
ኦማን ቴህራን የሆርሙዝ ወሽመጥን እንድታስተዳድር የሚያስችል ዕቅድ ማቅረቧን እና ምክረ ሃሳቡ የባሕረ ሰላጤው አገራትን ድጋፍ ማግኘቱን ሮይተርስ ዲፕሎማቶችን እና ምንጮችን ጠቅሶ ዘገበ። በዕቅዱ መሠረት በወሽመጡ ላይ የሚያልፉ መርከቦች በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ክፍያ እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ ተብሏል።
ጭምቅ ሃሳብ
- ውጊያቸውን ጋብ ያደረጉት አሜሪካ እና ኢራን ንግግር ላይ መሆናቸውን ፕሬዝዳንት ትራምፕ ተናገሩ
- በካስፒያን ባሕር የኢራን መርከብን የመታችው ዩክሬን ከቴህራን የተሰነዘረባትን የአጸፋ እርምጃ ዛቻ አጣጣለች
- በኢራን ጦርነት 18 የአሜሪካ ወታደሮች መገደላቸው እና ከ600 በላይ መቁሰላቸው ተገለጸ
የቀጥታ ሽፋን
- ከ 4 ሰአት በፊትየአሜሪካ ጦር በቅርቡ ኢራን ላይ ለፈጸመው ድብደባ የእስራኤልን ጦር ሠፈር መጠቀሙ ተገለጸ
የፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር በቅርቡ የአሜሪካ ጦር በኢራን ላይ ለፈጸመው ድብደባ የእስራኤልን ጦር ሠፈር መጠቀሙን ገለፁ።እዝራኤል ካትዝ የኢራን ባለሥልጣናት ይህንን እንደሚያውቁ ተናግረው ነገር ግን የአጸፋ ጥቃት አለመፈጸማቸውን ተናግረዋል።“እውነታው ኢራን የቀጣናው አገራት ላይ በሙሉ ጥቃት ስትፈጽም እስራኤል ላይ ግን ምንም እርምጃ አልወሰደችም። ምንም እንኳ ያ በሰዓት ውስጥ የሚቀየር ቢሆንም” ሲሉ ለእስራኤሉ መገናኛ ብዙኃን ቻናል 14 ተናግረዋል።የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ በዋይት ሐውስ ተገናኝተው ይወያያሉ።የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ኢራን በእስራኤል ላይ ጥቃት ለመፈጸም ብትሞክር “በሙሉ ኃይላችን” ምላሽ እንሰጣለን ሲሉ ዝተዋል።“እኔ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ እስራኤል ላይ ጥቃት ከተፈጸመ በሙሉ ኃይላችን ምላሽ ለመስጠት ተነጋግረናል” ሲሉ ጨምረው አብራርተዋል።ያጋሩ, የአሜሪካ ጦር በቅርቡ ኢራን ላይ ለፈጸመው ድብደባ የእስራኤልን ጦር ሠፈር መጠቀሙ ተገለጸ - ከ 5 ሰአት በፊትየሆርሙዝ ወሽመጥን ኢራን እንድታስተዳድረው ኦማን ዕቅድ ማቅረቧን ሮይተርስ ዘገበ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በሆርሙዝ ወሽመጥ በባንዳር አባስ አቅራቢያ መርከቦች ሲያልፉኦማን ቴህራን የሆርሙዝ ወሽመጥን እንድታስተዳድር የሚያስችል ዕቅድ ማቅረቧን እና ምክረ ሃሳቡ የባሕረ ሰላጤው አገራትን ድጋፍ ማግኘቱን ሮይተርስ ዲፕሎማቶችን እና ምንጮችን ጠቅሶ ዘገበ።በዕቅዱ መሠረትበወሽመጡ ላይ የሚያልፉ መርከቦች በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ክፍያ እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ ተብሏል።ዕቅዱ አሜሪካ እና እስራኤል ቴህራን ላይ ጦርነት ማወጃቸውን ተከትሎ በወሽመጡ ላይ የሚያልፉ መርከቦች እንቅስቃሴ መገታቱን ያስቀራል ተብሏል።ለሁለት ሳምንት ሲካሄድ የነበረውን የአየር ድብደባ ያስቆሙት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር “ጥሩ ንግግር እየተካሄደ” መሆኑን ተናግረዋል።ነገር ግን ኢራን ወደ ድርድር ጠረጴዛው የማትመለስ ከሆነ የአሜሪካ ጦር ድብደባውን እንደሚቀጥል ዝተዋል።ኢራን ግን ከአሜሪካ ጋር ንግግር ዳግም ለመጀመር ፍላጎት እነደሌላት በመግለጽ አስተባብላለች።ዋሺንግተን በቴህራን ላይ ጥቃት መፈጸም የጀመረችው ከሁለት ሳምንት በፊት ነበር።አሜሪካ እና እስራኤል የካቲት 221 2018 ዓ.ም. በቴህራን ላይ ጦርነት ከከፈቱ በኋላ ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ሙሉ በሙሉ ዘግታለች።ባለፈው ወር በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ስምምነት ከተደረሰ በኋላ ወሽመጡ በከፊል ለመርከቦች እንቅስቃሴ ክፍት ሆኖ ነበር።ነገር ግን ከሁለት ሳምንት በፊት ኢራን በወሽመጡ በኩል ፈቃድ ያላገኙ መርከቦች እያለፉ ነው በሚል ጥቃት በመፈጸሟ ስምምነቱ ፈርሷል።ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ከኦማን ጋር በመሆን ማስተዳደር እና መርከቦችን ክፍያ ማስከፈል እንደምትፈልግ ተናግራለች።ዋሺንግተን በበኩሏ የሆርሙዝ ወሽመጥ ከጦርነቱ በፊት እንደነበረው ያለምንም ክፍያ መርከቦች የሚተላለፉበት እንዲሆን ትፈልጋለች።አክላም በግዴታ ቀረጥ ማስከፈል ሕገወጥ ነው ስትል አስጠንቅቃለች።በኦማን ዕቅድ ዙሪያ ማብራሪያ የተሰጣቸው የባሕረ ሰላጤው አገር ባለሥልጣናት እና ዲፕሎማቶች ለሮይተርስ እንደተናገሩት በምክረ ሃሳቡ መሠረት ኢራን ወሽመጡን ብቻዋን የማትቆጣጠር ሲሆን ክፍያም ቢሆን በፈቃደኝነት ይሆናል ተብሏል።ኦማን ያቀረበችው ዕቅድ በኤዢያ የሚገኘው በማላካ ወሽመጥ ተግባራዊ ከሚደረገው ጋር ተመሳሳይ ነው። በማላካ ወሽመጥ ኢንዶኔዢያ፣ ማሊዢያ እና ሲንጋፖር መርከቦች በፈቃደኝነት ክፍያ እንዲፈጽሙ ይጠይቃሉ። ገንዘቡ የመርከቦችን ፍሰት ለማሻሻል፣ የአካባቢ ጥበቃ ለማካሄድ እና በአደጋ ጊዜ የሕይወት አድን ሥራዎችን ለመደገፍ ይውላል።