
አሜሪካ እና ኢራን ስምምነት ላይ ከመድረሳቸው በፊት በርካታ የማያግባቧቸውን ጉዳዮች መፍታት እንዳለባቸው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ተናገሩ። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስምምነት ለመፈረም ተቃርበው እንደሆነ ከቢቢሲ የተጠየቁት ጄዲ ቫንስ፤ አሁን ላይ መናገር እንደማይቻል ገልጸዋል።
ጭምቅ ሃሳብ
- አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ላይ መድረሳቸው እና ትራምፕ እስኪያጸድቁት እየተጠበቀ መሆኑ ተዘገበ
- ኦማን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የሚጣለውን ቀረጥ በማመቻቸት እንዳትሳተፍ አሜሪካ አስጠነቀቀች
- የፓኪስታን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አርብ ወደ ዋሺንግተን አምርተው ከማርኮ ሩቢዮ ጋር ሊነጋገሩ ነው
- የቀድሞው የየመን ፕሬዚዳንት አብድ ራቡህ ማንሱር ሃዲ ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ሕይወታቸው አለፈ
- አሜሪካ፤ ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ለማስተዳደር በመሠረተችው አዲስ ተቋም ላይ ማዕቀብ ጣለች
- የኢራን አብዮታዊ ዘብ በአጸፋ እርምጃ ‘የአሜሪካ አየር ኃይል ሰፈርን’ መምታቱን አስታወቀ
- አሜሪካ በሦስት ቀናት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ኢራን ላይ ጥቃት ፈጸመች
የቀጥታ ሽፋን
- ከ 1 ሰአት በፊትየቀድሞው የሲአይኤ ባለሥልጣን በቤታቸው 40 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ የወርቅ ጥፍጥፎች ተገኙባቸው
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesአንድ የአሜሪካ የስለላ ድርጅት (ሲአይኤ) የቀድሞ ባለሥልጣን ቤታቸው ሲፈተሽ 40 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ የወርቅ ጥፍጥፎች ተገኝተው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።የኤፍቢአይ መርማሪዎች ግለሰቡን የያዙት ስለትምህርት እና ወታደራዊ ታሪካቸው ዋሽተው እንደሆነ ማጣራት በሚያደርጉበት ጊዜ የወርቅ ጥፍጥፎችን ካገኙ በኋላ ነው።የፍርድ ቤት ሰነዶች እና ጉዳዩን የሚያውቁ ምንጮች እንዳሉት የቀድሞው የሲአይኤ ባለሥልጣን ዴቪድ ረሽ በአሁኑ ጊዜ በእስር ላይ ይገኛሉ።ሲቢኤስ ቴሌቪዥን እንደዘገበው ግለሰቡ የሕዝብ ንብረት በመስረቅ ወንጀል ተጠርጥረው ክስ ተመስርቶባቸዋል።ኤፍቢአይ በግለሰቡ ላይ የወርቅ ጥፍጥፎችን በሕገወጥ መንገድ በመያዝ፣ ከሚገባቸው በላይ ደሞዝ በመውሰድ፣ በተጭበረበረ ሁኔታ ወታደራዊ የእረፍት ፈቃድ በመውሰድ እና በርካታ ሐሰተኛ ቃል በመስጠት ከስሷቸዋል።ዴቪድ ረሽ በዚህ ዓመት ከኅዳር አስከ መጋቢት ወር ድረስ ባለው ጊዜ ከመንግሥት ከፍተኛ መጠን ያለው የውጭ ምንዛሪ እና በአስር ሚሊሊዮኖች ዶላር የሚያወጡ የወርቅ ጥፍጥፎችን ከሥራ ጋር ለተያያዙ ወጪዎች ጠይቀዋል በሚልም ተከስሰዋል።ያጋሩ, የቀድሞው የሲአይኤ ባለሥልጣን በቤታቸው 40 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ የወርቅ ጥፍጥፎች ተገኙባቸው - ከ 2 ሰአት በፊትበሮማኒያ መኖሪያ ሕንጻ በድሮን መመታቱን ተከትሎ ኔቶ ሩሲያን ኮነነ
የፎቶው ባለመብት,DSU via Reutersበሮማኒያ የጋራ መኖሪያ ሕንጻ በሩሲያ ድሮን መመታቱን ተከትሎ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን (ኔቶ) እና የአውሮፓ ኅብረት ባለሥልጣናት ሩሲያን አወገዙ።የሩሲያው ድሮን መኖሪያ ሕንጻውን ከመታ በኋላ እሳት እንደተነሳ እና ሁለት ሰዎች እንደቆሰሉ ተገልጿል።በዩክሬን እና ሞልዶቪያ ድንበር አቅራቢያ ባለው የሮማኒያ ምሥራቃዊ ከተማ ጋላቲ ክስተቱ ከተፈጠረ በኋላ የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አርስላ ቮን ደር ሌይን “የሩሲያ የጦርነት ግብዝነት አሁንም መስመሩን አልፏል” ብለዋል።ኔቶ ሩሲያን “ግድ የለሽ” ሲል አውግዟል።በአራት ዓመታት የዩክሬን ጦርነት ውስጥ የሩሲያ ድሮን በሮማኒያ ድንበር አቅራቢያ ቢታይም፤ የኔቶ አባል አገር ዜጎች ላይ ጉዳት ሲደርስ ግን የመጀመሪያው ነው።ስለ ክስተቱ ሩሲያ እስካሁን ምንም አስተያየት አልሰጠችም።የሮማኒያ የአደጋ መከላከል ተቋም እንዳለው በመኖሪያ ሕንጻው 10ኛ ፎቅ ላይ እሳት ተነስቷል። 70 ሰዎች ከሕንጻው እንዲወጡ ሲደረጉ፤ የተጎዱት ሁለት ሰዎች ሕክምና አግኝተዋል።ፕሬዝዳንት ኒኩሶር ዳን ከአገሪቱ ከፍተኛ መከላከያ ምክር ቤት ጋር አስቸኳይ ውይይት አድርገዋል።“የሩሲያ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ በሮማኒያ የደረሰ የከፋ ጉዳት ነው” ብለዋል።ያጋሩ, በሮማኒያ መኖሪያ ሕንጻ በድሮን መመታቱን ተከትሎ ኔቶ ሩሲያን ኮነነ - ከ 5 ሰአት በፊትአሜሪካ እና ኢራን ለስምምነት ቢቃረቡም የማያግባቧቸውን ጉዳዮች መፍታት እንዳለባቸው ተገለጸ
