
አሜሪካ እና ኢራን በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ውስጥ እያደረጉ ያሉት ቀጥተኛ ያልሆነ ንግግር በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ። ፕሬዝዳንቱ በፓኪስታን እና በኳታር አሸማጋዮች በኩል የሚደረገውን ንግግር “እጅግ ጥሩ ስብሰባ” ሲሉ ገልጸውታል።
ጭምቅ ሃሳብ
- ኢራን ስምምነቱ ከተጣሰ “ከፍተኛ እርምጃ” እንደምትወስድ አስታወቀች
- አሜሪካ እና ኢራን ግጭቱን “ለመግታት” መስማማታቸው ተገለጸ
- ፓኪስታን በአፍጋኒስታን ላይ ባደረሰችው ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ
- ኢራን እና አሜሪካ በቴክኒክ ጉዳዮች ውይይት እንደሚቀጥሉ ተዘገበ
- የደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ የፖሊስ አዛዥ ከግድያ ሙከራ አመለጡ
የቀጥታ ሽፋን
- 1 ሀምሌ 2026ፕሬዝዳንት ትራምፕ የአሜሪካ እና ኢራን ተደራዳሪዎች ንግግር በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ተናገሩ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesአሜሪካ እና ኢራን በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ውስጥ እያደረጉ ያሉት ቀጥተኛ ያልሆነ ንግግር በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ።ፕሬዝዳንቱ በፓኪስታን እና በኳታር አሸማጋዮች በኩል የሚደረገውን ንግግር “እጅግ ጥሩ ስብሰባ” ሲሉ ገልጸውታል።ወደ ሰሜን ዳኮታ ግዛት ከመብረራቸው በፊት ከጋዜጠኞች ጋር የተነጋገሩት ትራምፕ፤ “ኢራንን ከኒውክሌር ነጻ የማድረግ ሂደት በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው” ብለዋል።የኒውክሌር ጦር መሣሪያ የመገንባት ዕቅድ አላት የሚል ክስ የሚቀርብባት ኢራን፤ የኒውክሌር መርሃ ግብሯ ለሰላማዊ ዓላማ ብቻ እንደሚል በተደጋጋሚ ገልጻለች።ፕሬዝዳንት ትራምፕ “በጣም ጥሩ ስብሰባዎችን አድርገዋል፤ [የሚሆነውን] እናያለን” ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። “እጅግ በኃይለኛው መትተናቸዋል…ሆኖም በጣም በጥሩ ሁኔታ እየተቀራረብን ነው” ሲሉም ተደምጠዋል።ኳታር ውስጥ እየተደረገ ባለው ቴክኒካዊ ንግግር ላይ የአሜሪካ እና ኢራን ባለሥልጣናት ፊት ለፊት ለድርድር አልተቀመጡም።የአሜሪካ ዋነኛ ተደራዳሪ የሆኑት የፕሬዝዳንቱ ልዩ ልዑክ ስቲቭ ዊትኮፍ እና የ ትራምፕ አማች ጃሬድ ኩሽነር ወደ ዶሃ ተጉዘዋል።የሁለቱ አገራት ተደራዳሪዎች ንግግር ባለፈው ሳምንት የተከሰተውን ተኩስ ልውውጥ ተከትሎ የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ የሚያስችሉ ነጥቦችን በአሸማጋዮች አማካኝነት አንዳቸው ለሌላቸው ያቀርባሉ።ያጋሩ, ፕሬዝዳንት ትራምፕ የአሜሪካ እና ኢራን ተደራዳሪዎች ንግግር በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ተናገሩ
