እስራኤል የሊባኖስን ጥንታዊ አምባ መቆጣጠሯን ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲያካሂድ መጠየቃቸውን የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄን-ኖኤል ባሮው አስታወቁ። በደቡብ ሊባኖስ የሚገኘውን ታሪካዊ እና ስትራቴጂያዊ አምባ ሻቂፍ (ቢዩፎርት) እስራኤል በቁጥጥሯ ሥር ማዋሏን መከላከያ ሚኒስትሩ መግለጻቸው አይዘነጋም።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 3 ሰአት በፊትእስራኤል የሊባኖስን ጥንታዊ አምባ መቆጣጠሯን ተከትሎ የፀጥታው ምክር ቤት እንዲወያይ ተጠየቀቢዩፎርት አምባየፎቶው ባለመብት,Reutersእስራኤል የሊባኖስን ጥንታዊ አምባ መቆጣጠሯን ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲያካሂድ መጠየቃቸውን የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄን-ኖኤል ባሮው አስታወቁ።የእስራኤል ጦር ቢዩፎርት አምባን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገልጿል።የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር “የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲያካሂድ ጠይቄያለሁ። እንደ ማንኛውም አገር የእስራኤልን ራስን የመለከላከል መብት ዕውቅና ብንሰጠውም፤ በሊባኖስ ውስጥ የእስራኤል ወታደራዊ ዘመቻ መስፋፋቱን ምክንያታዊ የሚያደርግ ነገር የለም” ማለታቸውም ተዘግቧል።በደቡብ ሊባኖስ የሚገኘውን ታሪካዊ እና ስትራቴጂያዊ አምባ ሻቂፍ (ቢዩፎርት) እስራኤል በቁጥጥሯ ሥር ማዋሏን መከላከያ ሚኒስትሩ መግለጻቸው አይዘነጋም።ሚኒስትሩ እስራኤል ካትዝ የአገራቸው እግረኛ ጦር ሄዝቦላህን ዒላማ አድርጎ በደቡብ ሊባኖስ የሚያደርገውን ዘመቻ እንደሚያስፋፋም ገልጸዋል።የ900 ዓመት ዕድሜ ያለው ታሪካዊ አምባ ደቡብ ሊባኖስን ከበላይ ሆኖ ለመመልከት ምቹ ሲሆን፤ ወታደራዊ ጠቀሜታው የጎላ ነው።ያጋሩ, እስራኤል የሊባኖስን ጥንታዊ አምባ መቆጣጠሯን ተከትሎ የፀጥታው ምክር ቤት እንዲወያይ ተጠየቀ
  2. ከ 3 ሰአት በፊትእስራኤል የሊባኖስን ታሪካዊ እና ስትራቴጂያዊ አምባ መቆጣጠሯን አስታወቀችታሪካዊ እና ስትራቴጂያዊ አምባ ሻቂፍ (ቤይፎርት)የፎቶው ባለመብት,Reutersበደቡብ ሊባኖስ የሚገኘውን ታሪካዊ እና ስትራቴጂያዊ አምባ ሻቂፍ (ቢዩፎርት) እስራኤል በቁጥጥሯ ሥር ማዋሏን መከላከያ ሚኒስትሩ ተናገሩ።ሚኒስትሩ እስራኤል ካትዝ የአገራቸው እግረኛ ጦር ሄዝቦላህን ዒላማ አድርጎ በደቡብ ሊባኖስ የሚያደርገውን ዘመቻ እንደሚያስፋፋ ገልጸዋል።በቴሌግራም ገጻቸው “ከታሪካዊው የቢዩፎርት ውጊያ 44 ዓመታት በኋላ፣ በመጀመሪያው የ1982 የሊባኖስ ጦርነት የተገደሉ ጓዶች በሚታሰቡበት ዕለት፣ ሠራዊታችን ይሄንን አምባ አስመልሶ የእስራኤል ሰንደቅ አላማን ሰቅሏል” ብለዋል።“በጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ አመራር እና በእኔ ትዕዛዝ መሠረት የእስራኤል ጦር በሊባኖስ ዘመቻውን አስፋፍቶ ሊታኒ ወንዝን አልፎ ቢዩፎርትን ተቆጣጥሯል” ሲሉም አክለዋል።አምባው “በጋሊሊ አካባቢ ያሉ ሰፈራዎችን ለመከላከል እና የፀጥታ ኃይሎችን ደኅንነት ለማስጠቅ” ስትራቴጂያዊ መሆኑን ተናግረዋል።ኤኤፍፒ ዛሬ ያወጣቸው ምሥሎች በአምባው የእስራኤል ሰንደቅ አላማ ተሰቅሎ ያሳያሉ። የተኩስ ድምጽ እንደሚሰማ እና ጭስ ከርቀት እንደሚታይም ተገልጿል።አምባው ደቡብ ሊባኖስን ከበላይ ሆኖ ለመመልከት ምቹ ሲሆን፤ ወታደራዊ ጠቀሜታው የጎላ ነው።ከዚህ ቀደም የእስራኤል ጦር አምባውን ደቡብ ሊባኖስን ለመቆጣጠር ተጠቅሞበታል። የእስራኤል የግዳጅ ይዞታ ያከተመው በአውሮፓውያኑ 2000 ነበር።ያጋሩ, እስራኤል የሊባኖስን ታሪካዊ እና ስትራቴጂያዊ አምባ መቆጣጠሯን አስታወቀች
  3. ከ 8 ሰአት በፊትየእስራኤል ጦር በደቡብ ሊባኖስ ዘመቻውን እንደሚያስፋፋ ገለጸኔታንያሁየፎቶው ባለመብት,Reutersየእስራኤል እግረኛ ጦር ላታኒ ወንዝን ከተሻገረ በኋላ በደቡብ ሊባኖስ የጀመረውን ዘመቻ እንደሚያስፋፋ አስታወቀ።በተጨማሪ ዘመቻውን በደቡብ ሊባኖስ አካባቢዎች እንደሚያካሂድ ጦሩ ገልጿል።የእስራኤል እግረኛ ጦር ላቲኒ ወንዝን ከመሻገሩ በፊት የአየር ኃይሉ በሄዝቦላህ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ፈጽሟል።በላቲኒ ወንዝ ደቡባዊ ክፍል የሄዝቦላህ ዒላማዎች ላይ ጥቃት ከፈጸመ በኋላም ዘመቻውን የበለጠ እንደሚያጠናክር ገልጿል።ሄዝቦላህ ባደረሰው የድሮን ጥቃት አንድ የእስራኤል ወታደር መገደሉ ተገልጿል።የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋፍ ሳላም፤ እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ “ስልታዊ በሆነ መንገድ ከተሞችን እና መንደሮች በማውደም ንጹኃን ሸሽተው እንዲወጡ እያስገደደች ነው” ብለዋል።እስራኤል የምትሰነዝረው የአየር ጥቃት ደኅንነት እና መረጋጋትን ማወኩንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።በቀጣይ ሳምንት እስራኤል እና ሊባኖስ በዋሽንግተን ተገናኝተው በአሜሪካ አሸማጋይነት ድርድር ይቀጥላሉ ተብሎ ይጠበቃል።ያጋሩ, የእስራኤል ጦር በደቡብ ሊባኖስ ዘመቻውን እንደሚያስፋፋ ገለጸ
