ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦችን መምታቷን ተከትሎ፤ አሜሪካ ቴህራን ላይ አዲስ ዙር ጥቃት ከፈተች። የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ፤ ቀጣይ መግለጫ እስከሚሰጥ ድረስ ወሳኙ የባሕር መተላለፊያ ሆርሙዝ ተዘግቶ እንደሚቆይ አስታውቋል። አብዮታዊ ዘቡ፤ ዋሽንግተን ጥቃት በፈጸመች በሰዓታት ልዩነት በዮርዳኖስ የሚገኝ የአሜሪካ ጦር ሰፈር መምታቱን ገልጿል።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. 12 ሀምሌ 2026የቀድሞ የኳታር አሚር ሼክ ሐማድ ቢን ካሊፋ አል ታኒ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩየቀድሞው አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሐማድ አልየፎቶው ባለመብት,Reutersለ18 ዓመታት ኳታርን የመሩት እና የአሁኑ የአገሪቱ መሪ አባት የሆኑት የቀድሞው አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሐማድ አል ታኒ በ74 ዓመታቸው ሕይወታቸው ማለፉን የኳታር መንግሥት አስታወቀ።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቀድሞው መሪ ሕልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።የዘመናዊት ኳታር አርክቴክት ተብለው የሚታወቁት የቀድሞው መሪ ሕይወታቸው ያለፈው ዛሬ እሁድ እንደሆነ የአገሪቱ መንግሥት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።የቀድሞው መሪ አገሪቱን በመሩበት ከአውሮፓውያኑ 1995 እስከ 2013 ባለው ጊዜ ውስጥ ኳታር ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገት አስመዝግባለች።አነስተኛ በርሃማ አገር የነበረችው ኳታር ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገት፣ ዓለም አቀፍ እውቅና እንዲሁም ፖለቲካዊ ተጽዕኖ የማሳደር እንቅስቃሴ የጀመረችው በሼክ ሐማድ ቢን ካሊፋ አል ታኒ የሥልጣን ዘመን እንደነበር ሮይተርስ ዘግቧል።በእነዚህ ዓመታት ኳታር በባሕረ ሰላጤው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሆና መውጣት ችላለች። ኳታር የአረብ አብዮት “አረብ ስፕሪንግ” ተብሎ የሚታወቀውን የአረብ አገራት የተቃውሞ እንቅስቃሴ ስትደግፍ የነበረ ሲሆን በሶሪያ እና ሊቢያም ከአማጺያን ጎን ነበረች።በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጠቃሽ መገናኛ ብዙኃን የሆነው አልጀዚራም የተቋቋመው በቀድሞው መሪ የሥልጣን ዘመን ነው።በሥልጣን ዘመናቸው ቋሚ ሕገ መንግሥት እንዲኖር ያደረጉ ሲሆን የአካባቢ ምርጫም ተካሂዷል። ኳታር የ2022 ዓለም ዋንጫን የማዘጋጀት ዕድል ያገኘችው በእርሳቸው የመሪነት ዘመን ነው።ነጻ አስተሳሰብ የነበራቸው የቀድሞው መሪ፤ ብዙ ጊዜ ከአረብ ጎረቤቶቻቸው እና ምዕራባውያን አጋሮች ጋር ግጭት ውስጥ ይገቡ ነበር።የወታደራዊ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁት ብሪታኒያ ውስጥ ሲሆን ወደ አገራቸው ከተመለሱ በኋላ ወደ መሪነት ሥልጣን ከመምጣታቸው በፊት በሠራዊት አዛዥነት እና በመከላከያ ሚኒስትርነት አገልግለዋል።ሼክ ሐማድ ቢን ካሊፋ አል ታኒ ከ18 ዓመት የሥልጣን ዘመን በኋላ በ61 ዓመታቸው ሥልጣናቸውን ለልጃቸው አስረክበዋል።የቀድሞው አሚር በዚህ መልኩ ከሥልጣናቸው መውረዳቸው፤ መሪዎች እስከ ሞት ድረስ ሥልጣን ላይ በሚቆዩበት የባሕረ ሰላጤው ፖለቲካ የተለመደ አልነበረም።የቀድሞውን መሪ ሕልፈት ተከትሎ ከዛሬ ጀምሮ አራት የሐዘን ቀናት የታወጀ ሲሆን ከነገ ሰኞ እስከሚቀጥለው ሳምንት እሁድ ድረስ የመንግሥት ተቋማት እንደሚዘጉ ተገልጿል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአረብኛ ቋንቋ በፌስቡክ ባጋሩት ጽሑፍ፤ በአሚሩ ሞት የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል።የብሔራዊው የቴሌቪዥን ጣቢያ ትርጉም እንደሚያሳየው “ሼክ ሐማድ ቢን ኸሊፋ አል ታኒ በተለይም በአፍሪካ ቀንድ ሰላምን ለማስፈን፣ ለውይይትና ለድርድር መሠረት በመጣል ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ጥበበኛ መሪ እንደነበሩ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጽፈዋል።ለኢትዮጵያ “ትኩረት ይሰጡ” እንደነበር ያነሱት ዐቢይ፤ የቀድሞው መሪ የኢትዮጵያ ጉብኝት “ለሁለቱ ሀገራት ስትራቴጂያዊ አጋርነትና ለተፈረሙ የትብብር ስምምነቶች መሠረት የጣለ እንደነበር” መግለጻቸው ተዘግቧል።ያጋሩ, የቀድሞ የኳታር አሚር ሼክ ሐማድ ቢን ካሊፋ አል ታኒ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
