋል።አሁን ከባለሥልጣኗ ቤት የተያዙት ውድ ንብረቶች በጨረታ ተሽጠው ገንዘቡ ለሕዝብ እንደሚመለስ የጦሩ አዛዥ ተናግረዋል።በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በሚያጋሯቸው መልዕክቶች አነጋጋሪ የሆኑት የፕሬዝዳንቱ ልጅ ከሰሞኑ ባሠራጩት ጽሁፍ በዋና ከተማዋ ባሉ መንገዶች ላይ ጉድለት ከተገኘ የግንባታውን ኮንትራት የወሰዱትን ሰዎች አንገታቸውን እንደሚቀሉ አስጠንቅቀዋል።ያጋሩ, ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ በልጃቸው የሚመራ የፀረ ሙስና ዘመቻ በባለሥልጣናት ላይ ጀመሩ
  17. 20 ግንቦት 2026ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደረገው ድርድር ከመጨረሻው ምዕራፍ መድረሱን እና ካልተሳካ ግን ጥቃት እንደሚጀምሩ አስጠነቀቁዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ ረቡዕ ከኢራን ጋር የሚደረገው ድርድር የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መድረሱን አስታውቀው ከስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ ግን ጥቃት እንደሚፈጽሙ አስጠነቀቁ።ትራምፕ ‘ኦፕሬሽን ኤፒክ ፊዩሪ’ ብለው የሰየሙትን ዘመቻ በተኩስ አቁም ጋብ ካደረጉት ስድስት ሳምንታት ቢያልፉም በሁለቱ አገራት መካከል የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም የሚደረገው ንግግር ግን እምብዛም ለውጥ እያሳየ አይደለም።ፕሬዝዳንት ትራምፕ በዚህ ሳምንት በኢራን ላይ ተጨማሪ ጥቃት እንዲፈጸም ለማዘዝ ተቃርበው እንደነበር ተናግረው ለድርድር ተጨማሪ ጊዜ ለመስጠት በሚል መሰረዛቸውን ተናግረዋል።ትራምፕ ዛሬ ለጋዜጠኞች “ከኢራን ጋር የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሰናል። ምን እንደሚሆን እናያለን። ከስምምነት ላይ እንደርሳለን ወይንም ትንሽ አስቀያሚ የሆነ ነገር እናደርጋለን። ነገር ግን ያ አይሆንም ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ” ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።“ተጨማሪ ዕድል መስጠት እፈልጋለሁ፤ ምንም የሚያስቸኩለኝ ነገር የለም” ብለዋል።አክለውም “በሀሳብ ደረጃ ከብዙ ሰዎች ይልቅ ጥቂቶች ቢሞቱ እመርጣለሁ። በማንኛውም መንገድ ልናደርገው እንችላለን።”ቴህራን በበኩሏ ትራምፕ ጦርነት ለመጀመር እያሴሩ ነው ስትል በመወንጀል ማንኛውም ጥቃት ቢፈጸምባት ከመካከለኛው ምሥራቅ ባሻገር አጸፋ ለመስጠት ዝታለች።የአገሪቱ አብዮታዊ ዘቡ ባወጣው መግለጫ “በኢራን ላይ ዳግም ጥቃት ከተፈጸመ በአካባቢው የሚታሰበው ጦርነት አሁን ከቀጣናው ያልፋል” ብሏል።የኢራን ፓርላማ አፈጉባዔ እና ዋነኛ ተደራዳሪ የሆኑት ባጋር ጋሊባፍ በበኩላቸው በድምጽ ባስተላለፉት መልዕከት “ጠላት በይፋም ሆነ በስውር የሚያደርገው እንቅስቃሴ” አሜሪካኖች አዲስ ጥቃት ለመክፈት እየተዘጋጀ መሆኑን ያሳያል ብለዋል።የፓኪስታን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር በዛሬው ዕለት ቴህራን መሆናቸው ተሰምቷል። ኢራን አዲስ የሰላም ዕቅዷን በፓኪስታን በኩል ለአሜሪካ የሰጠችው በዚህ ሳምንት ነው።ነገር ግን የሰላም ዕቅዱ ከዚህ በፊት ካቀረበችው የሚለይ ነገር እንደሌለው ተንታኞች ተናግረዋል።ያጋሩ, ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደረገው ድርድር ከመጨረሻው ምዕራፍ መድረሱን እና ካልተሳካ ግን ጥቃት እንደሚጀምሩ አስጠነቀቁ