  4. ከ 8 ሰአት በፊትኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚፈጸም ወታደራዊ ጣልቃ ገብነትን እንደማትታገስ አስታወቀችየኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesበኢራን ጦር ውስጥ ቁልፍ ቦታ ያለው ኻታም አል-አናቢያ ማዕከላዊ ዕዝ “የሆርሙዝ ወሽመጥን አስተዳደር ለማሰናከል ማንኛውም ዓይነት ወታደራዊ እንቅስቃሴ” ቢካሄድ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠነቀቀ።“በሆርሙዝ ወሽመጥ ያለውን ዝውውር ለማወክ” ቢሞከርም የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ወታደራዊ እርምጃ መውሰዱ እንደማይቀር አስታውቋል።“ሁሉም መርከቦች እና የንግድ ጀልባዎች ማለፍ የሚችሉት ከእስላማዊ አብዮታዊ ዘቡ የባሕር ኃይል ፈቃድ አግኝተው በተዘረጋላቸው መስመር ብቻ ነው” በማለትም አክሏል።ይህንን አሠራር መጣስ “በአካባቢው ያለውን እንቅስቃሴ ደኅንነት የሚያውክ” እንደሆነ ገልጿል።አሜሪካ እና እስራኤል ኢራን ላይ ጥቃት መክፈታቸውን ተከትሎ ቴህራን በሆርሙዝ ወሽመጥ የምታደርገውን ቁጥጥር አጥብቃለች።አንዳንድ መርከቦች በኦማን ባሕር ዳርቻ አቅራቢያ በሚገኘው የሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ለማለፍ መሞከራቸውን ያልተረጋገጡ ሪፖርቶች ይጠቁማሉ።ያጋሩ, ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚፈጸም ወታደራዊ ጣልቃ ገብነትን እንደማትታገስ አስታወቀች
  5. ከ 9 ሰአት በፊትትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደራደሩባቸው ነጥቦች የበለጠ እንዲጠናከሩ መጠየቃቸው ተዘገበትራምፕየፎቶው ባለመብት,EPAፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር በሚደረገው ድርድር የቀረቡ በርካታ ነጥቦች ላይ ለውጥ እንዲደረግ መጠየቃቸውን የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።ኒው ዮርክ ታይምስ እንደዘገበው፤ ትራምፕ የድርድር ነጥቦቹ የበለጠ እንዲጠናከሩ ይፈልጋሉ። እንደ አዲስ ክለሳ የተደረገበት የድርድር ማዕቀፍም ለኢራን ተልኳል።አክሲዮስ ባወጣው ዘገባ፤ ከኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር እና ዩራንየም የማበልጸግ ሒደት ጋር የሚያያዙ የድርድሩ ነጥቦች እንዲጠናከሩ ትራምፕ ጠይቀዋል።ትራምፕ የስምምነቱን ረቂቅ ከተመለከቱ በኋላ ለውጥ እንዲደረግ መጠየቃቸውን ኒው ዮርክ ታይምስ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል።ትራምፕ እንዲደረግ የጠየቁት ለውጥ ድርድሩን በምን መንገድ ሊቀይረው እንደሚችል ግልጽ አይደለም።የኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር እና ክምችት ትራምፕ ጠንካራ ለውጥ እንዲደረግባቸው ከጠየቋቸው ነጥቦች መካከል እንደሚገኝበት አክሲዮስ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል።የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት እነዚህ ለውጦች ድርድሩን በቀናት ሊያራዝሙ ይችላሉ።ትራምፕ ባለፈው አርብ በዋይት ሀውስ አስቸኳይ ስብሰባ ቢያደርጉም የመጨረሻ ውሳኔያቸው ይፋ አልሆነም።የስምምነቱ ረቂቅ የትራምፕን ይሁንታ እየጠበቀ እንደነበር ኤኤፍፒ ዘግቧል። የኢራን ባለሥልጣናትም ረቂቁን ማጽደቃቸውን አላሳወቁም።ያጋሩ, ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደራደሩባቸው ነጥቦች የበለጠ እንዲጠናከሩ መጠየቃቸው ተዘገበ
  6. 30 ግንቦት 2026ኢራን በኩዌት ጦር ሰፈር ላይ በፈፀመችው የሚሳኤል ጥቃት በርካታ አሜሪካውያን ቆሰሉየአሊ አል ሳሌም የአየር ጦር ሰፈርየፎቶው ባለመብት,BBC Persiaከኢራን የተነሳ የሚሳይል ጥቃት ኩዌት ውስጥ ባለ የአየር ጦር ሰፈር በርካታ አሜሪካውያንን እንደተጎዱ ብሉምበርግ ዘገበ።ይህም የአሜሪካ–ኢራን ጦርነትን ለማቆም የሚደረጉ ጥረቶችን ይበልጥ ሊያወሳስብ ይችላል የተባለ አዲስ ጥቃት ነው።የኢራን ባሊስቲክ ሚሳይል ስብርባሪ በአሊ አል ሳሌም የአየር ጦር ሰፈር ላይ የወደቀ ሲሆን በርካታ አሜሪካውያንን ቀላል ጉዳት እንዲደርስባቸው አድርጓል። ጥቃቱ ሁለት ‘ኤምኪው-9 ሪፐር’ የተባሉ ድሮኖች ደግሞ ከባድ ጉዳት እንዳጋጠማቸው ቡሉምበርግ ዘግቧል። የጉዳቱ መጠን እና የተጎዱት ሰዎች ቁጥር ይህ ዘገባ እስከወጣበት ቅፅበት ድረስ አልታወቀም።