በመጪው ሰኞ ሰባተኛውን አጠቃላይ ምርጫን የሚታዘቡ የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢዎች አዲስ አበባ መግባታቸውን ኅብረቱ አስታወቀ። በቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚመራው የኅብረቱ ታዛቢዎች ከ37 አገራት የተውጣጡ እና 73 አባላትን የያዘ መሆኑን በመግለጫው ላይ ተገልጿል።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 26 ደቂቃዎች በፊትኢራን እና አሜሪካ ልዩነቶቻቸውን ያጠብባሉ ብላ ተስፋ እንደምታደርግ ቻይና ገለጸችየቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪየፎቶው ባለመብት,Reutersየቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ የኢራን ጦርነት ተፋላሚ ወገኖች የተኩስ አቁሙን ለማስቀጠል ቁርጠኛ ሆነው እንደሚቀጥሉ እና ልዩነቶቻቸውን ያጠብባሉ ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ገለጹ።አሜሪካ በደቡብ ኢራን የመከላከል ያለችውን ጥቃት ከፈጸመች በኋላ ቴህራን ማክሰኞ ዕለት ዋሺንግተንን የተኩስ አቁሙን በመጣስ ከስሳለች።ማርኮ ሩቢዮ በበኩላቸው በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግጭት ለማስቆም የሚደረገው ድርድር “የተወሰነ ቀናት ሊወስድ ይችላል” ብለዋል።ዋንግ በኒውዮርክ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ በተገኙበት ወቅት “ሰላም በተቻለ ፍጥነት ወደ መካከለኛው ምሥራቅ እንዲመለስ ተፋላሚ አካላት የተኩስ አቁምን ለማስቀጠል በቁርጠኝነት እንደሚቆዩ እና ልዩነቶቻቸውን ለማጥበብ ግማሽ መንገድ እንደሚገናኙ ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል።ዋንግ አክለውም ሁሌም እንደምንለው ሰላም እና መፍትሄ ለማምጣት ጊዜ ይፈልጋል ያሉት ሚኒስትሩ “ለረዥም ጊዜ የቆዩ ችግሮች ቶሎ አይፈቱም” ብለዋል።“ይሁን እንጂ በድርድሩ የሚደረግ እያንዳንዱ እርምጃ የበለጠ ተስፋን ይሰጣል፤ እንዲሁም ግጭቱ ቶሎ በተቋጨ ጊዜ የሰላማዊ ዜጎችን ጉዳት መቀነስ ይቻላል” ብለዋል።ያጋሩ, ኢራን እና አሜሪካ ልዩነቶቻቸውን ያጠብባሉ ብላ ተስፋ እንደምታደርግ ቻይና ገለጸች
  2. ከ 2 ሰአት በፊትየዩኬ የደህንነት ተቋም ሩሲያ ወሳኝ የመሠረተ ልማቶችን እና ዲሞክራሲን “ያለመታከት ዒላማ እያደረገች” ነው ሲል ወነጀለየሩሲያ ባንዲራየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየዩናይትድ ኪንግደም የስለላ፣ ደህንነት እና ሳይበር ኤጀንሲ ሩሲያ ያለ መታከት ወሳኝ መሠረተ ልማቶችን እና አገልግሎቶችን ማጥቃት በመቀጠሏ አገሪቱ አሳሳቢ እና ወሳኝ ጊዜ ላይ እንደምትገኝ ገለጸ።የዩኬ የስለላ ተቋም ኃላፊ የሆኑት አኔ ኪአስት በትለር ረቡዕ ዕለት የሩሲያ እርምጃ ለዩናይትድ ኪንግደም የሚኖረውን ስጋት በሚመለከት እንዲሁም እንዴት መመከት እንዳለባት የሚገልጽ ንግግር ያደርጋሉ ተብሏል።ከኃላፊዋ ንግግር ተቀንጭቦ የተጋራው መልዕከት ላይ ሩሲያ “ወሳኝ የሆነ መሠረተ ልማቶችን፣ የዲሞክራሲ ሂደቶችን፣ የአቅርቦት ሰንሰለቶችን እና የሕዝብ እምነትን ዒላማ አድርጋለች” ብለዋል።ሩሲያ በብሪታኒያ ግዛት ውስጥ የአገር ክህደት ወንጀልን በማበረታታት የምትወቀስ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዩኬ እና የኔቶ አባል አገራት ላይ በይፋ ያልታወጀ ‘የተቀናጀ ጦርነት’ ከፍታለች በሚል ትከሰሳለች።ክሬምሊን ውንጀላውን ያስተባብላል።በትለር ተቋማቸው “ግድየለሽነት የተሞላበት” ያሉትን የሳይበር ጥቃቶች ለመመከት እንዲሁም “የግድያ ሙከራዎችን” ለመከላከል ያለ እረፍት እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።አክለውም “በእንዲህ ዓይነት ጠብ አጫሪት እና ግርግር ውስጥ ተቋማችን ያለመታከት ከደህንነት እና መከላከያ አጋሮቻችን ጋር በመሆን የሩሲያን ስጋት ለመቀነስ ይሰራል” ብለዋል።ክሬምሊን የኬጂቢ ባልደረባ የነበረውን አሌክሳንደር ሊትቪኔንኮን በለንደን ሆቴል ውስጥ ሳለ በጠጣው ሻይ ውስጥ መርዛማ ኬሚካል በመጨመር ለመግደል ሙከራ አድርጓል መባሉን አስተባብሏል።እአአ በ2018 የቀድሞው የሩሲያ ወታደራዊ ደህንነት ባልደረባ የነበረውን ሰርጌይ ስክሪፓልን ለመግድል ሙከራ በማድረግ ተከስሷል።ሩሲያ እአአ በ2022 ዩክሬንን መውረሯን ተከትሎ ዩናይትድ ኪንግደም ከኪየቭ ጎን በመቆሟ በምዕራባውያን አገራት ላይ “የተቀናጀ ጦርነት” በመክፈት ትወነጀላለች።ያጋሩ, የዩኬ የደህንነት ተቋም ሩሲያ ወሳኝ የመሠረተ ልማቶችን እና ዲሞክራሲን “ያለመታከት ዒላማ እያደረገች” ነው ሲል ወነጀለ