የባሕረ ሰላጤው ምንጮች እስከ ሰኞ ምሽት ድረስ ከኢራን የተሰጠ ይፋዊ ምላሽ አለመኖሩን ተናግረዋል።የኦማን ባለሥልጣናት እና የኢራን ባለሥልጣናት በቴህራን በሳምንቱ መጨረሻ ተገናኝተው ተወያይተው ነበር።ያጋሩ, የሆርሙዝ ወሽመጥን ኢራን እንድታስተዳድረው ኦማን ዕቅድ ማቅረቧን ሮይተርስ ዘገበ - ከ 7 ሰአት በፊትየአሜሪካ ልዑካን የፈረንሳይን ንግግር በመቃወም የተመድ ጸጥታ ምክር ቤት ስብሰባን አቋርጠው ወጡ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የፈረንሳይ አምባሳደር ጀሮም ቦናፎንትአሜሪካ ልዑክ፤ የፈረንሳይ ተወካይ በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ያደረጉት ንግግር በመቃወም አዳራሹን ጥለው ወጡ። የፈረንሳዩ አምባሳደር በሰኞ ዕለቱ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር አሜሪካ በተመድ ጉባኤ የሰጠችውን ድምጽ ከአምባገነን መንግሥታት ጋር አነጻጽረዋል።የሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ የጀመረው ባለፈው ሳምንት የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ቮልከር ተርክን የሥልጣን ዘመን ለማራዘም ድምጽ በሰጠበት ወቅት አሜሪካ ከሰሜን ኮሪያ እና ሩሲያ ጋር በመሆን ተቃውሞዋን ካሰማች በኋላ ነው።የፈረንሳይ የተባበሩት መንግሥተት ተልዕኮ ከአርብ ዕለቱ ድምጽ የመስጠት ሂደት በኋላ የአሜሪካን ውሳኔ ከሰሜን ኮሪያ እና ሩሲያ በማነጻጸር ተችቷል። ተልዕኮው በኤክስ ገጹ ባጋራው ልጥፍ “አሜሪካ የሰብአዊ መብቶች ምልክት ነበረች፤ ከአሁን ወዲህ አይደለችም” ብሏል።ለዚህ ምላሽ የሰጡት የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ዋልትዝ፣ ፈረንሳይ “ከዓለማችን የከፉ ጨቋኞች ጋር ሲወዳጅ” ለነበረው የሰብአዊ መብቶች ኃላፊ ድምጽ ሰጥታለች በማለት ከስሰዋል። አምባሳደሩ ምን ለማለት እንደፈለጉ አላብራሩም።የተመድ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ቮልከር ተርክ ከዚህ ቀደም ሩሲያ ዩክሬን ውስጥ የምታካሂደውን ጦርነት እንዲሁም የእስራኤልን የጋዛ ዘመቻ ሲተቹ ነበር።የአሜሪካ ልዑክ አባላት የሰኞ ዕለቱን ስብሰባ ጥለው የወጡት፤ የፈረንሳይ አምባሳደር ጀሮም ቦናፎንት ንግግር ሲያደርጉ ነው። አስቸኳይ ስብሰባው የተጠራው ሩሲያ የምታካሂደው ዩክሬን ጦርነት ላይ ለመምከር ነበር።ፈረንሳይ ይህንን “አዋራጅ እና አክብሮት የጎደለው ንግግሯ ውድቅ” እስከምታደርግ ድረስ የዋሽንግተን ልዑካን ተመሳሳይ ተቃውሞ ማሰማት እንደቀሚጥሉ የአሜሪካ አምባሳደር ዳን ኔገሬ ተናግረዋል።በ144 አገራት ድጋፍ፣ በ10 ተቃውሞ እና 13 ድምጸ ተዐቅቦ በጸደቀው የተርክ የኃላፊነት ዘመን ላይ የተነሳው ውዝግብ፤ በአሜሪካ እና በተባበሩት መንግሥታት መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ያሳያል።የትራምፕም አስተዳደር ለተመድ ተቋማት የሚያደርገው ድጋፍ ያቋረጠ ሲሆን አሜሪካ ከበርካታ ተቋማት አባልነት እንድትወጣም አድርጓል።ያጋሩ, የአሜሪካ ልዑካን የፈረንሳይን ንግግር በመቃወም የተመድ ጸጥታ ምክር ቤት ስብሰባን አቋርጠው ወጡ - ከ 8 ሰአት በፊትዶናልድ ትራምፕ ዛሬ ከእስራኤሉ መሪ ኔታንያሁ እና ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ ጋር ይገናኛሉ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ ማክሰኞ በዋይት ሐውስ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እንዲሁም ከዩክሬን ፕሬዝዳንት ቭሎድሚር ዜሌንስለኪ ጋር እንደሚገናኙ ይጠበቃል።ትራምፕ መሪዎቹን የሚቀበሉት በኢራን እና ዩክሬን መካከል ያለው ውዝግብ ወደ ወሳኝ ምዕራብ በተሸጋገረበት ወቅት ነው። ዩክሬን ቅዳሜ ዕለት በካስፒያን ባሕር ሲጓዝ የነበረ የኢራን መርከብን የመታች ሲሆን ቴህራንም አጸፋውን እንደምትመልስ ዝታለች።የአሜሪካው ፕሬዝዳንትም ከሁለቱ አገራት መሪዎች ጋር ያላቸው ግንኙነት የተለያየ አቅጣጫ ይዟል።ትራምፕ ትኩረታቸውን ወደ ዩክሬን ያዞሩት የአገሪቱ ጦር የሩሲያ ኃይሎች ቁጥጥራቸውን ለማስፋት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ካስቆሙ በኋላ መሆኑ ተገልጿል።በሌላ በኩል የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ወደ ዋሽንግተን የሚያመሩት የትራምፕ አስተዳደር የኢራንን ጦርነት ለመቋጨት የሚያስችል ስምምነት ላይ የመድረስ ሂደት በሚፈለገው ፍጥነት አለመሄዱ እንዳላስደሰተው ከገለጸ በኋላ ነው።ኔታንያሁ እና ዜሌንስኪ ወደ ዋሽንግተን ያመሩት ባለፈው ሳምንት ሕይወታቸው ያለፈው ሪፐብሊካን የኮንግረስ አባል ሊንዚ ግርሃም ቀብር ስነ ስርዓት ላይ ለመገኘት ነው። የትራምፕ የቅርብ አጋር የነበሩት የኮንግረስ አባሉ ሊንዚ ግርሃም፣ ፕሬዝዳንቱ የዩክሬንን ጦርነት እንዲደግፉ በተደጋጋሚ ይወተውቱ ነበር።