ቡሉምበርግ እንደገለፀው ጥቃቱ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ የተፈፀመ ነው። የአሜሪካ ማዕከላዊ ኮማንድ (ሴንትኮም) ቅዳሜ ማለዳ በኢሜል አስተያየት እንዲሰጥ ለቀረቡለት ጥያቄዎች መልስ አልሰጠም።አሊ አል ሳሌም የአየር ጦር ሰፈር ከኩዌት ከተማ ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ 64 ኪ.ሜ ገደም ያህል ርቀት ላይ የሚገኝ ነው። የጦር ሰፈሩ በፐርሺያን ገልፍ ውስጥ የአሜሪካ ዋና የአየር እንቅስቃሴ ጣቢያ ሲሆን የአሜሪካ እና የአጋር ኃይሎችን ጦር ያስተናግዳል።በዚህ ሳምንት የአሜሪካ ጦር “የመከላከያ ጥቃት” ሲል የጠራውን ሁለት ዙር ጥቃት በኢራን ላይ ፈፅሟል። ጥቃቱ ባለፈው ሚያዝያ የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት ለማራዘም የሚካሄዱ ውይይቶችን ሊያበላሽግ ይችላል።ሁለቱም ወገኖች ሰፊ የሰላም ውይይት ለማድረግ ፍላጎት ቢያሳዩም፤ የሆርሙዝ ወሽመጥ የቁጥጥር ጉዳይን ጨምሮ በተለያዩ መሰረታዊ ጉዳዮች ግን ልዩነት አላቸው።ኢራን በሰርጡ የሚንቀሳቀሱ የንግድ መርከቦችን በተደጋጋሚ በማጥቃት የዓለም አንድ አምስተኛ የነዳጅ ማስተላለፊያን ዘግታለች።ያጋሩ, ኢራን በኩዌት ጦር ሰፈር ላይ በፈፀመችው የሚሳኤል ጥቃት በርካታ አሜሪካውያን ቆሰሉ
  7. 30 ግንቦት 2026በሊባኖስ በየ24 ሰዓቱ 11 ሕጻናት እንዲሚገደሉ ወይም እንደሚቆስሉ የመንግሥታቱ ድርጅት አስታወቀየሊባኖስ ሕጻናትየፎቶው ባለመብት,Reutersባለፉት ሳምንታት በሊባኖስ በየ24 ሰዓቱ 11 ሕጻናት እንደሚገደሉ ወይም እንደሚቆስሉ የመንግሥታቱ ድርጅት ሕጻናት ኤጀንሲ ዩኒሴፍ አስታወቀ።የመንግሥታቱ ድርጅት እስራኤል በሊባኖስ የምታካሄደውን ጥቃት እያሰፋች ባለችበት ወቅት ባወጣው በዚህ ሪፖርት ባለፉት ሰባት ቀናት ብቻ 77 ሕጻናት መገደላቸውን ይፋ አድርጓል።የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር መረጃን ተጠቅሞ ይፋ ባደረገው በዚህ ሪፖርት በሚያዚያ ወር የተኩስ አቁም ከተደረሰ በኋላ 1,655 ሕጻናት መገደላቸውን እና 212 መጎዳታቸውን ጠቅሷል።እስራአል በደቡባዊ ሊባኖስ የምትፈጽመውን ጥቃት አጠናክራ የቀጠለች ሲሆን ሐሙስ ዕለት በቤይሩት የሚገኝ ሕንጻን ደብድባለች። የዩኒሴፍ ቃል አቀባይ ሪካርዶ ፒርስ ሁሉም ወገኖች የተኩስ አቁሙን እንዲያከብሩ ጠይቀዋል።“በዓለም አቀፍ የሰብዓዊነት ሕግ ሕጻናት እና የሲቪል መሠረተ ልማቶች ጥበቃ ይደረግላቸዋል” ሲሉ አክለዋል።በሊባኖስ እና በእስራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ጦርነቱን ያቆማል ተብሎ ቢጠበቅም እስራኤል ከሄዝቦላህ ጋር የምታደርገውን ውጊያ ግን አጠናክራ ቀጥላለች።የዓለም ጤና ድርጅት አርብ ዕለት እስራኤል ወታደራዊ ዘመቻዋን ስታሰፋ በሊባኖሳውያን ጤና ላይ ከባድ ስጋት ደቅኗል ብሏል።ድርጅቱ አክሎም የተኩስ አቁም ከተደረሰ ጀምሮ በጤና ተቋማት ላይ 27 ጥቃቶች መድረሳቸው የገለጸ ሲሆን ይህም ለ25 ሰዎች ሞት እና ለ42ቱ ጉዳት ምክንያት ሆኗል ሲል ገልጿል።16 ሆስፒታሎች እና 13 የመጀመርያ ደረጃ ጤና ጣቢያዎች መውደማቸውንም ጨምሮ አስታውቋል።ያጋሩ, በሊባኖስ በየ24 ሰዓቱ 11 ሕጻናት እንዲሚገደሉ ወይም እንደሚቆስሉ የመንግሥታቱ ድርጅት አስታወቀ
  8. 30 ግንቦት 2026በእስራኤል እና በሊባኖስ ወታደራዊ ባለሥልጣናት መካከል “ውጤታማ” ውይይት መደረጉን ፔንታጎን አስታወቀየፔንታጎን አዛዥ የሆኑት ኢልብሪጅ ኮልቢየፎቶው ባለመብት,APየምስሉ መግለጫ,የፔንታጎን አዛዥ የሆኑት ኢልብሪጅ ኮልቢየእስራኤል እና የሊባኖስ ወታደራዊ ባለሥልጣናት አርብ ዕለት በዋሺንግተን “ውጤታማ” ውይይት ማድረጋቸውን የአሜሪካ ባለሥልጣናት ተናገሩ።የሁለቱ አገራት ወታደራዊ ባለሥልጣናት ንግግር በቀጣይ የሚደረገውን ዲፕሎማሲያዊ ውይይት የሚያግዝ መሆኑ ተጠቅሷል።የፔንታጎን አዛዥ የሆኑት ኢልብሪጅ ኮልቢ “ዛሬ በፔንታጎን የእስራኤል እና ሊባኖስ ወታደራዊ ልዑካንን በሁለቱ አገራት መካከል እየተካሄደ ያለውን የሰላም ንግግር ለማገዝ ውይይት አካሄደዋል” ሲሉ በኤክስ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።“ውጤታማ የሆነ በሚቀጥለው ሳምነት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሚያደርገው ፖለቲካዊ ንግግር የሚያግዝ ወታደራዊ ውይይት አድርገናል” ብለዋል።በሁለቱ አገራት መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ግን በእስራኤል እና በሊባኖሱ የሺአ ሙስሊም ታጣቂ ቡድን በሆነው ሄዝቦላህ መካከል ያለውን ግጭት ማቆም አልቻለም።እስራኤል በሊባኖስ የምታካሄደውን ወታደራዊ ዘመቻ አጠናክራ ቀጥላለች።ያጋሩ, በእስራኤል እና በሊባኖስ ወታደራዊ ባለሥልጣናት መካከል “ውጤታማ” ውይይት መደረጉን ፔንታጎን አስታወቀ