  3. ከ 3 ሰአት በፊትበቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚመራ የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን አዲስ አበባ ገባየቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታየምስሉ መግለጫ,የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታበመጪው ሰኞ ሰባተኛውን አጠቃላይ ምርጫን የሚታዘቡ የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢዎች አዲስ አበባ መግባታቸውን ኅብረቱ አስታወቀ።በቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚመራው የኅብረቱ ታዛቢዎች ከ37 አገራት የተውጣጡ እና 73 አባላትን የያዘ መሆኑን በመግለጫው ላይ ተገልጿል።ይህ አምባሳደሮችን፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ተወካዮች፣ የምርጫ ባለሙያዎች፣ የሰብኣዊ መብት፣ የሥርኣተ ፆታ፣ የወጣቶች እና የመገናኛ ብዙኃን ተወካዮችን ያከላተተ መሆኑ ተገልጿል።የአፍሪካ ኅብረት ማክሰኞ ግንቦት 18/2018 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ የምርጫ ታዛቢዎች በምርጫው ዕለት የድምጽ አሰጣጥ ሂደትን እና ቆጠራን ለመታዘብ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚሰማሩ መሆኑ አስታውቋል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመላ አገሪቱ ሰኞ ግንቦት 24 የሚደረገው ሰባተኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ለመታዘብ ከአፍሪካ ኅብረት ታዛቢዎች በተጨማሪ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) ታዛቢዎች እንደሚገኙ አስታውቋል።የአፍሪካ ብረት እና የኢጋድ የምርጫ ታዛቢዎች ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በኢትዮጵያ መንግሥት ግብዣ መሠረት መሆኑን የምርጫ ቦርድ እና ኅብረቱ አስታውቀዋል።የምርጫ ታዛቢ ቡድኑ ግምገማውን በኢትዮጵያ የምርጫ ሕግ፣ በአፍሪካ ኅብረት እንዲሁም አስፈላጊ በሆኑ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ለማድረግ በተቀመጡ መስፈተርቶች ላይ በመመሥረት ግምገማውን እንደሚያደርግ ተገልጿል።ታዛቢዎቹ ከምርጫ ቦርድ፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከዕጩዎች፣ ከመገናኛ ብዙኃን እንዲሁም ከሌሎች የምርጫ ታዛቢዎች ጋር በትብብር እንደሚሠሩ ተጠቅሷል።ታዛቢ ቡድኑ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱን ግንቦት 26/2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ይፋ የሚያደርግ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ የመጨረሻ ሪፖርቱን ደግሞ ከምረጫው በኋላ በሁለት ወር ውስጥ ያቀርባል ተብሏል።የኢትዮጵያ ሲቪክ ማኅበራት ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለመታዘብ ከ500 በላይ የሚሆኑ የረጅም ጊዜ ታዛቢዎችን ማሰማራታቸውን አስታውቀዋል።ያጋሩ, በቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚመራ የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን አዲስ አበባ ገባ
  4. ከ 5 ሰአት በፊትእስራኤል በጋዛ ከተማ በፈጸመችው ጥቃት አዲሱን የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ አዛዥ መግደሏን አስታወቀችጥቃቱ በተፈጸመበት አካባቢ በርካታ ሰዎች ተሰብሰብው ታይተዋልየፎቶው ባለመብት,Reutersእስራኤል ማክሰኞ ዕለት በጋዛ ከተማ በፈጸመችው ጥቃት በዲሱን የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ አዛዥ መግደሏን አስታወቀች።የእስራኤል ጦር በጋዛ ከተማ በተጨናነቀ የገበያ ስፍራ በሚገኝ የመኖሪያ ሕንጻ ላይ በፈጸመው ከፍተኛ የአየር ድብደባ ቢያንስ ሦስት ፍልስጤማውያን መሞታቸውን የሕክምና ባለሙያዎችና የዓይን እማኞች ተናግረዋል።ጥቃቱ የኢድ አል-አድሃ በዓል ከመከበሩ በፊት ጎዳናዎች በገበያተኞች ተጨናንቀው ባለበት ወቅት በጋዛ ከተማ መሃል በሚገኘው የአል-ካያሊ ሕንፃ የላይኛውን ሦስት ፎቅ ዒላማ ማድረጉ ተገልጿል።የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ቢሮ ቀደም ሲል የእስራኤል ጦር የሐማስን የጦር ክንፍ አዛዥ መሐመድ ኦዴህን ዒላማ እንዳደረገ አስታውቋል። ይህም የቀድሞው የጦር አዛዥ በተመሳሳይ ጥቃት ከተገደለ ከጥቂት ቀናት በኋላ የተፈጸመ ነው።ይህ እስራኤል ከሐማስ ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ካደረገች በኋላ በጋዛ የተፈጸመ የቅርብ ጊዜ ከባድ ጥቃት ነው።ኦዴህ በጥቃቱ መገደሉን በተመለከተ የእስራኤል መንግሥት ሲያስታውቅ ሐማስ ግን ምንም አስተያየት አልሰጠም።የነፍስ አድን ሠራተኞች በስፍራው ሲደርሱ በአካባቢው በደረሰው ከባድ ጉዳት እና በነበረው መጨናነቅ ምክንያት ወደ ላይኛው ፎቅ ለመውጣት ተቸግረዋል።የዓይን እማኞች ቢያንስ አምስት ሚሳኤሎች ሕንፃውን ከተለያየ አቅጣጫ በተመሳሳይ ጊዜ መምታታቸውን ተናግረዋል።አንድ ነዋሪ ጥቃቱ ከመፈጸሙ በፊት የሄሊኮፕተር ድምፅ መስማቱን ተናግሯል።ከቦታው የተገኘ ተንቀሳቃሽ ምስል እንደሚያሳየው አምቡላንሶች እና የሲቪል መከላከያ ሠራተኞች በተመታው ሕንፃ ውስጥ የተረፉ ሰዎች ካሉ ሲፈልጉ የሚያሳይ ሲሆን በአቅራቢያው በርካታ ሰዎች ተሰብስበው ነበር።የኔታንያሁቢሮ የእስራኤል የመከላከያ ሠራዊት መስከረም 26 2016 ዓ.ም. ሐማስ የፈጸመውን ጥቃት “ካቀነባበሩ ሰዎች መካከል አንዱን” መሐመድ ኦዴህን ዒላማ እንዳደረገውአስታውቋል።“ኦዴህ በበርካታ የእስራኤልዜጎችን እና የመከላከያ ሠራዊት አባላት ግድያ፣ ጠለፋ እና መቁሰል ተጠያቂ ነው” ሲል መግለጫውአክሏል።