  2. 12 ሀምሌ 2026አሜሪካ እና ኢራን ውጥረቱን እንዲያረግቡ አሸማጋይዋ ፓኪስታን ጠየቀችፓኪስታን የአሜሪካ እና ኢራን ድርድርን ባስተናገደችበት ወቅት ጎዳና ላይ የተሰቀሉ ቢልቦርዶችየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesበአሜሪካ እና ኢራን መካከል የሚደረገውን ንግግር ከሚያሸማግሉ አገራት አንዷ የሆነችው ፓኪስታን ሁለቱም ወገኖች ሰሞነኛውን ውጥረት እንዲያረግቡ ጠየቀች።የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢሻቅ ዳር ከኢራኑ አቻቸው አባስ አራግቺ ጋር በስልክ ተነጋግረዋል። ሁለቱ ሚኒስትሮች የተነጋገሩት ከዚህ ሳምንት መጀመሪያ አንስቶ ያገረሸው የሁለቱ አገራት የጥቃት ልውውጥ ትናንት ሌሊትም ከቀጠለ በኋላ ነው።አሜሪካ በሆርሙዝ የሚጓዙ መርከቦች በኢራን እንደተመቱ በመግለጽ ትናንት ሌሊት የቴህራን ወታደራዊ ይዞታዎች ላይ ጥቃት መፈጸሟን አስታውቃለች። ኢራን በበኩሏ ሆርሙዝ ወሽመጥን የዘጋች ሲሆን የአሜሪካ ጦር ሰፈር የሚገኝባቸው የቀጣናው አገራት ላይ ጥቃት አድርሳለች።ከኢራኑ አቻቸው ጋር የተነጋገሩት የፓኪስታኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰኔ ላይ በተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት መሠረት “ሁለቱም አካላት ውጥረትን የሚያረግብ መንገድን እንዲከተሉ እና [ከጥቃት] እንዲታቀቡ” መጠየቃቸውን መሥሪያ ቤታቸው አስታውቋል።የፓኪስታን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ ኢሻቅ ዳር “ግጭቶችን ለመፍታት እንዲሁም በቀጣናው ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋትን ለማስፈን ብቸኛው አዋጭ መንገድ ንግግር እና ዲፕሎማሲ መሆኑንም አስምረውበታል” ብሏል።በተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት መሠረት ሁለቱም አገራት ጥቃቶችን አቁመው ለመጨረሻ ድርድር መቅረብ ነበረባቸው። አሁን ውጥረቱ በማገርሸቱ የቀጣይ ድርድር እጣ ፋንታ ምን እንደሚሆን እስካሁን በግልፅ አልታወቀም።ያጋሩ, አሜሪካ እና ኢራን ውጥረቱን እንዲያረግቡ አሸማጋይዋ ፓኪስታን ጠየቀች
  3. 12 ሀምሌ 2026ኢራን በድጋሚ ሆርሙዝ ወሽመጥን ስትዘጋ፤ አሜሪካ ቴህራን ላይ አዲስ ዙር ጥቃት ከፈተችመርከቦችየፎቶው ባለመብት,Reutersኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦችን መምታቷን ተከትሎ አሜሪካ ቴህራን ላይ አዲስ ዙር ጥቃት ከፈተች።የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ፤ ቀጣይ መግለጫ እስከሚሰጥ ድረስ ወሳኙ የባሕር መተላለፊያ ሆርሙዝ ተዘግቶ እንደሚቆይ አስታውቋል።ለአሜሪካ “ጥቃትም” ከባድ ምላሽ እንደሚሰጥ መግለጹን የኢራን የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።አብዮታዊ ዘቡ፤ ዋሽንግተን ጥቃት በፈጸመች በሰዓታት ልዩነት በዮርዳኖስ የሚገኝ የአሜሪካ ጦር ሰፈር መምታቱን ገልጿል።የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ኳታር፣ ኩዌት እና ባህሬን በበኩላቸው ከኢራን ለተተኮሱባቸው ሚሳዔሎች እና ድሮኖች ምላሽ እየሰጡ መሆኑን አስታውቀዋል።ጋብ ብሎ የነበረው የሁለቱ አገራት ጦርነት በድጋሚ የተቀሰቀሰው በዚህ ሳምንት መጀመሪያ በሦስት ነዳጅ ጫኝ የንግድ መርከቦች ላይ ጥቃት ከደረሰ በኋላ ነው።ለዚህ ጥቃት ምላሽ የሰጠችው አሜሪካ ኢራንን ከደበደበች በኋላ የጥቃት ልውውጡ አገርሽቷል።የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ ባወጣው መግለጫ በዚህ ሳምንት ሦስተኛ ዙር ጥቃት የከፈተው የኢራን አብዮታዉ ዘብ የቆጵሮስ ሰንደቅ ዓላማን እያውለበለበ በሆርሙዝ ወሽመጥ ይጓዝ የነበረ መርከብን “በግልጽ ስላጠቃ” እንደሆነ ገልጿል።’ኤምቪ ጂኤፍኤስ ጋላክሲ’ የተባለው መርከብ የሞተር ክፍሉ ላይ በደረሰው ከፍተኛ ጉዳት የተነሳ “ጉዞውን መቀጠል እንዳልቻለ” ማዕከላዊ ዕዙ አስታውቋል። አንድ ሲቪል የመርከብ ሠራተኛ መጥፋቱንም ገልጿል።እንደ ዕዙ ገለጻ ኢራን ላይ በተፈጸመው ጥቃት የሚሳዔል እና ድሮን ሠፈሮች፣ የኮሚዩኒኬሽን ኔትዎርኮች እንዲሁም የባሕር ኃይል የክትትል ሥፍራዎችን ጨምሮ 140 የቴህራን ወታደራዊ ዒላማዎች ተመትተዋል።የኢራን አብዮታዊ ዘብ በበኩሉ የአሜሪካ ጥቃት “ደቡባዊ የባሕር ዳርቻ ላይ የሚገኙ በርካታ የባሕር ዳርቻ የጦር ሰፈሮችን እና የቴሌኮሚዩኒኬሽን ማማዎችን” ዒላማ ማድረጉን አስታውቋል።ለዚህ ጥቃት በተሰጠው “የመጀመሪያ ዙር” ምላሽ፤ ዮርዳኖስ ውስጥ የሚገኘውን ‘ፕሪንስ ሀሰን’ የአየር ኃይል ጦር ሰፈር እንዲሁም ሌሎች ዒላማዎችን መምታቱን ገልጿል። እንደ ኢራን ገለጻ በጥቃቱ የጦር ሰፈሩ የዕዝ እና ቁጥጥር ማዕከል እንዲሁም የኤምኪው9 ድሮን ማቆሚያዎች ወድመዋል።ከዚህ አስቀድሞ ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን መዝጋቷን የአገሪቱ መንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።ዘገባዎቹ እንደሚያስረዱት መተላለፊያው የተዘጋው የኢራን ጦር ባልተፈቀደ መስመር ለመጓዝ በሞከረ መርከብ ላይ ክሩዝ ሚሳዔል ካስወነጨፈ በኋላ ነው።እንደ አብዮታዊ ዘቡ ገለጻ፤ መርከቡ የተሰጡትን ትዕዛዞች በተደጋጋሚ ችላ በማለቱ “በማስጠንቀቂያ ተኩስ እንዲመታ እና እንዲቆም” ተደርጓል።ሆርሙዝ በመዘጋቱ ምክንያት ለሚፈጸም ማንኛው የአሜሪካ “ጥቃት”፤ የሚሰጠው ምላሽ “ከባድ” እንደሚሆን እና በቀጣናው የሚገኙ አዲስ የጦር ሰፈሮች ዒላማ እንደሚደረጉ አስጠንቅቆ ነበር።ያጋሩ, ኢራን በድጋሚ ሆርሙዝ ወሽመጥን ስትዘጋ፤ አሜሪካ ቴህራን ላይ አዲስ ዙር ጥቃት ከፈተች
