
የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ዛሬ ሐሙስ ጠዋት ኩዌት ውስጥ በሚገኘው አሊ አል-ሳሌም የአሜሪካ አየር ኃይል ጦር ሰፈር ላይ ፈጸምኩት ባለው ጥቃት ጉዳት ማድረሱን አስታወቀ።
ጭምቅ ሃሳብ
- የአሜሪካ ወታደሮች ላይ የተሰነዘረውን የጥቃት ሙከራ ተከትሎ ዋሽንግተን ኢራን ላይ “ከፍተኛ” ድብደባ ፈጸመች
- ሩሲያ በዩክሬን ባደረሰችው ጥቃት ሁለት ሕጻናትን ጨምሮ ስምንት ሰዎች ተገደሉ
- ታዋቂው ደራሲ ሳልማን ሩሽዲን ለመግደል የሞከረው ግለሰብ በሽብር ወንጀል ተፈረደበት
የቀጥታ ሽፋን
- ከ 1 ሰአት በፊትየኢራን አብዮታዊ ዘብ ኩዌት በሚገኝ የአሜሪካ አየር ኃይል ሰፈር ላይ ጉዳት ማድረሱን ገለጸ
የፎቶው ባለመብት,Anadolu via Getty Imagesየኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ዛሬ ሐሙስ ጠዋት ኩዌት ውስጥ በሚገኘው አሊ አል-ሳሌም የአሜሪካ አየር ኃይል ጦር ሰፈር ላይ ፈጸምኩት ባለው ጥቃት ጉዳት ማድረሱን አስታወቀ።በጥቃቱ የእሳት ቃጠሎ ተነስቶ ሁለት የድሮኖች መጠለያዎች እንዲሁም ለወታደራዊ አውሮፕላኖች እና ሄሊኮፕተሮች የሚውል የነዳጅ ማከማቻ እንደወደመ ገልጿል።ነገር ግን እስካሁን ይህን የአብዮታዊ ዘቡን ጥቃት እና አደረስኩት ያለውን ጉዳት በተመለከተ ከኩዌትም ሆነ ከአሜሪካ ባለሥልጣት ወይም ከገለልተኛ ወገን የተሰጠ ማረጋገጫም ሆነ ማስተባበያ የለም።የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ጥቃቱ “ዘመቻ ናስር 2” የተባለ መሆኑን እና የአሜሪካ ኃይሎች በቀጣናው ለመኖራቸው የተሰጠ ምላሽ መሆኑን ገልጿል።ነገር ግን ለጥቃቱ ጥቅም ላይ ስለዋሉት የጦር መሳሪያ ዓይነቶች፣ ስለደረሰው የውድመት መጠን ወይም በሰው ላይ ስለደረሰ ጉዳት ምንም ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።አብዮታዊ ዘቡ በኩዌት ሰሜን ምዕራብ ክፍል ውስጥ በሚገኘው የአሜሪካ ኃይሎች በሚገኙበት አሊ አል-ሳሌም አየር ኃይል ሰፈር ላይ ቀደም ሲል ጥቃት ፈጽሞ በአሜሪካ መገልገያዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ገልጾ ነበር።ኢራን በአሜሪካ ለሚፈጸምባት ጥቃት በመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ውስጥ በሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሠራዊት ሰፈሮች ላይ ተደጋጋሚ የድሮን እና የሚሳዔል ጥቃቶችን እየፈጸመች ነው።በተለይም በዮርዳኖስ፣ ኩዌት እና ባህሬን ውስጥ ያሉት የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች ከባድ ጉዳት ያደረሱ ጥቃቶች እንደተፈጸሙባቸው ተዘግቧል።ያጋሩ, የኢራን አብዮታዊ ዘብ ኩዌት በሚገኝ የአሜሪካ አየር ኃይል ሰፈር ላይ ጉዳት ማድረሱን ገለጸ - ከ 1 ሰአት በፊትቻይና ለኢራን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሚሳዔሎችን ልትሸጥ ነው መባሉን አስተባበለች
የፎቶው ባለመብት,Mehrnewsየምስሉ መግለጫ,ኢራን የአየር መከላከያ ሥርዓቷን ለማጠናከር እየሞከረች ነውቻይና ለኢራን በመቶዎች የሚቆጠሩ ከትከሻ ላይ የሚወነጨፉ የአየር መቃዋሚያ ሚሳዔሎችን ልታቀርብ ነው መባሉን መከላከያ ሚኒስቴሯ አስተባበለ።የጦር መሳሪያ ሽያጩን በተመለከተ ስለቀረበው ሪፖርት የተጠየቁት የቻይና የመከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጂያንፍ ቢን በሰጡት ምላሽ “ሐሰት” ሲሉ፣ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደግሞ ዘገባውን “መሠረተ ቢስ” ብሎታል።