የፎቶው ባለመብት,Reutersአሜሪካ እና ኢራን ስምምነት ላይ ከመድረሳቸው በፊት በርካታ የማያግባቧቸውን ጉዳዮች መፍታት እንዳለባቸው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ተናገሩ።ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስምምነት ለመፈረም ተቃርበው እንደሆነ ከቢቢሲ የተጠየቁት ጄዲ ቫንስ፤ አሁን ላይ መናገር እንደማይቻል ገልጸዋል።ሁለቱ አገራት ስምምነት ላይ ከደረሱ የተኩስ አቁሙ በ60 ቀናት ይራዘማል። ስለ ኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብርም ንግግር ይጀመራል።ኢራን እና አሜሪካ የስምምነት ማዕቀፍ ላይ ከስምምነት መድረሳቸውን የዋሽንግንተን ባለሥልጣናት ትናንት ሐሙስ ለቢቢሲ መግለጻቸው ይታወሳል።ሆኖም የኢራኑ ታስኒም የዜና ወኪል ስምምነቱ እንዳልተጠናቀቀ እና እንዳልተረጋገጠ ገልጿል።የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ “ዩራኒየም የማበልጸግ ጉዳይን ጨምሮ በአንዳንድ ነጥቦች ዙርያ” ድርድሮች እየተካሄዱ መሆኑን ተናግረዋል።ስምምነት ላይ ተደርሶ እንደሆነ ተጠይቀውም “እዚያ ነጥብ ላይ አልደረስንም፤ ግን ተቃርበናል። አሁንም ሥራችንን እንቀጥላለን” ብለው መልሰዋል።ኢራን ዩራኒየም ማበልጸግ እንድታቆም እና እስካሁን ያከማቸችውን እንድታስወግድም አሜሪካ ጠይቃለች።ሁለቱ አገራት የተኩስ አቁም ካደረጉ ወዲህ ውይይታቸው በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ እንደሆነ ትራምፕ ሲናገሩ ተደምጧል።ያጋሩ, አሜሪካ እና ኢራን ለስምምነት ቢቃረቡም የማያግባቧቸውን ጉዳዮች መፍታት እንዳለባቸው ተገለጸ - 28 ግንቦት 2026ኦማን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የሚጣለውን ቀረጥ በማመቻቸት እንዳትሳተፍ አሜሪካ አስጠነቀቀች
የፎቶው ባለመብት,Reutersኦማን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የሚጣል ቀረጥን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በማመቻቸት እንዳትሳተፍ አሜሪካ አስጠነቀቀች።አሜሪካ አክላም ማንኛውም አካል በዚህ ተሳትፎ የሚገኝ ከሆነ ቅጣት እንደሚጠብቀው ተናግራለች።የግምጃቤት ኃላፊው ስኮት ቤሴንት በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ “የዩናይትድ ስቴትስ በሆርሙዝ የባህር ወሽመት ላይ የክፍያ ስርዓትን ለመጫን የሚደረግ ማንኛውንም ጥረት አትታገስም”ብለዋል።”ኦማን በተለይ የአሜሪካ ግምጃ ቤት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለወሽመጡ የሚከፈል ክፍያን በማመቻቸት ላይ የተሳተፉ ወይንም ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆኑ አጋሮችን ዒላማ በማድረግ እንደሚቀጣ ማወቅ አለባት” ሲሉ ቤሴንትአስጠንቅቀዋል።ያጋሩ, ኦማን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የሚጣለውን ቀረጥ በማመቻቸት እንዳትሳተፍ አሜሪካ አስጠነቀቀች - 28 ግንቦት 2026አሜሪካ የኢራን አየር መንገዶች የሌሎች አገራት አውሮፕላን ማረፊያዎች እና አገልግሎቶች እንዳይጠቀሙ ልታደርግ ነው
የፎቶው ባለመብት,Reutersአሜሪካ የኢራን አየር መንገዶች የሌሎች አገራት አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎቶችን እንዳይጠቀሙ፣ ነዳጅ እንዳይሞሉ እና የቲኬት ሽያጫቸውን ልትገድብ መሆኑን የግምጃ ቤት ኃላፊው አስታወቁ።ስኮት ቤሴንት በኤክስ ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት እርምጃው በኢራን ላይ የተጀመረው የኢኮኖሚ ማዕቀብ ዘመቻ አካል መሆኑን በመጥቀስ የቴህራን አየር መንገዶች ላይ ማዕቀቡን ለመጣል መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።አሜሪካ የኢራን አየር መንገዶች ዓለም አቀፍ በረራ በሚያደርጉበት ወቅት የሌሎች አገራት አውሮፕላን ማረፊያዎችን እና አገልግሎቶችን እንዳይጠቀሙ በማድረግ ምታኔ ሃብታዊ ጫናዋን ልታጠናክር መሆኑን አስታውቃለች።የአሜሪካ ግምጃ ቤት ኃላፊ ስኮት ቤሴንት አክለውም የአሜሪካ ባሕር ኃይል በኢራን ወደቦች ላይ የጣለው እገዳ ለገበያ የሚቀርበው “የኢራን ድፍድፍ ነዳጅ መጠን እንዲቀንስ” በዚህም የተነሳ “የአገሪቱ ምጣኔ ኃብት እና መገበያያ ገንዘብ እንዲዳከም” ማድረጉን ገልጸዋል።ወታደሮቻቸው እየተከፈላቸው አይደለም፣ የፖሊስ አባላትም በሥራ ገበታቸው ላይ አይገኙም እንዲሁም ኻርግ ደሴት እንደተዘጋ ነው ያሉት ቤሴንት “ከድርድሩ የሚገኝ አጥጋቢ ምላሽ ብቻ ይህንን የቁልቁለት ጉዞ ያስቆመዋል” ሲሉ አስጠንቀቅቀዋል።ያጋሩ, አሜሪካ የኢራን አየር መንገዶች የሌሎች አገራት አውሮፕላን ማረፊያዎች እና አገልግሎቶች እንዳይጠቀሙ ልታደርግ ነው - 28 ግንቦት 2026አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት መድረሳቸውን እና ትራምፕ እስኪያጸድቁት እየተጠበቀ መሆኑን አክሲዮስ ዘገበ