የዩክሬን ጦርነት እና በመካከለኛው ምሥራው የሚካሄደው ግጭት ወሳኝ እጥፋት ላይ ናቸው። ሰኔ ላይ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ተፈራርመው የነበሩት አሜሪካ እና ኢራን፤ ለሁለት ሳምንት ገደማ አንዳቸው በሌላኛቸው ላይ ጥቃት ሲፈጽሙ ቆይተዋል። በዚህም የተነሳ የተኩስ አቁም ስምምነቱ እንደፈረሰ ተቆጥሯል።አሜሪካ ከ13 ቀናት ተከታታይ ጥቃት በኋላ እርምጃ መውሰድ ያቆመችው ለዲፕሎማሲ ሌላ ዕድል ለመስጠት መሆኑን ፕሬዝዳንት ትራምፕ ተናግረዋል።በሌላ በኩል ዩክሬን በሩሲያ ይዞታዎች ላይ ጥቃት እየፈጸመች ቢሆንም ግጭቱን መቼ ሊቋጭ እንደሚችል የሚጠቁም ምልክት እስካሁን አልታየም።ያጋሩ, ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ ከእስራኤሉ መሪ ኔታንያሁ እና ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ ጋር ይገናኛሉ - 28 ሀምሌ 2026በካስፒያን ባሕር የኢራን መርከብን የመታችው ዩክሬን ከቴህራን የተሰነዘረባትን የአጸፋ እርምጃ ዛቻ አጣጣለች
ዩክሬን በካስፒያን ባሕር ሲጓዝ የነበረ የኢራን የጭነት መርከብ ላይ ከፈጸመችው ጥቃት በኋላ ከቴህራን የተሰነዘረባትን የአጸፋ ዛቻ ውድቅ አደረገች።ድርጊቱ የኢራን እና የዩክሬንን ጦርነቶች በቀጥታ ያገናኘ የመጀመሪያው ክስተት ሆኗል።የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንድሪ ሲቢሃ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፤ “የኢራን ዛቻ ምክንያት የለሽ እና መሠረተ ቢስ ነው” ብለዋል።“ቴህራን ውስጥ ያለው አገዛዝ ከ2022 ጀምሮ ዩክሬናውያን የተገደሉባቸውን የጦር መሳሪያዎች [እያቀረበ] የሞስኮን ወንጀለኛ ጦርነት አጋግሏል፤ [በዚህም] ሩሲያ ዩክሬን ላይ የምትፈጽመው ወረራ ቀጥተኛ ተባባሪ ነው” ሲሉም ከስሰዋል።የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ፤ የአገሪቱ ጦር ኃይሎች በካስፒያን ባሕር ላይ በፈጸሙት የረጅም ርቀት ጥቃቶች “እጅግ ጥሩ ውጤት” ማስመዝገባቸውን ያስታወቁት ቅዳሜ ዕለት ነበር።በእነዚህ ጥቃቶች ከኢራን ጋር ግንኙነት ያላቸውን ወታደራዊ ጭነቶች ለማጓጓዝ ሲውሉ የነበሩ መርከቦች መመታታቸውንም ገልጸዋል።የዩክሬን ደኅንነት አገልግሎት በበኩሉ፤ በሰሜናዊ ካስፒያን ባሕር በሚገኝ የነዳጅ መሠረተ ልማት በድሮን መመታቱን አስታውቋል። የሩሲያ ሚሳዔል የታጠቀ ጀልባ እንዲሁም “ዓለም አቀፍ ማዕቀብ የተጣለባቸው የጭነት መርከቦች” ዒላማ መደረጋቸውንም ገልጿል።በሩሲያ የኢራን አምባሳደር ካዜም ጃላሊ፣ “አና” የተባለው መርከብ ጥቃት የተፈጸመበት ከቮልጋ ወንዝ 5 ኪሎ ሜትር ቆሞ በነበረበት ወቅት መሆኑን የኢራን መንግሥት የዜና ወኪል ተናግረዋል።በእስራኤል የዩክሬን አምባሳደር የሆኑት ዬቭገን ኮርኒቹክ በበኩላቸው፣ መርከቡ ከኢራን ወደ ሩሲያ ሊደርሱ የነበሩ የተለያዩ የድሮን እና ሚሳዔል ክፍሎችን ጭኖ እንደነበር ገልጸዋል። የሲቪሊያን የጭነት መርከብ አልነበረም ሲሉም ተከራክረዋል።አምባሳደሩ አክለውም ዩክሬን እና እስራኤል በተለያዩ ግንባሮች ተመሳሳይ “የክፋት ጥምረትን” እየተጋፈጡ ነው ሲሉም ለእስራኤሉ መገናኛ ብዙኃን ‘ኤን12’ ተናግረዋል።ኢራን እና ሩሲያ ጥብቅ ወታደራዊ ግንኙት አላቸው። ኢራን ዩክሬን ላይ ወረራ ከተከፈተባት የአውሮፓውያኑ 2022 አንስቶ አገር ውስጥ ያመረተቻቸውን ሻሄድ ድሮኖች ለሩሲያ ማቅረብ ጀምራለች። ሞስኮም እነዚህ ድሮኖች ላይ ማሻሻያ በማድረግ የዩክሬን ከተሞችን አጥቅታባቸዋለች።ያጋሩ, በካስፒያን ባሕር የኢራን መርከብን የመታችው ዩክሬን ከቴህራን የተሰነዘረባትን የአጸፋ እርምጃ ዛቻ አጣጣለች - 28 ሀምሌ 2026ውጊያቸውን ጋብ ያደረጉት አሜሪካ እና ኢራን ንግግር ላይ መሆናቸውን ፕሬዝዳንት ትራምፕ ተናገሩ
የፎቶው ባለመብት,Reutersአሜሪካ እና ኢራን ለተከታታይ ሦስተኛ ቀን ጥቃት ሳይለዋወጡ መዋላቸውን ተከትሎ፣ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቴህራን ጋር የሚደረገውን ጦርነት በተመለከተ “እጅግ ወዳጅነት የተሞላባቸው ድርድሮች እየተካሄዱ ነው” አሉ።ሰኞ ምሽት በፕሬዝዳንታዊው አውሮፕላን ‘ኤር ፎርስ ዋን’ ውስጥ ሆነው ጋዜጠኞችን ያነጋገሩት ትራምፕ፣ “አንዳች መልካም ነገር ሊፈጠር የሚችልበት ጥሩ ዕድል እንዳለ አስባለሁ” ሲሉ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።ይሁን እንጂ አሁን የሚደረገው ድርድር የሚከሽፍ ከሆነ ውጊያው ከመገታቱ በፊት “ስናደርግ የነበረውን ነገር ወደ መፈጸም እንመለሳለን” በማለት አስጠንቅቀዋል።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ይህንን ቢሉም ኢራን ግን ምንም ዓይነት ቀጥተኛ ድርድር እየተካሄደ አለመሆኑን አስታውቃለች።ትራምፕ እንዳሉት ከአርብ ዕለት አንስቶ ኢራን ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት ለመግታት የወሰኑት ሁለቱን ተፋላሚ አካላት የሚያሸማግሉ አገራት ለንግግሩ ሌላ ዕድል እንዲሰጡ ጥያቄ ስላቀረቡላቸው ነው።ኢራንም ጥቃት መፈጸም አቁማለች።