የቡድኑ ታጣቂ ክንፍ አዛዥ የነበሩት ኢዝ አድ-ዲን አል-ሃዳድ በግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ በእስራኤል የአየር ጥቃት ተገድለዋል።ይህ ጥቃት በአንድ የመኖሪያ ሕንፃ ላይ ያነጣጠረ ሲሆን ቢያንስ ሦስት ሰዎችን ገድሏል ሲሉ የዓይን እማኞች እና የአካባቢው ምንጭ ተናግረዋል።እስራኤል የተኩስ አቁም ከተደረሰበት እአአ ከጥቅምት 10 ጀምሮ በጋዛ ዙሪያ ጥቃቶችን ስትፈጽም ቆይታለች።ሐማስ እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነቱን በመጣስ እና ሲቪሎችን በማጥቃት በተደጋጋሚ ሲከስ ቆይቷል።የጋዛ የጤና ሚኒስቴር በተኩስ አቁም ስምምነቱ ወቅት በእስራኤል በተሰነዘረው ጥቃት ከ800 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ይፋ አድርጓል።ያጋሩ, እስራኤል በጋዛ ከተማ በፈጸመችው ጥቃት አዲሱን የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ አዛዥ መግደሏን አስታወቀች
  5. ከ 5 ሰአት በፊትእስራኤል በሊባኖስ በተከታታይ በፈጸመቻቸው ጥቃቶች ቢያንስ 31 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸየእስራኤል መከላከያ ሠራዊት በምሥራቅ ሊባኖስ በሚገኘው ቤካ ሸለቆ እና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ላይ ጥቃት በመክፈት ሄዝቦላህን እየመታ መሆኑን ይናገራል።እስራኤል በተከታታታይ በምሥራቃዊ እና ደቡባዊ ሊባኖስ በፈጸመችው ጥቃት በርካታ ሕጻናትን ጨምሮ ቢያንስ 31 ሰዎች መገደላቸውን የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።የእስራኤል ጦር በሊባኖስ የሚፈጽመውን ከባድ ጥቃት የቀጠለው ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በሄዝቦላህ ላይ የሚወሰደው ወታደራዊ እርምጃ እንዲጠናከር ትዕዛዝ ከሰጡ በኋላ ነው።የእስራኤል መከላከያ ከ100 በላይ የሄዝቦላህ መሠረተ ልማቶችን እና ተዋጊዎችን ዒላማ አደርጎ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል።ኔታንያሁ ሰኞ ምሽት በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት፤ እስራኤል “ከሄዝቦላህ ጋር ጦርነት ላይ” እንደሆነች ተናግረው ሠራዊቱ “አድቃቂ ምት” እንዲፈጽም ማዘዛቸውንም ገልጸዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እስራኤል በከፈተችው ወታደራዊ ዘመቻ “ከ600 በላይ አሸባሪዎች” መገደላቸውንም ተናግረዋል። “አሁን ከእኛ የሚጠበቀው ጥቃቱን ማጠናከር እና ጥንካሬውን ይበልጥ መጨመር ነው” ሲሉም ተደምጠዋል።ኔታንያሁ ማክሰኞ ዕለት በደህንነት ካቤኔ ስብሰባቸው ላይ “በሊባኖስ የምናካሄደውን ዘመቻ እያሰፋ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።“የእስራኤል ጦር በምድር ከፍተኛ ኃይል አሰማርቶ ዘመቻ እያካሄደ እና ገዢ መሬቶችን እየተቆጣጠረ ነው” ብለዋል።አክለውም በሰሜን እስራኤል የሚገኙ እስራኤላውያንን ከሄዝቦላህ ጥቃት ለመከላከል “የደህንነት ቀጣናዎች እየመሰረተ ነው” ብለዋል።በእስራኤል እና ሊባኖስ መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በተደጋጋሚ ተጥሷል።እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ በየዕለቱ የአየር ድብደባ የምትፈጽም ሲሆን ሄዝቦላህም ሮኬቶችን እና ድሮኖችን ይተኩሳል።የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት በምሥራቅ ሊባኖስ በሚገኘው ቤካ ሸለቆ እና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ላይ ጥቃት በመክፈት ሄዝቦላህን እየመታ መሆኑን ይናገራል።የተወሰኑ ጥቃቶች በተባበሩት መንግሥታት በቅርስነት የተመዘገበ እና የ900 ዓመት እድሜ እንዳለው የሚገመት ቤተ መንግሥት ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።ያጋሩ, እስራኤል በሊባኖስ በተከታታይ በፈጸመቻቸው ጥቃቶች ቢያንስ 31 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ
  6. 26 ግንቦት 2026በኢራን ለሦስት ወራት ተቋርጦ የነበረው የኢንተርኔት አገልግሎት ተጀመረበኢራን ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧልየፎቶው ባለመብት,Anadolu via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,በኢራን ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧልበኢራን ለሦስት ወራት ያህል ተቋርጦ የቆየው የኢንተርኔት አገልግሎት ዳግም መጀመሩን የአገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት አስታወቁ።ሞሃማድ ሬዛ አረፍ ማክሰኞ ዕለት በኤክስ ገጻቸው ላይ “ነጻ እና ቁጥጥር የሚደረግበት የኢንተርኔት አገልገሎት ለመስጠት የመጀመርያ እርምጃ ወስደናል” ብለዋል።ኔትብሎክስ እና ኬንቲክ የተባሉ የዓለም አቀፍ የኢንተርኔት ግንኙነትን የሚከታተሉ ተቋማት በኢራን ዛሬ ከምሳ ሰዓት ጀምሮ “በከፊል” የኢንተርኔት አገልግሎት መጀመሩን ተናግረዋል።በኢራን የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠው አሜሪካ እና እስራኤል የካቲት 21 2018 ዓ.ም. በአገሪቱ ላይ ጦርነት መክፈታቸውን ተከትሎ ነበር።የኢራን ባለሥልጣናት በጦርነቱ ወቅት ኢንተርኔት የተዘጋው ከደኅንነት ጋር በተያያዙ ምክንያት እንደሆነ ይናገራሉ። ይህንን በማድረግ ክትትል፣ ስለላ እና የሳይበር ጥቃቶችን ለመከላከል እንዳሰቡ ጠቁመዋል።በቴህራን የሚገኝ አንድ ግለሰብ ዛሬ የዋይፋይ አገልግሎት መጀመሩን ለቢቢሲ ተናግሯል።ኔትብሎክስ የኢንተርኔት አገልግሎት “የሚቀጥል” ስለመሆኑ “ግልጽ አይደለም” ብሏል።ያጋሩ, በኢራን ለሦስት ወራት ተቋርጦ የነበረው የኢንተርኔት አገልግሎት ተጀመረ