የፎቶው ባለመብት,Reutersአሜሪካ እና ኢራን የተኩስ አቁሙን በ60 ቀናት ለማራዘም እና በኒውክሌር ፕሮግራሟ ላይ ለመደራደር መስማማታቸው ተዘገበ።አክሲዮስ ሁለት የአሜሪካ ባለሥልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው ስምምነቱን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስኪያጸድቁት ድረስ እየተጠበቀ ነው።ሁለቱ አገራት ከስምምነት ላይ መድረሳቸው የተዘገበው ኢራን በኩዌት የሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሠፈር ላይ ጥቃት መሰንዘሯ ከተዘገበ በኋላ ነው።አክሲዮስ ሁለቱ አገራት መስማማታቸውን ከዘገበ በኋላ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ላይ ቅናሽ ታይቷል።አሜሪካ ሌሊት ላይ በኢራን የወደብ ከተማ ባንዳር አባስ ውስጥ በሚገኝ የአውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ ለአየር እና ለባሕር ኃይሏ ስጋት እንደሆኑ የገለጸቻቸውን ወታደራዊ ማዕከላት መምታቷን አስታውቃለች።የአሜሪካ ኃይሎች “በሆርሙዝ ወሽመጥ ዙሪያ ስጋት ደቅነው የነበሩ” አራት የኢራን ድሮኖችንም መትተው እንደጣሉ የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንትኮም) ገልጿል።እንደ ሴንትኮም ገለጻ ባንደር አባስ ውስጥ የሚገኘው ወታደራዊ ስፍራ ጥቃት የተፈጸመበት አምስተኛውን ድሮን ለመተኮስ ሲዘጋጅ ነው። የኢራን መገናኛ ብዙኃን ከከተማው በስተምሥራቅ አቅጣጫ የፍንዳታ ድምፆች መሰማታቸውን ዘግበዋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢራን አብዮታዊ ዘብ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የራዳር መከታተያውን አጥፍቶ ሊያልፍ የነበረ የአሜሪካ ነዳጅ ጫኝ መርከብን ማስቆሙን ታስኒም የዜና ወኪል ዘግቧል።ዘገባው እንዳመለከተው የአብዮታዊ ዘቡ ባሕር ኃይል በመርከቡ ላይ ተኩስ ከፍቶ ወደ መጣበት እንዲመለስ ማስገደዱንም ገልጿል።ያጋሩ, አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት መድረሳቸውን እና ትራምፕ እስኪያጸድቁት እየተጠበቀ መሆኑን አክሲዮስ ዘገበ - 28 ግንቦት 2026የፓኪስታን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አርብ ወደ ዋሺንግተን አምርተው ከማርኮ ሩቢዮ ጋር ሊነጋገሩ ነው
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የፓኪስታን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አይሻቅ ዳርየፓኪስታን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አይሻቅ ዳር አርብ ወደ ዋሺንግተን አምርተው ከአሜሪካው አቻቸው ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤታቸው አስታወቀ።ሚኒስትሩ ወደ ዋሺንግተን የሚያመሩት ኢዝላማባድ በኢራን እና በአሜሪካ መካከል በቋሚነት የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም የሚያስችል ሰላም እንዲመጣ ጥረት እያደረገች ባለችበት ወቅት ነው።የፓኪስታን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለቻው ዳር ከሩቢዮ ጋር በሚኖራቸው ውይይት “በሁለትዮሽ ግንኙነት እና የጋራ ፍላጎት ባላቸው ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች ላይ ሃሳብ ይለወወጣሉ” ብሏል።አሜሪካ እና ኢራን የሚያደርጉት የሰላም ንግግር ፍሬ ማፍራት ባለመቻሉ ዋሺንግተን በዚህ ሳምንት በተደጋጋሚ የአየር ድብደባዎች በደቡባዊ ኢራን ፈጽማለች።አሜሪካ የፈጸመችው ጥቃት ተከትሎ የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ የአጸፋ እርምጃ በመውሰድ “የአሜሪካ አየር ኃይል ሰፈርን” መምታቱን ተናግሯል።በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረገው ጦርነት ሦስት ወር የሞለው ሲሆን በሆርሙዝ ወሽመጥ ለሚደረግ የመርከብ ጉዞ መቆም እንዲሁም የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ መናር ምክንያት ሆኗል።ይህንን ሦስት ወር የሞላው ጦርነት ለማቆም የሚደረጉ ረጅም ድርድሮች እስካሁን መፍትሔ አላስገኙም።አሜሪካ ራሷን ለመከላከል እንደሆነ በመግለጽ በሦስት ቀናት ውስጥ ሁለቴ ኢራን ውስጥ ባሉ ዒላማዎች ላይ ጥቃት ፈጽማለች። እንደ አዲስ ጥቃቶች መፈጸማቸው የተኩስ አቁም ስምምነቱን አደጋ ላይ ጥሎታል።ያጋሩ, የፓኪስታን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አርብ ወደ ዋሺንግተን አምርተው ከማርኮ ሩቢዮ ጋር ሊነጋገሩ ነው - 28 ግንቦት 2026የቀድሞው የየመን ፕሬዚዳንት አብድ ራቡህ ማንሱር ሃዲ ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ሕይወታቸው አለፈ
የፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የቀድሞው የየመን ፕሬዚዳንት አብድ ራቡህ ማንሱር ሃዲ ሥልጣናቸውን የለቀቁት እአአ በ2022 ነበርየቀድሞው የየመን ፕሬዚዳንት አብድ ራቡህ ማንሱር ሃዲ በ80 ዓመታቸው በሳዑዲ አረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ ሕይወታቸው ማለፉ ተገለጸ።ለፕሬዚዳንቱ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለኤኤፍፒ እንዳስታወቁት ሃዲ “በሳዑዲ ዋና ከተማ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ሕመም ሕይወታቸው አልፏል” ብለዋል።ሃዲ በሳዑዲ በሚደገፈው መንግሥት እና በሁቲዎች መካከል ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ እአአ በ2015 ወደ ሪያድ በመሸሽ ኑሯቸውን በዚያ አድርገዋል።በፕሬዚዳንት አሊ አብዱላህ ሳላህ የሥልጣን ዘመን እአአ ከ1994 እስከ 2012 ድረስ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ያገለገሉት ሃዲ፣ የአረብ የጸደይ አብዮት ሳላህን ከሥልጣን ሲያወርዳቸው እርሳቸው ቦታውን ተረክበዋል።በየመን የሁቲ አማጺያን ተቃውሞ ተፋፍሞ ዋና ከተማዋን ሰነዓን በቁጥጥር ሥር ሲያውሉ ሃዲ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሸሽተዋል።እአአ በ2022 ሥልጣናቸውን ለፕሬዚዳንታዊ ምክር ቤት ሲያስረክቡ በየመን የተቀሰቀሰው ጦርነት በሺህዎች የሚቀጠሩትን በሞት ቀጥፎ አገሪቱን ለከፋ የሰብዓዊ ቀውስ አጋልጦ ነበር።ምንጮች ለኤኤፍፒ የሃዲ የቀብር ሥነ ስርዓት ነገ አርብ በሪያድ እንደሚፈጸም አስታውቀዋል።ያጋሩ, የቀድሞው የየመን ፕሬዚዳንት አብድ ራቡህ ማንሱር ሃዲ ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ሕይወታቸው አለፈ - 28 ግንቦት 2026የአውሮፓ ኅብረት የሆርሙዝ ሁኔታ በሚቀጥሉት ሳምንታት የማይሻሻል ከሆነ የአውሮፕላን ነዳጅ ላይ ተጽዕኖ እንደሚኖረው አስታወቀ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን በሳምንታት ውስጥ የሆርሙዝ ወሽመጥ ጉዳይ የማይሻሻል ከሆነ በአውሮፓ የአውሮፕላን ነዳጅ እጥረት ሊፈጠር ወይንም የዋጋ ጭማሪ ሊታይ እንደሚችል ሐሙስ ዕለት አስታወቀ።የአውሮፓ ኮሚሽን የኢነርጂ ቢሮ ከነዳጅ እና ጋዝ አስተባባሪ ቡድኖች ጋር ስብሰባ ካደረገ በኋላ ሐሙስ ዕለት መግለጫ አውጥቷል።“የነዳጅ ማስተባበሪያ ቡድኑ የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት በድፍድፍ ነዳጅ እና በዋና ዋና የፔትሮሊየም ምርቶች ላይ ተጽዕኖ ማሳረፉን አስታውቋል። እንዲሁም ሁሉም የአውሮፓ አገራት በዚህ ጉዳት ደርሶባቸዋል። እስካሁን በአውሮፓ ኅብረት የዋጋ ጭማሪ ቢታይም ተጠቃሚዎች ግን እጥረት አላጋጠማቸውም” ብሏል።“ይሁን እንጂ በሚቀጥሉት ሳምንታት ሁኔታው ለውጥ የማያሳይ ከሆነ በተለይ የአውሮፕላን ነዳጅ ላይ ገበያው ጭማሪ ሊያሳይ ወይንም እጥረት ሊፈጠር ይችላል” ሲል አስጠንቅቋል።ያጋሩ, የአውሮፓ ኅብረት የሆርሙዝ ሁኔታ በሚቀጥሉት ሳምንታት የማይሻሻል ከሆነ የአውሮፕላን ነዳጅ ላይ ተጽዕኖ እንደሚኖረው አስታወቀ - 28 ግንቦት 2026አሜሪካ እና ኢራን ጥቃት ከፈጸሙ በኋላ የነዳጅ ዋጋ ጨመረ
የፎቶው ባለመብት,Hindustan Times via Getty Imagesአሜሪካ እና ኢራን አንዳቸው በሌላኛቸው ላይ ጥቃት መፈጸማቸው ተኩስ አቁሙ ሊቋረጥ ይችላል የሚል ስጋት በመፍጠሩ፤ የነዳጅ ዋጋ በድጋሚ ጨመረ።በዛሬው ዕለት ሦስት ወር የሞላውን ጦርነት ሙሉ ለሙሉ ለመቋጨት የሚያስችል ስምምነት ላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይደረሳል የሚል ተስፋ መፈጠሩን ተከትሎ ረቡዕ ዕለት የነዳጅ ቅናሽ አሳይቶ ነበር። የዛሬው ጭማሪ ትናንት የታየውን ቅናሽ ወደ ቦታው የመለሰ ሆኗል።ለዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ በጠቋሚነት የሚወሰደው የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ የአንድ በርሜል ዋጋ ሐሙስ ንጋት ላይ ዋጋው በ3.75 በመቶ ጨምሮ 97.83 ዶላር ገብቷል። የአሜሪካው ዌስት ቴክሳስ ኢንተርሚዲየት (WTI) ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋም የ4 በመቶ ዕድገት በማሳየት በበርሜል ወደ 92.22 ዶላር አሻቅቧል።የነዳጅ ዋጋ እንዲጨምር ምክንያት የሆነው ጥቃት የተፈጸመው ቴህራን እና ዋሽንግተን ጦርነቱን ለመቋጨት ንግግራቸውን በቀጠሉበት ወቅት ነው። የካቲት ላይ በአሜሪካ እና በእስራኤል ጥቃት የተከፈተባት ኢራን በምላሹ የሆርሙዝ ወሽመጥን መዝጋቷ የዓለም የኤነርጂ ገበያ እንዲቃወስ አድርጓል።ከዓለም ነዳጅ እና ወደ ፈሳሽነት የተቀየረ የተፈጥሮ ጋዝ ውስጥ 20 በመቶው ገደማው የሚተለላፈው በዚህ ወሽመጥ ነው።ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የዓለም የኤነርጂ ዋጋ መዋዠቁን ቀጥሏል። ከጦርነቱ በፊት በበርሜል 70 ዶላር ሲሸጥ የነበረው ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ፤ 120 ዶላር የደረሰበት ጊዜም ነበር።ያጋሩ, አሜሪካ እና ኢራን ጥቃት ከፈጸሙ በኋላ የነዳጅ ዋጋ ጨመረ - 28 ግንቦት 2026አሜሪካ፤ ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ለማስተዳደር በመሠረተችው አዲስ ተቋም ላይ ማዕቀብ ጣለች
