የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ዋሽንግተን ከቴህራን ጋር የምታደርገው ድርድር እየተካሄደ ያልሆነው ሁለቱ አገራት የቀድሞው የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሌ ኻሜኒ የቀብር ስነ ስርዓት እስከሚጠናቀቅ በመወሰናቸው መሆኑን ለአክሲዮስ ተናገሩ። ትራምፕ፤ የኻሜኒ የቀብር ስነ ስርዓት ላይ የተወሰኑ ኢራናውያን ሲያለቅሱ በመመልከታቸው እንደተገረሙ ከአሜሪካው የዜና ምንጭ ጋር ባደረጉት የስልክ ቃለ መጠይቅ ገልጸዋል።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 1 ሰአት በፊትኢራን እና ኳታር ከአምስት ወራት በኋላ በድጋሚ የባሕር ንግድ ግንኙነት ጀመሩመርከብየፎቶው ባለመብት,Reuters“ለአምስት ወራት ገደማ” ተቋርጦ የነበረው የኢራን እና ኳታር የባህር የንግድ ግንኙነት በድጋሚ መጀመሩን በዶሃ የሚገኘው የኢራን የንግድ አታሼ አስታወቀ።ባለፈው የካቲት ላይ በአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት የተከፈተባት ኢራን፤ በወሰደችው የአጸፋ እርምጃ ዒላማ ካደረገቻቸው አገራት አንዷ ኳታር ነች። ኳታር ውስጥ የሚገኝ የአሜሪካ የጦር ሰፈር ጭምር በኢራን ተመትቷል።የዋሽንግተን እና ቴህራን ጦርነት ለመቋጨት የሚያደርጉትን ንግግር ከሚያሸማግሉ አገራት አንዷ ኳታር ነች።ሁለቱ አገራት የተቋረጠውን የባሕር ንግድ ልውውጥ እንደሚቀጥሉ የተሰማው፤ የኳታር ትራንስፖርት ሚኒስቴር የአገሪቱ የመርከብ ጉዞ እና ማሪታይም እንቅስቃሴ በድጋሚ መጀመሩን ካስታወቀ በኋላ ነው።የንግድ ልውውጡ የተጀመረው “ከሚመለከታቸው የኳታር መንግስት ባለስልጣናት ጋር በተደረገው ቅንጅት” አማካኝነት መሆኑን በኳታር የኢራን የንግድ አማካሪ የሆኑት አባስ አብዱልኻኒ ለቴህራን መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።ከዚህ አስቀድሞ መግለጫ ያወጣው የኳታር ትራንስፖርት ሚኒስቴር፤ ”በማንኛው ዓይነት መርከቦች እና የባህር ላይ ተሽከርካሪዎች” የሚደረግ ጉዞ መከፈቱን አስታውቆ ነበር። ሚኒስቴሩ ይህንን ከማለቱ አንድ ሳምንት በፊት ከንግድ መርከብ ውጪ ያሉ የባሕር ላይ ጉዞዎች እንዳይደረጉ አሳስቦ ነበር።ያጋሩ, ኢራን እና ኳታር ከአምስት ወራት በኋላ በድጋሚ የባሕር ንግድ ግንኙነት ጀመሩ