  7. 26 ግንቦት 2026እስራኤል በሊባኖስ መንደሮች ላይ በፈጸመችው ጥቃት አስራ አንድ ሰዎች መገደላቸው ተገለጸእስራኤል ሰኞ ዕለት በደቡባዊ ሊባኖስ ናቤታህ መንደር የፈጸመችው ጥቃትየፎቶው ባለመብት,Reutersእስራኤል በሄዝቦላህ ላይ የምትወስደውን ወታደራዊ እርምጃ እንደምታጠናክር ከገለጸች በኋላ በደቡብ እና ምሥራቃዊ ሊባኖስ በርካታ ድብደባዎችን መፈጸሟ ተገለጸ።የእስራኤል ጦር ከ100 በላይ የሄዝቦላህ መሠረተ ልማቶችን እና ተዋጊዎች ላይ የአየር ድብደባ መፈጸሙን ተናግሯል።በሚያዚያ ወር አጋማሽ ላይ በእስራኤል እና ሊባኖስ መካከል በአሜሪካ አደራዳሪነት የተኩስ አቁም ተደርሷል።የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር በቤካ ቫሊ በሚገኝ ማሽጋሃራ በተሰኘ መንደር በተፈጸመ ጥቃት ሁለት ሕጻናትን ጨምሮ 11 ሰዎች መገደላቸውን አስታውቋል።የእስራኤል ጦር ግን “የአሸባሪዎች እንቅስቃሴ” በታየበት አካባቢ ጥቃት መፈጸሙን ተናግሯል።የእስራኤል ጦር ጥቃቱን አጠናክሮ የቀጠለው ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በሄዝቦላህ ዒላማዎች ላይ “ጠንከር ያለ ጥቃት” እንዲፈጸም ትዕዛዝ ከሰጡ በኋላ ነው።በሁለቱ አገራት መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በተደጋጋሚ ተጥሷል።እስራኤል በተለይ በደቡባዊ ሊባኖስ በተደጋጋሚ የአየር ድብደባ የምትፈጽም ሲሆን ሄዝቦላህም ሮኬቶችን እና ድሮኖችን በሰሜን እስራኤል ወደሚገኙ አካባቢዎች ይተኩሳል።ያጋሩ, እስራኤል በሊባኖስ መንደሮች ላይ በፈጸመችው ጥቃት አስራ አንድ ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ
  8. 26 ግንቦት 2026ኢራን፣ አሜሪካ የፈጸመችው አዲስ ጥቃት የተኩስ አቁሙን የጣሰ ነው አለችኢራንየፎቶው ባለመብት,REUTERSአሜሪካ ራስን መከላከል በሚል አዲስ ጥቃት በደቡባዊ ኢራን ከፈጸመች በኋላ ቴህራን ዋሺንግተን የተኩስ አቁሙን ጥሳለች ስትል ከሰሰች።የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በበኩላቸው በሁለቱ አገራት መካከል የሚደረገውን ጦርነት ለማስቆም የሚደረገው ድርድር “ጥቂት ቀናት ሊወስድ ይችላል” ብለዋል።የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሜሪካ በደቡባዊ ኢራን ሆርሞዝጋን አውራጃ ጥቃት መፈጸሟን አስታውቆ የተኩስ አቁሙ “ግልጽ ጥሰት ነው” ሲል ተናግሯል።የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው አሜሪካ “ጠብ አጫሪ እና ተቀባይነት ለሌለው ድርጊቷ” ተጠያቂ ትሆናለች ብሏል።አሜሪካ ጥቃት የፈጸመችበት ሆርሞዝጋን ክልል ከሆርሙዝ ወሽመጥ ጋር የሚዋሰን ነው።ኢራን በመግለጫው “ያለምንም ጥርጥር የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ምላሽ ሳይሰጥ የሚተወው ምንም ክፋት የለም እንዲሁም የኢራን ዜጎችን ከመከላከልም ወደ ኋላ አይልም” ብላለች።ሁለቱ አገራት እስከ ትናንት ሰኞ ድረስ በመግባቢያ ሰነዱ ዙሪያ የሚደረገው ንግግር ለውጥ ማሳየቱን ሲናገሩ ነበር።አሜሪካ እና ኢራን የሚያደርጉት ንግግር በስምምነት ከተቋጨ ለሦስት ወር የዘለቀውን ጦርነቱን ያስቆማል፣ የሆርሙዝ ወሽመጥን ያስከፍታል እንዲሁም የተኩስ አቁሙን በ60 ቀናት ይራዘማል ተብሎ ነበር።የአሜሪካ ጦር በደቡብ ኢራን የሚገኙ የሚሳዔል ማከማቻዎች እና ፈንጂ የሚጥሉ ጀልባዎችን ዒላማ በማድረግ አዲስ ዙር ጥቃት መክፈቱን አስታወቋል።የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ ባወጣው መግለጫ ጥቃቱ “ራስን መከላከል” እንደሆነ አስታውቋል። ዓላማውም “በኢራን ኃይሎች ስጋት የተጋረጠባቸው ወታደሮቻችንን መከላከል ነው” ብሏል።ያጋሩ, ኢራን፣ አሜሪካ የፈጸመችው አዲስ ጥቃት የተኩስ አቁሙን የጣሰ ነው አለች
  9. 26 ግንቦት 2026የኢራኑ ጠቅላይ መሪ “ባሕረ ሰላጤው ከዚህ በኋላ የአሜሪካ ጦር ሰፈር መጠለያ አይሆንም” አሉየኢራኑ ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የኢራኑ ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒየኢራኑ ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ ለኢድ አል አድሃ በዓል ባስተላለፉት መልዕክት እስራኤልን “አደገኛ” በማለት ከዚህ በኋላ የፋርስ ባሕረ ሰላጤ አካባቢ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች መቀመጫ አይሆንም ሲሉ ገለጹ።ጠቅላይ መሪው በጽሁፍ ባስተላለፉት እና በመንግሥት ቴሌቪዥን በተነበበው መልዕክታቸው ላይ እስራኤልን “በቀጣናው አደገኛ እና ገዳይ ህመም” በማለት “መወገድ ይገባታል” ማላታቸውን ኢራኑ ዜና ወኪል ታስኒም ዘግቧል።