  4. 11 ሀምሌ 2026የኢራን ጠቅላይ መሪ ለአባታቸው ግድያ “የበቀል እርምጃ” እንደሚወሰድ ተናገሩሞጅታባ ኻሜኒየፎቶው ባለመብት,Tasnim News Agencyየኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ በጽሑፍ ባስተላለፉት መልዕክት አባታቸው ላይ ለተፈጸመው ግድያ “የበቀል እርምጃ” መወሰድ እንዳለበት አሳሰቡ።የቀድሞው ጠቅላይ መሪ አያቶላህ ዓሊ ኻሜኒ አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጦርነት በከፈቱበት የመጀመሪያው ቀን መገደላቸው ይታወሳል።የአባታቸው የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ለተገኙ ሰዎች ምስጋና ያቀረቡት ሞጅታባ ኻሜኒ “ንጹህ ደምን ለመበቀል ቃል እንገባለን” ብለዋል።“ወንጀለኛ እና የተዋረዱ ገዳዮች በከፈቷቸው ሁለት ጦርነቶች ለተገደሉ ሰማዕታትም የበቀል እርምጃ ይኖራል” ሲሉም አክለዋል።አዲሱ ጠቅላይ መሪ “ይህ በቀል የአገራችን ፍላጎት ነው። እንደምንፈጽመው ጥርጥር የለም” ብለዋል።የአባታቸው አያቶላህ ዓሊ ኻሜኒን ግድያ ተከትሎ አዲሱ ጠቅላይ መሪ ኃላፊነቱን ተረክበዋል።እስካሁን ድረስ በይፋ ያልታዩ ሲሆን በቪድዮ እና በድምጽም መልዕክት አላስተላለፉም።በአባታቸው የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ያልተገኙት ሞጅታባ ኻሜኒ መልዕክት የሚያደርሱት በጽሑፍ ብቻ ነው።ያጋሩ, የኢራን ጠቅላይ መሪ ለአባታቸው ግድያ “የበቀል እርምጃ” እንደሚወሰድ ተናገሩ
  5. 11 ሀምሌ 2026ኢራን እና ኦማን ስለ ሆርሙዝ ወሽመጥ ሊወያዩ ነውአባስ አራግቺ ከኦማን ባለሥልጣናት ጋርየፎቶው ባለመብት,isnaየኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ከኦማን ባለሥልጣናት ጋር ለመወያየት ሙስካት መግባታቸው ተገለጸ።ኢራን እና ኦማን የሆርሙዝ ወሽመጥን ጨምሮ ቀጣናዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ውይይት እንደሚያደርጉም ተገልጿል።በኢስላማባድ ስምምነት አንቀጽ 5 መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል “ተገቢውን መተላለፊያ” ለማበጀት እንደሚወያዩ ተዘግቧል።የሆርሙዝ ወሽመጥ ጉዳይ በኢራን እና አሜሪካ መካከል ከፍተኛ ውጥረት አስከትሏል።የኳታር ልዑካን ከኢራን ባለሥልጣናት ጋር ለመወያየት ወደ ቴህራን አምርተዋል።የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ፣ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አማች ጃሬድ ኩሽነር፣ የአሜሪካ ልዩ ልዑክ ስቲቭ ዊትኮፍ እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮም ወደ ኦማን እንደሚሄዱ የሚጠቁሙ መረጃዎች ወጥተዋል።ያጋሩ, ኢራን እና ኦማን ስለ ሆርሙዝ ወሽመጥ ሊወያዩ ነው
  6. 11 ሀምሌ 2026ኢራን ከአሜሪካ ጋር ለመደራደር አለመጠየቋን አስታወቀችኢስማኤል ባጋይየፎቶው ባለመብት,isnaየኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢስማኤል ባጋይ፤ አገራቸው ከአሜሪካ ጋር ለመደራደር ጥያቄ አለማቅረቧን ተናገሩ።ነገር ግን ድርድር ለማድረግ ከቀጣናዊ አሸማጋይ የቀረበላቸውን ጥያቄ ተቀብለዋል። አሸማጋዮች ወደ ቴህራን አቅንተው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚደረግ ተናግረዋል።“ከአሜሪካ ጋር ለመደራደር አልጠየቅንም። ሆኖም ግን ሁልጊዜም ኃላፊነት ስለሚሰማን ቀጣናዊ አደራዳሪዎችን አሻፈረኝ አላልናቸውም” ብለዋል ቃል አቀባዩ።የመግባቢያ ሰነዱ ከተፈረመ ሳምንታት ብቻ ቢቆጠሩም “አሜሪካ ብዙ የስምምነቱን ክፍል መጣሷን” ተናግረዋል።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ድርድሩ እንዲቀጥል መስማማታቸውን ገልጸዋል።አሜሪካ እና ኢራን ድርድራቸውን ለመቀጠል መስማማታቸውን ትራምፕ ያሳወቁት ኳታር ከአሜሪካ ጋር በመቀናጀት አሸማጋዮችን ከአገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር እንዲነጋገሩ ወደ ቴህራን ከላከች በኋላ ነው።ያጋሩ, ኢራን ከአሜሪካ ጋር ለመደራደር አለመጠየቋን አስታወቀች