ሁለቱ አገራት የሚያደርጉትን ውጊያ ጋብ ያደረጉት፣ ለሁለት ሳምንት ገደማ አንዳቸው በሌላኛቸው ይዞታ ላይ ጥቃት ሲያደርሱ ከቆዩ በኋላ ነው። ውጊያው ማገርሸቱም ሰኔ ላይ የተፈረመውን ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት አደጋ ውስጥ ከትቶታል።የአሜሪካ ጦር የፈጸማቸው ጥቃቶች “ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ የንግድ መርከብ ጉዞን አደጋ ላይ ለመጣል ያላትን አቅም ለማዳከም” ያለሙ እንደሆኑ በወቅቱ ገልጾ ነበር። ይህ አዲስ ውጊያ የተቀሰቀሰው ኢራን በወሳኙ የነዳጅ መተላለፊያ መስመር ላይ የተጓዙ መርከቦችን ከመታች በኋላ ነበር።የሁለቱ አገራት ግጭት ረግቦ ሊቆይ ይችላል የሚል ተስፋ በመፈጠሩም በዓለም አቀፍ ገበያ የነዳጅ ዋጋ በ9% ቀንሶ በበርሜል 87.59 ዶላር ሲሸጥ ታይቷል።ፕሬዝዳንታዊ አውሮፕላናቸው ውስጥ ሆነው ጋዜጠኞችን ያነጋገሩት ትራምፕ፤ ለአምስት ወራት ስትዋጋ ቆየችው አሜሪካ የተተኳሽ ክምችቷ እየቀነሰ ነው በሚል የወጡ ዘገባዎችን አጣጥለዋል።“እጅግ ብዙ ተተኳሽ አለን። መካከለኛ ደረጃ [መሣሪያዎችም] በብዛት አሉን፤ ምንም ቢሆን ልንጠቀምበት ከምንችለው በላይ [አለን]” ብለዋል። “ብዙ አለን፤ ግን ተጨማሪ ቢኖረን ደስ ይለኛል” ሲሉም ተናግረዋል።በተጨማሪም ትራምፕ “በርካታ መሣሪያዎች” እየተመረቱ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም ከፍተኛ ዋጋ ያለው አሜሪካ ሰራሹ ‘ፓትሪዮትስ’ የተሰኙት ፀረ ባለስቲክ ሚሳዔሎች እየተመረቱ መሆኑንም አስታውቀዋል።ያጋሩ, ውጊያቸውን ጋብ ያደረጉት አሜሪካ እና ኢራን ንግግር ላይ መሆናቸውን ፕሬዝዳንት ትራምፕ ተናገሩ - 27 ሀምሌ 2026በኢራን ጦርነት 18 የአሜሪካ ወታደሮች መገደላቸው እና ከ600 በላይ መቁሰላቸው ተገለጸ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,በጦርነቱ 18 ወደታሮች ሲገደሉ 624 የአሜሪካ ወታደሮች ቆስለዋልፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ካዘዙበት ያለፈው የካቲት ወዲህ 18 የአሜሪካ ወታደሮች መገደላቸውን እና ቢያንስ 624 ደግሞ መቁሰላቸውን ከአገሪቱ መከላከያ መስሪያ ቤት ‘ፔንታገን’ የወጣ መረጃ አመለከተ።ጉዳቱ ከደረሰባቸው መካከል 417 በኢራን ላይ ከተካሄደው ‘ኤፒክ ፊዩሪ’ ከተባለው ዘመቻ ጋር ሲያያዙ፣ 207 ያህሉ ደግሞ ‘በባሕር ማዶ ዘመቻዎች’ ላይ የተሳተፉ እንደሆነ ተጠቅሷል።ባለፈው ሳምንት ፔንታገን በጦርነቱ ውስጥ የተገደሉ እና የቆሰሉ ወታደሮችን መረጃ የከለሰ ሲሆን፣ በዚህም በኢራን ጦርነት ከተገደሉ ወታደሮች መካከል የነበሩ አራት አባላቱን ስም በባሕር ማዶ ዘመቻ ላይ ከተገደሉት ዝርዝር ውስጥ አካትቷል።የመከላከያ ሚኒስቴሩ የመረጃ ቋት ላይ በኢራን በተካሄደው ዘመቻ እስካለፈው ማክሰኞ ድረስ የተገደሉት 18 እና የቆሰሉ 482 ወታደሮች ዝርዝር ይዞ ቆይቷል። ከዚያ በኋላ ግን በተካሄደው ክለሳ ከሟቾቹ ዝርዝር ላይ አራት ወታደሮች ተቀንሰው ቁጥሩ 14 ሆኗል።ምንም ዓይነት ማብራሪያ ሳይሰጥ በቆሰሉት እና በሞቱት ወታደሮች ስም ዝርዝር ላይ የተደረገው ለውጥ፣ ‘ግልጽነትን የሚያደናቅፍ ነው’ በሚል በቀድሞው የአገሪቱ ጦር ኃይል ከፍተኛ መኮንን ሌተናንት ቤን ሆጅስ ትችት ቀርቦበታል።የፔንታገን ቃል አቀባይ ሾን ፓርኔል በበኩላቸው በጦር ጉዳተኞች አሃዝ ላይ የተደረገው ለውጥ “ጊዜያዊ የመረጃ መዛባት ነው” ብለዋል።“የባሕር ማዶ ዘመቻዎች” የሚለው ዘርፍ ከዚህ ቀደም ያልነበረ ሲሆን በመከላከያ መስሪያ ቤቱ ድረ ገጽ ላይ የታየው ከእሁድ ጀምሮ መሆኑን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል።በዚህም ክፍል ላይ በቅርቡ ሕይወታቸውን ያጡ አራት ወታደሮችን ስም በሟች እንዲሁም 207 ደግሞ በቆሰሉ መዝግቧል። ነገር ግን የቆሰሉት ወታደሮች በኢራኑ ጦርነት የተጎዱ ስለመሆናቸው ግልጽ አይደለም።አራቱ ወታደሮች የተገደሉት በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተደረሰው ተኩስ አቁም ከፈረሰ በኋላ ነው። በድጋሚ በአሜሪካ ጥቃት የተፈጸመባት ኢራን በቀጣናው የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮችን ዒላማ አድርጋለች።ኢራን ከአስር ቀናት በፊት ዮርዳኖስ ውስጥ የሚገኝ የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ ባደረሰችው የሚሳዔል ጥቃት ሦስት ወታደሮች ተገድለዋል። አንዱ ደግሞ ኢራቅ ውስጥ የኢራን ድሮንን ለማክሸፍ በተወሰደ እርምጃ ወቅት ነበር የተገደለው።አሜሪካ ለ13 ተከታታይ ቀናት በኢራን ላይ ጥቃት ስትፈጽም ኢራንም በምላሹ በቀጣናው ባሉ የአሜሪካ ወታደራዊ ተቋማት ላይ የሚሳዔል እና የድሮን ጥቃት አድርሳለች።ከአርብ ጀምሮ ባለፉት ሦስት ቀናት የአሜሪካ ጥቃት መቆሙን ተከትሎ ኢራንም የአጸፋ እርምጃዋን ጋብ አድርጋለች።ያጋሩ, በኢራን ጦርነት 18 የአሜሪካ ወታደሮች መገደላቸው እና ከ600 በላይ መቁሰላቸው ተገለጸ - 27 ሀምሌ 2026ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥ አሁንም በቁጥጥሯ ስር መሆኑን አስታወቀች