ሞጅታባ የአባታቸው መገደል ተከትሎ የጠቅላይ መሪነቱን ሥልጣን ከተረከቡ በኋላ እስካሁን ድረስ ለሕዝብ በይፋ ያልታዩ ሲሆን፣ መልዕክታቸውን በጽሁፍ ሲያስተላልፉ ቆይተዋል።በአሁኑ መልዕክታቸው በኢራን ላይ ጦርነት ከተከፈተ በኋላ ነገሮች እየተቀያየሩ መሆናቸውን በማንሳት የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች በባሕረ ሰላጤው አገራት ውስጥ ቦታ እንደማይኖራቸውን ገልጸዋል።ጠቅላይ መሪው “ጊዜን ወደ ኋላ መመለስ እንደማይቻል እርግጥ እንደሆነው ሁሉ፤ በቀጣናው ያሉ አገራት እና መሬት ከዚህ በኋላ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች መጠለያ አይሆኑም” ሲሉ የአሜሪካ ሚና በአካባቢው እንደማይኖር አመለክተዋል።ጨምረውም “በቀጣናው ለክፉ ተግባር መጠለያ የሆኑት ጦር ሰፈሮች አይኖሩም እንዲሁም ተጨማሪ ወታደራዊ ሰፈሮች አይመሠረቱም” በማለት “አሜሪካ ከቀን ወደ ቀን ከዚህ በፊት ከነበረችበት ደረጃ እየወረደች ነው” ብለዋል።ጠቅላይ መሪው ባለፉት ወራት በተካሄደው ጦርነት አሜሪካ እና እስራኤል ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው በመጥቀስ “በኢራን ከባድ ምት እስራኤል አቅመ ቢስ” እንደሆነች እና አሜሪካም “ከባድ ጥፊ እንደቀመሰች” ገልጸዋል።ያጋሩ, የኢራኑ ጠቅላይ መሪ “ባሕረ ሰላጤው ከዚህ በኋላ የአሜሪካ ጦር ሰፈር መጠለያ አይሆንም” አሉ
  10. 26 ግንቦት 2026ኢራን “የአጸፋ እርምጃ መውሰድ ተገቢ እና የማይቀር” መሆኑን ገለጸችየኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብየፎቶው ባለመብት,EPAየኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ፤ በአሜሪካ ጦር ለሚፈጸም ማንኛውም የተኩስ አቁም ጥሰት “የአጸፋ እርምጃ መውሰድ ተገቢ እና የማይቀር” እንደሆነ አስታወቀ።እስላማዊ አብዮታዊ ዘቡ አሜሪካ በደቡብ ኢራን የከፈተችውን ጥቃት ሳይጠቅስ በሕዝብ ግንኙነቱ በኩል ባወጣው መግለጫ “የአሜሪካ ጦር በቀጣናው ጣልቃ ገብነቱን እና ጠብ ጫሪነቱን ቀጥሎ በፐርዥያ ባሕረ ሰላጤ ወደ ኢራን የአየር ክልል እና ወደ እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ መከላከያ ሰፈር ገብቷል” ብሏል።“በጥንቃቄ የደኅንነት ቅኝት ካደረግን በኋላ የግዛት ሉዓላዊነታችንን ለመከላከል ኤምኪው-9 ድሮን መትተን ጥለናል” ሲልም አክሏል።አርኪው-4 ድሮን እና ኤፍ-35 ተዋጊ ጄት እንደመታ እና እርምጃው “በውሃ የተሸፈነውን አካባቢ ጥለው እንዲሸሹ እንዳስገደዳቸው” አስታውቋል።እነዚህ ጥቃቶች መቼ እና የት እንደተፈጸሙ በግልጽ አላስቀመጠም።የአሜሪካ ጦር ባወጣው መግለጫ በደቡብ ኢራን የሚገኙ የሚሳዔል ማከማቻዎች እና ፈንጂ የሚጥሉ ጀልባዎችን ዒላማ በማድረግ አዲስ ዙር ጥቃት መክፈቱን ይፋ አድርጓል።የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ ጥቃቱ “ራስን መከላከል” እንደሆነ ገልጾ፤ ዓላማውም “በኢራን ኃይሎች ስጋት የተጋረጠባቸው ወታደሮቻችንን መከላከል ነው” ብሏል።የኢራን መገናኛ ብዙኃን ትናንት ምሽት በባንደር አባስ የወደብ ከተማ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ ፍንዳታ መሰማቱን ዘግበዋል።ያጋሩ, ኢራን “የአጸፋ እርምጃ መውሰድ ተገቢ እና የማይቀር” መሆኑን ገለጸች
  11. 26 ግንቦት 2026ኳታር ለኢራን 12 ቢሊየን ዶላር ልትሰጥ ነው መባሉን አስተባበለችየኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርኢራን ከአሜሪካ ጋር በሚደረገው ድርድር ከስምምነት እንድትደርስ ለማድረግ 12 ቢሊዮን ዶላር ለመስጠት ሃሳብ አቅርባለች መባሉን መሠረተ ቢስ በማለት ኳታር አስተባበለች።የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማጂድ አል እንሳሪ በኤክስ የሶሻል ሚዲያ መድረክ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ የአገራቸው ዲፕሎማሲያዊ ሚና በግልጽ የሚታወቅ መሆኑን በመጥቀስ የወጡ ዘገባዎች ያላትን “ታማኝ ዓለም አቀፍ የሰላም ጥረቶች አመቻችንት የሚያጠለሽ ነው” ብለዋል።ይህ የሚኒስትሩ አስተያየት የተሰማው በርካታ ከፍተኛ የኢራን ባለሥልጣናት ከአሜሪካ ጋር የሚደረገውን ድርድር ለመቋጨት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ኳታርን እየጎበኙ ባለበት ጊዜ ነው።ኢራን ከአሜሪካ ጋር በሚደረገው ድርድር በኳታር ያለውን ጨምሮ በውጭ አገራት እንዳይንቀሳቀስ የታገደባት ሃብቷ እንዲለቀቅ እየጠየቀች ነው። ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት አገሪቱ በኳታር ውስጥ 12 ቢሊዮን ዶላር የሚሆን ገንዘብ ታግዶባታል።በኒውክሌር መረሃ ግብሯ ምክንያት ከምዕራበባውያን በተለይም ከአሜሪካ ጋር በገባችው እሰጣ ገባ ተደራራቢ ዕቀባ የተጣለባት ኢራን ባለፈው የካቲት ወር በአሜሪካ እና በእስራኤል በተከፈተባት ጥቃት ጦርነት ውስጥ ገብታለች።ለጥቂት ወራት የዘለቀው ጦርነት በተኩስ አቁም ጋብ ብሎ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ድርድር እየተደረገ የሚገኝ ሲሆን፣ ኢራን ከስምምነት ለመድረስ በቅድመ ሁኔታ ካቀረበቻቸው ነጥቦች መካከል በውጭ ያለው ሃብቷ እንዲለቀቅላት የሚጠይቀው ይገኝበታል።ያጋሩ, ኳታር ለኢራን 12 ቢሊየን ዶላር ልትሰጥ ነው መባሉን አስተባበለች