  18. 20 ግንቦት 2026የኢራን ዋነኛ ተደራዳሪ አሜሪካ “አዲስ ጦርነት ለመጀመር” ትፈልጋለች አሉየኢራን ፓርላማ አፈ ጉባዔ ሞሐመድ ባጋር ጋሊባፍየፎቶው ባለመብት,EPAየኢራን ፓርላማ አፈ ጉባዔ ሞሐመድ ባጋር ጋሊባፍ አሜሪካ አዲስ ጦርነት ለመጀመር ትፈልጋለች ሲሉ ተናገሩ። አፈጉባዔው አክለውም አሜሪካ እስላማዊ ሪፐብሊክ ኢራን እጅ እንደምትሰጥ ተስፋ ታደርጋለች ብለዋል።ጋሊባፍ በኢራን መገናኛ ብዙኃን ላይ በሰጡት የድምጽ አስተያየት “ጠላት በግልጽም ሆነ በስውር የሚያደርገው እንቅስቃሴ ከፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫና ባሻገር ወታደራዊ ዓላማዎቹን ፈጽሞ እንዳልተዋቸው እና አዲስ ጦርነት ለመጀመር እንደሚፈልግ ያሳያል” ብለዋል።አፈ ጉባዔው አክለውም “ሁኔታውን በቅርበት ስንከታተለው ዩናይትድ ስቴትስ ኢራናውያን እጃቸውን ይሰጣሉ ብላ ተስፋ ታደርጋለች” ብለዋል።ታስኒም የዜና ወኪል ላይ በድምጽ በተላለፈ መልዕክታቸው የአገሪቱ መከላከያ በተኩስ አቁሙ ወቅት “ጥንካሬውን ዳግም መገንባቱን” ተናግረዋል።ጋሊባፍ “ጠላት ኢራንን ዳግም ቢያጠቃ እንዲጸጸት እናደርገዋለን” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ላይ ዳግመኛ ጦርነት ለመክፈት ጥቂት ሰዓት ሲቀራቸው ሃሳባቸውን መለወጣቸውን ተናግረው ነበር።ፕሬዚዳንቱ የኢራን ባለሥልጣናት ከአሜሪካ ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ “እየለመኑ” እንደነበረም ገልጸዋል።ትራምፕ በድጋሚ ኢራን ላይ ጥቃት መሰንዘር ሊያስፈልግ ይችላል ማለታቸውም ተዘግቧል።ከኢራን ጋር በቀጣይ ቀናት ስምምነት ላይ ካልተደረሰ ጥቃት መፈጸም እንደሚቀጥሉ አስጠንቅቀዋል።ያጋሩ, የኢራን ዋነኛ ተደራዳሪ አሜሪካ “አዲስ ጦርነት ለመጀመር” ትፈልጋለች አሉ
  19. 20 ግንቦት 20266 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ የጫኑ መርከቦች የሆርሙዝ ወሽመጥን አቋረጡበሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የምትቀዝፍ መርከብየፎቶው ባለመብት,Reutersለሁለት ወራት በባሕረ ሰላጤው አገራት ቆመው የነበሩ ሦስት ግዙፍ ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ረቡዕ ዕለት የሆርሙዝ ወሽመጥን ማቋረጣቸው ተገለጸ።ከመካከለኛው ምሥራቅ ወደ ቻይና እና ደቡብ ኮሪያ የሚጓጓዝ 6 ሚሊዮን በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ የጫኑ ናቸው የተባሉት እነዚህ መርከቦች ወደ እስያ ጉዞ መጀመራቸውን ኤልኤስኢጂ እና ኬፕለር የተባሉ የመርከብ እንቅስቃሴን የሚከታተሉ ተቋማት አስታውቀዋል።እነዚህ ግዙፍ ነዳጅ ጫኝ መርከቦች በዚህ ወር ኢራን እንዲያልፉ ከፈቀደችላቸው እና ባሕረ ሰላጤውን ለቅቀው ከወጡ በጣት የሚቆጠሩ መርከቦች መካከል መሆናቸው ተገልጿል።የካቲት 21 2018 ዓ.ም. እስራኤል እና አሜሪካ በቴህራን ላይ ጦርነት ከከፈቱ በኋላ የዓለም አንድ አምስተኛ ነዳጅ የሚተላለፍበት ሆርሙዝ በመዘጋቱ ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ተከስቷል።