  7. 11 ሀምሌ 2026ትራምፕ፤ ኢራን ልትገድላቸው ከሞከረች ከፍተኛ ጥቃት እንደሚፈጸምባት ተናገሩትራምፕየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ኢራን ግድያ ልትፈጽምባቸው የምትሞክር ከሆነ ከፍተኛ ጥቃት እንደሚደርስባት ዛቱ።በትሩዝ ሶሻል የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ “አንድ ሺህ ሚሳዔሎች ኢራን ላይ አነጣጥረው እየጠበኩ ነው” በማለት ጽፈዋል።የኢራን መንግሥት የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ለመግደል ከሞከረ “ተጨማሪ አንድ ሺህ ሚሳዔሎች በፍጥነት እንደሚዘጋጁ” አስጠንቅቀዋል።“ኢራንን ሙሉ በሙሉ ለማውደም” ትዕዛዝ እንደተሰጠ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ የአሜሪካ ወታደሮች በተጠንቀቅ መቆማቸውን አክለዋል። የማኅበራዊ ሚዲያ መልዕክታቸውንም “አላህ ይመስገን” በሚል ጽሑፍ አጠናቀዋል።ኢራን ትራምፕን ለመግደል አሲራለች የሚል የስለላ መረጃ እስራኤል ለአሜሪካ አቀብላለች።በቀድሞው ጠቅላይ መሪ አያቶላህ ዓሊ ኻሜኒ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ትራምፕ እንዲገደሉ የሚጠይቁ መፈክፎች ታይተዋል፤ ተደምጠዋል።የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ፕሬዝዳንቱን ለመግደል መወጠኑን አስተባብሏል።ያጋሩ, ትራምፕ፤ ኢራን ልትገድላቸው ከሞከረች ከፍተኛ ጥቃት እንደሚፈጸምባት ተናገሩ
  8. 11 ሀምሌ 2026ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ላይ ላለመተኮስ በይፋ ቃል እንድትገባ አሜሪካ ጠየቀችየሆርሙዝ ወሽመጥየፎቶው ባለመብት,Reutersኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥ እንደሚከፈት እና በወሽመጡ የሚያልፉ መርከቦች ላይ ጥቃት እንደማታደርስ በይፋ ቃል እንድትገባ እንደምትፈልግ አሜሪካ አስታወቀች።የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ማንነታቸው ያልተገለጸ ባለሥልጣንን ጠቅሰው እንደዘገቡት፤ ቴህራን ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አማካሪዎች በግል በሰጠችው ማብራሪያ መርከቦች ላይ መተኮሷ ስህተት መሆኑን አምናለች።ኢራን ጥቃቱ የተፈጸመው ከቁጥጥር ውጭ በሆኑ ውስጣዊ ኃይሎች መሆኑን አስታውቃለች።ባለፉት ቀናት የተኩስ ልውውጥ ቢያደርጉም ሁለቱም ወገኖች ንግግራቸውን ለመቀጠል መስማማታቸውን ትራምፕ ተናግረዋል።ኢራን እና አሜሪካ የፈረሙት የመግባቢያ ሰነድ፤ ቴህራን በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚያልፉ መርከቦች ደኅንነታቸው እንዲጠበቅ ታደርጋለች።ከሰሞኑ የተነሳው ግጭት የመግባቢያ ሰነዱን ያፈረሰ መሆኑን ሁለቱም አገራት ገልጸዋል።በኢራን እና በአሜሪካ መካከል የሚደረገው ድርድር እንዲቀጥል መስማማታቸውን የገለጹት ትራምፕ፤ ቀደም ሲል የነበረው የተኩስ አቁም ስምምነት ግን ማብቃቱን ለቴህራን ማሳወቃቸውን ተናግረዋል።ቴህራን በመሠረተ ልማቶቿ ላይ ጥቃት የሚፈጸም ከሆነ አጸፋውን እንደምትመልስ አስጠንቅቃለች።ያጋሩ, ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ላይ ላለመተኮስ በይፋ ቃል እንድትገባ አሜሪካ ጠየቀች
  9. 10 ሀምሌ 2026ፕሬዝዳንት ትራምፕ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ድርድር ለመጀመር መስማማታቸውን ገለጹትራምፕየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ፕሬዝዳንት ትራምፕበኢራን እና በአሜሪካ መካከል የሚደረገው ድርድር እንዲቀጥል መስማማታቸውን፤ ነገር ግን ቀደም ሲል የነበረው የተኩስ አቁም ማብቃቱን ለኢራን እንዳረጋገጡላቸው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ተናገሩ።”የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ድርድሩን እንድንቀጥል ጠይቀውናል። እኛም ይህንን ለማድረግ ተስማምተናል” በማለት ፕሬዝዳንት ትራምፕ በትሩዝ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።አክለውም “ነገር ግን አሜሪካ ተደርሶ የነበረው የተኩስ አቁም ማብቃቱን በማያሻማ ሁኔታ አሳውቃቸዋለች” ብለዋል።ለወራት የዘለቀውን ጦርነት ለማስቆም ሁለቱ አገራት ከሳምንታት በፊት የመግባቢያ ስምምነት ደርሰው ግጭቱ ጋብ ብሎ የነበረ ቢሆንም ካላፈው ማክሰኞ ጀምሮ አሜሪካ በከፈተችው ጥቃት ጦርነቱ ዳግም ተቀስቅሷል።አሜሪካ እና ኢራን ድርድራቸውን ለመቀጠል መስማማታቸውን ትራምፕ ያሳወቁት ኳታር ከአሜሪካ ጋር በመቀናጀት አሸማጋዮችን ከአገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር እንዲነጋገሩ ወደ ቴህራን ከላከች በኋላ ነው።አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን ለሲኤንኤን እንደተናገሩት የትራምፕ አስተዳደር ስትራቴጂ በኢራን ላይ ጥቃት በመሰንዘር ግጭቱ እንዳይባባስ ጋብ በማድረግ ለዲፕሎማሲያዊ ጥረት በር መክፈት ነው።ያጋሩ, ፕሬዝዳንት ትራምፕ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ድርድር ለመጀመር መስማማታቸውን ገለጹ