  9. 30 ግንቦት 2026ፒት ሄግሴት ከኢራን ጋር ስምምነት የማይደረስ ከሆነ አሜሪካ ጥቃቶችን ለመጀመር ዝግጁ መሆኗን ተናገሩየአሜሪካ ጦር ጄትየፎቶው ባለመብት,reutersየአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ቅዳሜ ዕለት ከቴህራን ጋር ስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ አሜሪካ ጥቃቶችን እንደገና ለመጀመር ዝግጁ ነች አሉ።የዋሽንግተን እና የቴህራን ተደራዳሪዎች ያሏቸውን ዋና ዋና ልዩነቶች ለማጥበብ እየሰሩ መሆኑ ተገልጿል።በሲንጋፖር የሚገኙት ሄግሴት “አስፈላጊ ከሆነ [ጥቃቶችን] እንደገና የመጀመር አቅም አለን… ከበቂ በላይ አቅም አለን” ሲሉ ተደምጠዋል።አክለውም “የእኛ የመሣሪያ ክምችት በዚያም ሆነ በዓለም ዙሪያ ለጥቃቶቹ በጣም የተደራጀ ነው፤ ስለዚህ በጣም ጥሩ ይዞታ ላይ ነን” ብለዋል።ሄግሴት በእስያ የመከላከያ ሚኒስትሮች፣ አዛዦች እና ዲፕሎማቶች በተገኙበት የሻንግሪ-ላ ጉባዔ ላይ ንግግር ሲያደርጉ አሜሪካ ከኢራን ጋር ግጭት ውስጥ ብትገባም ለእስያ-ፓስፊክ ቀጣና ጀርባዋን እንዳልሰጠች ተናግረዋል።”በአንድ ጊዜ ሁለት ነገሮችን ማድረግ እንችላለን። የመከላከያ ኢንዱስትሪዎቻችንን በከፍተኛ ሁኔታ እያስታጠቅን ስለሆነ ሁሉም (የዘመቻ) ዕቅዶቻችን በዓለም ዙሪያ በአግባቡ እንደሚሳለጡ ለማረጋገጥ በቅርቡ በሁለት እጥፍ፣ ሦስት እና አራት እጥፍ መሣሪያዎችን እናመርታለን” ብለዋል።የፔንታጎን ኃላፊው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ታጋሽ” እንደሆኑ እና ኢራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ እንዳታገኝ የሚያረጋግጥ “ትልቅ ስምምነት” ማድረግ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል ።አርብ ዕለት ትራምፕ የኢራንን ጦርነት ለማስቆም በሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ የተደረሰው የተኩስ አቁም ለተጨማሪ 60 ቀናት ለማራዘም በሚያስችለው ስምምነት ላይ “የመጨረሻ ውሳኔ” ለመስጠት ተሰብስበው የነበረ ቢሆንም ውጤቱ ግን አልተገለጸም።ያጋሩ, ፒት ሄግሴት ከኢራን ጋር ስምምነት የማይደረስ ከሆነ አሜሪካ ጥቃቶችን ለመጀመር ዝግጁ መሆኗን ተናገሩ
  10. 30 ግንቦት 2026ትራምፕ ከኢራን ጋር ስለተደረሰው ስምምነት ከባለሥልጣኖቻቸው ጋር ቢመክሩም ውሳኔው ሳይገለጽ ቀረየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አርብ ዕለት ከረዳቶቻቸው ጋር ከኢራን ጋር የተኩስ አቁም ለማራዘም ስለተደረሰው ስምምነት ተገናኝተው ቢወያዩም ቀጣዩ እርምጃ ምን መሆን እንዳለበት ግልጽ ሳይሆን መጠናቀቁ ተገለጸ።ፕሬዚዳንቱ ኢራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ወይንም ቦምብ እንደማይኖራት፣ የሆርሙዝ ወሽመጥ ዳግም ሲከፈት “ያልተገደበ የመርከቦች ፍሰት በሁለቱም አቅጣጫ” አንዲኖር መፍቀድ እና ማንኛውም በውሃው ውስጥ የተቀመጠ ፈንጂ “መወገድ” እንዳለበት መስማማት ይኖርባታል ብለዋል።ስብሰባው የተካሄደው በዋይት ሐውስ ውስጥ በሚገኘው እና ትልልቅ ቀውሶች ሲያጋጥሙ በሚሰበሰቡበት ‘ሲችዌሽን ሩም’ ውስጥ እንደነበር ተገልጿል።ኢራን አስቀድማ የኒውክሌር ፕሬግራሟ ሙሉ በሙሉ ለሰለማዊ አገልግሎት እንደሚውል ተናግራለች።ሐሙስ ዕለት ሁለቱ አገራት በመግባበያ ሰነዱ ማዕቀፍ ዙሪያ መስማማታቸው ተገልጾ የትራምፕ እና የኢራን አመራር ይሁንታ እየተጠበቀ መሆኑን የአሜሪካ ባለሥልጣናት ተናግረው ነበር።ስምምነቱ የተኩስ አቁሙን በ60 ቀናት የሚያራዝም እና በኢራን የኒውክሌር ፕሮግራም ዙሪያ ወደፊት ለመነጋገር የሚል እንደበር ተገልጿል።የዋይት ሐውስ ባለሥልጣናት በአሜሪካ ለቢቢሲ አጋር ሲቢኤስ ነውስ “ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለአሜሪካ ጥሩ የሆነ እና ቀይ መስመሩን የማያልፍ ስምምነት ይፈጽማሉ። ኢራን የኒውኬሌር ጦር መሣሪያ በጭራሽ ሊኖራት አይችልም” ሲሉ ተናግረዋል።በሚያዚያ ወር መጀመርያ ላይ የተኩስ አቁሙ በሁለቱ አገራት መካከከል ተግባራዊ ከሆነ ጀምሮ ትራምፕ በተደጋጋሚ ከኢራን ጋር ከስምምነት ለመድረስ መቃረባቸውን የተናገሩ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ግን ተጨባጭ ውጤት አልታየም።አርብ ዕለት ትራምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የጣሉትን እገዳ ለማንሳት እና በወሽመጡ ውስጥ መንቀሳቀሻ አጥተው የቆሙ መርከቦች “ወደ ቤታቸው ማምራት’ እንዲጀምሩ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረው ነበር።አከለውም አሜሪካ የኢራንን የተብላላ ዩራኒየም እንድታስወግድ እና እንድታወድም እንድትፈቅድ ጠይቀዋል።“እምብዛም አስፈላጊ ያልሆኑ ሌሎች ጉዳዮች ላይ ተስማምተናል” በማለት “ቀጣዩ እርምጃ እስኪታወቅ ድረስ ምንም ስምምነት አይኖርም” ሲሉ አክለዋል።በኋላ ላይ ዋይት ሀውስ ለቢቢሲ በሲችዌሽን ሩም ሲካሄድ የነበረው ስብሰባ መጠናቀቁን አረጋግጧል።ባለሥልጣናት በስብሰባው ላይ ስለተነሱት ጉዳዮች ተጨማሪ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።የኢራን ፋርስ ዜና ወኪል የትራምፕ አስተያየት “የሐሰት እና እውነት ቅይጥ ነው” ሲለ አስተያየት ሰጥቷል።የዜና ወኪሉ በመግባቢያ ስምምነቱ ላይ የኒውክሌር መሣሪያዎችን ስለማውደም የቀረበ ምንም ነገር የለም ብሏል።የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኤል ባጋይ ለአገር ውስጥ ቴሌቪዥን “ጦርነቱን በማስቆም ላይ ያተኮረ ውይይት ተደርጓል፤ በኒውክሌር ጉዳይ ምንም ድርድር የለም” ሲሉ ተናግረዋል።ያጋሩ, ትራምፕ ከኢራን ጋር ስለተደረሰው ስምምነት ከባለሥልጣኖቻቸው ጋር ቢመክሩም ውሳኔው ሳይገለጽ ቀረ
