አሜሪካ በሳዑዲ አረቢያ የሚገኝ ጦሯን ለመቀነስ ወይም የተወሰነውን ወታደራዊ ኃይል ከሳዑዲ አስወጥታ ወደ ሌላ ቦታ ለማዘዋወር እያሰበች እንደሆነ ዋል ስትሪት ጆርናል የተመለከተውን ሪፖርት ጠቅሶ ዘገበ። አሜሪካ ይሄንን እርምጃ ለመውሰድ እያሰበች ያለው በዋሽንግተን እና በሪያድ መካከል ያለውን ውጥረት ተከትሎ ነው ተብሏል።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 9 ሰአት በፊትዜጋዬ ተገድሏል ያለችው ጋና ከደቡብ አፍሪካ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ ውስጥ ገባችዶላ እና ጋሻ የያዙ ተቃዋሚ ሰልፈኞችየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ማክሰኞ ዕለት አፍሪካውያን ስደተኞች ደቡብ አፍሪካን ለቅቀው የሚጠይቁ ሰልፈኞች በተለያዩ ከተሞች አደባባይ ወጥተው ነበርአንድ ጋናዊ በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ካለው ፀረ ስደተኞች ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ተገደለ መባሉን ተከትሎ በሁለቱ አገራት መካከል ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ ተቀስቅሷል።የጋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዜጋው ኬፕ ታውን ውስጥ በመገደሉ ይፋዊ ተቃውሞውን እና ለፖሊስ አቤቱታ ማቅረቡን ገልጿል።የደቡብ አፍሪካ የፍትሕ ሚኒስትር ግን “የጋና ባለሥልጣናት መደበኛ ካልሆኑ ስደተኞች ጋር በተያያዘ ባለው ሁኔታ ላይ የሐሰት መረጃዎችን እያስተላለፉ ነው” ሲሉ ተቃውሞ አሰምተዋል።የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ በበኩሉ ተገደለ ስለተባለው ጋናዊ መረጃ እንደሌለው፤ ነገር ግን ከወንጀል ጋር በተያያዘ ስለተገደለ ሌላ ጋናዊ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አሳውቋል።የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሥልጣን የሆኑት ክሌይሰን ሞንዬላ ከፀረ ስደተኞች ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ጋናዊ ተገድሏል መባሉን “የፈጠራ ታሪክ ነው” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።ጋና በዜጋዋ ላይ የተፈጸመውን ግድያ በመቃወም ባወጣችው መግለጫ “የማንንም ሕይወት መንጠቅ ተቀባይነት የሌለው ድርጊት በመሆኑ ተጠያቂዎቹ በአፋጣኝ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው” ስትል ጠይቃለች።”የደቡብ አፍሪካ ባለሥልጣናት በግድያው ዙሪያ ፈጻሚዎቹ ተይዘው ለፍርድ እንዲቀርቡ የሚደያርግ ሙሉ፣ ግልጽ እና ፈጣን ምርመራ እንዲያደርጉ እንፈልጋለን” ብሏል የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ።የጋና አንድ ሬዲዮ ጣቢያ እንደዘገበው የተገደለው ጋናዊ ለ20 ዓመታት ያህል በደቡብ አፍሪካ ውስጥ የኖረ የልብስ ስፌት ባለሙያ እየነበረ ሲሆን በተቃዋሚዎች በጥይት ተገድሏል። አስከሬኑን ወደ አገሩ ለመውሰድ በጋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ጥረት እየተደረገ ነው።ባለፈው ማክሰኞ ፀረ ስደተኞች ተቃዋሚዎች አፍሪካውያን ስደተኞች ደቡብ አፍሪካን ለቅቀው እንዲወጡ ያስቀመጡት ቀነ ገደብ የነበረ ሲሆን፣ በተለያዩ ከተሞች ውስጥ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል።ጋና፣ ማላዊ እና ናይጄሪያ ከቀነ ገደቡ በፊት የተወሰኑ ዜጎቻቸውን ከደቡብ አፍሪካ ካስወጡ አገራት መካከል ናቸው። እስካሁን 25 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ደቡብ አፍሪካን ለቅቀው ወጥተዋል።ያጋሩ, ዜጋዬ ተገድሏል ያለችው ጋና ከደቡብ አፍሪካ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ ውስጥ ገባች