ሮይተርስ ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ሦስት ምንጮችን ጠቅሶ ቻይና በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የመጀመሪያዎቹን ከ300 እስከ 400 የሚደርሱ ቻይና ሠራሽ የአየር መከላከያ መሳሪያዎችን ለኢራን እንደምታቀርብ ዘግቦ ነበር።በስምምነቱ ኪውደብሊው-12 እና ኤፍኤን-16 የተባሉ ሚሳዔሎችን ጨምሮ ዋጋቸው ከ60 እስከ 70 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ የጦር መሳሪያዎችን ቻይና ለኢራን እንደምታቀርብ ገልጿል።የመጀመሪያዎቹ የጦር መሳሪያዎች በምዕራብ ቻይና ከምትገኘው ከተማ ኡሩምኪ ተነስተው በፓኪስታን በኩል ወደ ኢራን እንደሚጓጓዙ የሮይተርስ ምንጮች ተናግረዋል።ፓኪስታን በበኩሏ በእንዲህ ዓይነቱ የጦር ማሳሪያ ዝውውር ውስጥ እጇ እንደሌለበት በመግለጽ ዘገባውን “የፈጠራ እና የተዛባ” ብለዋለች።ኪውደብሊው-12 እና ኤፍኤን-16 የአየር መከላከያ ማሳሪያዎች ከምድር ወደ አየር የሚወነጨፉ እና በዝቅተኛ ከፍታ የሚበሩ የአውሮፕላኖችን፣ የሄሊኮፕተሮችን እንዲሁም የድሮኖችን ሙቀት በመከተል ዒላማቸውን የሚመቱ ናቸው።ኢራን ከቻይና መሳሪያዎቹን ስለመግዛቷ የተዘገበው ለወራት በአሜሪካ እና በእስራኤል በተፈጸመባት ጥቃት የተዳከመውን የአየር መከላከያ ሥርዓቷን መልሳ ለመገንባት እና ለማጠናከር ጥረት እደያረገች ባለበት ጊዜ ነው።ያጋሩ, ቻይና ለኢራን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሚሳዔሎችን ልትሸጥ ነው መባሉን አስተባበለች - ከ 3 ሰአት በፊትበኬንያ ፀረ- ተባይ ኬሚካል የተረጨበት ቲማቲም ለ15 ዝሆኖች ሞት ምክንያት እንደሆነ ተገለጸ
የፎቶው ባለመብት,De Agostini Editorial / Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,በአምቦስሊ ብሔራዊ ፓርክ እና አካባቢው ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ ዝሆኖች እንደሚንቀሳቀሱ ይገመታልበደቡባዊ ኬንያ፣ አምቦስሊ ብሔራዊ ፓርክ አቅራቢያ ሞተው የተገኙት 15 ዝሆኖች በአካባቢው ከሚገኝ እርሻ ፀረ-ተባይ ኬሚካል የተረጨበት ቲማቲም በመመገባቸው ሳይመረዙ እንዳልቀረ ተገለጸ።የአገሪቷ የዱር እንስሳት ጥበቃ አገልግሎት እንዳለው ከዝሆኖቹ በተወሰደ ናሙና ላይ በተደረገ የመጀመሪያ ደረጃ የቤተ ሙከራ ምርመራ ‘ሳይናይድ’ የተባለ ኬሚካላዊ ውህድ ተገኝቷል።ኬሚካሉ በተወሰኑ እፅዋት እና ምግቦች ውስጥ የሚገኝ እንዲሁም በኢንደስትሪዎች ጥቅም ላይ የሚውል ነው።ከዝሆኖች መካከል አስሩ የመንቀሳቀስ ችግር አጋጥሟቸው የተገኙ ሲሆን፣ በሁለት ቀናት ውስጥ ሞተዋል።ቀሪዎቹ አምስቱ ግን ሕይወታቸው አልፎ ነበር የተገኙት። በክስተቱ ላይ የሚካሄደው ምርመራ እንደቀጠለ ነው።የዝሆኖቹ ሞት ያጋጠመው ከአውሮፓውያኑ ሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 24 ባለው አንድ ወር ውስጥ እንደሆነም የዱር እንስሳት ጥበቃ አገልግሎቱ ገልጿል።ክስተቱ ዝሆኖች ምግብ እና ውሃ ለመፈለግ በሚንቀሳቀሱበት የፓርኩ አቅራቢያ እየተስፋፋ ባለው የእርሻ እንቅስቃሴ ላይ ስጋት እንዲፈጠር አድርጓል።ፓርኩ እና አካባቢው አምቦስሊ ሥነ ምኅዳር በመባል የሚታወቅ ሲሆን፣ በዱር እንስሳት ሃብቷ ከምትታወቀው ታንዛኒያ ጋር የሚያዋሰን ሰፊ አካባቢ ነው።ባለሥልጣናት እንዳሉት አደንን በማስቆም የተሳካ ውጤት በተመዘገበበት በቀጠናው፣ ይህን ያህል ቁጥር ያላቸው ዝሆኖች ሞት ሲመዘገብ በአስርተ ዓመታት ውስጥ የመጀመሪያው ነው።