  11. 29 ግንቦት 2026“ከስምምነት የተደረሰው በድርድር ሳይሆን በሚሳዔሎቼ ነው” ኢራንሞሐመድ ባጊር ጋሊባፍየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ሞሐመድ ባጊር ጋሊባፍአሜሪካ እና ኢራን ለሳምንታት ሲያካሂዱት የነበረው ድርድር ወደ ስምምነት መቃረቡ እየተነገረ ባለበት በአሁኑ ሰዓት “ኢራን ፍላጎቷ ተቀባይነት ያገኘው በንግግር ሳይሆን በሚሳዔሎቿ ነው” ሲሉ ከፍተኛ ባለሥልጣኗ ተናገሩ።በኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ውስጥ ከፍተኛ ተደማጭነት ያላቸው የአገሪቱ ፓርላማ አፈ ጉባዔ እና ከአሜሪካ ጋር በሚደረገው ንግግር ዋነኛ ተደራዳሪ የሆኑት ሞሐመድ ባጊር ጋሊባፍ በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ የኢራን ወታደራዊ አቅም ተጽእኖ ፈጥሯል ብለዋል።ጋሊባፍ ከአሜሪካ ጋር እየተካሄደ ስላለው ድርድር ሦስት ነጥቦችን አስቀምጠዋል። የመጀመሪያው “ስምምነት ላይ የተደረሰው በንግግር ሳይሆን በሚሳዔሎቻችን ነው። በድርድሮቹ ላይ ያደረግነው ይህንን ማስረዳት ነው” ብለዋል።ሁለተኛው ነጥባቸው ደግሞ በድርድሩ ላይ በሁለቱ ወገኖች መካከል ስላለው አለመተማመን በማንሳት “ዋስትና እና ቃላትን አናምንም፤ ብቸኛው መመዘኛ ተግባር ነው። ሌላኛው ወገን የሚጠበቅበትን ሳያደርግ ምንም ዓይነት እርምጃ አይወሰድም” ሲሉ ቀዳሚው እርምጃ ከአሜሪካ በኩል መሆን እንዳለበት አመልክተዋል።የኢራኑ ከፍተኛ ባለሥልጣን በቁጥር ሦስት ላይ ያስቀመጡት ሃሳብ “የየትኛውም ስምምነት አሸናፊው በቀጣይ ለሚመጣው ጦርነት በተሻለ ሁኔታ የተዘጋጀ ነው” የሚል ሲሆን ከስምምነቱ በኋላ ኢራን ለየትኛውም ዓይነት ጥቃት ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።የካቲት ወር መጨረሻ ላይ ተጀምሮ አራት ወራትን ባስቆጠረው ጦርነት አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ከባድ ጉዳትን ቢያደርሱም፤ ኢራንም በበኩሏ በእስራኤል እና በዙሪያዋ ባሉ እና የአሜሪካንን ጦር ባስጠለሉ የባሕረ ሰላጤው አገራት ላይ ቀላል የማይባል ጉዳትን አድርሳለች።በተጨማሪም ለዓለም የነዳጅ እና የጋዝ ምርት ዝውውር ወሳኝ የሆነውን የሆርሙዝ ወሽመጥን በመዝጋት በመላው ዓለም ላይ ከፍተኛ ተጽእኖን አሳድራለች።ያጋሩ, “ከስምምነት የተደረሰው በድርድር ሳይሆን በሚሳዔሎቼ ነው” ኢራን
  12. 29 ግንቦት 2026አሜሪካ ከሮማኒያ ጎን እንደምትቆም እና የኔቶ አባላትን እንደምትከላከል ገለጸችአምባሳደር ማት ዊታከርየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,አምባሳደር ማት ዊታከርበሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) የአሜሪካ አምባሳደር ማት ዊታከር ዋሽንግተን የኔቶ አጋር ከሆነችው ሮማኒያ ጎን እንደምትቆም ገለጹ።አምባሳደር ዊታከር በሮማኒያ ግዛት የተፈፀመውን እና “ግድየለሽ” ያሉትን ጥቃት አውግዘዋል።“ሃሳባችን በጋላቲው ጥቃት ከተጎዱት ጋር ነው። የኔቶ አባል አገራት ግዛትን እያንዳንዱን ስንዝር እንከላከላለን” ሲሉ አምባሳደሩ አክለዋል።የትራምፕ አስተዳደር በዩክሬን እየተካሄደ ስላለው ጦርነት እንዲሁም በጎረቤቶቿ ላይ ስለሚፈፀመው ሰፊ የሉዓላዊነት ጥሰት ያለው አቋም ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን አስተዳደር የተለየ ነው።ከባይደን በተለየ ትራምፕ ለቭላድሚር ፑቲን ቅርብ ናቸው። በአውሮፓውያኑ በ2023 ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በፑቲን ላይ የእስር ማዘዣ ቢያወጣም ትራምፕ በአሜሪካ ግዛት ፑቲንን ተቀብለው አስተናግደዋል።በዚህ ወር መጀመሪያ ላይም ዩክሬን እና ሩሲያ ሶቭየት ኅብረት ናዚ ጀርመንን ያሸነፈችበትን የድል ቀን ለማክበር በሚል በየራሳቸው ያደረጉትን የተናጠል ተኩስ አቁም በመጣስ እርስ በእርሳቸው ከተካሰሱ በኋላ ትራምፕ አገራቱ የሦስት ቀን የተኩስ አቁም እንደሚያደርጉ አስታውቀው ነበር።ያጋሩ, አሜሪካ ከሮማኒያ ጎን እንደምትቆም እና የኔቶ አባላትን እንደምትከላከል ገለጸች