  10. 10 ሀምሌ 2026የኻሜኒ ድረ ገጽ የቀድሞውን ጠቅላይ መሪ የመቃብር ቦታ ምሥል ይፋ አደረገየቀድሞው ጠቅላይ መሪ የመቃብር ሥፍራየፎቶው ባለመብት,.የቀድሞው የኢራን ጠቅላይ መሪ የኻሜኒ ድረ ገጽ የኢራንን እስላማዊ ሪፐብሊክ የቀድሞ መሪ የመቃብር ሥፍራን የሚያሳይ ምሥል ይፋ አደረገ።ኻሜኒ የቀብር ሥነ ሥርዓት ከሌሎች አራት የቤተሰብ አባሎቻቸው ጋር ሐሙ ዕለት በሰሜን ምሥራቅ ኢራን ውስጥ በምትገኘው ቅዱስ ከተማ ማሻድ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተገኙበት ተፈፅሟል።የቀድሞው ጠቅላይ መሪ በመጀመሪያው ቀን የእስራኤል እና የአሜሪካ የተቀናጀ ጥቃት የተገደሉት ከአራት ወራት በፊት ነበር።ከእርሳቸውም ጋር በርካታ የኢራን ወታደራዊ እና የፖለቲካ ባለሥልጣናት እንዲሁም ሴት ልጃቸው ቡሽራ ኻሜኒ፣ የልጅ ልጃቸው ዛህራ ሞሃመዲ፣ የልጃቸው ሞጅታባ ኻሜኒ ሚስት ዛህራ ሃዳድ እና የልጃቸው ሆዳ ኻሜኒ ባል ኢስባህ ኡል ሃዳ ባጌሪ ተገድለዋል።በቀድሞው ጠቅላይ መሪ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ የአገራት መሪዎች እና ባለሥልጣናት የተገኙ ሲሆን እርሳቸውን የተካው ልጃቸው ሞጅታባ ኻሜኒ አልተገኘም።የኻሜኒ የቀብር ሥነ ሥርዓት የተፈፀመው ፕሬዝደንት ትራምፕ “ተኩስ አቁሙ አብቅቷል” ካሉ በኋላ አሜሪካ በኢራን ላይ የከፈተችው ጥቃት ለሁለተኛ ቀን በቀጠለበት ጊዜ ነበር።ያጋሩ, የኻሜኒ ድረ ገጽ የቀድሞውን ጠቅላይ መሪ የመቃብር ቦታ ምሥል ይፋ አደረገ
  11. 10 ሀምሌ 2026ኢራን መሠረተ ልማቶቿ ከተመቱ በአሜሪካ እና በእስራኤል ላይ ጥቃት እንደምትፈጽም አስታወቀችአውሮፕላን ተሸካሚ የአሜሪካ የጦር መርከብየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ከማክሰኞ ሌሊት ጀምሮ አሜሪካ በኢራን ላይ ጥቃት እየፈጸመች ነውበኢራን እና በአሜሪካ መካከል ግጭቱ ካገረሸ በኋላ በመሠረተ ልማቶቿ ላይ ጥቃት የሚፈጸም ከሆነ አጸፋውን እንደምትመልስ እና እስራኤልም ከኢራን የአጸፋ ጥቃት እንደማትተርፍ የኢራን የብሔራዊ ደኅንነት የበላይ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ አስጠነቀቁ።ዋና ፀሐፊው ሞሐመድ ባቂር ዞልቃድር በአገሪቱ ቴሌቪዥን በተላለፈ መግለጫቸው “ቀደም ሲል እንዳስታወቅነው በመሠረተ ልማቶቻችን ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች አጸፋን የሚያስከትሉ ሲሆን፣ ከእነዚህ ክፋቶች ጀርባ ያለው ወንጀለኛው ጽዮናዊ መንግሥትም ተዋጊዎቻችን ከሚፈጽሙት ጥቃት የሚያመልጥ አይሆንም” ሲሉ ተናግረዋል።ተኩስ አቁም አድርገው የነበሩት አሜሪካ እና ኢራን በዚህ ሳምንት መጀመሪያ አካባቢ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ በሚተላለፉ መርከቦች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ወደ ግጭት ተመልሰዋል።አሜሪካ፣ ኳታር እና ሳዑዲ አረቢያ በሦስት መርከቦች ላይ ለተፈጸመው ጥቃት ኢራንን ተጠያቂ ሲያደርጉ ኢራን ግን አስተባብላለች።በመርከቦቹ ላይ ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ አሜሪካ ከማክሰኞ ሌሊት ጀምራ ኢራን ውስጥ በሚገኙ በርካታ ዒላማዎች ላይ ጥቃት ስትፈጽም፣ ኢራን ደግሞ በፋርስ ባሕረ ሰላጤው አገራት ውስጥ በሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች ላይ የአጸፋ እርምጃ ወስዳለች።ያጋሩ, ኢራን መሠረተ ልማቶቿ ከተመቱ በአሜሪካ እና በእስራኤል ላይ ጥቃት እንደምትፈጽም አስታወቀች
  12. 10 ሀምሌ 2026ሜክሲኮ በአሜሪካ ይዞታ ሥር ሆነው የሞቱ ዜጎቿን በተመለከተ ክስ ልትመሠርት ነውበስደተኞች እና ጉምሩክ ባለሥልጣን የተገደለው ሎሬንዞ ሳልጋዶ አሩጆ ቤተሰቦችየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በስደተኞች እና ጉምሩክ ባለሥልጣን የተገደለው ሎሬንዞ ሳልጋዶ አሩጆ ቤተሰቦችሜክሲኮ በአሜሪካ ይዞታ ሥር እያሉ የሞቱ ዜጎቿን በተመለከተ የወንጀል ክስ እንደምትመሠርት አስታወቀች።የሜክሲኮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሮቤርቶ ቬልሳኮ እንደተናገሩት ብዙ ዜጎቻቸው በአሜሪካ ይዞታ ሥር ሳሉ በመሞታቸው “የሕግ እርምጃ” ይወስዳሉ።በአሜሪካ የስደተኞች እና ጉምሩክ ባለሥልጣን (አይስ) ተይዘው የነበሩ 14 የሜክሲኮ ዜጎች መሞታቸውን ገልጸዋል። ሦስት ተጨማሪ ዜጎቻቸው ደግሞ “በእስር ሒደት ላይ” መሞታቸውን ተናግረዋል።ሜክሲኳውያኑ መሞታቸው በአገሪቱ ካስነሳው ተቃውሞ በተጨማሪ ያለፈው ረቡዕ በአሜሪካ ሂዩስተን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተቃውሞ ሰልፍ አድገዋል።የተቃውሞ ሰልፍ ከመካሄዱ አንድ ቀን አስቀድሞ ሎሬንዞ ሳልጋዶ አሩጆ የተባለ የሜክሲኮ ዜጋ በስደተኞች እና ጉምሩክ ባለሥልጣን ባልደረባ ተገድሏል።የአሜሪካ የአገር ውስጥ ደኅንነት መሥሪያ ቤት (ዲኤችኤስ) በኤክስ ገጹ ባወጣው መግለጫ “አይስ [የስደተኞች እና ጉምሩክ ባለሥልጣን] ሕገ ወጥ ሰውን በቁጥጥር ሥር ለማዋል በወሰደው የሕግ ማስከበር እርምጃ መኪና ለማስቆም ሞክሯል” ብሏል።ግለሰቡ የተገደለው “ከመያዝ ለማምለጥ ሲሞክር” እንደሆነም ገልጿል።ቤተሰቦቹ እንዳሉት ግን ሎሬንዞ ተተኩሶበት የተገደለው ወደ ሥራ እየሄደ ሳለ ነው።ያጋሩ, ሜክሲኮ በአሜሪካ ይዞታ ሥር ሆነው የሞቱ ዜጎቿን በተመለከተ ክስ ልትመሠርት ነው
