
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ከኢራን ጋር ስምምነት ላይ የማይደረስ ከሆነ የተጀመረውን “ስራ እንደሚያጠናቅቁ” መናገራቸውን ተከትሎ፤ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዛቻ እስከቀጠለ ድረስ ድርድር እንደማይጀመር ገለጹ።
ጭምቅ ሃሳብ
- የኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣናት በታደሙበት የቀድሞው መሪ አያቶላህ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ጠቅላይ መሪው ሳይገኙ ቀሩ
- በአያቶላህ አሊ ኻሜኒ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ የሚታየው ቀይ ባንዲራ ምንድን ነው?
- ኢራን ለአያቶላህ አሊ ኻሜኒ ግድያ “ፍትሕ እንደምትፈልግ” የጦር አዛዧ ተናገሩ
- “ስምምነት ላይ እንደርሳለን አልያም የጀመርነውን እንጨርሳለን“- ትራምፕ
- የኻሜኒ ገዳዮች ላይ “የበቀል እርምጃ እንዲወሰድ” ኢራናውያን ጠየቁ
የቀጥታ ሽፋን
- ከ 6 ሰአት በፊትየፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት በሶርያ ጉብኝት ላይ ሳሉ በደረሰ ፍንዳታ 18 ሰዎች ተጎዱ
የፎቶው ባለመብት,Reutersበሶርያ ዋና ከተማ ደማስቆ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አርፈውበት የነበረ ሆቴል አቅራቢያ በተከሰተ ፍንዳታ 18 ሰዎች መጎዳታቸውን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።የጸጥታ ኃይሎች ሁለት ፈንጂ መሣሪያዎችን አግኝተው የማክሸፍ እንቅስቃሴ ሲጀምሩ ፍንዳታው መድረሱን ‘ሳና’ የተባለው የመንግስት የዜና ወኪል ዘግቧል።ዘገባው እንደሚያመለክተው፤ አንደኛው መሣሪያ የቆመ ተሽከርካሪ ውስጥ ተቀምጦ ነበር፤ ሌላኛው ደግሞ በቆሻሻ ማጠራቀሚያ ተደብቋል።ከሶሪያው መሪ አህመድ አል ሻራ ጋር ለመወያየት ወደ ደማስቆ የተጓዙት ፕሬዝዳንት ማክሮን፤ በወቅቱ በፕሬዝዳንታዊው ቤተ መንግሥት ውስጥ ነበሩ። ፕሬዝዳንቱ ደህና እንደሆኑ እና ፍንታውን እንዳልሰሙ ባለስልጣናቶቻቸው ገልጸዋል።የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት የሶሪያ ጉብኝታቸውን ሲያጠናቅቁ ለኔቶ ጉባኤ ወደ ቱርክ እንደሚጓዙ ይጠበቃል።የሶርያ መገናኛ ብዙኃን እንደገለጹት፤ ከተጎዱት መካከል አራቱ የፖሊስ አባላት ናቸው። የአገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር የጥቃቱን ፈጻሚዎች ለመለየት ምርመራ እንደጀመረም ተዘግቧል።ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተለቀቁ ቪዲዮዎች እና ምስሎች፤ ሆቴል አቅራቢያ ከቆመ ተሽከርካሪ ላይ ጭስ እና እሳት ሲነሳ አሳይተዋል።ቢቢሲ አረቢክ ያነጋገራቸው አንድ የአይን እማኝ፤ የመጀመሪያው ፍንዳታ ሲከሰት በቱሪዝም ሚኒስቴር ዋና መሥሪያ ቤት ፊት ለፊት ቆመው እንደነበር ገልጸዋል።እማኙ እንደሚያስረዱት፤ የመጀመሪያው ቦምብ ከፈነዳ በኋላ የደኅንነት ኃይሎች አጠራጣሪ ቁሶችን እየፈለጉ ነበር። ይህንን በሚያደርጉበት ሰዓት “ከመጀመሪያው ፍንዳታ በግምት 20 ሜትር ያህል ርቀት ላይ ሁለተኛ ፍንዳታ” መከሰቱን ተናግረዋል።የዓይን እማኙ፤ “የመጀመሪያው ፍንዳታ ንብረቶችን ቢጎዳም፤ ሰው አልቆሰለም። ሁለተኛው ፍንዳታ ግን በበርካታ የደኅንነት ኃይሎች እና በትራፊክ ፖሊስ አባላት ላይ ጉዳት አድርሷል” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።ከፍንዳታው በኋላ ማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ የጻፉት ፕሬዝዳንት ማክሮን፤ “ምንም ነገር የሶሪያ ሴቶች እና ወንዶች በሙሉ ሉዓላዊነቷ፣ ደህንነቷ፣ ብዝሃነቷ እና አንድነቷ በተጠበቀ ሶሪያ ለመኖር ያላቸውን ምኞት አያደናቅፍም” ብለዋል።
የፎቶው ባለመብት,Reutersያጋሩ, የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት በሶርያ ጉብኝት ላይ ሳሉ በደረሰ ፍንዳታ 18 ሰዎች ተጎዱ