  13. 29 ግንቦት 2026ፑቲን በሮማኒያ ስለተከሰከሰው ድሮን ‘እንደሚያውቁ’ ክሬሚሊን አስታወቀጥቃት ከተፈጸመበት ሕንጻ እና ፖሊሶችየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,ጥቃት የተፈጸመበት የሕንጻ ክፍልበሮማኒያ ስለተከሰከሰው ድሮን ቭላድሚር ፑቲን እንደሚያውቁ የሩሲያ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን የፕሬዚደንቱን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭን ጠቅሶ ዘገበ።ታስ በዘገባው ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።በሮማኒያ ምሥራቃዊ ከተማ ጋላቲ ትናንት አንድ ድሮን በመኖሪያ ሕንፃ ላይ ተከስክሶ በሕንፃው ላይ እሳት መነሳቱ እና በአደጋው ሁለት ሰዎች መቁሰላቸው ተገልጿል።የሮማኒያ ፕሬዚደንት ኒኩሰር ዳን በዩክሬን እና ሞልዶቫ ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው ጋላቲ ለተከሰከሰው ድሮን ሩሲያን ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ አድርገዋል።”ኃላፊነት የጎደለው” ሲሉም ክስተቱን አውግዘዋል።ፕሬዚደንት ዳን አስተዳደራቸው በደቡብ ምሥራቅ ከተማ ኮንስታንታ የሚገኘውን የሩሲያ ቆንስል እደሚያባርር እና ቆንስላውንም እንደሚዘጋ መናገራቸውን የአገሪቷ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።ኤኤፍፒ የዜና ወኪል ቆንስላው ምንም ማብራሪ እንዲሰጥ ሳይጠየቅ ከሥራ መታገዱን ዘግቧል።የአውሮፓ ኅብረት እና ኔቶን ጨምሮ አገራት ክስተቱን አውግዘዋል።የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛኻሮቫ በበኩላቸው በሮማኒያ ከድሮኑ ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን ጡዘት ምዕራባውያኑ ባለፈው ሳምንት በስታሮቢልስክ የተፈፀመውን ጥቃት አቅጣጫ ለማስቀየር እየተጠቀሙበት ነው ብለዋል።የሩሲያ ባለሥልናት እንዳሉት ዩክሬን ሩሲያ በምትቆጣጠረው ምሥራቃዊ ዩክሬን ስታሮቢልስክ የተማሪዎች ማደሪያ ላይ በፈፀመችው ሦስት ተከታታይ የድሮን ጥቃቶች 21 ተማሪዎች ተገድለዋል።ዩክሬን ግን ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ አላደረኩም ብላለች።ያጋሩ, ፑቲን በሮማኒያ ስለተከሰከሰው ድሮን ‘እንደሚያውቁ’ ክሬሚሊን አስታወቀ
  14. 29 ግንቦት 202616 ተማሪዎች በሞቱበት በኬንያው የትምህርት ቤት የእሳት አደጋ 8 ተማሪዎች ተጠርጥረው ተያዙፖሊስ እና የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች አስከሬኖችን ሲያወጡየምስሉ መግለጫ,ፖሊስ እና የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች አስከሬኖችን ሲያወጡበሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ 16 ተማሪዎች ከሞቱ በኋላ የኬንያ ባለሥልጣናት ስምንት ተማሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አስታወቁ።መርማሪዎች እንዳሉት ስምምንቱ ተማሪዎች የተያዙት የአደጋውን ምክንያት ለማወቅ በተደረገው ምርመራ የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት እሳቱ ሆን ተብሎ መከሰቱን የሚያመለክቱ ጥርጣሬዎች በመገኘታቸው ነው።ረቡዕ ለሐሙስ አጥቢያ ከዕኩለ ሌሊት በኋላ በትምህርት ቤቱ የተማሪዎች ማደሪያ ሕንጻ በተነሳው እሳት 16 ተማሪዎች ሲሞቱ ከ70 በላይ የሚሆኑደግሞ ቆስለዋል።ፖሊስ እንዳስታወቀው ተጠርጣሪ ተማሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ወደ ቤታቸው ከሄዱ በኋላ ክትትል ተደርጎባቸው ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ በትምህርት ቤቱ አካባቢ ተደብቀው ነው።አሰቃቂ ጉዳት ካደረሰው የእሳት አደጋ ጋር በተያያዘ አሁን በፖሊስ እጅ የሚገኙት ስምንት ተማሪዎች በቀዳሚነት ከተያዙት 13 ተማሪዎች መካከል የተለዩ ናቸው።መርማሪዎች ከአንድ መቶ በላይ ተማሪዎች በሚኖሩበት ሕንጻ ላይ የተከሰተው የእሳት አደጋ ሆን ተብሎ የተነሳ ነው በሚል ጥርጣሬ ላይ ምርመራቸውን አተኩረዋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ በአደጋው የሞቱ ተማሪዎችን የመለየቱ ሂደት በመዘግየቱ ቤተሰቦች በከባድ ሐዘን ላይ ሲሆኑ፣ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች ሕክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ቦርድ የተማሪዎች ደኅንነትን የሚያስጠብቁ ደንቦችን ባለማስከበሩ እንዲበተን ሲደረግ፤ የትምህርት ቤቱ ዳይሬከተር ላይ የዲሲፕሊን ምርመራ እየተደረገባቸው ነው።ያጋሩ, 16 ተማሪዎች በሞቱበት በኬንያው የትምህርት ቤት የእሳት አደጋ 8 ተማሪዎች ተጠርጥረው ተያዙ