የፎቶው ባለመብት,CENTCOMየምስሉ መግለጫ,አሜሪካ ለ13 ተከታታይ ቀናት በኢራን ላይ ጥቃት ስትፈጽም ቆይታለችከአሜሪካ ጋር የሚደረገው ጦርነት ጋብ ማለቱን ተከትሎ ኢራን ወሳኝ የሆርሙዝ ወሽመጥ በቁጥጥሯ ስር መሆኑን እንዲሁም የተቋረጠው የሰላም ንግግር እንዲጀመር አለመጠየቋን አስታወቀች።አሜሪካ ለ13 ተከታታይ ቀናት በኢራን ላይ ጥቃቶችን በፈጸመችበት ወቅት፤ ቴህራንም በመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ውስጥ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮችን በሚሳዔል እና ድሮን ዒላማ ስታደረግ ቆይታለች።ትራምፕ ለሁለት ሳምንት ገደማ የቆየውን የአየር ጥቃት ያቆሙት፣ ዘመቻው ኢራን በሆርሙዝ ላይ ያላትን ቁጥጥር ለመስበር የወጠነውን ግብ እንዳላሳካ በአማካሪዎቻቸው ከተገለጸላቸው በኋላ መሆኑ ተዘግቧል።አሜሪካ ጥቃቱን እስካቆመች ድረስ፣ ኢራን በበኩሏ የምትወስደውን እርምጃ እንደምትገታ አስታውቃለች።አንድ ባለሥልጣን ለሮይተርስ እንደገለጹት የአሜሪካ ወታደራዊ አዛዦች ዘመቻው ዓላማውን እየሳተ ነው በማለት ፕሬዝዳንቱን መክረዋቸዋል።ባለሥልጣኑ ጨምረውም የአሜሪካ ጦር ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የሆኑት ጄነራል ዳን ኬይን በቀጣናው ያሉ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮችን ከጥቃት ለመከላከል የሚያስችል የመሳሪያ ክምችታቸው እየተመናነመነ መሆኑን መናገራቸውን አመልክተዋል።የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የፕሬዝዳንት ትራምፕ ሲቪል እና ወታደራዊ አማካሪዎች በኢራን ላይ የሚፈጸመው ጥቃት እንዲቆም ምክር መስጠታቸውን ዘግበዋል።በተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ማይክ ዋልትዝ በኢራን ላይ የሚፈጸመው ጥቃት የቆመው ለድርድር በር ለመክፈት ነው ሲሉ ተናግረዋል።የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ግን ከአሜሪካ ጋር የሚካሄደው የሰላም ንግግር መልሶ እንዲጀመር ጥያቄ እንዳላቀረበች አሳውቋል። የአሜሪካ ጥቃት አለመሳካቱን እና ወሳኙ የሆርሙዝ ወሽመጥ በቁጥጥሯ ስር መሆኑን ኢራን አስታውቃለች።አሜሪካ ሁለት ሳምንት ለሚጠጋ ጊዜ በኢራን ላይ ባካሄደችው ጥቃት ምክንያት የነዳጅ ዋጋ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቶ ነበር። ባለፉት ቀናት ጥቃቱ ጋብ ማለቱን ተከትሎ ደግሞ ከፍተኛ ቅናሽ ማሳየቱ ተዘግቧል።ያጋሩ, ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥ አሁንም በቁጥጥሯ ስር መሆኑን አስታወቀች - 27 ሀምሌ 2026ከሁቲዎች ጥቃት በኋላ በቀይ ባሕር የሚደረግ የመርከቦች ጉዞ መቀዛቀዙ ተዘገበ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየየመን ሁቲዎች በቀይ ባሕር ዳርቻ በሚገኝ የሳዑዲ አረቢያ የነዳጅ መሠረተ ልማት ላይ ጥቃት ከፈጸሙት በኋላ፣ በባብ ኤል መንደብ ወሽመጥ በኩል የሚደረግ የመርከብ ጉዞ መቀዛቀዙን ሮይተርስ ዘገበ።የዜና ወኪሉ ‘ኬፕለር’ የተሰኘውን የመረጃ ምንጭ ጠቅሶ ያወጣው ዘገባ እንደሚያሳየው እሁድ ዕለት በባብ ኤል መንደብ በኩል ያለፉ የንግድ መርከቦች 11 ናቸው። ካለፉት ወራት ጋር ሲነጻጸር ይህ ቁጥር ዝቅተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።በወሽመጡ በኩል ከተለላፉ መርከቦች ውስጥ ሰባቱ ነዳጅ ጫኝ ሲሆኑ፣ ከእነዚህ መካከልም ሦስቱ ወደ ቀይ ባሕር መግባታቸውም ዘገባው ጠቅሷል።የሳዑዲ አረቢያን የኤክስፖርት ምርት ጉዞ ማስተጓጎል የሚፈልጉት ሁቲዎች፤ ባለፈው ሳምንት የባሕር ጉዞ ማዕቀብ” መጣላቸውን ገልጸው ነበር። ቀጥሎም ይህንን እገዳ ጥሰዋል የተባሉ ሁለት የአገሪቱ ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን መትተዋል።በተጨማሪም በሳዑዲ አረቢያ በጂዛን ከተማ የሚሳዔል ጥቃት ማድረሳቸውን ገልጸዋል። ሳዑዲም በወሰደችው የአጸፋ ምላሽ በየመን የወደብ ከተማ ሆዴይዳ እና በቅርብ ያለ ደሴት ላይ የሚገኙ የታጣቂ ቡድኑ ዒላማዎች ላይ የአየር ጥቃት ፈጽማለች።እነዚህ ጥቃቶች በቀይ ባሕር የሚደረግ ጉዞ ላይ መስተጓጎል ፈጥረዋል። የቀይ ባሕር መስመር በአሜሪካ እና በኢራን ጦርነት ምክንያት ሆርሙዝ ወሽመጥ በመዘጋቱ ችግር ውስጥ ለገባው የነዳጅ ምርት ጉዞ መተንፈሻ ሆኖ ነበር።ያጋሩ, ከሁቲዎች ጥቃት በኋላ በቀይ ባሕር የሚደረግ የመርከቦች ጉዞ መቀዛቀዙ ተዘገበ - 27 ሀምሌ 2026የጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ እና የኒው ዮርክ ከንቲባ ማምዳኒ ውዝግብ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ኔታኒያሁ እና ማምዳኒበኒው ዮርክ ከተማ ከንቲባ ዞህራን ማምዳኒ የእስራ ዛቻ የደረሰባቸው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፣ ጷጉሜን ላይ በከተማዋ በሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ እንደሚገኙ አስታወቁ።