የደቡብ ኮሪያን ባንዲራ የሚያውለበልበው እና 2 ሚሊዮን በርሜል የኩዌት ድፍድፍ ነዳጅን የጫነው ግዙፍ መርከብ ሁለት የቻይና መርከቦችን ተከትሎ ወሽመጡን ረቡዕ ዕለት አቋርጧል።የኬፕለር መረጃ እንደሚያሳየው መርከቡ ጭነቱን ለማራገፍ የአገሪቱ የነዳጅ ማጣሪያ ወደሚገኝበት ኡስላን እያመራ ነው።የደቡብ ኮሪያ ኤነርጂ ኩባንያ ኤስኬ ኢነርጂ በጉዳዩ ላይ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል።ያጋሩ, 6 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ የጫኑ መርከቦች የሆርሙዝ ወሽመጥን አቋረጡ
  20. 20 ግንቦት 2026የዓለም ጤና ድርጅት በኢቦላ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከዚህ በላይ እንደሚጨምር አስታወቀየዲሞክራቲክ ኮንጎ ባለሥልጣናት 51 ሰዎች በኢቦላ መያዛቸው በምርመራ መረጋገጡን አስታውቀዋልየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የዲሞክራቲክ ኮንጎ ባለሥልጣናት 51 ሰዎች በኢቦላ መያዛቸው በምርመራ መረጋገጡን አስታውቀዋልየዓለም ጤና ድርጅት በኢቦላ መያዛቸው የተጠረጠረ ሰዎች 600 መድረሳቸውን እና በቫይረሱ ምክንያቱ እንደሞቱ የሚገመቱ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 139 መድረሱን አስታወቀ።ድርጅቱ አክሎም ቫይረሱን ለመመርመር ረዘም ያለ ጊዜ በመውሰዱ የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ተናግሯል።በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ብቻ 51 ሰዎች በኢቦላ መያዛቸው ሲረጋገጥ በጎረቤት ኡጋንዳ ደግሞ አንድ ግለሰብ በቫይረሱ መያዙ በምርመራ ተደርሶበታል ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ረቡዕ ዕለት ተናግረዋል።በጄኔቫ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ኃላፊው በአሁን ሰዓት የተከሰተው የኢቦላ ቫይረስ ቡንዲቡግዮ የተባለው ዝርያ ሲሆን “ከሁለት ወራት በፊት” መሰራጨት እንደጀመረ ይገመታል ብለዋል።እሁድ ዕለት የዓለም ጤና ድርጀት ባይረሱ ወረርሽኝ የሚባል ደረጃ ላይ አለመድረሱን በመግለጽ የዓለም አቀፍ ስጋት የሆነ የኅብረተሰብ ጤና አደጋ ነው ሲል አውጇል።ዶ/ር ቴድሮስ የድርጅቱ ጤና ባለሙያዎች ማክሰኞ ዕለት ተሰብስበው “የወረርሽኝ አደጋ” አለመሆኑ ላይ መስማማታቸውን ተናግረዋል።”ድርጅቱ የጤና ስጋቱን በብሔራዊ እና ቀጣናው ደረጃ ከፍተኛ መሆኑን በዓለም አቀፍ ደረጃ ግን አነስተኛ መሆኑን ገምግሟል” ብለዋል።በኢቦላ መያዛቸው በምርመራ የተረጋገጠው የዲሞክራቲክ ኮንጎ ዜጎች የሚኖሩት ቫይረሱ በጀመረበትት ኢቱሪ ነው። በኡጋንዳ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሁለት ሕሙማን ደግሞ ከኮንጎ መትተው ካምፓላ ያረፉ መሆናቸው ተገልጿል።የድርጅቱ ኃላፊ “በኮንጎ ያለው ስርጭት ሰፊ መሆኑን እናውቃለን” ሲሉ አክለዋል።በኮንጎ በቫይረሱ መያዝዋ የተረጋገጠው የመጀመርያዋ ሴት ነርስ ናት።ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከዚህ ቀደም 17 ጊዜ የኢቦላ ወረርሽኝ አጋጥሟት የሚያውቅ ቢሆንም ቡዲቡግዮ የተባለው ዝርያ ግን ላለፉት አስርት ዓመታት ተከስቶ አያውቅም።ያጋሩ, የዓለም ጤና ድርጅት በኢቦላ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከዚህ በላይ እንደሚጨምር አስታወቀ