በአምቦስሊ ብሔራዊ ፓርክ እና አካባቢው ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ ዝሆኖች እንደሚገኙበት ይገመታል።ያጋሩ, በኬንያ ፀረ- ተባይ ኬሚካል የተረጨበት ቲማቲም ለ15 ዝሆኖች ሞት ምክንያት እንደሆነ ተገለጸ - ከ 4 ሰአት በፊትኡጋንዳዊው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ችሎት ውስጥ ራሳቸውን ከሳቱ በኋላ ሆስፒታል ገቡ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,ኪዛ ቤሲጄ ላለፉት ሁለት ዓመታት በእስር ላይ ይገኛሉኡጋንዳዊው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ኪዛ ቤሲጄ፣ ችሎት ውስጥ ሳሉ ራሳቸውን ስተው ከወደቁ በኋላ ጽኑ ህሙማን ክፍል መግባታቸውን ባለቤታቸው ተናገሩ።የተባበሩት መንግሥታት የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያ ድርጅት (ዩኤንኤድስ) ኃላፊ የሆኑት ባለቤታቸው ዊኒ ብያኒማ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፣ “ ራሳቸውን አያውቁም፤ መናገር አይችሉም፤ ለሚያነቃቃ መድኃኒት እንኳ ምላሽ አይሰጡም” ብለዋል።የ70 ዓመቱ ፖለቲከኛ ከአውሮፓውያኑ ኅዳር 2024 ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛሉ።ዋና ጠበቃቸውም ባለፈው ወር የታሰሩ ሲሆን “የአገር ክህደት ተግባርን ባለማሳወቅ” ክስ ቀርቦባቸዋል።ፖለቲከኛው ችሎት ውስጥ ራሳቸውን ስተው ሲወድቁ የመንግሥት ጠበቆች እንዲወክሏቸው መሾማቸውን እየተቃወሙ ነበር።ከዚያም በእስር ቤቱ ጠባቂዎች ወደ ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።ለረዥም ጊዜ በሥልጣን ላይ ያሉትን ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒን በመገዳደር አራት ጊዜ ለፕሬዚደንትነት የተወዳደሩት ፖለቲከኛው፣ ከኬንያ ታፍነው ወደ ኡጋንዳ የተወሰዱት ከሁለት ዓመት በፊት ነበር።ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከረዳታቸው ኦቤይድ ሉታሌ ጋር በእስር ላይ ይገኛሉ።በሁለቱም ላይ የአገር ክህደት ክስ ቀርቦባቸዋል።አቃቤ ሕግ፣ ፖለቲከኛው እና ረዳታቸው “የፕሬዝዳንት ሙሴቪንን መንግሥት ለመጣል ሴራ ጠንስሰዋል” ሲል ነው ክስ ያቀረበባቸው። እነርሱ ግን ክሱን አስተባብለዋል።በኡጋንዳ የአገር ክህደት ከባድ ወንጀል ሲሆን፣ ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ ሞት ሊፈረድበት ይችላል።ያጋሩ, ኡጋንዳዊው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ችሎት ውስጥ ራሳቸውን ከሳቱ በኋላ ሆስፒታል ገቡ - ከ 6 ሰአት በፊት“አሜሪካ ስጋት ሆና እስከቀጠለች ድረስ የሆርሙዝ ወሽመጥ አይከፈትም”- ኢራን
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ባወጣው መግለጫ “አሜሪካ ስጋት ሆና እስከቀጠለች ድረስ የሆርሙዝ ወሽመጥ ዳግመኛ አይከፈትም” ሲል አቋሙን አስታወቀ።የአሜሪካ ባለሥልጣናት “ማስፈራራት እና ማጋነን” የሚቀጥሉ ከሆነ እንዲሁም አሜሪካ በቀጣናው በሚገኘው ዓለም አቀፍ ውሃ ላይ የምታደርገው እንቅስቃሴ እስከቀጠለ ድረስ የሆርሙዝ ወሽመጥ እንደማይከፈት አብዮታዊ ዘቡ አመልክቷል።የኢራን መንግሥት የሚያስተዳድረው ኢርና እንደዘገበው የአገሪቱ ጦር “ዛቻ እና ማስፈራሪያ ነገሩን የበለጠ የሚያባብስ እና የሚያጠላልፍ ነው” ሲል አስጠንቅቋል።አገራትን በስም ሳይጠቅስም “ወራሪዎችን የሚረዱ አገራት ባህሪያቸውን ካላስተካከሉ ከፍተኛ ቅጣት ይጠብቃቸዋል” ብሏል።