ከአሜሪካ ጋር በተደረሰው ስምምነት ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚያልፉ መርከቦችን ምንም ዓይነት ክፍያ መጠየቅ እንደማትችል እና ይህንን የምታደርግ ከሆነ ከዓለም አቀፍ ሕግ ጋር የሚቃረን ነው ሲሉ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 1 ሰአት በፊትኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦችን ማስከፈል አትችልም ስትል አሜሪካ አስጠነቀቀችመርከብየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesከአሜሪካ ጋር በተደረሰው ስምምነት ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚያልፉ መርከቦችን ምንም ዓይነት ክፍያ መጠየቅ እንደማትችል እና ይህንን የምታደርግ ከሆነ ከዓለም አቀፍ ሕግ ጋር የሚቃረን ነው ሲሉ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ።ማርኮ ሩቢዮ ይህንን ያሉት ኢራን እና ኦማን በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ስለሚደረጉ የባሕር ላይ ጉዞዎች እና ከሚሰጠው አገለግሎት ጋር ያሉ ወጪዎችን በተመለከተ ውይይት ማድረቸጋውን ተከትሎ ነው።ሁለቱ አገራት ኦማን ውስጥ ካደረጉት ውይይት በኋላ ባወጡት የጋራ መግለጫ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮቻቸው አማካኝነት የጋራ ግብረ ኃይል በመመሥረት ከተጎራባች አገራት እና ከሚመለከታቸው ወገኖች ጋር ምክክር እንደሚያካሂዱ ገልጸዋል።ኢራን እና ኦማን ከአሜሪካ ጋር በተደረሰው ስምምነት ትግበራ ላይ ለመመካከር ባደረጉት ውይይት አገራቱ በወሳኙ የባሕር መተለላፊያ ላይ ያላቸው ሉዓላዊነት ተከብሮ በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚያልፉ መርከቦችን ደኅንነት ለማረጋገጥ ያላቸውን ቁርጠኝነት ለመግለጽ የታለመ ነው።አሜሪካ እና አስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት ከከፈቱበት ከየካቲት ወር መጨረሻ አንስቶ እስካለፈው ሳምንት ድረስ የሆርሙዝ ወሽመጥ በኢራን ዝግ ተደርጎ የቆየ ሲሆን፣ አሜሪካ ደግሞ በኢራን ላይ የባሕር ላይ እገዳ ጥላ ቆይታለች።ያጋሩ, ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦችን ማስከፈል አትችልም ስትል አሜሪካ አስጠነቀቀች
  2. ከ 4 ሰአት በፊትኢራን እና ኦማን የሆርሙዝ ወሽመጥ አስተዳደር እና ክፍያን በጋራ እንደሚወስኑ አስታወቁየሆርሙዝ ወሽመጥየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesኢራን እና ኦማን በጋራ ባወጡት መግለጫ የሆርሙዝ ወሽመጥ የሚገኝበት ወሳኝ የባሕር መተላለፊያ ላይ ሉዓላዊ መብት እንዳላቸው ተናገሩ።በመግለጫው የሆርሙዝ ወሽመጥ ደኅንነቱ ተጠብቆ ዓለም አቀፍ የመርከቦች መተለላፊያ ሆኖ እንዲቀጥል በጋራ ለመሥራት ቁርጠኛ እንደሆኑም አስታውቀዋል።በቀጣይ የሆርሙዝ ወሽመጥ አስተዳደርን እና መርከቦች ለመተላለፊ የሚፈጽሙትን ክፍያ ጉዳይ በጥምር ኮሚቴ አማካኝነት እንደሚመለከቱም ገልጸዋል።የሁለቱ አገራት መሪዎች በኦማን ዋና ከተማ ሙስካት ከተወያዩ በኋላ ነው መግለጫውን ያወጡት።በስዊትዘርላንድ የነበሩት የኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣናት፤ የእስላማዊ ሪፐብሊክ የፓርላማ አፈ ጉባዔ መሐመድ ባጋር ጋሊባፍ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አባስ አራግቺ ወደ ኦማን አቅንተው ከንጉሥ ሐቲሀም ቢን ታሪቂ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር ቡሳዲ ጋር ተወያይተዋል።ያጋሩ, ኢራን እና ኦማን የሆርሙዝ ወሽመጥ አስተዳደር እና ክፍያን በጋራ እንደሚወስኑ አስታወቁ