  15. 29 ግንቦት 2026እስራኤል ጋዛ ውስጥ የሐማስ ወታደራዊ አዛዥን መግደሏን አስታወቀችየሐማስ ተዋጊዎችየፎቶው ባለመብት,EPA-EFE/REX/Shutterstockየእስራኤል ጦር ሠራዊት ሰሜናዊ ጋዛ ሰርጥ ውስጥ በፈጸመው ጥቃት ኢማድ ሐሳን ሁሴን አስሊም የተባለውን የሐማስ ተዋጊዎች አዛዥ መግደሉን አስታወቀ።ሠራዊቱ በኤክስ ላይ ባወጣው መረጃ የእስራኤል የአገር ውስጥ ደኅንነት መሥሪያ ቤት ከሆነው ሽን ቤት ጋር በመሆን ረቡዕ ዕለት በፈጸመው ጥቃት አስሊም “መደምሰሱን” አስታውቋል።ጨምሮም ኢማድ ሐሳን ሁሴን አስሊም ዘይቱን የተባለው የሐማስ ባታሊዮን አዛዥ እና የጋዛ ከተማ ብርጌድ የተባለው ኃይል ምክትል አዛዥ መሆኑን ጦሩ ገልጿል።አዛዡ በጋዛ ውስጥ በእስራኤል ወታዳሮች ላይ የተፈጸሙ “በርካታ የሽብር ጥቃቶችን የመራ” እና “ተጨባጭ ስጋት የደቀነ ነው” በማለት ከስሶታል።የኢማድ ሐሳን ሁሴን አስሊም መገደልን በተመለከተ የእስራኤል ሠራዊት ያወጣውን መግለጫ በተመለከተ ከሐማስ በኩል አስካሁን የተሰጠ ማረጋገጫም ሆነ ማስተባበያ የለም።ነገር ግን የአዛዡ መገደል ከተረጋገጠ አስሊም ባለፉት ሁለት ሳምንታት የተገደለ ሦስተኛው የሐማስ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር ይሆናል።በዚህ ሳምንት ሞሐመድ ኦዴህ የተባለው ሌላኛው የቡድኑ ከፍተኛ አመራር በእስራኤል በተፈጸመ ጥቃት ከሚስቱ እና ከሁለት ልጆቹ ጋር ተገድሏል።በተጨማሪም ኢዝ አልዲን አል ሃዳድ የተባለው የፍልስጤማዊው ቡድን ወታደራዊ ክንፍ የሆነው ቃሳም ብርጌድ ዋና አዛዥ ከሳምንታት በፊት በተፈጸመ ጥቃት ተገድሏል።ያጋሩ, እስራኤል ጋዛ ውስጥ የሐማስ ወታደራዊ አዛዥን መግደሏን አስታወቀች
  16. 29 ግንቦት 2026የቀድሞው የሲአይኤ ባለሥልጣን በቤታቸው 40 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ የወርቅ ጥፍጥፎች ተገኙባቸውየወርቅ ጥፍጥፎችየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesአንድ የአሜሪካ የስለላ ድርጅት (ሲአይኤ) የቀድሞ ባለሥልጣን ቤታቸው ሲፈተሽ 40 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ የወርቅ ጥፍጥፎች ተገኝተው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።የኤፍቢአይ መርማሪዎች ግለሰቡን የያዙት ስለትምህርት እና ወታደራዊ ታሪካቸው ዋሽተው እንደሆነ ማጣራት በሚያደርጉበት ጊዜ የወርቅ ጥፍጥፎችን ካገኙ በኋላ ነው።የፍርድ ቤት ሰነዶች እና ጉዳዩን የሚያውቁ ምንጮች እንዳሉት የቀድሞው የሲአይኤ ባለሥልጣን ዴቪድ ረሽ በአሁኑ ጊዜ በእስር ላይ ይገኛሉ።ሲቢኤስ ቴሌቪዥን እንደዘገበው ግለሰቡ የሕዝብ ንብረት በመስረቅ ወንጀል ተጠርጥረው ክስ ተመስርቶባቸዋል።ኤፍቢአይ በግለሰቡ ላይ የወርቅ ጥፍጥፎችን በሕገወጥ መንገድ በመያዝ፣ ከሚገባቸው በላይ ደሞዝ በመውሰድ፣ በተጭበረበረ ሁኔታ ወታደራዊ የእረፍት ፈቃድ በመውሰድ እና በርካታ ሐሰተኛ ቃል በመስጠት ከስሷቸዋል።ዴቪድ ረሽ በዚህ ዓመት ከኅዳር አስከ መጋቢት ወር ድረስ ባለው ጊዜ ከመንግሥት ከፍተኛ መጠን ያለው የውጭ ምንዛሪ እና በአስር ሚሊሊዮኖች ዶላር የሚያወጡ የወርቅ ጥፍጥፎችን ከሥራ ጋር ለተያያዙ ወጪዎች ጠይቀዋል በሚልም ተከስሰዋል።ያጋሩ, የቀድሞው የሲአይኤ ባለሥልጣን በቤታቸው 40 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ የወርቅ ጥፍጥፎች ተገኙባቸው
  17. 29 ግንቦት 2026በሮማኒያ መኖሪያ ሕንጻ በድሮን መመታቱን ተከትሎ ኔቶ ሩሲያን ኮነነመኖሪያ ሕንጻየፎቶው ባለመብት,DSU via Reutersበሮማኒያ የጋራ መኖሪያ ሕንጻ በሩሲያ ድሮን መመታቱን ተከትሎ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን (ኔቶ) እና የአውሮፓ ኅብረት ባለሥልጣናት ሩሲያን አወገዙ።የሩሲያው ድሮን መኖሪያ ሕንጻውን ከመታ በኋላ እሳት እንደተነሳ እና ሁለት ሰዎች እንደቆሰሉ ተገልጿል።በዩክሬን እና ሞልዶቪያ ድንበር አቅራቢያ ባለው የሮማኒያ ምሥራቃዊ ከተማ ጋላቲ ክስተቱ ከተፈጠረ በኋላ የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አርስላ ቮን ደር ሌይን “የሩሲያ የጦርነት ግብዝነት አሁንም መስመሩን አልፏል” ብለዋል።ኔቶ ሩሲያን “ግድ የለሽ” ሲል አውግዟል።በአራት ዓመታት የዩክሬን ጦርነት ውስጥ የሩሲያ ድሮን በሮማኒያ ድንበር አቅራቢያ ቢታይም፤ የኔቶ አባል አገር ዜጎች ላይ ጉዳት ሲደርስ ግን የመጀመሪያው ነው።ስለ ክስተቱ ሩሲያ እስካሁን ምንም አስተያየት አልሰጠችም።የሮማኒያ የአደጋ መከላከል ተቋም እንዳለው በመኖሪያ ሕንጻው 10ኛ ፎቅ ላይ እሳት ተነስቷል። 70 ሰዎች ከሕንጻው እንዲወጡ ሲደረጉ፤ የተጎዱት ሁለት ሰዎች ሕክምና አግኝተዋል።ፕሬዝዳንት ኒኩሶር ዳን ከአገሪቱ ከፍተኛ መከላከያ ምክር ቤት ጋር አስቸኳይ ውይይት አድርገዋል።“የሩሲያ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ በሮማኒያ የደረሰ የከፋ ጉዳት ነው” ብለዋል።ያጋሩ, በሮማኒያ መኖሪያ ሕንጻ በድሮን መመታቱን ተከትሎ ኔቶ ሩሲያን ኮነነ