በሆርሙዝ ወሽመጥ በስተደቡብ በኩል “ደኅንነቱ ባልተጠበቀ መንገድ ለማለፍ የሞከሩ ሁለት ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ትናንት ምሽት እንዲመለሱ መደረጉን” አስታውቋል።በሆርሙዝ ወሽመጥ በስተደቡብ በኩል “ደኅንነቱ ባልተጠበቀ መንገድ ለማለፍ የሞከሩ ሁለት ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ትናንት ምሽት እንዲመለሱ መደረጉን” አስታውቋል።የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንትኮም) “የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ መርከቦች የሚያልፉበትን መንገድ መወሰን አይችልም” ብሏል።ያጋሩ, “አሜሪካ ስጋት ሆና እስከቀጠለች ድረስ የሆርሙዝ ወሽመጥ አይከፈትም”- ኢራን - ከ 6 ሰአት በፊትአሜሪካ እና ኢራን ወደ ግጭት መመለሳቸው እንዳሳሰበው ተመድ ገለጸ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesአሜሪካ እና ኢራን ግጭት አቁመው ወደ ዲፕሎማሲ መንገድ እንዲመለሱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጠየቁ።የዋና ጸሐፊው ቃል አቀባይ ፋራህ ሐቅ በኒው ዮርክ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ “ [ጉቴሬዝ ሁለቱ አገራት] ወደ ድርድር ጠረጴዛ የማይመለሱ ከሆነ ግጭቱ ይስፋፋል ብለው ይሰጋሉ። ባለፉት ሰዓታት ውስጥ የታየውም ይሄ ነው” ብለዋል።“እየታየ ያለው ነገር አወንታዊ አይደለም። የተመድ ዋና ጸሐፊ ተዋጊዎቹ ግጭቱን አቁመው በድጋሚ ወደ ድርድር እንዲመለሱ ይፈልጋሉ” ሲሉም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።በፓኪስታን እና ኳታር አሸማጋይነት ድርድሮች መቀጠላቸውን ቃል አቀባዩ ፋራህ ጠቅሰዋል።ከሰሞኑ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “እጅግ ወዳጅነት የተሞላባቸው ድርድሮች” እየተካሄዱ መሆኑን ቢናገሩም ኢራን ንግግር ተጀምሯል መባሉን አስተባብላለች።ያጋሩ, አሜሪካ እና ኢራን ወደ ግጭት መመለሳቸው እንዳሳሰበው ተመድ ገለጸ - ከ 6 ሰአት በፊትበሀዋሳ ከተማ በረዶ ቀላቅሎ በጣለ ከባድ ዝናብ የአንዲት እናት ሕይወት አለፈ
የፎቶው ባለመብት,Hawassa City Communicationበሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማ በረዶ እና ከባድ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለ ኃይለኛ ዝናብ፤ የአንድ ሰው ሕይወት እንዳለፈ እና 10 ሰዎች ላይ “መጠነኛ ጉዳት” መድረሱን የከተማው አስተዳደር ለቢቢሲ ገለጸ።ትናንት ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም. ያጋጠመው ከባድ ዝናብ ከአመሻሽ 11 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት አካባቢ እንደቆየ የሀዋሳ ከተማ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ምርጫዬ ደመቀ ለቢቢሲ ተናግረዋል።ዝናቡ በተለምዶ አረብ ሰፈር፣ ስልጤ ሰፈር እና መናኽሪያ ተብለው በሚጠሩ አካባቢዎች ላይ ጉዳት እንዳደረሰ የገለጹት ኃላፊው፤ የአንዲት ሴት ሕይወት ማለፉንም አስረድተዋል።የሁለት ልጆች እናት የሆነችው ሴት በዝናቡ ሰዓት በጥሩ ይዞታ ላይ ባልነበረ መኖሪያ ቤቷ ውስጥ እንደነበረችም ገልጸዋል። ቤቷ ውስጥ እንዳለች ሕይወቷ ማለፉንም ጠቁመዋል።