  13. 10 ሀምሌ 2026በስፔን ሰደድ እሳት ቢያንስ 11 ሰዎች ሲሞቱ፣ 19 ሰዎች የደረሱበት አልታወቀምየእሳት አደጋ ሠራተኞችየፎቶው ባለመብት,Reutersበደቡብ ስፔን፣ አንዳሉሲያ ግዛት በተነሳው ሰደድ እሳት ምክንያት ቢያንስ 11 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ።የግዛቱ አስተዳዳሪ ጁአናማ ሞሬኖ እንዳሉት 19 ሰዎች እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም።በወደቀ የኤሌክትሪክ መስመር ምክንያት ሰደድ እሳቱ እንደተነሳ እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ስርጭቱን ለመቆጣጠር እየሞከሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።በደቡብ አውሮፓ እስከ 40 ዲግሪ ሴንቲግሬድ የሚደርስ የሙቀት ወጀብ መከሰቱ በተለያዩ አካባቢዎች ሰደድ እሳት እያስከተለ ነው።በፈረንሳይ፣ ፖርቹጋል እና ስፔን የእሳት አደጋ ሠራተኞች አደጋዎችን ለመቆጣጠር እየሞከሩ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።በስፔን በሰደድ እሳት የሞቱ 11 ሰዎች አስከሬን ቤዳር በተባለች አነስተኛ መንደር ውስጥ ተገኝቷል። አብዛኞቹ ሰዎች የውጭ አገራት ዜጎች መሆናቸውን የግዛቱ አስተዳዳሪ ተናግረዋል።ያጋሩ, በስፔን ሰደድ እሳት ቢያንስ 11 ሰዎች ሲሞቱ፣ 19 ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም
  14. 10 ሀምሌ 2026ቻይና በድጋሚ ጥቅም ላይ የሚውል ሮኬት አስወነጨፈችሎንግ ማርች 10ቢ የተባለው ሮኬትየፎቶው ባለመብት,China Aerospace Science and Technology Corporationቻይና በአገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በድጋሚ ጥቅም ላይ መዋል የሚችል ሮኬት ማስወንጨፏ ተገለጸ።በአገሪቱ የሕዋ ሳይንስ ዘርፍ ትልቅ ስኬት እንደሆነ ተመልክቷል።ዛሬ አርብ፤ ሎንግ ማርች 10ቢ የተባለው ሮኬት ከደቡባዊ ቻይና ሀይናን ተወንጭፎ ወደ ምድር መመለሱ ተገልጿል።አሜሪካ በድጋሚ ጥቅም ላይ የሚውሉ ሮኬቶች በማምረት በሕዋ ሳይንስ ያላትን ሥፍራ ቻይና መገዳደር የምትችልበት መንገድ ነው።የኢሎን መስክ ‘ስፔስ ኤክስ’ እና የጄፍ ቤዞስ ‘ብሉ ኦሪጅን’ እንደገና ጥቅም ላይ የሚውሉ ሮኬቶች ያመርታሉ።ሮኬቶች አንዴ ጥቅም ላይ ከዋሉ በኋላ መልሰው አገልግሎት እንደማይሰጡ ይታመናል።ከምድር ሮኬቶች ሲወነጨፉ ጉዳት ስለሚደርስባቸው እና በድጋሚ ጥቅም ላይ ስለማይውሉ የጠፈር መንኮራኩር መላክ ከፍተኛ ወጪ ይጠይቃል።ሮኬቶችን ለማስወንጨፍ የሚያስችለው ክፍል ዳግመኛ ጥቅም ላይ እንዲውል ማስቻል በከፍተኛ መጠን ወጪውን ይቀንሳል።ያጋሩ, ቻይና በድጋሚ ጥቅም ላይ የሚውል ሮኬት አስወነጨፈች
  15. 10 ሀምሌ 2026የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከአሜሪካ ጋር በማበሯ ዋጋ ትከፍላለች – ኢራንበዱባይ ከተማ የምሽት ሰማይ ላይ የሚታይ የኢራን ጥቃት የፈጠረው ጭስየፎቶው ባለመብት,Muskaan Katariaየምስሉ መግለጫ,ጦርነቱ በተፋፋመበት ጊዜ ኢታን ኤምሬትስን በሚሳዔሎች እና በድሮኖች በተደጋጋሚ አጥቅታለችየተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ለወራት ጥቃት እየፈጸመች ካለችው አሜሪካ ጋር የምታደርገው ትብብር ዋጋ ያስከፍላትል ሲሉ አንድ የኢራን የምክር ቤት አባል ተናገሩ።በኢራን ፓርላማ ውስጥ የብሔራዊ ደኅንነት ኮሚሽን አባል የሆኑት ኢስማኤል ኮዋሳሪ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አሜሪካ በአገራቸው ላይ እንደ አዲስ ከከፈተችው ጥቃት ጀርባ አለች ሲሉ ከስሰዋል።በዚህም ምክንያት አሜሪካ እየፈጸመችው ላለው ጥቃት ኤምሬትስ “ከዋሽንግተን ጋር ባላት ትብብር የተነሳ ዋጋ ትከፍላለች” ሲሉ የባሕረ ሰላጤዋን አገር አስጠንቅቀዋል።አስማኤል በተጨማሪም በኢራን ላይ እየተፈጸመ ካለው ጥቃት ጋር በተያያዘ “እየወሰደችው ባለቻቸው እርምጃዎች የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከኢራን ጠላቶች ጋር ተሰልፋለች፤ ለዚህም የሚያስከፍላት ዋጋ በጣም ከባድ እንደሚሆን ልታውቀው ይገባል” ብለዋል።የኢራን ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ቀደም ሲል እንዳስታወቁት “ለወራሪ” ኃይሎች ማንኛውንም ድጋፍ የሚሰጥ ከኢራን የአጸፋ ቅጣት ይጠብቀዋል በማለት ያስተላለፉትን ማስጠንቀቂያ የምክር ቤት አባሉ አጽንኦት ሰጥተው ጠቅሰዋል።ስለዚህም ኤምሬትስ በቀጣናው ያሉትን ለአሜሪካ ጦር ሰፈሮች በምትሰጠው ድጋፍ ምክንያት “የባሕር እንቅስቃሴ መስመሯ፣ የባቡር እና የአየር ትራንስፖርት መሠረተ ልማቶቿ እንዲሁም የነዳጅ እና የጋዝ ተቋማቷ የኢራን ጦር ሠራዊት እርምጃ በሚወስዱበት ጊዜ ዋነኛ ዒላማዎች ይሆናሉ” በማለት አስጠንቅቀዋል።ያጋሩ, የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከአሜሪካ ጋር በማበሯ ዋጋ ትከፍላለች – ኢራን