  18. 29 ግንቦት 2026አሜሪካ እና ኢራን ለስምምነት ቢቃረቡም የማያግባቧቸውን ጉዳዮች መፍታት እንዳለባቸው ተገለጸጄዲ ቫንስየፎቶው ባለመብት,Reutersአሜሪካ እና ኢራን ስምምነት ላይ ከመድረሳቸው በፊት በርካታ የማያግባቧቸውን ጉዳዮች መፍታት እንዳለባቸው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ተናገሩ።ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስምምነት ለመፈረም ተቃርበው እንደሆነ ከቢቢሲ የተጠየቁት ጄዲ ቫንስ፤ አሁን ላይ መናገር እንደማይቻል ገልጸዋል።ሁለቱ አገራት ስምምነት ላይ ከደረሱ የተኩስ አቁሙ በ60 ቀናት ይራዘማል። ስለ ኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብርም ንግግር ይጀመራል።ኢራን እና አሜሪካ የስምምነት ማዕቀፍ ላይ ከስምምነት መድረሳቸውን የዋሽንግንተን ባለሥልጣናት ትናንት ሐሙስ ለቢቢሲ መግለጻቸው ይታወሳል።ሆኖም የኢራኑ ታስኒም የዜና ወኪል ስምምነቱ እንዳልተጠናቀቀ እና እንዳልተረጋገጠ ገልጿል።የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ “ዩራኒየም የማበልጸግ ጉዳይን ጨምሮ በአንዳንድ ነጥቦች ዙርያ” ድርድሮች እየተካሄዱ መሆኑን ተናግረዋል።ስምምነት ላይ ተደርሶ እንደሆነ ተጠይቀውም “እዚያ ነጥብ ላይ አልደረስንም፤ ግን ተቃርበናል። አሁንም ሥራችንን እንቀጥላለን” ብለው መልሰዋል።ኢራን ዩራኒየም ማበልጸግ እንድታቆም እና እስካሁን ያከማቸችውን እንድታስወግድም አሜሪካ ጠይቃለች።ሁለቱ አገራት የተኩስ አቁም ካደረጉ ወዲህ ውይይታቸው በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ እንደሆነ ትራምፕ ሲናገሩ ተደምጧል።ያጋሩ, አሜሪካ እና ኢራን ለስምምነት ቢቃረቡም የማያግባቧቸውን ጉዳዮች መፍታት እንዳለባቸው ተገለጸ
  19. 28 ግንቦት 2026ኦማን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የሚጣለውን ቀረጥ በማመቻቸት እንዳትሳተፍ አሜሪካ አስጠነቀቀችየጭነት መርከብየፎቶው ባለመብት,Reutersኦማን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የሚጣል ቀረጥን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በማመቻቸት እንዳትሳተፍ አሜሪካ አስጠነቀቀች።አሜሪካ አክላም ማንኛውም አካል በዚህ ተሳትፎ የሚገኝ ከሆነ ቅጣት እንደሚጠብቀው ተናግራለች።የግምጃቤት ኃላፊው ስኮት ቤሴንት በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ “የዩናይትድ ስቴትስ በሆርሙዝ የባህር ወሽመት ላይ የክፍያ ስርዓትን ለመጫን የሚደረግ ማንኛውንም ጥረት አትታገስም”ብለዋል።”ኦማን በተለይ የአሜሪካ ግምጃ ቤት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለወሽመጡ የሚከፈል ክፍያን በማመቻቸት ላይ የተሳተፉ ወይንም ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆኑ አጋሮችን ዒላማ በማድረግ እንደሚቀጣ ማወቅ አለባት” ሲሉ ቤሴንትአስጠንቅቀዋል።ያጋሩ, ኦማን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የሚጣለውን ቀረጥ በማመቻቸት እንዳትሳተፍ አሜሪካ አስጠነቀቀች
  20. 28 ግንቦት 2026አሜሪካ የኢራን አየር መንገዶች የሌሎች አገራት አውሮፕላን ማረፊያዎች እና አገልግሎቶች እንዳይጠቀሙ ልታደርግ ነውየአሜሪካ ግምጃ ቤት ኃላፊ ስኮት ቤሴንትየፎቶው ባለመብት,Reutersአሜሪካ የኢራን አየር መንገዶች የሌሎች አገራት አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎቶችን እንዳይጠቀሙ፣ ነዳጅ እንዳይሞሉ እና የቲኬት ሽያጫቸውን ልትገድብ መሆኑን የግምጃ ቤት ኃላፊው አስታወቁ።ስኮት ቤሴንት በኤክስ ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት እርምጃው በኢራን ላይ የተጀመረው የኢኮኖሚ ማዕቀብ ዘመቻ አካል መሆኑን በመጥቀስ የቴህራን አየር መንገዶች ላይ ማዕቀቡን ለመጣል መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።አሜሪካ የኢራን አየር መንገዶች ዓለም አቀፍ በረራ በሚያደርጉበት ወቅት የሌሎች አገራት አውሮፕላን ማረፊያዎችን እና አገልግሎቶችን እንዳይጠቀሙ በማድረግ ምታኔ ሃብታዊ ጫናዋን ልታጠናክር መሆኑን አስታውቃለች።የአሜሪካ ግምጃ ቤት ኃላፊ ስኮት ቤሴንት አክለውም የአሜሪካ ባሕር ኃይል በኢራን ወደቦች ላይ የጣለው እገዳ ለገበያ የሚቀርበው “የኢራን ድፍድፍ ነዳጅ መጠን እንዲቀንስ” በዚህም የተነሳ “የአገሪቱ ምጣኔ ኃብት እና መገበያያ ገንዘብ እንዲዳከም” ማድረጉን ገልጸዋል።ወታደሮቻቸው እየተከፈላቸው አይደለም፣ የፖሊስ አባላትም በሥራ ገበታቸው ላይ አይገኙም እንዲሁም ኻርግ ደሴት እንደተዘጋ ነው ያሉት ቤሴንት “ከድርድሩ የሚገኝ አጥጋቢ ምላሽ ብቻ ይህንን የቁልቁለት ጉዞ ያስቆመዋል” ሲሉ አስጠንቀቅቀዋል።ያጋሩ, አሜሪካ የኢራን አየር መንገዶች የሌሎች አገራት አውሮፕላን ማረፊያዎች እና አገልግሎቶች እንዳይጠቀሙ ልታደርግ ነው