የፎቶው ባለመብት,Reutersየአሜሪካ ግምጃ ቤት ኢራን በሆርሙዝ በኩል የሚደረጉ የባሕር ጉዞዎችን ለመቆጣጠር በቅርቡ ባቋቋመችው “የፋርስ ባሕረ ሰላጤ ወሽመጥ ባለሥልጣን” (Persian Gulf Strait Authority) ላይ ማዕቀብ መጣሉን አስታወቀ።ግምጃ ቤቱ ባወጣው መግለጫ፤ የዚህ መስሪያ ቤት መቋቋም የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ከሚያልፉ መርከቦች ገቢ ለመሰብሰብ” የሚያደርገው ሙከራ አካል ነው ብሏል።በዚህም ምክንያት መስሪያ ቤቱ እና “ከተቋሙ ጋር የሚተባበሩ በሙሉ” የማዕቀብ ዝርዝር ውስጥ መግባታቸውን አስታውቋል።የተከፈተባትን ጦርነት ተከትሎ ሆርሙዝ ወሽመጥን የዘጋችው ኢራን፤ ይህንን ተቋም የመሠረተችው አሜሪካ ወደ ወደቦቿ የሚደረጉ ጉዞዎች ላይ እግድ ከጣለች በኋላ ነው።ተቋሙ በወሽመጡ የሚደረግ የመርከቦች ጉዞን የመቆጣጠር እና የማቀናጀል ሥልጣን አለው።ባለ ሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከዚህ ቀደም በቲውተር ገጹ ባወጣው ካርታ በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚገኝ “የክትትል ዞን” አሳይቷል። በዚህ ዞን ውስጥ የሚደረግ ጉዞ ከተቋሙ ጋር “መቀናጀት እንደሚያስፈልገውም” አስታውቋል።በዚህ የወሽመጡ ክፍል በኩል ማለፍ የሚፈልጉ መርከቦች ከፋርስ ባሕረ ሰላጤ ወሽመጥ ባለሥልጣን ፈቃድ ማግኘት እንዳለባቸውም አሳስቧል።ባለፉት ቀናትም በዚህ የውሃ ክፍል የሚያልፉ መርከቦች በኢራን ኃይሎች ታጅበው እንዲጓዙ ወይም እንዲቆሙ እንደተደረጉ ዘገባዎች አመልክተዋል።ያጋሩ, አሜሪካ፤ ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ለማስተዳደር በመሠረተችው አዲስ ተቋም ላይ ማዕቀብ ጣለች - 28 ግንቦት 2026እስራኤል የደቡባዊ ሊባኖስ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ አዘዘች
የፎቶው ባለመብት,AFPየምስሉ መግለጫ,እስራኤል ረቡዕ ዕለት በደቡባዊ ጣይር ከተማ ድብደባዎችን ከፈፀመች በኋላ ወደ ሰማይ የሚጎን ጭስ ታይቷልየእስራኤል ጦር በደቡባዊ ሊባኖስ የሚገኝን ግዙፍ ክፍል “የግጭት ዞን” የሚል ምድብ ውስጥ እንዳስገባው በመግለጽ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጠ።የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት፤ ነዋሪዎች ከድንበር 40 ኪሎ ሜትር ገደማ በዛህራኒ ወንዝ ሰሜን አቀጣጫ እንዲጓዙ አሳስቧል።ጦሩ እጅግ ከባድ የሆነ የኃይል እርምጃ እንደሚወስድ ያስታወቀ ሲሆን፤ ሄዝቦላህ በተደጋጋሚ የተኩስ አቁሙን ጥሷል በሚል ከስሷል።የተኩስ አቁሙ ከታወጀ ከሚያዚያ መጀመሪያ ወዲህ 14 በመቶ የሚሆነውን የሊባኖስ ግዛት ከሚሸፍነው አካባቢ ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ ሲጠየቅ ይህ የመጀመሪያው ነው።ረቡዕ ዕለት እስራኤል በደቡባዊ ጣይር ከተማ ድብደባዎችን ፈፅማለች። እስራኤልን የተኩስ አቁም ስምምነቱን በመጣስ የሚከስሰው ሄዝቦላህ ተዋጊዎቹ ከእስራኤል ወታደሮች ጋር መጋጨታቸውን ተናግሯል።የረቡዕ ጥቃት የመጣው ሄዝቦላህ በሊባኖስ ግዛት በሚገኙ ወታደሮች እና በሰሜናዊ እስራኤል ንፁሃን ላይ የድሮን ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የምድር ዘመቻቸውን እንደሚያስፋፉ ካስታወቁ በኋላ ነው።ባለፉት 24 ሰዓታት የእስራኤል ጦር ዘጠኝ የአካባቢውን ለቃችሁ ውጡ መመሪያዎችን አውጥቷል። ይህም በእስራኤል-ሊባኖስ ድንበር ግዙፍ ግጭት ይቀሰቀሳል የሚል ስጋት የደቀነ ሲሆን፤ በርካታ ሰዎችንም እንደሚያፈናቅል ተገምቷል።ያጋሩ, እስራኤል የደቡባዊ ሊባኖስ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ አዘዘች - 28 ግንቦት 2026የኢራን አብዮታዊ ዘብ በአጸፋ እርምጃ ‘የአሜሪካ አየር ኃይል ሰፈርን’ መምታቱን አስታወቀ
የፎቶው ባለመብት,EPAአሜሪካ የፈጸመችው ጥቃት ተከትሎ የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ወሰድኩት ባለው የአጸፋ እርምጃ “የአሜሪካ አየር ኃይል ሰፈርን” መምታቱን አስታወቀ።አሜሪካ ሌሊት ላይ በኢራን የወደብ ከተማ ባንዳር አባስ ውስጥ በሚገኝ የአውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ ለአየር እና ለባሕር ኃይሏ ስጋት እንደሆኑ የገለጸቻቸውን ወታደራዊ ማዕከላት መምታቷን አስታውቃለች።የኢራን አብዮታዊ ዘብ ጥቃቱ ምንም ጉዳት እንዳላደረሰ በመጥቀስ በምላሹ የአሜሪካ የወረራ ጥቃት መነሻ ነው ባለው የአየር ኃይል ሰፈር ላይ ጥቃት መፈጸሙን የኢራን ዜና ወኪል ታስኒም ይዞት በወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል።ይህ ጥቃት የተፈጸመበት ወታደራዊ ማዕከል የት እንደሚገኝ ግን በትክክል አልተገለጸም።የአብዮታዊ ዘቡ ጨምሮም “የጠብ ጫሪነት ጥቃቶች አጸፋ እንደሚሰጣቸው” በማመልከት ጥቃቶች የሚቀጥሉ ከሆነ “የበለጠ ከባድ” ምላሽ እንደሚኖር ገልጿል።ከአብዮታዊ ዘቡ ጋር ቅርብ የሆነው ታስኒም የዜና ወኪል ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው አሜሪካ ሌሊት ላይ የፈጸመችው ጥቃት ምንም ነገር በሌለበት ቦታ ላይ መሆኑን እና ፍንዳታውም የተሰማው ከዚያ ጋር የተያያዘ መሆኑን አመልክቷል።ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢራን አብዮታዊ ዘብ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የራዳር መከታተያውን አጥፍቶ ሊያልፍ የነበረ የአሜሪካ ነዳጅ ጫኝ መርከብን ማስቆሙን ታስኒም የዜና ወኪል ዘግቧል።ዘገባው እንዳመለከተው የአብዮታዊ ዘቡ ባሕር ኃይል በመርከቡ ላይ ተኩስ ከፍቶ ወደ መጣበት እንዲመለስ ማስገደዱንም ገልጿል።ያጋሩ, የኢራን አብዮታዊ ዘብ በአጸፋ እርምጃ ‘የአሜሪካ አየር ኃይል ሰፈርን’ መምታቱን አስታወቀ - 28 ግንቦት 2026አሜሪካ በሦስት ቀናት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ኢራን ላይ ጥቃት ፈጸመች
የፎቶው ባለመብት,US Navy via Getty Imagesየአሜሪካ ጦር በኢራን ስትራቴጂካዊ የወደብ ከተማ ባንደር አባስ የሚገኝ ወታደራዊ ስፍራን ዒላማ ያደረጉ የአየር ጥቃቶችን መፈጸሙን አስታወቀ።የአሜሪካ ኃይሎች “በሆርሙዝ ወሽመጥ ዙሪያ ስጋት ደቅነው የነበሩ” አራት የኢራን ድሮኖችንም መትተው እንደጣሉ የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንትኮም) ገልጿል።እንደ ሴንትኮም ገለጻ ባንደር አባስ ውስጥ የሚገኘው ወታደራዊ ስፍራ ጥቃት የተፈጸመበት አምስተኛውን ድሮን ለመተኮስ ሲዘጋጅ ነው። የኢራን መገናኛ ብዙኃን ከከተማው በስተምስራቅ አቅጣጫ የፍንዳታ ድምፆች መሰማታቸውን ዘግበዋል።ጥቃቱ የተፈጸመው በአሜሪካ እና ኢራን መካከል የተደረሰው ጠንካራ ያልሆነ ተኩስ አቁም ተግባራዊ መሆን ባላቆመበት ነው።በሆርሙዝ ወሽመጥ ለሚደረግ የመርከብ ጉዞ መቆም እንዲሁም የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ መናር ምክንያት የሆነውን ይህንን ሦስት ወር የሞላው ጦርነት ለማቆም የሚደረጉ ረጅም ድርድሮች እስካሁን መፍትሔ አላስገኙም።አሜሪካ ራሷን ለመከላከል እንደሆነ በመግለጽ ኢራን ውስጥ ባሉ ዒላማዎች ላይ ጥቃት ስትፈጽም ይህ በሦስት ቀናት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። እንደአዲስ ጥቃቶች መድረሳቸው የተኩስ አቁም ስምምነቱን አደጋ ላይ ጥሎታል።ሴንትኮም የተወሰደውን ወታደራዊ እርምጃ “የተመጠነ፣ በግልጽ ራስን የመከላከል የሆነ እንዲሁም የተኩስ አቁም ስምምነቱን ለማስቀጠል ያለመ” ሲል ገልጾታል።አሜሪካ ሰኞ ዕለት ደቡባዊ ኢራን ላይ በፈጸመችው ጥቃት የኢራንን የሚሳኤል ጣቢያዎች እና በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ፈንጂ ለማጥመድ የሞከሩ መርከቦች ዒላማ እንደተደረጉ ተገልጿል። ሴንትኮም እነዚህ ጥቃቶች የተወሰዱት “ወታደሮቻችንን ከኢራን ኃይሎች ከሚመጡ ስጋቶች ለመጠበቅ” ነው ብለዋል።ጥቃቶቹን “ትልቅ የተሰስ አቁም ጥሰት” ስትል ያወገዘችው ኢራን፤ “የትኛውም ጠበኛ ድርጊት ምላሽ ሳይሰጠው እንደማያልፍ” ዝታለች።የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ማክሰኞ ዕለት የአሜሪካ ድሮንን መትቶ መጣሉን እንዲሁም ወደ ኢራን የአየር ክለል የገቡ ተዋጊ ጄት እና ድረኖን ላይ ተኩስ መክፈቱን ገልጿል። እነዚህ እርምጃዎች የተወሰዱት መቼ እንደነበር ግን አልተጠቀሰም።ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ትናንት በተካሄደ የካቢኔ ስብሰባ ላይ፤ ኢራን “በንዴት እየተደራደረች ነው” ሲሉ ተደምጠዋል። አክለውም በመጪው ህዳር የሚካሄደው የአጋማሽ ጊዜ የሥልጣን ዘመን ምርጫ የጦርነት ስትራቴጂያቸው ላይ ተጽዕኖ እንደማያሳድር ተናግረዋል።ያጋሩ, አሜሪካ በሦስት ቀናት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ኢራን ላይ ጥቃት ፈጸመች - 27 ግንቦት 2026ትራምፕ ከኢራን ጋር የተደረገው ድርድር “እስካሁን አልተሳካም” አሉ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር እየተደረገ ያለው ድርድር “እስካሁን አልተሳካም” አሉ።ድርድሩ “ገና ደስተኛ አላደረገንም” ያሉት ትራም “ነገር ግን [ደስተኛ] እንሆናለን” ብለዋል።ትራምፕ በአስተዳደራቸው ሥር ካሉ ባለሥልጣናት ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ “መሆን ያለበት በዚህ መንገድ ነው፤ አለበለዚያ ግን እንጨርሰዋለን” ሲሉም ገልጸዋል።የኢራን ባለሥልጣናት ድርድሩን እያካሄዱ ያሉት “ደካማ ሆነው ነው” ብለዋል።“ምን እንደሚሆን እናያለን። ተመልሰን ሥራውን መጨረስ ይኖርብን ይሆናል። ወይም አይኖርብንም” ሲሉም አክለዋል።የኢራን መሪዎች “ስምምነት ላይ ለመድረስ ይፈልጋሉ” ሲሉም ትራምፕ ተደምጠዋል።የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በበኩላቸው ስምምነት ላይ መድረስ እንደሚፈልጉ ገልጸው “ካልተሳካ ግን ፕሬዝዳንቱ አማራጭ አላቸወ” ብለዋል።በሌላ በኩል ኢራን ከአሜሪካ ጋር በምታደርገው ድርድር፤ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ የሚገኝ፣ ይፋዊ ያልሆነ፣ የመግባቢያ ሰነድ ማዕቀፍ ረቂቅ እንደደረሳት የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ቢዘግቡም ዋይት ሀውስ ግን ይሄንን “ፍጹም ፈጠራ” ሲል አስተባብሏል።ያጋሩ, ትራምፕ ከኢራን ጋር የተደረገው ድርድር “እስካሁን አልተሳካም” አሉ - 27 ግንቦት 2026ኢራን “የመግባቢያ ሰነድ ረቂቅ” ደርሶኛል ብትልም አሜሪካ አስተባበለች