  3. ከ 4 ሰአት በፊትእስራኤል የኢንተርኔት መገናኛዎችን በድብቅ ወደ ኢራን ማስገባቷን የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር ተናገሩየቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔትየምስሉ መግለጫ,የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔትሕዝባዊ ተቃውሞ ሲቀሰቀስ መንግሥት የኢንተርኔት አገልግሎት በሚያቋርጥበት ጊዜ የሚሠሩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የኢንተርኔት መገናኛ መሳሪያዎችን ከዓመታት በፊት እስራኤል ወደ ኢራን አስርጋ ለማስገባት መሥራቷን የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ።የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት በሥልጣን ላይ ሳሉ ኢራናውያን ተቃዋሚዎች ኢንተርኔት በሚቋረጥ ጊዜ ግንኙነታቸውን ለማስቀጠል የሚያስችሉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የስታርሊንክ የኢንተርኔት መቀበያዎችን በድብቅ ወደ ኢራን ለማስገባት ያለመ ዕቅድ መጀመራቸውን ተናግረዋል።ቤኔት ኢየሩሳሌም ውስጥ በተካሄደ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር እንዳሉት፤ ዓላማቸው የተቃዋሚዎችን ግንኙነት እና እንቅስቃሴ ማቀናጀት በማስቻል የኢራንን መንግሥት ከሥልጣን እንዲወገድ ማድረግ ነበር።”በሚያሳዝን ሁኔታ አሁን ያለው [የኔታኒያሁ] መንግሥት እየተካሄደ የነበረውን ፕሮግራም በማስቆሙ ኢራን ውስጥ ተቃውሞው ሲቀሰቀስ አስፈላጊው የግንኙነት መሳሪያ በቦታው አልነበረም” ሲሉ ቁጭታቸውን ገልጸዋል።የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ጽህፈት ቤት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት ለሰነዘሩት አስተያየት እስካሁን ምላሽ አልሰጠም።እንዲሁም የስታርሊንክ ኢንተርኔት መገናኛ አቅራቢ ድርጅት የሆነው ስፔስኤክስም በጉዳዩ ላይ ያለው ነገር የለም።ናፍታሊ ቤኔት ከእስራኤል ተቃዋሚዎች መካከል ተጠቃሹ ሲሆኑ በመጪው ምርጫ ዋነኛው ዕጩ ሊሆኑ ይችላሉ እየተባለ ነው። ወደ ሥልጣን የሚመለሱ ከሆነ የኢራንን መንግሥት ለማዳከም እንደሚሠሩም ተናግረዋል።ለዚህም በኢራን ላይ የሚወሰደው እርምጃ ከቅጥተኛ ወታደራዊ ጥቃት ባሻገር “የኢኮኖሚ እና የኢንዱስትሪ አሻጥሮችንም” እንደሚያካትቱ ገልጸዋል።ናፍታሊ ቤኔት ከአራት ዓመት በፊት ለአንድ ዓመት ያህል ቤንያሚን ኔታኒያሁን ለአጭር ጊዜ ከሥልጣን ያስወገደውን የቀኝ እና የግራ ክንፍ እንዲሁም የመሃል ፓርቲዎች ጥምር መንግሥትን በጠቅላይ ሚኒስትርነት መርተዋል።ቤኔት ጠቅላይ ሚኒስትር ከመሆናቸው በፊት የኔታኒያሁ አማካሪ ሆነው ሠርተዋል።ያጋሩ, እስራኤል የኢንተርኔት መገናኛዎችን በድብቅ ወደ ኢራን ማስገባቷን የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር ተናገሩ
  4. ከ 5 ሰአት በፊትኢራን የኒውክሌር ቁጥጥር እንዲደረግ ባትስማማ ኖሮ ድርድር ሳይካሄድ ይቀር እንደነበር ትራምፕ ገለጹፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ኢራን ሙሉ በሙሉ እና ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የኒውክሌር ቁጥጥር እንዲደረግ ፈቅዳለች” አሉ።ኢራን ዓለም አቀፍ የኒውክሌር ተቆጣጣሪዎች ወደ አገሪቱ እንዲገቡ ልትፈቅድ ነው መባሉን ብታስተባብልም፤ ትራምፕ “ለከፍተኛ ደረጃ የኒውክሌር ቁጥጥር ተስማምታለች” ብለዋል።ይህ የኢራን ስምምነት “ለረዥም ጊዜ እና እስከ ወዲያኛው” እንደሚዘልቅ ጠቅሰው “የኒውክሌር ታማኝነትን የሚያረጋግጥ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።“ኢራን ለዚህ ባትስማማ ኖሮ ተጨማሪ ድርድሮች አይኖሩም ነበር” በማለት አክለዋል።የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢስማኤል ባጋይ ከሰዓታት በፊት ዓለም አቀፍ የኒውክሌር ተቆጣጣሪዎች ወደ አገሪቱ እንዲገቡ እና የደረሰውን ጉዳት እንዲመለከቱ አለመፈቀዱን ገልጸዋል።የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ኢራን ለኒውክሌር ተቆጣጣሪዎች ፈቃድ መስጠቷን ተናግረዋል።ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ “በዚህ እና በሌሎችም ኢራን ባቀረበቻቸው ስምምነቶች መነሻነት ነው የሆርሙዝ ወሽመጥ ተከፍቶ እንዲቀጥል እንዲሁም በባሕር መተላለፊያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ እንዳይጣል የተስማማሁት” ብለዋል።ያጋሩ, ኢራን የኒውክሌር ቁጥጥር እንዲደረግ ባትስማማ ኖሮ ድርድር ሳይካሄድ ይቀር እንደነበር ትራምፕ ገለጹ
  5. ከ 6 ሰአት በፊትየኬንያው የጤና ሚኒስትር የኢቦላ ለይቶ ማቆያ ማዕከል ግንባታ እንዲቆም ወሰኑየኢቦላ ምርመራየፎቶው ባለመብት,EPAየኬንያ የጤና ሚኒስትር ኤደን ዱአሌ በአሜሪካ የሚደገፈው አወዛጋቢው የኢቦላ ለይቶ ማቆያ ማዕከል ግንባታ እንዲቋረጥ ውሳኔ አሳለፉ።ሚኒስትሩ ውሳኔውን ከማሳወቃቸው ከአንድ ቀን በፊት ፍርድ ቤትን በመድፈር ጥፋተኛ መባላቸው አይዘነጋም።ዛሬ ማክሰኞ ፍርድ ቤት የቀረቡት ሚኒስትሩ ይቅርታ ጠይቀው በኛኙኪ ግዛት በሚገኝ ወታደራዊ ሰፈር የሚገነባው የኢቦላ ለይቶ ማቆያ ማዕከል “በአፋጣኝ እና ሙሉ በሙሉ እንዲቆም” ማዘዛቸውን አስታውቀዋል።ባለፈው ወር የመብት ተሟጋች ቡድኖች ያቀረቡትን አቤቱታ ተከትሎ የኬንያ ፍርድ ቤት 50 አልጋዎች ያሉት የለይቶ ማቆያ ማዕከል ግንባታ እንዲቆም ውሳኔ አሳልፏል።ሆኖም ግን ሰኞ ዕለት የዋለው ችሎት የጤና ሚኒስትሩ ትዕዛዝ ችላ ብለው ግንባታው እንዲቀጥል በመወሰናቸው ፍርድ ቤትን በመድፈር ጥፋተኛ ብሏቸዋል።ማዕከሉ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በተቀሰቀሰው የኢቦላ ቫይረስ የተጠረጠሩ አሜሪካዊያን ለይቶ ማቆያ እንዲሆን ታስቦ ነበር።የጤና ሚኒስትሩ ኤደን ዱአሌ “ድርጊቴ፣ ችላ ባይነቴ፣ አለመረዳቴ ወይም የተዛባ ግንዛቤዬ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ እንዳላከብር በማድረጉ ይቅርታ እጠይቃለሁ” ብለዋል።የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኛ ፓትሪሽያ ናዩንዲ የሚኒስትሩን ይቅርታ ተቀብለው “በጥብቅ ማስጠንቀቂያ” አሰናብተዋቸዋል።የኢቦላ ለይቶ ማቆያ ማዕከል ግንባታ በኬንያውያን ዘንድ ቁጣ እና ተቃውሞ አስነስቷል። ፖሊስ ተቃዋሚዎችን ለመበተን ሲሞክር ሦስት ሰዎች ተገድለዋል።ያጋሩ, የኬንያው የጤና ሚኒስትር የኢቦላ ለይቶ ማቆያ ማዕከል ግንባታ እንዲቆም ወሰኑ
  6. ከ 9 ሰአት በፊትየአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ለኢራን ጦርነት ላወጣው 80 ቢሊዮን ዶላር ጥያቄ አቀረበየመከላከያ ሚኒስትር ፔት ሄግሴትየምስሉ መግለጫ,የመከላከያ ሚኒስትር ፔት ሄግሴትየአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር በአብዛኛው ለኢራን ጦርነት ያወጣውን ወጪ ለመሸፈን ወደ 80 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው ለአገሪቱ ምክር ቤት አባላት አስታወቀ።የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት የበጀት ጥያቄው ገና በይፋ አለመቅረቡን ቢገልጽም፣ የመከላከያ ሚኒስትሩ ፔት ሄግሴት ባለፉት ቀናት ወደ አሜሪካ ምክር ቤት በመሄድ ከእንደራሴዎች ጋር እየተገናኙ መሆናቸው ተዘግቧል።አሶሺየትድ ፕሬስ ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ነገር ግን በይፋ ለመግለጽ ሥልጣን የሌላቸውን ሁለት ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ለኢራን ጦርነት የወጣውን ገንዘብ የተመለከተ ጥያቄ ባለፈው ዓመት ለምክር ቤት አባላት ቀርቧል።ምክትል የመከላከያ ሚኒስትር ስቴፈን ፋይንበርግ በበኩላቸው ከበርካታ የምክር ቤት አባላት ጋር በቀረበው የገንዘብ ጥያቄ ላይ ከመነጋገራቸው በተጨማሪ ዝርዝሩ ለምክር ቤቱ የአስተዳደር እና የበጀት ጽህፈት ቤት መቅረቡ ተገልጿል።ፔንታገን በመባል የሚታወቀው የመከላከያ መሥሪያ ቤት ግን በጉዳዩ ላይ አስተያየቱን ተጠይቆ ምላሽ አልሰጠም።ይህ የበጀት ጥያቄ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር ጦርነት ውስጥ መግባታቸውን ከተቃወሙት የምክር ቤት አባላት በአሜሪካውያን ላይ ያጋጠመውን የኑሮ ውድነት እንደምክንያት በማቅረብ ቀላል የማይባል ተቃውሞ እንደሚገጥመው ይጠበቃል።ግንቦት ወር ላይ በምክር ቤቱ በተካሄደው የጥያቄ እና መልስ መድረክ ላይ “በርካታ ሕዝብ ለተቃወመው ጦርነት አሜሪካውያን ለፍተው ያገኙትን ገንዘብ እያወጣችሁ ነው” በማለት ዴሞክራቷ የምክር ቤት አባል ፓቲ መሪ የመከላከያ ሚኒስትሩ ሄግሴትን መናጋራቸው ይታወሳል።ያጋሩ, የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ለኢራን ጦርነት ላወጣው 80 ቢሊዮን ዶላር ጥያቄ አቀረበ
  7. 23 ሰኔ 2026የአሜሪካ ባለሥልጣናት ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ የሰው ሕይወት ባጠፋው ቴስላ መኪና ላይ ምርመራ ጀመሩቴስላ መኪና የውስጥ ክፍልየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ቴስላ ሞዴል 3 እጅግ ዘመናዊ እና በራሱ መሽከርከር የሚችል ተሽከርካሪ ነው (ፎቶው አደጋው የደረሰበት መኪና አይደለም)የአሜሪካ የትራንስፖርት ደኅንነት ባለሥልጣናት አንድ ቴስላ መኪና በድንገት ከመንገድ ወጥቶ ከመኖሪያ ቤት ጋር በመጋጨት የአንድ ሰው ሕይወት ካለፈ በኋላ ምርመራ ማድረግ መጀመራቸው ተገለጸ።ባለፈው ሳምንት አርብ በአገሩ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት ሁለት ሰዓት ቴክሳስ ግዛት ውስጥ ከመንገድ ወጥቶ አደጋ ስላደረሰው ቴስላ መኪና የአሜሪካ ብሔራዊ የመንገዶች ትራፊክ ደኅንነት አስተዳደር ሰኞ ዕለት ምርመራ ማድረግ ጀምሯል።በቴስላ በተገጨመው ቤት ውስጥ የነበረችው ሴት ከባድ ጉዳት ከደረሰባት በኋላ በአደጋው ምክንያት ሕይወቷ ማለፉን ፖሊስ አስታውቋል።ፖሊስ ጨምሮም የመኪናው ሹፌር በአደጋው ወቅት በአደገኛ ዕጽም ሆነ በአልኮል ተጽእኖ ስር አልነበረም። አሽከርካሪው ለመርማሪዎች እንደተናገረው አደጋው የደረሰው መኪናው አውቶማቲክ ሆኖ በራሱ እየተሽከረከረ በነበረበት ጊዜ ነው።የአሜሪካ መንገዶች ደኅንነት አስተዳደር ቃል አቀባይ እንዳሳወቀው “መሥሪያ ቤቱ በአደጋው ላይ ልዩ ምርመራ ማካሄድ ጀምሯል።”የዓለማችን የመጀመሪያው አሜሪካዊው ትሪሊየነር ንብረት የሆነው የዘመናዊው መኪና አምራች ቴስላ ተወካይ መንግሥት በተሽከርካሪው ላይ እያካሄደ ስላለው ምርመራ አስተያየት ቢጠየቅም ምላሽ አልሰጠም።የፖሊስ ሪፖርት እንደሚያመለክተው ሞዴል 3 የተባለው ቴስላ መኪና አሽከርካሪ “መኪናው ከቁጥጥሩ ውጪ ሆኖ ከመንገድ በመውጣት ከመኖሪያ ቤት ጋር በመጋጨቱ” የሰው ሕይወት ጠፍቷል።ያጋሩ, የአሜሪካ ባለሥልጣናት ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ የሰው ሕይወት ባጠፋው ቴስላ መኪና ላይ ምርመራ ጀመሩ
  8. 23 ሰኔ 2026የምያንማር ጦር በስድስት ወር ውስጥ ከ700 በላይ ንጹኃንን መግደሉን የተባበሩት መንግሥታት ገለጸየምያንማር ወታደራዊ መሪ መኪና ላይየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምያንማር ጦር ባለፈው ዓመት በምርጫ ወቅት በስድስት ወር ውስጥ ለተመዘገቡት ከ700 በላይ የንጹኃን ሰዎች ሞት ተጠያቂ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ገለጸ።ካለፈው ነሐሴ እስከ ጥር ድረስ ያለውን ጊዜ የሸፈነ አዲስ ሪፖርት ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው 224 ሴቶች እና 153 ሕጻናትን ጨምሮ ቢያንስ 702 ሰዎች እንደተገደሉ ከታማኝ ምንጮች ተረጋግጧል።ጥናቱ የሸፈነው ከአምስት ዓመት በፊት መፈንቅለ መንግሥት ያወጀው ሠራዊት ምርጫ እንደሚካሄድ ያፋ ካደረገ በኋላ ያሉትን ስድስት ወራት ነው። ምርጫው ተቃዋሚዎች በመገለላቸው ምክንያት የተጭበረበረ እንደሆነ በሰፊው ይታመናል።“የዓለም አቀፍ እገዛ መቀነስ የሚሊዮን ሰዎችን ስቃይ እያባባሰ ነው” ሲል ሪፖርቱ አስጠንቅቋል።የምያንማር ጦር በ2021 መፈንቅለ መንግሥት መካሄዱን ካወጀ በኋላ በተቀሰቀሰው የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ፤ ሚሊዮኖች ተፈናቅለዋል። ሰፊው የአገሪቱ ክፍልም በታጣቂዎች እጅ ወድቋል።የተመድ የሰብአዊ መብቶች ጽሕፈት ቤት ያወጣው ሪፖርት እንደሚገልጸው የአየር ጥቃት “ብቸኛው ግዙፍ የውድመት እና ስቃይ ምክንያት” ሆኖ ቀጥሏል።ጥቅምት ወር ላይ በተፈጸመ ጥቃት አራት ሕጻናትን ጨምሮ 23 ሰዎች ተገድለዋል። ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ተሰብስበው 60 ሰዎች ደግሞ ተተኳሽ ሲወድቅ በፍንጥርጣሪ ተጎድተዋል።ታኅሣሥ ላይ ደግሞ ሠራዊቱ በሻይ ቤት ላይ በፈጸመው ጥቃት ኳስ ለመመልከት ተሰብስበው የነበሩ ቢያንስ 19 ሰዎች እንደተገደሉ እና 20 ሰዎች እንደቆሰሉ ሪፖርቱ ገልጿል።ያጋሩ, የምያንማር ጦር በስድስት ወር ውስጥ ከ700 በላይ ንጹኃንን መግደሉን የተባበሩት መንግሥታት ገለጸ
  9. 23 ሰኔ 2026ኢራን የኒውክሌር ተቆጣጣሪዎች እንዲገቡ ልትፈቅድ ነው መባሉን አስተባበለችየአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስየፎቶው ባለመብት,Reutersጦርነቱን ለመቋጨት ከአሜሪካ ጋር የተደረገው የመጀመሪያው ዙር ንግግር መጠናቀቁን ተከትሎ ኢራን ዓለም አቀፍ የኒውክሌር ተቆጣጣሪዎች ወደ አገሪቱ እንዲገቡ ልትፈቅድ ነው መባሉን የቴህራን መንግሥት አስተባበለ።የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ በስዊትዘርላንድ ከተካሄደው ድርድር ባደረጉት ንግግር ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኤነርጂ ኤጀንሲ ጋር የሚካሄዱ ውይይቶች “ዛሬ ጭምር” ሊጀመሩ ይችላሉ ብለው ነበር።የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ግን ለአገሪቱ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን በሰጠው ማብራሪያ፤ የኒውክሌር ቁጥጥርን በተመለተከተ የተገባ “አዲስ ቃል የለም” ብለዋል።የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ቫንስ ሰኞ ጠዋት ላይ በስዊትዘርላንድ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ ወቅት የኒውክሌር ተቆጣጣሪዎች ወደ ኢራን የሚመለሱት መቼ እንደሆነ ተጠይቀዋል።ለዚህም ምላሽ ሲሰጡ ሂደቱ “ቢያንስ በዚህ ሳምንት” እንደሚጀመር፤ ከተቆጣጣሪዎቹ ጋር የሚደረገው ንግግር ግን “ዛሬ ጭምር ሊካሄድ እንደሚችል” ገልጸዋል።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕም ኢራን “በዋና ዋና የጦር መሣሪያዎች ላይ ፍተሻ እንዲካሄድ ትስማማለች” ሲሉ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ጽፈዋል።‘ኢርና’ ለተሰኘው ለኢራን መንግሥት የዜና ወኪል ቃለ መጠይቅ የሰጡት የቴህራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኤል ባቃኢ ግን አገራቸው የኔውክሌር ተቆጣጣሪዎችን በተመለከተ “ምንም አይነት አዲስ ቃል” እንዳልገባች ተናግረዋል።ከተባበሩት መንግሥታት ተቆጣጣሪዎች ጋር የሚደረግ ማንኛውም ግንኙነት የሚከናወነው “በፓርላማው እና በጠቅላይ የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት በተቀመጡት ነባር አሰራሮች” መሠረት እንደሆነም አጽንኦት ሰጥተዋል።ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ እስካሁን በጉዳዩ ላይ አስተያየት አልሰጠም።ኢራን የኤጀንሲው ወደ የኒውክሌር ስፍራዎች እንዳይጓዝ የከለከለችው ባለፈው ዓመት በተካሄደው የ12 በቀናት ጦርነት ወቅት እስራኤል እና አሜሪካ የኒውክሌር ጣቢያዎችን ከደበደቡ በኋላ ነው።ይህንን ውሳኔ ተከትሎም የመንግሥታቱ ድርጅት ተቆጣጣሪ ተቋም የቀሩትን ባለሙያዎቹን ከኢራን አስወጥቷል።ያጋሩ, ኢራን የኒውክሌር ተቆጣጣሪዎች እንዲገቡ ልትፈቅድ ነው መባሉን አስተባበለች
  10. 23 ሰኔ 2026አሜሪካ በኢራን ነዳጅ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ አላላችየኢራን ባንዲራ እና የሚቃጠል ነዳጅየፎቶው ባለመብት,Reutersዋሽንግተን ከአስርት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢራን ነዳጅ በአሜሪካ ዶላር እንዲሸጥ በመፍቀድ ቴህራን ላይ የጣለችውን ማዕቀብ በጊዜያዊነት አነሳች።ለ60 ቀናት የሚቆየውን የማዕቀብ ማላላት እርምጃ ሰኞ ምሽት ይፋ ያደረገው የአሜሪካ ግምጃ ቤት ነው። ይህ እርምጃ የኢራንን ኢኮኖሚ አንቆ የያዘው እና ለረጅም ጊዜ የቆየው የአሜሪካ ማዕቀብ ዋነኛ ምሰሶዎች እንዲወገዱ ያደርጋል።በዚህ የአስቸኳይ ጊዜ ፈቃድ መሠረት ኢራን እስከ ነሐሴ ወር ድረስ ድፍድፍ ነዳጅ እንዲሁም የፔትሮኬሚካል ምርቶችን ማምረት፣ መሸጥ እና መላክ ትችላለች። ይህ የማዕቀብ እፎይታ የኢራን ነዳጅ በቀጥታ ወደ አሜሪካ እንዲገባም ያስችላል።በተጨማሪም የኢራን የባንክ ዝውውር፣ ኢንሹራስ እና ትራንስፖርት ዘርፍ ላይ የተጣለው ማዕቀብ መነሳቱ ቴህራን ከዚህ ቀደም ድፍድፍ ነዳጇን ለመሸጥ ስትከተል የነበረውን ውስብስብ አሰራር ያስቀራል።የግምጃ ቤት ኃላፊው ስኮት ቤንሰንት እንደተናገሩት ለ60 ቀናት የሚቆይ የማዕቀብ እፎይታ የተሰጣት ኢራን በምላሹ ወሳኙ የባሕር መተላለፊያ የሆነውን የሆርሙዝ ወሽመጥ ለመክፈት ቃል ገብታለች።የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኤነርጂ ኤጀንሲ የኒውክሌር ተቆጣጣሪዎችም ወደ አገሪቱ እንዲገቡ ትፈቅዳለች ብለዋል።ኢራን ግን ይህ ተቆጣጣሪዎች ወደ አገሪቱ እንዲገቡ ልትፈቅድ ነው መባሉን አስተባብላለች።አሜሪካ የማዕቀብ ማላላት እርምጃውን የወሰደችው ስዊዘርላንድ ውስጥ ሁለቱን አገራት ሲያደራድሩ የነበሩት አሸማጋዮች ጥሩ መሻሻል መታየቱን ከገለጹ በኋላ ነው።ኳታር እና ፓኪስታን ሰኞ ዕለት ባወጡት መግለጫ አሜሪካ እና ኢራን “በ60 ቀናት ውስጥ የመጨረሻ ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያስችል ፍኖተ ካርታ” ላይ መስማማታቸውን አስታውቀዋል።የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስም የመጀመሪያው ዙር ንግግር “በጣም ጥሩ መሠረት” መጣሉን ተናግረዋል።ያጋሩ, አሜሪካ በኢራን ነዳጅ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ አላላች
  11. 22 ሰኔ 2026በኳታር የጋዝ ማቀነባበሪያ ላይ ባጋጠመ ፍንዳታ 13 ሰዎች ሞቱፍንዳታየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesበግዙፉ የኳታር የጋዝ ማምረቻ ተቋም ላይ በደረሰ ፍንዳታ ቢያንስ 13 ሰዎች እንደሞቱ እና 66 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገለጸ።ራስ ላፋን በተሰኘው የኢንዱስትሪ ዞን ውስጥ የሚገኘው እና ወደ ፈሳሽነት የተቀየረ የተፈጥሮ ጋዝ ዋነኛ ማቀነባበሪያው የሆነው ስፍራ እሁድ ምሽት “የቴክኒካል አደጋ” እንዳጋጠመው የኳታር የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።በዚህ አደጋ ምክንያት የከተማው ሰማይ ብርቱካናማ ቀለም ይዞ ታይቷል። የእሁድ ዕለቱ ፍንዳታ ከራስ ላፋን 70 ኪሎ ሜትር ርቀት በሚገኘው ማዕከላዊ ዶሃ ጭምር ተሰምቷል።በዚህ ጥቃት የሞቱት ሰዎች የሕንድ እና የፓኪስታን ዜግነት ያላቸው እንደሆኑ ተገልጿል።ፍንዳታው በአገሪቱ ኤክስፖርት ምርት ላይ ተጽዕኖ እንደማይኖረው የተናገሩት የኳታር የኤነርጂ ሚኒስትር ሳዐድ ሸሪዳ አል ካቢ፤ “ያጋጠመው አደጋ ነው፤ በተፈጥሮውም ትንኮል ወይም በጠበኛ ድርጊት [የተከሰተ] አይደለም” ብለዋል።ጥቃቱ የደረሰበት ስፍራ የሚገኝበት ራስ ላፋን በዓለም ትልቁ ሰው ሰራሽ ወደብ ሲሆን በውስጡም የዓለም ትልቁን ወደ ፈሳሽነት የተቀየረ የተፈጥሮ ጋዝ ለውጭ ገበያ ማቅረቢያ ተቋምን ይዟል።የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነትን ተከትሎ ስፍራው በኢራን ጥቃቶች ተፈጽመውበት ነበር። የአሁኑን ፍንዳታ ምክንያት ለማወቅ ምርመራ መጀመሩን የኤነርጂ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።ያጋሩ, በኳታር የጋዝ ማቀነባበሪያ ላይ ባጋጠመ ፍንዳታ 13 ሰዎች ሞቱ
  12. 22 ሰኔ 2026የአሜሪካ እና ኢራን ንግግር ውጤት እያስገኘ መሆኑን ምክትል ፕሬዝዳንት ቫንስ ገለጹአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንትየፎቶው ባለመብት,Reutersአሜሪካ እና ኢራን ስዊትዘርላንድ ውስጥ እየካሄዱት ባለው ንግግር “መልካም ውጤቶች መገኘታቸውን” እና የተሳካ የመጨረሻ ስምምነት ላይ ለመድረስ “ጥሩ መሠረት መጣሉን” የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ተናገሩ።ንግግሩ ከተጀመረ በኋላ የኢራን ልዑካን ረግጠው ለመውጣት ቢዝቱም በሁለቱ አገራት ተወካዮች መካከል የሚካሄደው ድርድር ለረጅም ሰዓታት ቀጥሎ ነው አዎንታዊ ደረጃ ላይ መድረሱ የተነገረው።የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኤነርጂ የኒውክሌር ተቆጣጣሪዎች ተመልሰው ወደ ኢራን በመግባት በመጀመሪያ ደረጃው ንግግር ስምምነት የተደረሰባቸውን ነጥቦች ማክበሯን ያረጋግጣሉ ተብሏል።በአሜሪካም በበኩሏ ኢራን የተለያዩ የእህል ምርቶችን ከውጭ ለመግዛት እንድትችል ለማድረግ ሲባል የታገደባት ሀብት እንዲንቀሰቀስ ትፈቅዳለች።ወሳኙ የባሕር ላይ መተላለፊያ ሆርሙዝ ወሽመጥ “ክፍት ነው” ያሉት የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት፣ በሊባኖስ የሚካሄደውን ጦርነት በተመለከተም ተገቢው ቅንጅት እና ቴክኒካዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ንግግር ማድረግ እንደሚቀጥል አመልክተዋል።ያጋሩ, የአሜሪካ እና ኢራን ንግግር ውጤት እያስገኘ መሆኑን ምክትል ፕሬዝዳንት ቫንስ ገለጹ
  13. 22 ሰኔ 2026የመጀመሪያው ቀን ድርድር ሲጠናቀቅ፤ በቀጣይ ቀናት የቴክኒክ ውይይት እንደሚቀጥል ተገለጸየኢራን ልዑካንየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየኢራን እና አሜሪካ የመጀመሪያ ቀን ድርድር የተገባደደ ሲሆን፤ ሳምንቱን በሙሉ በስዊትዘርላንድ የቴክኒክ ጉዳዮች ውይይት እንደሚቀጥል ተገልጿል።አደራዳሪዎቹ ኳታር እና ፓኪስታን “የኢስላማባድ የመግባቢያ ሰነድ ማዕቀፍን በተመለከተ የመጀመሪያው ዙር ንግግር ተገባዷል” ብለዋል።በተቀረው የሳምንቱ ቀናት የቴክኒክ ውይይት እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።አሜሪካ እና ኢራን በቀጣይ 60 ቀናት ውስጥ የመጨረሻ ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ላይ መስማማታቸው ተመልክቷል።በሊባኖስ ጦርነቱን ማስቆም የሚቻልበት መንገድ መዘርጋት ላይም መግባባት ላይ መደረሱን አሸማጋዮቹ አስታውቀዋል።የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ድርድሩን “ትልቅ ለውጥ” የታየበት እንደሆነ በኤክስ ገጻቸው ተናግረዋል።“በነዳጅ እና በፔትሮኬሚካል የወጪ ንግድ ላይ የተጣለው እገዳተነስቷል” ሲሉም አክለዋል።የኢራን እና አሜሪካ የመጀመሪያ ቀን ድርድርየፎቶው ባለመብት,EPA/Shutterstockያጋሩ, የመጀመሪያው ቀን ድርድር ሲጠናቀቅ፤ በቀጣይ ቀናት የቴክኒክ ውይይት እንደሚቀጥል ተገለጸ
  14. 22 ሰኔ 2026በኢራን እና አሜሪካ የመጀመሪያ ቀን ድርድር ምን ጉዳዮች ተነሱ?ሉስርኔ በተባለ ሐይቅ የተካሄደው ድርድር አወንታዊ እና ገንቢ ድባብ እንደታየበት ተገልጿልየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ሉስርኔ በተባለ ሐይቅ የተካሄደው ድርድር አወንታዊ እና ገንቢ ድባብ እንደታየበት ተገልጿልአሸማጋዮቹ ኳታር እና ፓኪስታን በጋራ ባወጡት መግለጫ የድርድር ሒደቱን የሚከታተል የፖለቲካ ኮሚቴ እና በሊባኖስ ጦርነት የሚያስቆም ቡድን መመሥረቱን አስታውቀዋል።“ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ኮሚቴ በ60 ቀናት ውስጥ የመጨረሻ ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ላይ ተስማምቷል” ብለዋል።የአሜሪካ እና ኢራን ድርድር በስዊትዘርላንድ የተካሄደ ሲሆን፤ ኳታር እና ፓኪስታን በጋራ ባወጡት መግለጫ የመጀመሪያውን ቀን ድርድር ነጥቦችን እንደሚከተለው ዘርዝረዋል፦
    • ሉስርኔ በተባለ ሐይቅ የተካሄደው ድርድር አወንታዊ እና ገንቢ ድባብ እንደታየበት ተገልጿል።
    • ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ኮሚቴ ድርድሩን በዋናነት የሚከታተል ይሆናል።
    • ዋነኛ ተደራዳሪዎች የደረሱበትን ለኮሚቴው ያስታውቃሉ።
    • ኮሚቴው ግጭትን ለማስቆም ከተቋቋመው ቡድን ጋር በመሆን የኒውክሌር፣ የማዕቀብ እና የመግባቢያ ሰነዱ አተገባበርን ይከታተላል።
    • በስምምነቱ አንቀጽ 5 መሠረት የሆርሙዝ ወሽመጥን ለማስከፈት እንዲሁም በተደራዳሪዎች መካከል አለመግባባት እንዳይኖር የንግግር መስመር ክፍት ይሆናል።
    • ግጭትን ለማስቆም የተቋቋመው ቡድን በሊባኖስ ድርድር እንዲደረግ እና ወታደራዊ ግጭት እንዲቆም ያደርጋል።
    ያጋሩ, በኢራን እና አሜሪካ የመጀመሪያ ቀን ድርድር ምን ጉዳዮች ተነሱ?
  15. 22 ሰኔ 2026ኢራን የነዳጅ ማዕቀብ እንደተነሳላት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገለጹድርድርየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ “በነዳጅ እና በፔትሮኬሚካል የወጪ ንግድ ላይ የተጣለው እገዳ መነሳቱን” ገለጹ።ከድፍድፍ ነዳጅ እና ከተፈጥሮ ጋዝ የሚገኘው ፔትሮኬሚካል የወጪ ንግድ ላይ የተጣለው ማዕቀብ ከመነሳቱ በተጨማሪ በኢራን የባሕር መተላለፊያ ላይ ተጥሎ የነበረው ክልከላ መነሳቱንም አክለዋል።በተጨማሪም ማዕቀብ ተጥሎባቸው የነበሩ “የተወሰኑ የኢራን ሃብቶች እንደተለቀቁ” ተናግረዋል።የማዕቀቦች መነሳት የኢራንን የምጣኔ ሃብት መልሶ ግንባታ እንደሚደግፍ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል።“በሊባኖስ ያለው ጦርነት እንዲቆም” የኳታር እና ፓኪስታን ልዑካን ላበረከቱት አስተዋጽኦም አመስግነዋል።ኢራን እና አሜሪካ የተስማሙበት መግባቢያ ሰነድ አንቀጽ 1፣ 10 እና 11 ለድርድሩ ዋነኛ መነሻ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።አንቀጽ 1- አሜሪካ፣ ኢራን እና አጋሮቻቸው ሊባኖስን ጨምሮ በሁሉም ግንባሮች “በአፋጣኝ እና በዘላቂነት” ተኩስ ማቆም አለባቸው ይላል።አንቀጽ 10- ዋሽንግተን ለነዳጅ ኤክስፖርት እና ለፔትሮሊየም ምርቶች አስፈላጊውን ፈቃድ እንድትሰጥ እና ባንክ እና መጓጓዣን ጨምሮ በሌሎችም ዘርፎች ውሳኔው እንደሚተገበር ይገልጻል።አንቀጽ 11- ማዕቀብ የተጣለባቸውን የኢራን ሃብቶች ይመለከታል።ያጋሩ, ኢራን የነዳጅ ማዕቀብ እንደተነሳላት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገለጹ
  16. 22 ሰኔ 2026የአሜሪካ እና የኢራን የመጀመሪያ ዙር ድርድር ‘አበረታች ውጤት’ እንዳሳየ ተገለጸየአሜሪካ ልዑካንየፎቶው ባለመብት,Reutersየአሜሪካ እና የኢራን የመጀመሪያ ዙር ድርድር “አበረታች ውጤት” እንዳሳየ አሸማጋዮቹ ኳታር እና ፓኪስታን አስታወቁ።ድርድሩ ትናንት እሑድ በስዊትዘርላንድ ተጀምሯል። ሁለቱ አገራት ከስምምነት ላይ የደረሱት ባለፈው ሳምንት እንደነበር ይታወሳል።ኳታር እና ፓኪስታን ዛሬ ሰኞ በጋራ ባወጡት መግለጫ “ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ኮሚቴ በ60 ቀናት ውስጥ የመጨረሻ ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ላይ ተስማምቷል” ብለዋል።በያዝነው ሳምንት የቴክኒክ ጉዳዮችን በተመለከተ ውይይት እንደሚቀጥል በመግለጫው ተመልክቷል።በድርድሩ ተሳታፊ የሆኑ የአሜሪካ ዲፕሎማት እንደተናገሩት ውይይቱ “ከኢራን የወጡ አወዛጋቢ መልዕክቶችን ማጥራት ላይ ያተኮረ ነው”።በተጨማሪም በሊባኖስ የተኩስ አቁም ስምምነትን ማስተግበር እና የሆርሙዝ ወሽመጥን ማስከፈት የውይይቱ ግቦች መሆናቸውን ገልጸዋል።ተደራዳሪዎችየፎቶው ባለመብት,Reutersያጋሩ, የአሜሪካ እና የኢራን የመጀመሪያ ዙር ድርድር ‘አበረታች ውጤት’ እንዳሳየ ተገለጸ