የኒው ዮርክ ከንቲባ ማንዳኒ፣ የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ኔታንያሁ ላይ ያወጣውን የእስር ማዘዣ ለማስፈጸም ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንደሚያስሩ ተናግረው ነበር። ባለፈው ሳምንት ላይ ግን እስሩን ለመፈጸም የሚያስችል ሕጋዊ ሥልጣን እንደሌላቸው መረዳታቸውን ገልጸዋል።ሰኞ ዕለት ለሌላ ጉብኝት ወደ አሜሪካ የተጓዙት የእስራኤሉ መሪ እሁድ ከፎክስ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ ማምዳኒ እንደሚያስሯቸው መግለጻቸው እንደማያሳስባቸው ተናግረዋል። አክለውም የኒው ዮርኩን ከንቲባ “ጥላቻ በመቀስቀስ” ወንጅለዋል።ኔታንያኑ ነገ ማክሰⶉ በዋይት ሐውስ ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የሚገናኙ ሲሆን፤ ባለፈው ሳምንት ሕይወታቸው ባለፈው የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ሊንዚ ግርሃም የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይም ይገኛሉ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዞ ላይ ኒው ዮርክ ከተማ አልተካተተችም።ኔታንያሁ በቃለ መጠይቁ፣ ማንዳኒ “ጥላቻ እየቀሰቀሰ ነው። የአይሁዶች፣ የክርስቲያኖች፣ የሙስሊሞች፣ የሁሉም ኒው ዮርከሮች ከንቲባ ሊሆን ይገባው ነበር” ብለዋል።“ነገር ግን አንድ ቡድንን በሌላው ላይ ለማስነሳት እየሞከረ ነው። አሜሪካውያን አይሁዶችን አነጋግሬያለሁ፤ በአሁኑ ሰዓት ፍራቻ ውስጥ ናቸው” ሲሉም ከስሰዋል።ለፍልስጤም መብቶች ጠንካራ ድጋፍ ያላቸው ከንቲባ ማምዳኒ፤ የእስራኤል ጦር ጋዛ ውስጥ የሚያካሂደው ዘመቻ ላይ ያሰሙት ተቃውሞ ባለፈው ዓመት ባደረጉት የምርጫ ቅስቀሳ ላይ ዋነኛ የክርክር ርዕስ ነበር።ማምዳኒ ባለፈው ሳምንት ባደረጉት ንግግር ኔታንያሁን ‘የጦር ወንጀለኛ” ሲሉ ጠርተዋቸዋል።ከንቲባ ለመሆን የምርጫ ቅስቀሳ ባደረጉበት ወቅትም ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋዛ ውስጥ ፈጽመውታል ባለው የጦር ወንጀል ምክንያት ያወጣውን የእስር ማዘዣ እንደሚያስፈጽሙ ገልጸው ነበር።እስራኤል ጋዛ ውስጥ የጦር ወጅንል ተፈጽሟል የሚለውን ክስ አትቀበለውም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኔታንያሁም የቀረቡባቸውን ክሶች “ሐሰተኛ” ሲሉ ጠርተዋቸዋል።ያጋሩ, የጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ እና የኒው ዮርክ ከንቲባ ማምዳኒ ውዝግብ - 27 ሀምሌ 2026ኢራን ከአሜሪካ ጋር ድርድር እያደረገች አለመሆኑን አስታወቀች
የፎቶው ባለመብት,IRIBየምስሉ መግለጫ,የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢስማኤል ባጋይየኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አገራቸው ከአሜሪካ ጋር መልዕክቶችን መለዋወጧን ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት መደበኛ የሆነ ድርድር እየተደረገ አለመሆኑን ገለጹ።ኢስማኤል ባጋይ ቴህራን አሁን ቅድሚያ የምትሰጠው ሉዓላዊነቷን መከላከል፣ የግዛት አንድነቷን ማስጠበቅ እና ለሕዝቧ መብት መሆኑን ገልጸው ወደ ድርድር ፈጥነው እንደማይገቡ ተናግረዋል።ቃል አቀባዩ ዋሺንግተን ዲፕሎማሲን በወታደራዊ እርምጃ ውድቅ ታደርጋለች ሲሉ የኮነኑ ሲሆን አሜሪካ ወደ ድርድር ለመመለስ ያለውን ሁኔታ አበላሽታዋለች ብለዋል።ባጋይ ከአውስትራሊያው ኦአርኤፍ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “መልዕክቶችን እየተለዋወጥን ነው፤ ነገር ግን አሁን ቅድሚያ የምንሰጠው ለኢራን ሉዓላዊነት፣ ለግዛት አንድነት እና ለሕዝቧ መብት መከበር ነው” ብለዋል።የቃል አቀባዩ አስተያየት ምንም እንኳ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል መደበኛ ድርድር ባይጀመርም ቀጥተኛ ያልሆነ ግንኙነት እየተካሄደ መሆኑን ይጠቁማል።ከዚህ ቀደም ቀጣናዊ አደራዳሪዎች ፓኪስታን እና ኳታር በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የመልዕክት ልውውጥ በማቀላጠፍ ረገድ ሚና ነበራቸው።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባዩ አስተያየት የተሰማው አሜሪካ ለሁለት ሳምንት ስታካሄድ የነበረውን ጥቃት ማቆሟን ከገለጸች በኋላ ነው።የጥቃቶቹ መቆም ዳግም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሊጀመር ይችላል የሚል ተስፋ አጭሯል።በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት በመካከለኛው ምሥራቅ ያለውን የነዳጅ አቅርቦት አስተጓጉሏል።ያጋሩ, ኢራን ከአሜሪካ ጋር ድርድር እያደረገች አለመሆኑን አስታወቀች - 27 ሀምሌ 2026አሜሪካ በኢራን ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት ማቆሟን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ቅናሽ አሳየ