  16. 10 ሀምሌ 2026‘ዶናልድ ትራምፕን ለመግደል አዲሱ የኢራን ዕቅድ’ትራምፕ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው ከመድረግ ሲወርዱየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ትራምፕ ፔንሲልቬኒያ ውስጥ ለተደረገባቸውን የግድያ ሙከራ ኢራን ላይ ጣታቸውን ይጠቁማሉኢራን ከወራት በፊት በተከፈተባት ጦርነት ጠቅላይ መሪዋን እና ከፍተኛ ባለሥልጣናቷን የገደሉባትን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ለመበቀል አዲስ ዕቅድ ማውጣቷ ተዘገበ።ኢራን በፕሬዝዳንት ትራምፕ ላይ ግድያ ለመፈጸም አዲስ ዕቅድ ማዘጋጀቷን በተመለከተ እስራኤል ለአሜሪካ መረጃ መስጠቷን ዎል ስትሪት ጆርናል ጋዜጣ ዘግቧል።”የአሜሪካን መሪ፣ እኔን ሊገድሉ ይፈልጋሉ” እና “ስሜ በሁሉም ዝርዝራቸው ውስጥ ይገኛል” በማለት ፕሬዝዳንት ትራምፕ መረጃው እንዳሳሰባቸው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጉዳዩን በይፋ አንስተው በተደጋጋሚ መናገራቸውን እንደሚያመልክት ጋዜጣው ዘግቧል።እስራኤል የኢራንን ዕቅድ በተመለከተ ለፕሬዝዳንት ትራምፕ የሰጠችው መረጃ ከሁለት ዓመት በፊት ፔንሲልቬኒያ ውስጥ የተደረገባቸውን የግድያ ሙከራ የሚያካትት ሲሆን፣ ፕሬዝዳንቱም መረጃውን ከደኅንነት ስጋት ባሻገር ለፖለቲካ ዓላማቸው እየተጠቀሙበት መሆኑን አመልክቷል።የትራምፕ ተቺዎች መረጃውን ትራምፕ ከሕዝቡ ድጋፍ ለማግኘት የሚጠቀሙበት ነው ቢሉም፣ የኢራን አብዮታዊ ዘብ በቀድሞው የትራምፕ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ በነበሩት ጆን ቦልተን ላይ አድርጎታል የተባለው የግድያ ሙከራ በትራምፕም ላይ ሊፈጸም ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሯል።ከአውሮፓውያኑ 1950 ወዲህ የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች በነበሩት ጆን ኤፍ ኬኔዲ ላይ ከተፈጸመው ግድያ አንስቶ በትሩማን፣ በፎርድ እና በሬጋን ላይ ያልተሳኩ የግድያ ሙከራዎች ተፈጽመዋል።አንዳንዶች የግድያ ሙከራዎች የፖለቲካ ድጋፍ ለማግኘት ጥቅም ላይ ይውላል ቢሉም ፕሬዝዳንት ትሩማን እና ፎርድ ከተሞከረባቸው ግድያ በኋላ በሕዝብ ዘንድ የነበራቸው ተቀባይነት ሲያሽቆለቁል፣ ሮናልድ ሬጋን ግን ከተሞከረባቸው ግድያ በኋላ ተቀባይነታቸው ጨምሯል።ያጋሩ, ‘ዶናልድ ትራምፕን ለመግደል አዲሱ የኢራን ዕቅድ’
  17. 10 ሀምሌ 2026ኢራን እና አሜሪካ ወደ ድርድር እንዲመለሱ ለማድረግ ጥረት መጀመሩ ተዘገበኢራንየፎቶው ባለመብት,Atta Kenare / AFP via Getty Imagesኳታር፣ ፓኪስታን እና ሌሎችም ቀጣናዊ አደራዳሪዎች አሜሪካ እና ኢራንን ወደ ውይይት ለመመለስ ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ተዘገበ።የአሜሪካው አክሲዮስ እንደዘገበው አሸማጋዮቹ አሜሪካ እና ኢራን እንደ አዲስ የገቡበትን ግጭት አቁመው ኒውክሌርን የተመለከተ ውይይት እንዲቀጥሉ ለማድረግ እየሞከሩ ነው።አክሲዮስ በአሜሪካ እና በአሸማጋዮቹ አገራት የሚገኙ ሁለት ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው ውይይቶች እንዲቀጥሉ ጥረቶች ተጀምረዋል።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከትናንት በስትያ ከኢራን ጋር የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ እንዲሁም የተኩስ አቁሙ “አብቅቶለታል” ብለዋል።ፕሬዝዳንቱ በኢራን ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ተከትሎ ሁለቱ አገራት ወደ ግጭት ተመልሰዋል።ትራምፕ ትኩረታቸው የሆርሙዝ ወሽመጥን ማስከፈት መሆኑን ተናግረዋል።የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ በበኩሉ የሆርሙዝ ወሽመጥ በአገሪቱ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር እንደሚገኝ ገልጿል።አክሲዮስ እንደዘገበው ትራምፕ አሁንም ቢሆን የለየለት ጦርነት ውስጥ ተመልሰው መግባት አይፈልጉም።የአሜሪካ ጦር ለሁለት ተከታታይ ቀናት በፈጸመው ጥቃት በኢራን ወደ 90 ዒላማዎችን መምታቱን አስታውቋል። የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ በኩዌት፣ በባሕሬን እና በኳታር የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ የድሮን ድብደባ መፈጸሙን ገልጿል።ያጋሩ, ኢራን እና አሜሪካ ወደ ድርድር እንዲመለሱ ለማድረግ ጥረት መጀመሩ ተዘገበ
  18. 9 ሀምሌ 2026የአሜሪካ እና ኢራን ግጭት ዋና ዋና ክስተቶችበአሜሪካ ጥቃት የተመታ የባሕር ዳርቻየፎቶው ባለመብት,Mehr News Agencyአሜሪካ እና ኢራን ወደ ጦርነት መመለሳቸው መካከለኛው ምሥራቅን በውጥረት ሞልቶታል።በሁለቱ አገራት መካከል የመግባቢያ ስምምነት ከተፈረመ ወዲህ ከባድ የተኩስ ልውውጥ የተደረገው ያሳለፍነው ማክሰኞ ነው።የኢራን የጤና ሚኒስቴር ማክሰኞ እና ረቡዕ በተፈጸሙ ጥቃቶች 14 ሰዎች መገደላቸውን አረጋግጧል።ረቡዕ እና ዛሬም ተከታታይ ጥቃቶች መፈጸማቸው ተዘግቧል። የግጭቱ ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦
    • የአሜሪካ ጦር ለሁለት ተከታታይ ቀናት በፈጸመው ጥቃት በኢራን ወደ 90 ዒላማዎችን መምታቱን አስታውቋል።
    • የቢቢሲ መረጃ ማጣሪያ ቢቢሲ ቬሪፋይ ያረጋገጣቸው ተንቀሳቃሽ ምሥሎች በደቡብ ምሥራቅ ኢራን ቻባሀር ከተማ የመቆጣጠሪያ ማማ ላይ የደረሰ ጉዳትን ያሳያሉ።
    • በሰሜናዊ የኢራን ክፍል አቃላ ከተማ የባቡር ሃዲድ በተዘረጋበት ድልድይ ላይ ጉዳት መድረሱንም ማረጋገጥ ተችሏል።
    • የኢራን መገናኛ ብዙኃን የኒውክሌር ማብላያ ላይ ዛሬ ከሰዓት ጥቃት መፈጸሙን ዘግበዋል።
    • ኢራን በኩዌት፣ በባህሬን እና በኳታር የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ የድሮን ድብደባ መፈጸሟን አስታውቃለች።
    • ባህሬን ከኢራን የተሰነዘሩባትን ጥቃቶች ማክሸፍ መቻሏን ስትገልጽ፤ በኩዌት በተተኮሰ የሚሳዔል ስብርባሪዎች አንድ ሰው ላይ ጉዳት መድረሱ ይፋ ተደርጓል።
    • የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ በዮርዳኖስ የሚገኝ የአሜሪካ ወታደራዊ ሰፈር ላይ 10 ሚሳዔል መተኮሱን ገልጿል። ዮርዳኖስ በበኩሏ ስምንት ሚሳዔሎችን መትታ መጣሏን አስታውቃለች።
    ቢቢሲ ያረጋገጣቸው ተንቀሳቃሽ ምሥሎች በደቡብ ምሥራቅ ኢራን ቻባሀር ከተማ መቆጣጠሪያ ማማ ላይ የደረሰ ጉዳትን ያሳያሉየፎቶው ባለመብት,Instagramየምስሉ መግለጫ,ቢቢሲ ያረጋገጣቸው ተንቀሳቃሽ ምሥሎች በደቡብ ምሥራቅ ኢራን ቻባሀር ከተማ መቆጣጠሪያ ማማ ላይ የደረሰ ጉዳትን ያሳያሉበሰሜናዊ የኢራን ክፍል አቃላ ከተማ የባቡር ድልድይ ላይ ጉዳት መድረሱንም ማረጋገጥ ተችሏልየፎቶው ባለመብት,Tasnimየምስሉ መግለጫ,በሰሜናዊ የኢራን ክፍል አቃላ ከተማ የባቡር ድልድይ ላይ ጉዳት መድረሱንም ማረጋገጥ ተችሏልያጋሩ, የአሜሪካ እና ኢራን ግጭት ዋና ዋና ክስተቶች
  19. 9 ሀምሌ 2026የአሜሪካ ጥቃት የሚቀጥል ከሆነ ኢራን እራሷን እንደምትከላከል አስታወቀችአባስ አራግቺየፎቶው ባለመብት,EPAየምስሉ መግለጫ,የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺለተከታታይ ሁለት ቀናት በአሜሪካ ጥቃት የተሰነዘረባት ኢራን ጥቃቱ የሚቀጥል ከሆነ እራሷን የመከላከል እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች።የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ባወጡት መግለጫ አሜሪካ በተከታታይ በተለያዩ የኢራን ክፍሎች ላይ እየፈጸመችው ያለው ጥቃት “በጽኑ የሚወገዝ” መሆኑን አመለክተዋል።ጥቃቶቹን ከሳምንታት በፊት ባለፈው ሰኔ ወር በሁለቱ አገራት መካከል የተደረሰውን ባለ 14 ነጥብ የመግባቢያ ስምምነትን የሚጥስ ነው ሲሉ ወቅሰዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተደረሰውን ስምምነት ዋነኛ አሸማጋይ ለሆኑት ለፓኪስታኑ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ለሆኑት ፊልድ ማርሻል አሲም ሙኒር እንደተናገሩት “የአሜሪካ ጥቃት የሚቀጥል ከሆነ ኢራን እራሷን ትከላከላለች” ብለዋል።በተጨማሪም አራግቺ ከኦማን እና ከቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር መወያየታቸው የተነገረ ሲሆን፣ አገራት በባሕረ ሰላጤው የተፈጠረው ውጥረት እንዲረግብ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንዲፈለግ ጥሪ እያቀረቡ ነው።ያጋሩ, የአሜሪካ ጥቃት የሚቀጥል ከሆነ ኢራን እራሷን እንደምትከላከል አስታወቀች
  20. 9 ሀምሌ 2026አሜሪካ እና ኢራን ወደ ጦርነት ሲመለሱ፣ ኢራናውያን አደባባይ ወጥተው የኻሜኒን ቀብር እየፈጸሙ ነውበማሻድ አደባባይ የተሰበሰቡ ሰዎችየፎቶው ባለመብት,Reutersአሜሪካ በኢራን ላይ ለሁለተኛ ቀን የምትፈጽመው ጥቃት በቀጠለበት እና ኢራን የአጸፋ እርምጃ በጎረቤቶቿ ላይ እየወሰደች ባለበት በአሁኑ ጊዜ በጦርነቱ ጅማሬ ላይ የተገደሉት የቀድሞው ጠቅላይ መሪ የመጨረሻ የቀብር ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው።ላለፉት ቀናት በተለያዩ አገራት እና ከተሞች ውስጥ ሲዘዋወር የነበረው የአያቶላህ አሊ ኻሜኒ አስከሬን ወደ ትውልድ ከተማቸው ማሻድ ተወስዶ ዛሬ ግብአተ መሬቱ ይጠናቀቃል።በሰሜን ምሥራቃዊ ኢራን ውስጥ በምትኘው ቅዱስ ከተማ ማሻድ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ አደባባይ ወጥተው ጎዳናዎች በሐዘንተኞች መጨናነቃቸው ተዘግቧል።የካቲት ወር ማብቂያ ላይ አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጦርነት በከፈቱበት የመጀመሪያ ዕለት የተገደሉት ኻሜኒ የስንብት እና ቀብር ሥነ ሥርዓት ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ የሚጠናቀቅ ይሆናል።በማሻድ ጎዳና ላይ የተሰበሰቡ ሰዎችየፎቶው ባለመብት,Reutersበማሻድ አደባባይ የተሰበሰቡ ሰዎችየፎቶው ባለመብት,Reutersያጋሩ, አሜሪካ እና ኢራን ወደ ጦርነት ሲመለሱ፣ ኢራናውያን አደባባይ ወጥተው የኻሜኒን ቀብር እየፈጸሙ ነው