የፎቶው ባለመብት,EPAኢራን ከአሜሪካ ጋር በምታደርገው ድርድር፤ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ የሚገኝ፣ ይፋዊ ያልሆነ፣ የመግባቢያ ሰነድ ማዕቀፍ ረቂቅ እንደደረሳት የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ቢዘግቡም ዋይት ሀውስ ግን ይሄንን “ፍጹም ፈጠራ” ሲል አስተባብሏል።የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ኦሊቪያ ዌልስ “ፕሬዝዳንት ትራምፕ እንደተናገሩት ድርድሩ እየተሻሻለ ነው። [ፕሬዝዳንቱ] ቀይ መስመሮቻቸውን በግልጽ አስምረዋል” ብለዋል።የኢራን መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ከሆነ ቴህራን በአንድ ወር ውስጥ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ያለውን የጉዞ መጠን ከጦርነቱ አስቀድሞ ወደነበረው ትመልሳለች። በምላሹ አሜሪካ ወታደሮቿን ከኢራን ዙርያ ታስወጣለች፤ በባሕር ኃይሉ ላይ የጣለችውን ማዕቀብም ታነሳለች።የመርከቦችን ጉዞ ማስተዳደሪያ መንገድ የሚወሰነው በኢራን እና ኦማን እንደሆነ ተገልጿል።ነገር ግን “ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለአሜሪካ ሕዝብ የሚጠቅም እና ኢራን መቼም ቢሆን ኒውክሌር መሣሪያ እንዳይኖራት የሚያግድ ስምምነት ብቻ ነው የሚቀበሉት” ብለዋል።የኢራን የብሔራዊ ደኅንነት ጠቅላይ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ እና የዓለም አቀፍ ደኅንነት ምክትል ዳይሬክተር አሊ ባግሪ፤ ቴህራን ከዋሽንግተን ጋር እያደረገችው ባለው ድርድር የዩራኒየም ጉዳይ በአጀንዳነት እንዳልቀረበ ተናግረዋል።በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚያልፉ መርከቦችን በማስተዳደር ረገድ ኢራን እና ኦማን ሚና እንዲኖራቸው እየተደራደሩ መሆኑን አረጋግጠዋል።“በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የማለፍ ሁኔታ እና አካሄድ የኢራን ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ከነበረው ፈጽሞ የተለየ ይሆናል” ብለዋል።“ሁሉም ነጥቦች ላይ ካልተስማማን በስተቀር ስምምነት ላይ ደርሰናል ብለን አናምንም” ሲሉም አክለዋል።ያጋሩ, ኢራን “የመግባቢያ ሰነድ ረቂቅ” ደርሶኛል ብትልም አሜሪካ አስተባበለች - 27 ግንቦት 2026ኢራን በዩራኒየም ይዞታዋ ላይ እንደማትደራደር አስታወቀች
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,አሊ ባግሪኢራን ከአሜሪካ ጋር እያደረገችው ባለው ድርድር የዩራኒየም ጉዳይ በአጀንዳነት እንዳልቀረበ በኢራን የብሔራዊ ደኅንነት ጠቅላይ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ እና የዓለም አቀፍ ደኅንነት ምክትል ዳይሬክተር አሊ ባግሪ ተናገሩ።ባለሥልጣኑ ይህንን ያሉት በሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ ውስጥ እየተካሄደ ባለው 14ኛው ከፍተኛ የደኅንነት ባለሥልጣናት ስብሰባ ወቅት በተጓዳኝ ለተነሳላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ነው።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግን ቀደም ሲል የዳበረው የኢራን ዩራኒየም ክምችት፤ በሚደረስ ስምምነት ወደ አሜሪካ ተወስዶ ወይም በሌላ ስፋራ ላይ እንዲወድም እንደሚደረግ ተናግረው ነበር።የተኩስ አቁም ከተደረገ በኋላ ለወራት ያለመቋጫ እየተካሄደ ያለው የኢራን እና የአሜሪካ ድርድር ወደ ስምምነት መቃረቡን የአሜሪካ ባለሥልጣናት ባለፉት ቀናት ሲናገሩ ቆይተዋል።የኢራን የኒውክሌር ፕሮግራም ዋነኛ መነጋገሪያ ቢሆንም አሳልፋ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኗን እና የድርድሩ ቀይ መስመር መሆኑን በተደጋጋሚ ስትገልጽ ነበር።ፕሬዝዳንት ትራምፕ ግን ኢራን በኒውክሌር ፕሮግራሟ ላይ የቀረበላትን ሃሳብ የማትቀበል ከሆነ ሌላ ዙር ከባድ ጥቃት እንደሚጠብቃት እያስጠነቀቁ ነው።ያጋሩ, ኢራን በዩራኒየም ይዞታዋ ላይ እንደማትደራደር አስታወቀች - 27 ግንቦት 2026የኮንጎ ግጭት ኢቦላን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት እንዳሰናከለ ዶ/ር ቴድሮስ ገለጹ
የፎቶው ባለመብት,Reutersበዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያለው ግጭት የኢቦላን ሥርጭት ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት ላይ ጫና ማሳደሩን የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም ገለጹ።በአገሪቱ “ግጭት እና አደገኛ በሽታ” መደራረባቸውን የተናገሩት ዶ/ር ቴድሮስ፤ በኢቱሪ ግዛት በሽታውን የመከላከል እንቅስቃሴ ማድረግ መስተጓጎሉን አክለዋል።ኃላፊው በኤክስ ገጻቸው ባወጡት መግለጫ የዓለም ጤና ድርጅት “ቦምብ እየዘነበ የማኅበረሰቡን እምነት ማግኘት ወይም ታማሚዎችን መለየት አይችልም”ዶ/ር ቴድሮስ ቫይረሱን በቁጥጥር ሥር የማዋል ጥረቱን ለመምራት ዛሬ ኮንጎ እንደሚገቡ ተገልጿል። በኢቦላ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 220 ደርሷል።የአገሪቱ መንገዶች አመቺ ባለመሆናቸው የእርዳታ ሠራተኞች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው ለመሥራት ተቸግረዋል። ግጭት እና መፈናቀልም የጤና ሥርዓቱን አናግተዋል። በተጨማሪም ዓለም አቀፍ እርዳታ ተቋርጧል።ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በቫይረሱ የተያዙባት ኢቱሪ ግዛት ከአውሮፓውያኑ 2021 አንስቶ በወታደራዊ አስተዳደር ሥር ናት።ያጋሩ, የኮንጎ ግጭት ኢቦላን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት እንዳሰናከለ ዶ/ር ቴድሮስ ገለጹ - 27 ግንቦት 2026ኢራን እና አሜሪካ ልዩነቶቻቸውን ያጠብባሉ ብላ ተስፋ እንደምታደርግ ቻይና ገለጸች
የፎቶው ባለመብት,Reutersየቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ የኢራን ጦርነት ተፋላሚ ወገኖች የተኩስ አቁሙን ለማስቀጠል ቁርጠኛ ሆነው እንደሚቀጥሉ እና ልዩነቶቻቸውን ያጠብባሉ ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ገለጹ።አሜሪካ በደቡብ ኢራን የመከላከል ያለችውን ጥቃት ከፈጸመች በኋላ ቴህራን ማክሰኞ ዕለት ዋሺንግተንን የተኩስ አቁሙን በመጣስ ከስሳለች።ማርኮ ሩቢዮ በበኩላቸው በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግጭት ለማስቆም የሚደረገው ድርድር “የተወሰነ ቀናት ሊወስድ ይችላል” ብለዋል።ዋንግ በኒውዮርክ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ በተገኙበት ወቅት “ሰላም በተቻለ ፍጥነት ወደ መካከለኛው ምሥራቅ እንዲመለስ ተፋላሚ አካላት የተኩስ አቁምን ለማስቀጠል በቁርጠኝነት እንደሚቆዩ እና ልዩነቶቻቸውን ለማጥበብ ግማሽ መንገድ እንደሚገናኙ ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል።ዋንግ አክለውም ሁሌም እንደምንለው ሰላም እና መፍትሄ ለማምጣት ጊዜ ይፈልጋል ያሉት ሚኒስትሩ “ለረዥም ጊዜ የቆዩ ችግሮች ቶሎ አይፈቱም” ብለዋል።“ይሁን እንጂ በድርድሩ የሚደረግ እያንዳንዱ እርምጃ የበለጠ ተስፋን ይሰጣል፤ እንዲሁም ግጭቱ ቶሎ በተቋጨ ጊዜ የሰላማዊ ዜጎችን ጉዳት መቀነስ ይቻላል” ብለዋል።ያጋሩ, ኢራን እና አሜሪካ ልዩነቶቻቸውን ያጠብባሉ ብላ ተስፋ እንደምታደርግ ቻይና ገለጸች - 27 ግንቦት 2026የዩኬ የደህንነት ተቋም ሩሲያ ወሳኝ የመሠረተ ልማቶችን እና ዲሞክራሲን “ያለመታከት ዒላማ እያደረገች” ነው ሲል ወነጀለ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየዩናይትድ ኪንግደም የስለላ፣ ደህንነት እና ሳይበር ኤጀንሲ ሩሲያ ያለ መታከት ወሳኝ መሠረተ ልማቶችን እና አገልግሎቶችን ማጥቃት በመቀጠሏ አገሪቱ አሳሳቢ እና ወሳኝ ጊዜ ላይ እንደምትገኝ ገለጸ።የዩኬ የስለላ ተቋም ኃላፊ የሆኑት አኔ ኪአስት በትለር ረቡዕ ዕለት የሩሲያ እርምጃ ለዩናይትድ ኪንግደም የሚኖረውን ስጋት በሚመለከት እንዲሁም እንዴት መመከት እንዳለባት የሚገልጽ ንግግር ያደርጋሉ ተብሏል።ከኃላፊዋ ንግግር ተቀንጭቦ የተጋራው መልዕከት ላይ ሩሲያ “ወሳኝ የሆነ መሠረተ ልማቶችን፣ የዲሞክራሲ ሂደቶችን፣ የአቅርቦት ሰንሰለቶችን እና የሕዝብ እምነትን ዒላማ አድርጋለች” ብለዋል።ሩሲያ በብሪታኒያ ግዛት ውስጥ የአገር ክህደት ወንጀልን በማበረታታት የምትወቀስ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዩኬ እና የኔቶ አባል አገራት ላይ በይፋ ያልታወጀ ‘የተቀናጀ ጦርነት’ ከፍታለች በሚል ትከሰሳለች።ክሬምሊን ውንጀላውን ያስተባብላል።በትለር ተቋማቸው “ግድየለሽነት የተሞላበት” ያሉትን የሳይበር ጥቃቶች ለመመከት እንዲሁም “የግድያ ሙከራዎችን” ለመከላከል ያለ እረፍት እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።አክለውም “በእንዲህ ዓይነት ጠብ አጫሪት እና ግርግር ውስጥ ተቋማችን ያለመታከት ከደህንነት እና መከላከያ አጋሮቻችን ጋር በመሆን የሩሲያን ስጋት ለመቀነስ ይሰራል” ብለዋል።ክሬምሊን የኬጂቢ ባልደረባ የነበረውን አሌክሳንደር ሊትቪኔንኮን በለንደን ሆቴል ውስጥ ሳለ በጠጣው ሻይ ውስጥ መርዛማ ኬሚካል በመጨመር ለመግደል ሙከራ አድርጓል መባሉን አስተባብሏል።እአአ በ2018 የቀድሞው የሩሲያ ወታደራዊ ደህንነት ባልደረባ የነበረውን ሰርጌይ ስክሪፓልን ለመግድል ሙከራ በማድረግ ተከስሷል።ሩሲያ እአአ በ2022 ዩክሬንን መውረሯን ተከትሎ ዩናይትድ ኪንግደም ከኪየቭ ጎን በመቆሟ በምዕራባውያን አገራት ላይ “የተቀናጀ ጦርነት” በመክፈት ትወነጀላለች።ያጋሩ, የዩኬ የደህንነት ተቋም ሩሲያ ወሳኝ የመሠረተ ልማቶችን እና ዲሞክራሲን “ያለመታከት ዒላማ እያደረገች” ነው ሲል ወነጀለ