የፎቶው ባለመብት,APየምስሉ መግለጫ,የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በ6.4 በመቶ ወርዶ በበርሜል 90.58 ዶላር እየተሸጠ ነውየአሜሪካ እና የኢራን ግጭት ለሁለት ሳምንት ያህል ከቀጠለ በኋላ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ መቆሙን ተከትሎ ሰኞ ዕለት የዓለም አቀፉ የነዳጅ ዋጋ በ6 በመቶ ቅናሽ አሳየ።አሜሪካ ለተከታታይ ሁለት ሳምንት በኢራን ላይ የፈጸመችውን ድብደባ ካቆመች በኋላ ኢራን የአጸፋ ምላሽ እንደማትሰጥ በመግለጿ ግጭቱን ለማርገብ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ሊገኝ እንዲሁም የሆርሙዝ ወሽመጥ ሊከፈት ይችላል የሚል ተስፋ አጭሯል።የዓለም ነዳጅ ዋጋ ተመን የሆነው የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በ6.4 በመቶ ወርዶ በበርሜል 90.58 ዶላር እየተሸጠ ነው።በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ጦርነት ከተጀመረ በኋላ የሆርሙዝ ወሽመጥ በመዘጋቱ እና ግጭቱ ወደ ቀይ ባሕርም በመስፋፋቱ የብሬንት ዋጋ ባለፈው ሳምንት በበርሜል 100 ዶላር ደርሶ ነበር።በየመን የሚገኙት የሁቲ ታጣቂዎች የሳዑዲ አረቢያ መርከቦች በቀይ ባሕር ላይ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ላይ ባለፈው ሳምንት እገዳ ጥለዋል።ይህም የዓለም ከፍተኛ ነዳጅ ላኪ የሆነችው አገር ምርቷን ለውጭው ዓለም ገበያ እንዳታቀርብ ከፍተኛ እንቅፋት ፈጥሯል።በተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ማይክ ዋልዝ ለፎክስ ኒውስ እሁድ ዕለት እንደተናገሩት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቴህራን ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት የገቱት ለዲፕሎማሲ ጥረት ዕድል ለመስጠት ነው ብለዋል።የኢራኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ ዛሬ ሰኞ በሰጡት መግለጫ የሆርሙዝ ወሽመት ዝግ እንደሆነ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።የሁቲ ታጣቂዎች በቀይ ባሕር ላይ የሚቀዝፉ የሳዑዲ መርከቦች ላይ ጥቃት መፈጸማችን ካስታወቁ በኋላም በባብ ኤል መንደብ በኩል የመርከቦች እንቅስቃሴ ተቀዛቅዟል።ያጋሩ, አሜሪካ በኢራን ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት ማቆሟን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ቅናሽ አሳየ - 27 ሀምሌ 2026አዲሱ የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዩክሬንን መደገፍ እንደሚቀጥሉ ተናገሩ
የፎቶው ባለመብት,PA Mediaአዲሱ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር አንዲ በርንሀም ለዩክሬን የሚያደርጉትን “ጽኑ ድጋፍ” ለመቀጠል ቃል ገቡ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ጋር ዛሬ ሰኞ ውይይት ያደርጋሉ።ከውይይቱ አስቀድመው እንደተናገሩትም ለዩክሬን የሚደረገውን ድጋፍ እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣን ከተረከቡ አንድ ሳምንታቸው ሲሆን፤ የመጀመሪያ ዓለም አቀፍ ጎብኚያቸው ዜሌንስኪ ይሆናሉ።ውይይቱ የሁለቱን አገራት ግንኙነት “እንደሚያጠናክር” ተገልጿል። መሪዎቹ የባሕር ኃይል ይጎበኛሉ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ “እንግሊዝ ከዩክሬን ጎን ትቆማለች፤ ድጋፋችን አይቋረጥም። ለዩክሬንን ዘላቂ ሰላም እና ፍትሕ ሳናሰፍን ወደኋላ አንልም” ብለዋል።ያጋሩ, አዲሱ የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዩክሬንን መደገፍ እንደሚቀጥሉ ተናገሩ - 27 ሀምሌ 2026ኔታንያሁ የኒው ዮርክ ከንቲባን “ጥላቻን በማነሳሳት” ወነጀሉ
የፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የኒው ዮርክ ከንቲባ በቁጥጥር ስር ሊያውሏቸው ቢዝቱም በመንግሥታቱ ድርጅት ጉባዔ ላይ ለመታደም ማቀዳቸውን ተናገሩ።የኒው ዮርክ ከንቲባ የሆኑት ዞህራን ማምዳኒ ባለፈው ሳምንት ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ያወጣውን የእስር ማዘዣ ለማስፈጸም ተናግረው የነበረ ቢሆንም በኋላ ላይ የሕግ ድጋፍ እንደሌላቸው በመግለጽ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ለፎክስ ኒውስ እሁድ ዕለት እንደተናገሩት ማምዳኒ ቀደም ሲሉ በሰጡት አስተያየት “ስጋት እንደማይገባቸው”ተናግረው ከንቲባው “ጥላቻን ያነሳሳሉ” ሲሉ ወንጅለዋቸዋል።