  12. 26 ግንቦት 2026በኢራን ጦርነት ምክንያት በመላው ዓለም የሚሳዔል መከላከያ ሥርዓት መዳከሙን ዘለንስኪ ተናገሩዘለንስኪየዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ “በኢራን ጦርነት ምክንያት በመላው ዓለም የባለስቲክ ሚሳዔል መቃወሚያ ሥርዓት እጥረት ተፈጥሯል” አሉ።ለተፈጠረው እጥረት “መፍትሔ መገኘት አለበት” ሲሉም ፕሬዝዳንቱ አሳስበዋል።ዘለንስኪ አክለውም “የዩክሬንን የአየር መከላከያ ለማጠናከር ከሁሉም አካላት ጋር እየሠራን እንገኛለን። ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው” ብለዋል።በዩክሬን መዲና ኪቭ “ስልታዊ ጥቃቶች” እንደምትሰነዝር ያስታወቀችው ሩሲያ በበኩሏ የውጭ አገራት ዜጎች ከተማዋን ለቅቀው እንዲወጡ ማሳሰቢያ ሰጥታለች።የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ፤ አሜሪካ ለአገራቸው ተጨማሪ ድጋፍ የምታደርግበትን መንገድ በተመለከተ ውይይቶች ይቀጥላሉ ብለዋል።አውሮፓ በቂ የሚሳዔል መቃወሚያ ሥርዓት እንዲኖራት በሚል ዩክሬን መሣሪያውን የምታመርትበትን ፍጥነት መጨመሯንም ገልጸዋል።ያጋሩ, በኢራን ጦርነት ምክንያት በመላው ዓለም የሚሳዔል መከላከያ ሥርዓት መዳከሙን ዘለንስኪ ተናገሩ
  13. 26 ግንቦት 2026ማርኮ ሩቢዮ ከኢራን ጋር ስምምነት ላይ የመድረስ ዕድል መኖሩን በድጋሚ ገለጹማርኮ ሩቢዮየፎቶው ባለመብት,ulia Demaree Nikhinson / POOL / AFP via Getty Imagesዋሽንግተን ቴህራን ላይ አዲስ ጥቃት ብትከፍትም ስምምነት ላይ መድረስ የሚቻልበት ዕድል “አሁንም እንዳለ” የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስር ማርኮ ሩቢዮ ተናገሩ።አሜሪካ ያደረሰችው ጥቃት የኢራን የሚሳዔል ሥርዓት እና ጀልባዎች ላይ ጉዳት ቢያደርስም ሩቢዮ ዛሬ ባደረጉት ንግግር የስምምነት ላይ መድረስ ይቻላል ብለዋል።“በኳታር በሚደረገው ውይይት ለውጥ የሚመጣ ከሆነ እናያለን” ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ “ፕሬዝዳንቱ ግሩም ስምምነት ላይ ይደርሳሉ፤ አልያም ስምምነት አይኖርም” ሲሉ ገልጸዋል።በኳታር በሚደረገው ውይይት ላይ የቀረበው የሰላም ዕቅድ ውስጥ ያለው “የቃላት አጠቃቀም እና ምርጫ መታየት ስላለት” ንግግሩ ቀናት ሊወስድ እንደሚችል ጠቁመዋል።የሆርሙዝ ወሽመጥ መከፈት እንዳለበት አስረግጠው የተናገሩት ማርኮ ሩቢዮ “እየሆነ ያለው ነገር ሕገ ወጥ ነው። ዓለም ላይ አለመረጋጋት ፈጥሯል፤ ተቀባይነትም የለውም” ሲሉ አክለዋል።ያጋሩ, ማርኮ ሩቢዮ ከኢራን ጋር ስምምነት ላይ የመድረስ ዕድል መኖሩን በድጋሚ ገለጹ
  14. 26 ግንቦት 2026በኪቭ “ስልታዊ ጥቃት” ለመሰንዘር የዛተችው ሩሲያ የውጭ ዜጎች ከከተማዋ እንዲወጡ አሳሰበችኪቭየፎቶው ባለመብት,Reutersበዩክሬን መዲና ኪቭ አዲስ “ስልታዊ ጥቃቶች” እንደምትሰነዝር ያስታወቀችው ሩሲያ፤ የውጭ አገራት ዜጎች ከተማዋን ለቅቀው እንዲወጡ ማሳሰቢያ ሰጠች።ሩሲያ ከቀናት በፊት በዩክሬን መዲና ከፍተኛ ጥቃት ያደረሰች ሲሆን፤ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ የከፋው ነው ተብሏል።ሩሲያ በቀጣይ የምትፈጽመው ጥቃት “ውሳኔ የሚሰጥባቸው ማዕከላት ላይ ያነጣጠረ” መሆኑን አስታውቃለች።የሰው አልባ አውሮፕላን ማምረቻ ፋብሪካዎችን ጨምሮ ሌሎችም ተቋማት ዒላማ እንደሚደረጉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።የውጭ አገራት ዜጎች እና ዲፕሎማቶች ኪቭን “በተቻለው ፍጥነት” ለቅቀው እንዲወጡም መሥሪያ ቤቱ አሳስቧል።ዩክሬናውያን ከአስተዳደራዊ እና ወታደራዊ ተቋማት ሕንጻዎች እንዲርቁም አስጠንቅቋል።ዩክሬን በበኩሏ የሩሲያ ዛቻ “ሃፍረተ ቢስ የሆነ ጫና ማሳደሪያ መንገዷ ነው” ስትል አጣጥላለች።የዩክሬን አጋር አገራት ሞስኮ ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ እንዲጨምሩም ጠይቃለች።ሩሲያ ለውጭ አገራት ዜጎች ማስጠንቀቂያ መስጠቷ “የውጭ ዲፕሎማቶች መቀመጫዎች ከዒላማዎቿ መካከል እንደሚገኙበት ያሳያል” ስትልም ዩክሬን ስጋቷን ገልጻለች።ያጋሩ, በኪቭ “ስልታዊ ጥቃት” ለመሰንዘር የዛተችው ሩሲያ የውጭ ዜጎች ከከተማዋ እንዲወጡ አሳሰበች
  15. 26 ግንቦት 2026እስራኤል ሄዝቦላህ ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት እንደምታጠናክር ኔታንያሁ ተናገሩደቡባዊ ሊባኖስ ውስጥ እስራኤል የፈጸመችው ጥቃትየፎቶው ባለመብት,Reutersየእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ሄዝቦላህ ላይ የሚፈጸመው ጥቃት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን ተከትሎ የአገሪቱ ጦር በመላው ሊባኖስ አዲስ ዙር ጥቃት ማድረስ መጀመሩን አስታወቀ።የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት በምስራቅ ሊባኖስ በሚገኘው ቤካ ሸለቆ እና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ላይ ጥቃት በመክፈት ሄዝቦላህን እየመታ መሆኑን ገልጿል።ሄዝቦላህ በበኩሉ የእስራኤል ወታደሮች፣ ታንኮች፣ የጦር ሰፈሮች፣ ሕንፃዎች እና ሌሎች ስፍራዎችን ዒላማ ያደረጉ 22 የድሮን እና የሮኬት ጥቃቶችን በመፈጸም አጸፋውን መመለሱን አስታውቋል።ሊባኖስ እና እስራኤል በዚህ ወር መጀመሪያ የደረሱበትን ተኩስ አቁም በ45 ቀናት ለማራዘም ስምምነት ቢፈጽሙም ውጊያው ቀጥሏል።