ሰዎች ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ በሰዎች ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። ኃላፊው እንደሚገልጹት በቤቶች እና ተሽከርካሪዎች ላይ የደረሰውን ጉዳት መጠን ለመለየት ግብረ ኃይል ተሰማርቷል።የከተማው አስተዳደር ትናንት በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መረጃ በረዶ እና ኃይለኛ ንፋስ በቀላቀለው ዝናብ ምክንያት የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች ጭምር መውደቃቸውን ገልጿል። በዚህም ምክንያት “አንዳንድ የከተማዋ ክፍሎች የመብራት አገልግሎት” መቋረጡንም አስታውቆ ነበር።ይህንን ክስተት ተከትሎ፣ መሰል የዝናብ እና የጎርፍ አደጋዎች የሚያደርሱት ጉዳቶችን ለመቀነስ ነዋሪዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጥራቱ በየነ ጠይቀዋል። ከመንግሥት የሚሰጡ መመሪያዎችን እንዲከተሉ እና ለአደጋ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በዘንድሮው የክረምት ወቅት ለጎርፍ አደጋ የመጋለጥ ስጋት እንዳለባቸው ከገለጻቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች አንዱ ሐዋሳ ከተማ ነው። ከሲዳማ ክልሉ ዋና ከተማ በተጨማሪም በሁሉም ክልሎች ውስጥ ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች እንዳሉ ተቋሙ በትንበያው አስቀምጧል።በትግራይ ክልል በማዕከላዊ ዞን ቀይህ ተኽሊ ወረዳ ባለፈው ሳምንት ሐምሌ 14 ቀን በረዶ እና ኃይለኛ ንፋስ በቀላቀለ ዝናብ ምክንያት የአንድ ታዳጊ ህይወት ማለፉ ይታወሳል።በዚህ ክስተት 10 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን፣ ከ200 በላይ እንስሳት መሞታቸውን እንዲሁም ከአንድ ሺህ ሄክታር በላይ አዝዕርት መውደሙን የወረዳው ምክትል ኃላፊ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የፎቶው ባለመብት,Hawassa City Communication
የፎቶው ባለመብት,Hawassa City Communication
የፎቶው ባለመብት,Hawassa City Communicationያጋሩ, በሀዋሳ ከተማ በረዶ ቀላቅሎ በጣለ ከባድ ዝናብ የአንዲት እናት ሕይወት አለፈ - ከ 9 ሰአት በፊትታዋቂው ደራሲ ሳልማን ሩሽዲን ለመግደል የሞከረው ግለሰብ በሽብር ወንጀል ተፈረደበት
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesታዋቂው ደራሲ ሳልማን ሩሽዲን ለመግደል በመሞከር 25 ዓመት ተፈርዶበት እስር ቤት ያለው ግለሰብ በተጨማሪ የሽብር ወንጀል ክሶች ተፈረደበት።ክሱ የሽብር ቡድኖችን በግብዓት መደገፍን ይጨምራል። ከእነዚህ ቡድኖች መካከል አሜሪካ እና ዩናይትድን ኪንግደምን ጨምሮ ሌሎች አገራትም ሽብርተኛ ብለው የፈረጁት ሄዝቦላህ ይገኝበታል።ሀዲ ማራር በኒው ዮርክ የፌደራል ፍርድ ቤት ረቡዕ ዕለት ተፈርዶበታል።የኢራን ሃይማኖታዊ መሪ በአውሮፓውያኑ 1989 ሳልማን ሩሽዲ እንዲገደል ያወጡትን ፋትዋ ለመፈጸም መሞከሩን ዐቃቤ ሕግ ገልጿል።ድንበር ተሻጋሪ የሽብር ድርጊት በመፈጸም እና ለሄዝቦላህ ድጋፍ በመስጠትም ተፈርዶበታል።ተሸላሚው ደራሲ በፍርድ ቤት ቃሉን ሲሰጥ ሕይወቱን ያረፈውን የእሳት አደጋ ተከላካይ አመስግኗል።ሳልማን ሩሽዲ መድረክ ላይ ንግግር እያደረገ ሳለ በደረሰበት የስለት ጥቃት አንደ ዐይኑን አጥቷል።ሕንድ የተወለደው እና የእንግሊዝ እና የአሜሪካ ጥምር ዜግነት ያለው ሩሽዲ፤ በዘመናዊው ዓለም ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆኑት ደራሲያን መካከል አንዱ መሆኑ ይነገርለታል።ያጋሩ, ታዋቂው ደራሲ ሳልማን ሩሽዲን ለመግደል የሞከረው ግለሰብ በሽብር ወንጀል ተፈረደበት - 30 ሀምሌ 2026ሩሲያ በዩክሬን ባደረሰችው ጥቃት ሁለት ሕጻናትን ጨምሮ ስምንት ሰዎች ተገደሉ
የፎቶው ባለመብት,Reutersሩሲያ በዩክሬን ላይ በፈጸመችው የሚሳዔል ጥቃት ሁለት ሕጻናትን ጨምሮ ስምንት ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ።ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ረቡዕ በሰጡት ማስጠንቀቂያ ሩሲያ “መጠነ ሰፊ ጥቃት” ልታደርስ ትችላለች ብለዋል።ዛሬ ሐሙስ ንጋት ላይ በርካታ የሚሳዔል እና ድሮን ጥቃቶች መፈጸማቸውን የዩክሬን ጦር አስታውቋል።ጥቃቶቹ የተፈጸሙት ዜሌንስኪ ከአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው።ዩክሬን ሚሳዔል መቃወሚያ የሆነውን ‘ፓትሪዮት ኢንተርሴፕተር’ እንድታመርት ፈቃድ እንዲሰጣት ዜሌንስኪ ጠይቀዋል።በዩክሬን ክሪቭ ሪህ ከተማ በደረሰው ጥቃት የሞቱት ሕጻናት ዕድሜያቸው 5 እና 12 መሆኑን ባለሥልጣናት ተናግረዋል።ጉዳት ከደረሰባቸው ስምንት ሰዎች መካከል ሁለቱ ሕጻናት መሆናቸውም ተገልጿል።በመዲናዋ ኪቭ ምሽት ላይ በሦስት ሕንጻዎች በተነሳ እሳት ሳቢያ አንድ ሰው መሞቱን የከተማዋ ከንቲባ ቪታል ክሊትሾኮ በቴግራም ገጻቸው አስታውቀዋል።ያጋሩ, ሩሲያ በዩክሬን ባደረሰችው ጥቃት ሁለት ሕጻናትን ጨምሮ ስምንት ሰዎች ተገደሉ - 30 ሀምሌ 2026የአሜሪካ ወታደሮች ላይ የተሰነዘረውን የጥቃት ሙከራ ተከትሎ ዋሽንግተን ኢራን ላይ “ከፍተኛ” ድብደባ ፈጸመች
የፎቶው ባለመብት,Reutersየአሜሪካ ጦር ኢራን በዋሽንግተን ኃይሎች ላይ ለሰነዘረቻቸው የሚሳዔል ጥቃት ሙከራዎች የአጸፋ ምላሽ ለመስጠት ሲል፤ ረቡዕ ምሽት ኢራን ላይ “ከፍተኛ” ድብደባ መፈጸሙን አስታወቀ።በዚህ ጥቃት “በርካታ” የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ዒላማዎች መመታታቸውን የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንትኮም) ገልጿል።አሜሪካ ጋብ አድርጋው የነበረውን ድብደባ በድጋሚ የጀመረችው፤ ማክሰኞ ዕለት ኢራን በዮርዳኖስ በሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሠፈሮች እንዲሁም በሆርሙዝ ወሽመጥ ጉዞ ላይ የነበሩ መርከቦች ላይ ሚሳዔሎችን በማስወንጨፏ እንደሆነ ዕዙ ተናግሯል።የአሁኑ መካረር የታየው አሜሪካ እና ሳዑዲ በጋራ ኢራቅ ውስጥ የሚገኙ የኢራን ተቀጽላዎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ በገለጹ ማግሥት ነው። ይህ ወታደራዊ እርምጃ የጦርነቱን አድማስ አስፍቶታል።የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ ለአንድ ሰዓት ገደማ የቆየውን የረቡዕ ምሽት ጥቃት “ኢራን ትናንት በመካከለኛው ምሥራቅ በሚገኙ የአሜሪካ ኃይሎች ላይ ለሰነዘረችው የጥቃት ሙከራ የተሰጠ ኃይለኛ ምላሽ” ሲል ገልጾታል። በኢራን የተወነጨፉ ሚሳዔሎች በሙሉ እንዲከሽፉ መደረጋቸውንም አክሏል።በአሜሪካ ጥቃት የኢራን “ወታደራዊ የዕዝ ማዕከላት፣ የሜሳዔል እና የድሮን ተቋማት፣ የባሕር ዳርቻ ቁጥጥር እና መከላከያ ስፍራዎች፣ እና የባሕር ኃይል አቅሞች” ዒላማ መደረጋቸውም ተገልጿል።ይህ ጥቃት ከመፈጸሙ አስቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ለኢራን ሙከራ ምላሽ እንደሚሰጥ ዝተው ነበር።የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ በበኩሉ ዮርዳኖስ ውስጥ የሚገኘው የአሜሪካ አየር ኃይል ጦር ሠፈር እና የዕዝ ማዕከልን ዒላማ ያደረገው “ህጻናት ገዳይ በሆነችው አሜሪካ ለተፈጸሙት የጥቃት ድርጊቶች ምላሽ ለመስጠት” እንደሆነ ገልጿል።አሜሪካ እና እስራኤል ባለፈው የካቲት ወር ኢራን ላይ ወታደራዊ ጥቃት በከፈቱበት ወቅት፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጦርነቱ የሚቆየው ለጥቂት ሳምንታት ብቻ እንደሆነ ተናግረው ነበር። ይሁን እንጂ ግጭቱ ሊያበቃ እንደሆነ የሚጠቁም ምልክት ሳይታይበት አምስተኛ ወሩን ደፍኗል።የአሜሪካው የዜና ምንጭ አክሲዮስ ስማቸው ያልተጠቀሰ አንድ የዋሽንግተን ባለሥልጣንን ዋቢ አድርጎ ባወጣው ዘገባ፤ ትራምፕ ከሳዑዲ አረቢያ የመከላከያ ሚኒስትር ልዑል ካሊድ ቢን ሰልማን ጋር መገናኘታቸውን አስነብቧል።የሳዑዲው መከላከያ ሚኒስትር አገራቸው ውጥረቱ እንዲረግብ እንደምትፈልግ ማሳወቃቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ የዋይት ሀውስን አስተያየት ለማካተት ጥያቄ አቅርቧል።አሜሪካ ለ13 ተከታታይ ቀናት ጥቃት ስትፈጽምበት፤ ኢራንም አጸፋውን ስትመልስበት የቆየው ግጭት ለቀናት አንጻራዊ መረጋጋት ከታየበት በኋላ በድጋሚ ተቀጣጥሏል።አንዳች አይነት ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ ይመጣል የሚል ተስፋ በታየባቸው ያለፉት ቀናት ሁለቱም ወገኖች ጥቃት መፈጸም አቁመው ነበር።ፕሬዝዳንት ትራምፕ “እጅግ ወዳጅነት የተሞላባቸው ድርድሮች” እየተካሄዱ መሆኑን ተናግረው ነበር። ኢራን ግን ንግግር ተጀምሯል መባሉን አስተባብላለች።ያጋሩ, የአሜሪካ ወታደሮች ላይ የተሰነዘረውን የጥቃት ሙከራ ተከትሎ ዋሽንግተን ኢራን ላይ “ከፍተኛ” ድብደባ ፈጸመች - 29 ሀምሌ 2026አሜሪካ እና ሳዑዲ በኢራቅ ውስጥ የፈጸሙትን ጥቃት ኢራን አወገዘች
የፎቶው ባለመብት,AFPየኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሜሪካ እና ሳዑዲ አረቢያ በጥምረት ኢራቅ ውስጥ የፈጸሙትን ጥቃት “በጽኑ እንደሚያወግዝ” አስታወቀ።ጥቃቱ የአሜሪካ እና ሳዑዲ ጥቃት ጦርነቱን በመካከለኛው ምሥራቅ ለማስፋፋት ያለመ ነው ሲልም ወቅሷል።ኢራን ሁለቱን አገራት “ነውጠኛ” ስትል ያወገዘች ሲሆን፣ የፈጸሙት ጥቃት የተባበሩት መንግሥታት ስምምነትን እንደሚጥስም አስታውቃለች።ጥቃቱ የአሜሪካ እና የጽዮናዊው [እስአኤል] መንግሥት “ፍላጎት” እንደሆነ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ ይጠቅሳል።“ጽዮናዊው መንግሥት ጦርነቱን እና ግጭቱን ወደ ምዕራብ እስያ ማስፋፋት ይፈልጋል” ሲልም የእስራኤልን መንግሥት ከስሷል።አሜሪካ እና ሳዑዲ በኢራቅ የሚገኙ እና በኢራን የሚደገፉ ታጣቂዎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ገልጸዋል።የኢራቅ ‘ፖፑላር ሞቢላይዜሽን ፎርስ’ ቡድን በጥቃቱ ቢያንስ 20 አባላቱ እንደተገደሉበት እና 32 እንደቆሰሉበት አስታውቋል።የአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንትኮም) “ኢራቅ ውስጥ በኢራን የሚደገፈው አሸባሪ ቡድን ላይ አነጣጥረን ጥምር ጥቃት [ከሳዑዲ አረቢያ ጋር] ፈጽመናል” ብሏል።ሳዑዲ በበኩሏ ጥቃቱ የተፈጸመው ቡድኑ የነዳጅ ማውጫዎቿን ዒላማ ካደረገ በኋላ እነደሆነ አስታውቃለች።ያጋሩ, አሜሪካ እና ሳዑዲ በኢራቅ ውስጥ የፈጸሙትን ጥቃት ኢራን አወገዘች - 29 ሀምሌ 2026አሜሪካ በ8 የኢራን የነዳጅ መርከቦች እና 10 ተቋማት ላይ ማዕቀብ ጣለች
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የአሜሪካ ግምጃ ቤት በኢራን ንብረቶች ላይ እገዳ መጣሉን አስታውቋልየአሜሪካ ግምጃ ቤት የኢራን ንብረት የሆኑ ስምንት ነዳጅ ጫኝ መርከቦች እና አሥር ተቋማት ላይ ማዕቀብ መጣሉን አስታወቀ።የአሜሪካ ግምጃ ቤት (የገንዘብ ሚኒስቴር) በድረ ገጹ ባወጣው መግለጫ ማዕቀብ ከተጣለባቸው ተቋማት ስድስቱ ቻይና ይገኛሉ።አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችው የባሕር ላይ እንቅስቃሴ ገደብ ባለበት እንደቀጠለ ነው።በኢራን ደቡባዊ የባሕር ዳርቻ በተጣለው እገዳ ምክንያት የአሜሪካ ኃይሎች ብዙ መርከቦች እንዳያልፉ ከልክለዋል።የአሜሪካ ግምጃ ቤት የጣለው አዲስ ማዕቀብ የተሰማው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራንን “ክፉኛ ለመደብደብ” ከዛቱ ከሰዓታት በኋላ ነው።ፕሬዝዳንቱ ከፎክስ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ጦራቸው በኢራን ላይ ላለፉት ቀናት ያቆመውን ጥቃት መልሶ እንደሚጀምር አመልክተዋል።ያጋሩ, አሜሪካ በ8 የኢራን የነዳጅ መርከቦች እና 10 ተቋማት ላይ ማዕቀብ ጣለች - 29 ሀምሌ 2026ኢራን የአሜሪካ ጦር ሰፈርን ማጥቃቷን ተከትሎ ትራምፕ ኢራንን “ክፉኛ” እንደሚመቱ ዛቱ
የፎቶው ባለመብት,@CENTCOMየምስሉ መግለጫ,የአሜሪካ የጦር መርከቦች በፋርስ ባሕረ ሰላጤኢራን ዮርዳኖስ ውስጥ በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ ማክሰኞ ዕለት ለሰነዘረችው የሚሳዔል ጥቃት አጸፋ “ከባድ ጥቃት” እንደሚፈጸምባት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስታወቁ።ፕሬዝዳንቱ ለፎክስ ኒውስ እንደተናገሩት “በከባዱ እንመታቸዋለን. . . ቅጣት ይጠብቃቸዋል. . . ልክ እናስገባቸዋልን…” በማለት ጦራቸው በኢራን ላይ ላለፉት ቀናት ያቆመውን ጥቃት እንደሚጀምር አመልክተዋል።የአሜሪካ ሠራዊት ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንትኮም)፤ የኢራን አብዮታዊ ዘብ ማክሰኞ በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ኃይሎችን ዒላማ ያደረጉ በርካታ ሚሳዔሎች በመተኮስ “ድንገተኛ ጥቃት ለመፈጸም ሞክሯል” በማለት፤ ነገር ግን ሁሉም ሚሳዔሎች “በተሳካ ሁኔታ” መክሸፋቸውን ገልጿል።ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን ላይ ከባድ ጥቃት እንደሚፈጸም የተናገሩት ሠራዊታቸው ለ13 ተከታታይ ቀናት በኢራን ላይ ሲፈጽም የቆየውን ጥቃት ባለፈው አርብ ካቆመ በኋላ ነው።ኢራን በአሜሪካ ለተፈጸመባት ጥቃት ዮርዳኖስን ጨምሮ በመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ውስጥ በሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች ላይ የአጸፋ እርምጃ በመውሰድ የአሜሪካ ወታደሮችን መግደሏ ተዘግቧል።የአሜሪካ ጥቃት መቆሙን ተከትሎ ኢራንም የአጸፋ ጥቃቷን አቁማ የነበረ ሲሆን፣ ባለፉት ቀናት ሁለቱን አገራት ለማቀራረብ እና የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል።ፕሬዝዳንት ትራምፕ እንዳሉት በኢራን ላይ ጥቃት የሚፈጸም ከሆነ ኢራንም አጸፋ መመለሷ አይቀሬ መሆኑን ባለፉት ሳምንታት የነበሩት ሁኔታዎች ያመለክታሉ።ያጋሩ, ኢራን የአሜሪካ ጦር ሰፈርን ማጥቃቷን ተከትሎ ትራምፕ ኢራንን “ክፉኛ” እንደሚመቱ ዛቱ - 29 ሀምሌ 2026በጃፓን በተከሰተው ርዕደ መሬት ሳቢያ 13 ሰዎች ