የአሜሪካ እና ኢራን ባለሥልጣናት ነገ ኳታር ውስጥ ለድርድር እንደሚገናኙ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስታወቁ። ዋነኞቹ የአሜሪካ ተደራዳሪዎች ጃሬድ ኩሽር እና ስቲቭ ዊትኮፍ ወደ ዶሃ እንደሚበርሩ ዋይት ሀውስ ገልጿል።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. 29 ሰኔ 2026ዴሞክራቲክ ኮንጎ የኢቦላ ሥርጭትን ለመግታት በዋና ከተማዋ የሚደረጉ የሕዝብ ኹነቶችን አገደችየሙቀት መለኪያ የያዘች ሴትየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የአገር ውስጥ ሚኒስቴር፤ የኢቦላ ቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት ሲባል ዋና ከተማዋ ኪንሻሳ እና በሌሎች ሦስት ከተሞች ውስጥ ሰዎች የሚሰበሰቡባቸው ኹነቶች እንዳይካሄዱ ክልከላ መጣሉን አስታወቀ።በአገሪቱ የተከሰተው የገዳዩ በሽታ ወረርሽኝ እስካሁን ድረስ ከዋና ከተማዋ 1,800 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ በሚገኙት በሦስት ምሥራቃዊ ግዛቶች ውስጥ መሠራጨቱ ተረጋግጧል። ባለሥልጣናቱ በሽታው 18 ሚሊዮን ነዋሪዎች ባሏት ኪንሻሳ ውስጥም ሊሠራጭ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው።ተመሳሳይ ዕገዳ ተጣለባቸው ሌሎቹ ሦስት ከተሞች ኢቦላ መገኘቱ ከተረጋገጠባቸው አካባቢዎች ጋር ይጎራበታሉ።የዴሞክራቲክ ኮንጎ ታዋቂ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች እርምጃው በሚቀጥለው ሳምንት ረቡዕ ሊካሄድ የታቀደውን የተቃውሞ ሰልፍ ለማደናቀፍ ያቀደ ነው በሚል ተቃውመውታል።‘ላሙካ’ የተሰኘው የተቃዋሚ ጥምረት ቃል አቀባይ ፕሪንስ ኢፔንጌ፤ በበሽታው ኪንሻሳ ውስጥ መከሰቱ ባለመረጋገጡ የመንግሥት ውሳኔ “ፖለቲካዊ” ነው ሲሉ ተችተዋል። “ሕጋዊ አይደለም። ይህንን ውሳኔ ልንቀበል አንችልም” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።‘ኤንቮል’ የተሰኘው ሌላ የተቃዋሚ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ ደግሞ፤ ተቃዋሚዎች እገዳውን ችላ በማለት ሰልፉ ላይ እንዲገኙ አሳስበዋል። የተላለፈው ትዕዛዝ “ከሕብረተሰብ ጤና ውሳኔነት ይልቅ ፖለቲካዊ እርምጃ ነው” ብለዋል።የዴሞክራቲክ ኮንጎ መንግሥት ስለቀረበው ትችት እስካሁን ምላሽ አልሰጠም።በሚቀጥለው ሳምንት እንዲካሄድ የታቀደው ሰልፍ የተዘጋጀው ‘ሲ64’ በተባለው እና በቅርቡ የወጣ ሕግን ለመቃወም በተቋቋመው ጥምረት የተዘጋጀ ነው። ተቃዋሚዎች፤ ሕጉ ፕሬዝዳንቱ ፌሊክ ቲሼኬዲ ከሁለት የሥልጣን ዘመን በላይ በመሪነት እንዲቆዩ እንደሚያስችላቸው ይገልጻሉ።ያጋሩ, ዴሞክራቲክ ኮንጎ የኢቦላ ሥርጭትን ለመግታት በዋና ከተማዋ የሚደረጉ የሕዝብ ኹነቶችን አገደች
  2. 29 ሰኔ 2026የቀድሞው አሜሪካ ፕሬዝዳንት ባይደን፣ ትራምፕን “ከንቱ” ሲሉ ዘለፉየቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesበሳምንቱ መጨረሻ በተካሄደ የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ ንገግር ያደረጉት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ተተኪያቸው ዶናልድ ትራምፕ የሚያስገነቧቸውን “የታይታ ፕሮጀክቶች” በማንሳት “ከንቱ” ሲሉ ዘለፉ።ባይደን በቅዳሜ ዕለቱ የዴሞክራቲክ ፓርቲ ዝግጅት ንግግራቸው ፕሬዝዳንት ትራምፕ በዋይት ሐውስ የግብር አዳራሽ ለመገንባት እንዲሁም የዋሽንግተንን አንጸባራዊ የውሃ ገንዳ ለማደስ የያዙትን ዕቅድ አጣጥለዋል።ቢቢሲ የባይደንን ንግግር በተመለከተ ከዋይት ሐውስ አስተያየት ለማግኘት ጥያቄ አቅርቧል።ፕሬዝዳንት ትራምፕ የቀድሞው መሪ በሥልጣን ላይ ሳሉ የፈጸሟቸውን ተግባራት በተደጋጋሚ ተችተዋል፤ ባይደንም ተመሳሳይ ምላሽ ሰጥተዋል።ይሁን እንጂ ባይደን 10 ደቂቃ በቆየው የቅዳሜ ዕለቱ ንግግራቸው ያሰሙት ትችት ከምንጊዜውም የበለጠ ጠንካራ ነበር።“የታይታ ፕሮጀክቶቹ ብቻ አይደሉም፤ የግብር አዳራሽ ለመሥራት የዋይት ሐውስ የቀኝ ክንፍን ማፍረሱ፣ በኬኔዲ ሴንተር ሕንጻ ላይ የገዛ ራሱን ለማክበር ስሙን ማስቀመጡ፣ አንጸባራቂውን የውሃ ገንዳ ለመጠገን የራሱን የውሃ ገንዳ ሰው መቅጠሩ ጭምር ነው” ብለዋል።“ውይ! እንዴት ያለው ከንቱ [ሰው] ነው” ሲሉም አክለዋል።ባይደን በንግግራቸው የጠቀሱት ፕሬዝዳንት ትራምፕ በ‘ጆን ኤፍ ኬኔዲ ሴንተር ፎር ፐርፎርሚንግ አርትስ’ ሕንጻ የፊት ገጽ ላይ ስማቸውን ለማስፈር ያደረጉትን ሙከራ ነው።ፕሬዝዳንቱ ስማቸውን አጽፈው የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤት እንዲወርድ ትዕዛዝ አስተላልፏል።ፕሬዝዳንቱ 400 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣውን የግብር አዳራሽ ለመገንባት ሲሉ የቤተ መንግሥቱ የቀኝ ክንፍ እንዲፈርስ በማድረጋቸው የሚቀርብባቸውን ወቀሳ ሲከላከሉ ቆይተዋል።ግንባታው የአገር ደኅንነት እና የመንግሥት እንግዳዎችን ለማስተናገድ አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል።ያጋሩ, የቀድሞው አሜሪካ ፕሬዝዳንት ባይደን፣ ትራምፕን “ከንቱ” ሲሉ ዘለፉ
  3. 29 ሰኔ 2026ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን ጥያቄ መሠረት ነገ ዶሃ ውስጥ ንግግር ይደረጋል አሉፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካ እና ኢራን ባለሥልጣናት ነገ ኳታር ውስጥ ለድርድር እንደሚገናኙ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስታወቁ።ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሑፍ፤ “ኢራን ስብሰባ እንዲደረግ ጠይቃለች። ነገ ዶሃ ውስጥ ይካሄዳል” ብለዋል።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ነገ ማክሰኞ ይካሄዳል ስላሉት ስብሰባ ተጨማሪ ማብራሪያ አልሰጡም።የዋይት ሐውስ ቃል አቀባይ ካሮላይን ሌቪት ግን ዋነኞቹ የአሜሪካ ተደራዳሪዎች ጃሬድ ኩሽር እና ስቲቭ ዊትኮፍ “በዚህ ሳምንት ዶሃ ውስጥ የሚካሄድ የከፍተኛ ባለሥልጣናት ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ወደ ዶሃ እንደሚበርሩ” ለፎክስ ኒውስ ተካግረዋል።ከዚህ የከፍተኛ ባለሥልጣናት ስብሰባ ጎን ለጎን የቴክኒካል ንግግር እንደሚካሄድም አክለዋል።የኢራን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካዜም ጋሪባባዲ ግን ዛሬ በሰጡት አስተያየት ሁለቱ አገራት በዚህ ሳምንት ቴክኒካዊ ንግግር ለማድረግ ዕቅድ ይዘዋል መባሉን አስተባብለው ነበር።የኢራን ቴክኒካዊ ድርድር ቡድን ኃላፊ የሆኑት ጋሪባባዲ “የሌላኛውን ወገን ግዴታዎች አፈጻጸም መከታተልን ጨምሮ ከኳታር ጋር የሚደረጉት ምክክሮች ቢቀጥሉም፤ የሥራ ቡድኖቹ ቴክኒካዊ ንግግር ዶሃ ውስጥ ይካሄዳል በሚል በአንዳንድ መገናኛ ብዙኃን የተሠራጨው ዘገባ ግን የተረጋገጠ አይደለም” ብለዋል።የኢራኑ ባለሥልጣን ይህንን ከማለታቸው አስቀድሞ የተወሰኑ መገናኛ ብዙኃን ስማቸው ያልተጠቀሰ የአሜሪካ ባለሥልጣናትን ዋቢ በማድረግ፤ ቴህራን እና ዋሽንግተን የሚፈጽሟቸውን የአጸፋ ጥቃቶች ለማቆም እና ድርድሩን ለመቀጠል መስማማታቸውን ዘግበው ነበር።የአሜሪካዎቹ የዜና ምንጮች ሲኤንኤን እና አክሲዮስ ደግሞ የቴክኒካዊ ድርድሩ ቀጣይ ክፍል ነገ ማክሰኞ ኳታር ውስጥ እንደሚካሄድ አስነብበው ነበር።እነዚህ ዘገባዎች የወጡት አሜሪካ እና ኢራን አንዳቸው ሌላኛቸው የተኩስ አቁም ስምምነቱን እንደጣሱ በመግለጽ ክስ ሲያሰሙ ከቆዩ በኋላ ነው። ባለፉት ቀናት በሆርሙዝ ወሽመጥ ውስጥ እና በዙሪያው በርካታ ጥቃቶች የተፈጸመዋል።ያጋሩ, ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን ጥያቄ መሠረት ነገ ዶሃ ውስጥ ንግግር ይደረጋል አሉ
  4. 29 ሰኔ 2026የደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ የፖሊስ አዛዥ ከግድያ ሙከራ አመለጡሜጀር ጀነራል ፌሮዝ ካሀንየፎቶው ባለመብት,Gallo via Getty Imagesከደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ የፖሊስ አዛዦች አንዱ የሆኑት ሜጀር ጀነራል ፌሮዝ ካሀን ከግድያ ሙከራ ማምለጣቸውን ፖሊስ አስታወቀ።የወንጀል ምርመራ ክፍል ምክትል ኃላፊ የሆኑት ሜጀር ጀነራል ፌሮዝ ትናንት እሑድ ምሽት ወደ ቤታቸው እየነዱ ሳለ ጥይት እንደተተኮሰባቸው ተገልጿል። ወደ ድንገተኛ የሕክምና ክፍል መወሰዳቸውም ተዘግቧል።በደቡብ አፍሪካ በፖሊስ ኃይል የሚፈጸም ወንጀልን በተመለከተ ምርመራ የሚያካሂድ ኮሚቴ የተዋቀረ ሲሆን፤ ከፍተኛ የፖሊስ አዛዡ ከቀናት በኋላ ለኮሚቴው ቃላቸውን እንደሚሰጡ ይጠበቅ ነበር።የደቡብ አፍሪካ የፖሊስ ቃል አቀባይ ብርጋዲየር አትሌንዳ ሜት ክስተቱ ላይ ምርመራ መከፈቱን አስታውቀዋል።“ክስተቱ፤ መርማሪ ኮሚቴው ፊት ሊቀርቡ ከመሆኑ ጋር የተያያዘ ነው ማለት ወቅቱን ያልጠበቀ እና ኃላፊነት የጎደለው ነው” ብለዋል።የምርመራ ኮሚቴው የተዋቀረው ከፍተኛ የፖሊስ አዛዥ ሌተናንት ጀነራል ናለናሀል ምክዌንዚ የወንጀል ቡድኖች በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ሰርገው ገብተዋል ብለው በመክሰሳቸው ነበር።ያጋሩ, የደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ የፖሊስ አዛዥ ከግድያ ሙከራ አመለጡ