ኔታንያሁ ሰኞ ምሽት በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት፤ እስራኤል “ከሄዝቦላህ ጋር ጦርነት ላይ” እንደሆነች ተናግረዋል። ሠራዊቱ “አድቃቂ ምት” እንዲፈጽም ማዘዛቸውንም ገልጸዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እስራኤል በከፈተችው ወታደራዊ ዘመቻ “ከ600 በላይ አሸባሪዎች” መገደላቸውንም ተናግረዋል። “አሁን ከእኛ የሚጠበቀው ጥቃቱን ማጠናከር እና ጥንካሬውን ይበልጥ መጨመር ነው” ሲሉም ተደምጠዋል።ቤዛልል ስሞትሪች እና ኢታማር ቤን ግቪር የተባሉት ሁለት ቀኝ አክራሪ የእስራኤል ሚኒስትሮች ሊባኖስ ውስጥ የሚካሄደውን ጨምሮ የጦሩ ወታደራዊ ዘመቻ እንዲስፋፋ ጠይቀዋል።ሰኞ ዕለት ድሮኖች እና ሮኬቶችን በመጠቀም በደቡብ ሊባኖስ እንዲሁም በሰሜን እስራኤል የሚገኙ ስፍራዎችን ማጥቃቱን የገለጸው ሄዝቦላህ፤ እርምጃውን የወሰደው በእስራኤል “የተኩስ አቁም ጥሰት” ምክንያት እንደሆነ ተናግሯል።ይፋዊ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሌላቸው ሊባኖስ እና እስራኤል በሚቀጥለው ሳምንት ዋሽንግተን ውስጥ ተጨማሪ ድርድር ለማድረግ ቀጠሮ ይዘዋል። የሊባኖስ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አውን፤ የእስራኤል ጦር ከደቡብ ሊባኖስ ሙሉ በሙሉ እንዲወጣ ጠይቀዋል።ያጋሩ, እስራኤል ሄዝቦላህ ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት እንደምታጠናክር ኔታንያሁ ተናገሩ
  16. 26 ግንቦት 2026የአሜሪካ ጦር በደቡብ ኢራን አዲስ ጥቃት መክፈቱን አስታወቀየጦር አውሮፕላንየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካ ጦር በደቡብ ኢራን የሚገኙ የሚሳዔል ማከማቻዎች እና ፈንጂ የሚጥሉ ጀልባዎችን ዒላማ በማድረግ አዲስ ዙር ጥቃት መክፈቱን አስታወቀ።የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ ባወጣው መግለጫ ጥቃቱ “ራስን መከላከል” እንደሆነ አስታውቋል። ዓላማውም “በኢራን ኃይሎች ስጋት የተጋረጠባቸው ወታደሮቻችንን መከላከል ነው” ብሏል።የማዕከላዊ ዕዙ ቃል አቀባይ ካፕቴን ቲም ሀውኪንስ “የአሜሪካ ጦር በተኩስ አቁሙ መሠረት ቢታቀብም ወታደሮችን ይከላከላል” ብለዋል።የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ኢስማኤል ባጊ ከአሜሪካ ጋር የሚደረገው ድርድር መሻሻል ቢያሳይም ግጭቱን የሚያስቆም ስምምነት ላይ “በቅርብ ጊዜ እንደማይደረስ” መግለጻቸው ይታወሳል።የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ ቃል አቀባይ እንደተናገሩት እንደ አዲስ የተከፈተው ጥቃት የተፈጸመው በደቡባዊ የኢራን ግዛት የምትገኘው ባንዳር አባስ የወደብ ከተማ ላይ ነው።የወደብ ከተማዋ በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚገኘው የኢራን ባሕር ኃይል መቀመጫ መሆኗን የኒው ዮርክ ታይምስ ዘገባ ይጠቁማል።የኢራን ብሔራዊ ጣቢያ እንደዘገበው የከተማዋ ባለሥልጣናት ፍንዳታ መስማታቸውን ተከትሎ ምርመራ ማካሄድ ጀምረዋል።ኢራን ከአሜሪካ ለተከፈተባት ጥቃት እስካሁን ምላሽ አልሰጠችም። የአሁኑ ጥቃት በሁለቱ አገራት የሰላም ድርድር ላይ ምን ጫና እንደሚያሳድርም ግልጽ አይደለም።ጥቃቱን ተከትሎ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ “አሁንም ቢሆን ስምምነት ላይ መድረስ ይቻላል” ብለዋል።ትናንት የኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ውይይት አድርገዋል።ያጋሩ, የአሜሪካ ጦር በደቡብ ኢራን አዲስ ጥቃት መክፈቱን አስታወቀ
  17. 25 ግንቦት 2026ትራምፕ አረብ እና ሙስሊም አገራት ከእስራኤል ጋር ስምምነት እንዲፈርሙ ግፊት እያደረጉ ነውትራምፕየፎቶው ባለመብት,EPA/Shutterstockአሜሪካ ከኢራን ጋር ከስምምነት ለመድረስ መቃረቧን እየገለጹ ያሉት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዚያ በፊት ግን ዋነኞቹ ሙስሊም አገራት ከእስራኤል ጋር የአብረሃም ስምምነትን እንዲፈርሙ ጥሪ አቀረቡ።ድርድሩ “በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ነው” ያሉት ፕሬዝዳንቱ ከኢራን ጋር የሚካሄደውን ጦርነት የሚያስቆመው ስምምነት ከመፈረሙ በፊት ብዙሃኑ ሕዝባቸው ሙስሊም የሆኑ ስድስት አገራት ከእስራኤል ጋር ያላቸውን ግንኙነት የሚያሻሽለውን ስምምነት መፈረም እንዳለባቸው አስታውቀዋል።ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደረገውን ስምምነት ከስድስት ዓመት በፊት ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ እና ባህሬን በማስከተልም ሞሮኮ እና ሱዳን ከእስራኤል ጋር ከተፈራረሙት የአብረሃም ስምምት ጋር አስተሳስረው እያቀረቡት ነው።ከበርካታ ሙስሊም እና አረብ አገራት መሪዎች ጋር መነጋገራቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የጠቀሱት ትራምፕ ውስብስቡን ሥራ አሜሪካ መሥራቷን በመግለጽ “በተከታይነት እነዚህ አገራት በሙሉ ቢያንስ የአብረሃም ስምምነትን መፈረም ይጠበቅባቸዋል” ብለዋል።ከእነዚህም መካከል ሳዑዲ አረቢያ፣ ኳታር፣ ፓኪስታን፣ ቱርክ፣ ግብፅ እና ዮርዳኖስን በመጥቀስ ስምምነቱን እንዲፈርሙ እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል።ነገር ግን ግብፅ እና ዮርዳኖስ ከእስራኤል ጋር ግንኙነት ያላቸው ሆነው ሳለ ለምን እንደጠቀሷቸው ግልጽ አይደለም። እስራኤል ከቱርክ ጋር ለረጅም ጊዜ የቆየ የሻከረ ግንኙነት ያላት ሲሆን፣ የጋዛውን ጦርነት ተከትሎ የበለጠ ተቃቅረዋል።የተጠቀሱት አገራት የአብረሃም ስምምነትን የሚፈርሙ ከሆነ እስራኤል ከአብዛኞቹ አረብ እና ሙስሊም አገራት ጋር ያላትን ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ የሚያሻሽል ነው።ያጋሩ, ትራምፕ አረብ እና ሙስሊም አገራት ከእስራኤል ጋር ስምምነት እንዲፈርሙ ግፊት እያደረጉ ነው
  18. 25 ግንቦት 2026አንድ መኪና ከዝሆን ጋር ተጋጭቶ ሦስት ሰዎች ሲሞቱ አራት ቆሰሉአደጋው የደረሰበት መኪናየፎቶው ባለመብት,Uganda Police Forceበኡጋንዳ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ አንድ መኪና ከዝሆን ጋር ተጋጭቶ ቢያንስ ሦስት ሰዎች መሞታቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ።ፖሊስ እንዳለው እሁድ ማታ በኡጋንዳ ሰሜናዊ ምዕራብ ክፍል ውስጥ በተከሰተው አደጋ ከሞቱት በተጨማሪ ሌሎች አራት ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።ተሽከርካሪው ሰባት የአገሪቱ ገቢዎች ባለሥልጣናትን አሳፍሮ እየተጓዘ ሳለ ነበር ከዝሆኑ ጋር የተጋጨው። በአደጋው የተጎዱት ሰዎች በአካባቢው ወደሚገኝ ከዚያም ወደ ዋና ከተማዋ ካምፓላ ተወስደዋል።ስለአደጋው መግለጫ ያወጡት ባለሥልጣናት በሰዎች ላይ የሞት እና የአካል ጉዳት ከመድረሱ ውጪ በዝሆኑ ላይ ስለደረሰው ጉዳት ያሉት ነገር የለም።በኡጋንዳ ውስጥ ከዱር እንስሳት ጋር በተያያዘ የሚከሰት የመኪና አደጋ በተደጋጋሚ እንደሚያጋጥም ይነገራል። የአገሪቱ የዱር እንስሳት ባለሥልጣን አሽከርካሪዎች በመንገዳቸው ላይ ለእንስሳት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።”አሽከርካሪዎች ለእንስሳት በተከለሉ ጥብቅ አካባቢዎች በኩል በሚያልፉበት ጊዜ እንስሳቱ በብዛት መንገዶችን ስለሚያቋርጡ በጥንቃቄ እንዲያሽከረክሩ” ጠይቋል።ያጋሩ, አንድ መኪና ከዝሆን ጋር ተጋጭቶ ሦስት ሰዎች ሲሞቱ አራት ቆሰሉ
  19. 25 ግንቦት 2026ትራምፕ ከኢራን ጋር ስምምነት ላይ ሊደረስ እንደሚችል ተናገሩትራምፕየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ስምምነት ላይ ሊደረስ የሚችልበት እንዳለ አስረግጠው ተናገሩ።ከቴህራን ጋር እየተካሄደ ያለውን ድርድር አጥብቀው የተከላከሉት ፕሬዝዳንቱ የተቿቸውን ዴሞክራቶች እና ሪፐብሊካኖች “ከኢራን ጋር የሚካሄደው ድርድር ስላለው አቅም የማያውቁ ደደቦች” ሲሉም አንቋሸዋል።በትሩዝ ሶሻል ማኅበራዊ ሚዲያቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ ፖለቲከኞቹን “ትልልቅ ድሎቼን የሚኮንኑ ከፋፋይ ግለሰቦች” ብለዋል።“ከኢራን ጋር የሚደረሰው ስምምነት ታላቅ እና ትርጉም ይሆናል፤ አልያም ምንም ስምምነት አይኖርም” ሲሉም ትራምፕ ተናግረዋል።የትራምፕ አስተዳደር በኢራን ያለው ፖለቲካዊ ዓላማ ላይ ዴሞክራቶች እና ሪፐብሊካን የሕዝብ እንደራሴ አባላትም ሳይቀር ጥያቄ ማንሳት ጀምረዋል።ከቴህራን ጋር የሚደረገውን ንግግር ከተቹ መካከል የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ እና የቀድሞ የትራምፕ የብሔራዊ ደኅንነት አማካካሪ ጆን ቦልተን ይጠቀሳሉ።ያጋሩ, ትራምፕ ከኢራን ጋር ስምምነት ላይ ሊደረስ እንደሚችል ተናገሩ
  20. 25 ግንቦት 2026ከፍተኛ የኢራን ባለሥልጣናት ኳታር መግባታቸው ተዘገበየውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አባስ አራግቺየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesከአሜሪካ ጋር የሚደረገውን የሰላም ድርድር በዋነኛነት የሚመሩት የኢራን ባለሥልጣናት ኳታር ዋና ከተማ ዶሃ መግባታቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘገበ።የኢራን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ መሐመድ ባጋር ጋሊባፍ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አባስ አራግቺ ወደ ኳታር ያደረጉት ጉዞ የተጠበቀ እንዳልሆነ ተገልጿል።የኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከሼኽ ታሚም ቢን ሐማድ አል ታሒኒ ጋር ውይይት ለማድረግ ዶሃ መሄዳቸው ተዘግቧል።ውይይታቸው በዋነኛነት የሆርሙዝ ወሽመጥ እና የዩራንየም ጉዳይን የሚመለከት እንደሚሆን የሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል።የኢራን ብሔራዊ ባንክ ገዢ አብዶልናስር ሔማቲ “ማዕቀብ የተጣለባቸው የባንክ ሒሳቦችን በተመለከተ ለሚደረግ ድርድር” ወደ ኳታር ማቅናታቸውን የቴህራን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።ባለፈው ሳምንት ደግሞ የኳታር ልዑካን ወደ ኢራን አቅንተው እንደነበር ይታወሳል።ኢራን እንደ ቅድመ ሁኔታ ካቀረበቻቸው ነጥቦች መካከል አሜሪካ ከፋይናንስ ይዞታዎቿ ላይ ማዕቀብ እንድታነሳ የሚጠይቀው ይገኝበታል።ያጋሩ, ከፍተኛ የኢራን ባለሥልጣናት ኳታር መግባታቸው ተዘገበ