ኔታንያሁ “እርሱ የሁሉም የኒውዮርክ ነዋሪዎች፣ አይሁዶች፣ ክርስቲያኖች፣ ሙስሊሞች ከንቲባ መሆን አለበት፤ ነገር ግን አንዱን ቡድን በሌላኛው ላይ ለማነሳሳት እየሞከረ ነው” ሲሉተናግረዋል።ኔታንያሁ ሐሙስ ዕለት በኒው ዮርክ የተፈፀመውን ሁለት የስለት ጥቃት ጠቅሰዋል፤ በዚህ ጥቃት አንድ ተጠርጣሪ አንድ አይሁዳዊ እና አንድ እስያዊን ወግቷል።ፖሊሶች ተጠርጣሪው በስለት ጥቃት ሲያደርስ “አላህ አክበር” እያለ ይጮህ ነበር። ከእያንዳንዱ ተጎጂ ጋር በተያያዘ በጥላቻ ወንጀሎች ክስ ተመስርቶበታል።ሁለቱም ሰዎች ከጥቃቶቹ የተረፉ ሲሆን ይህም ከከተማዋ የአይሁድ እና የእስያ አሜሪካውያን መሪዎች ውግዘት አስከትሏል።ከዚያ በኋላ ኔታንያሁ በሰጡት ቃለ ምልልስ በኒው ዮርክ የሚኖሩ አይሁዶች “ፈርተዋል” ብለዋል።ያጋሩ, ኔታንያሁ የኒው ዮርክ ከንቲባን “ጥላቻን በማነሳሳት” ወነጀሉ - 27 ሀምሌ 2026የኢራን ሕግ አውጪዎች ዩክሬን በካስፒያን ባሕር ላይ ለፈጸመችው ጥቃት የአጸፋ ምላሽ እንደሚሰጡ ዛቱ
የፎቶው ባለመብት,Anadoluየምስሉ መግለጫ,ዩክሬን በካስፒያን ባሕር ላይ እየቀዘፈ የነበረ የኢራን የንግድ መርከብ ላይ ጥቃት ፈጽማ አንድ ባህረተኛ መግደሏ ተገልጿልዩክሬን በካስፒያን ባሕር ላይ እየቀዘፈ የነበረ የኢራን የንግድ መርከብ ላይ የድሮን ጥቃት ከፈጸመች በኋላ አንድ ከፍተኛ የኢራን ሕግ አውጪ የአጸፋ ምላሽ እንደሚሰጥ አስጠነቀቁ።በኢራን ላይ የሚፈጸም ማንኛውም ጥቃት የአጻፋ ምላሽ አለው ያሉት የሕግ አውጪው ይህንን አሜሪካ እና እስራኤል ያውቃሉ ብለዋል።የኢራን ፓርላማ ብሔራዊ ደህንነት እና የውጭ ፖሊሲ ኮሚሽን ሰብሳቢ የሆኑት ኢብራሂም አዚዝ በኤክስ ገጻቸው ላይ ባጋሩት መልዕክት አሜሪካ እና እስራኤል “ማንኛውም በኢራን ላይ የሚፈጸም ጥቃት ምንጊዜም ዋጋ እንደሚያስከፍል ያውቃሉ። ይህ ደግሞ ዛሬም እውነት ነው” ብለዋል።አክለውም “ዩክሬን በቅርቡ ኢራን ድርጊቱ ምላሽ ሳያገኝ እንደማትተወው ትማራለች” ብለዋል።አዚዝ “አሳንሰው የሚገምቱን ዝርዝር እየጨመረ ነው የመጣው” ብለዋል።እሁድ ዕለት የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ ዩክሬን በኢራን የንግድ መርከብ ላይ የፈጸመችው ጥቃት የመንግሥታቱን ድርጅት ቻርተር የጣሰ መሆኑን ተናግረዋል።አክለውም በጥቃቱ አንድ ባህረተኛ መገደሉን አሳውቀው “ምላሽ ሳይሰጠው አይቀርም” ብለዋል።የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ በኤክስ ገጻቸው ላይ አገራቸው በካስፒያን ባሕር ላይ ረዥም ርቀት ሚሳዔሎችን በማስወንጨፍ “ጠንካራ ውጤቶችን” ማግኘቷን አስታውቀዋል።አክለውም ጥቃቱ የተፈጸመው “ኢራን በተሳተፈችበት ወታደራዊ ጭነት በጫነች መርከብ ላይ” መሆኑን ተናግረዋል።ያጋሩ, የኢራን ሕግ አውጪዎች ዩክሬን በካስፒያን ባሕር ላይ ለፈጸመችው ጥቃት የአጸፋ ምላሽ እንደሚሰጡ ዛቱ - 27 ሀምሌ 2026የአሜሪካ አምባሳደር ትራምፕ ጥቃቱን ያስቆሙት ለንግግር ቦታ ለመስጠት ነው አሉ
የፎቶው ባለመብት,Reutersፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ላይ የሚፈጸመውን ድብደባ እንዲቆም ያደረጉት ለዲፕሎማሲ ተጨማሪ ጊዜ ለመስጠት መሆኑን በመንግሥታቱ ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር አስታወቁ።አምባሳደር ማይክ ዋልዝ እሁድ ዕለት ለፎክስ ኒውስ በሰጡት ቃለ ምልልስ ፕሬዚዳንቱ “ለንግግር የተወሰነ ቦታ ለመስጠት” ጥቃተ እንዲቆም ማድረጋቸውን ተናግረዋል።የኢራን ጦር ቃል አቀባይ እሁድ ዕለት ቴህራን በቀጣናው ላይ የምትፈጽመውን “የአጸፋ” ጥቃቶች ማቆሟን ተናግረዋል።በዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን መካከል በሰኔ ወር የተደረሰው የተኩስ አቁም ከፈረሰ በኋላ የአሜሪካ ጦር ለሁለት ተከታታይ ሳምንቶች በየዕለቱ ኢራን ላይ ድብደባ ሲፈጽም ቆይቷል።ቴህራንም በምላሹ በጎረቤት አገራት የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሠፈሮች ላይ ሚሳዔሎችን ስታስወነጭፍ ቆይታለች።አምባሳደሩ ትራምፕ ጥቃቱ እንዲቆም ያደረጉት ለአጭር ጊዜ ስለመሆኑ kኤንቢሲ ተጠይቀው ሲመልሱ “ለአሁኑ እዚያ ድረስ ሄጄ መመለስ አልፈልግም። ፕሬዚዳንቱ ሁሉንም አማራጮች ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠዋል” ብለዋል።ኒውዮርክ ታይምስ የአስተዳደሩ ባለሥልጣናት ጥቃቶች እየሰፉ የሚመጡ ከሆነ የአየር መከላከያ ጦር መሣሪያዎች እየሳሱ ይመጣሉ ማለታቸውን መዘገቡን በተመለከተ ዋልዝ ሲጠየቁ አጣጥለውታል።“የአሜሪካ ጦር . . . ዘመቻውን በሚፈለገው መልኩ ውጤታማ ለማድረግ የሚያስፈልጉት ሁሉም ነገሮች አሉት” ብለዋል።እስከ እሁድ ምሽት ድረስ ትራምፕ ጥቃቱ ስለመቆሙ በይፋ ያሉት ነገር የለም።ነገር ግን ቀደም ሲል በትሩዝ ሶሻል ገጻቸው ላይ የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች የኢራንን መርከቦች እና የኻርግ ደሴቶችን ሲደበድቡ የሚያሳይ በሰው ሠራሽ አስተውሎት የተሰራ ምስል አጋርተው ነበር።ያጋሩ, የአሜሪካ አምባሳደር ትራምፕ ጥቃቱን ያስቆሙት ለንግግር ቦታ ለመስጠት ነው አሉ
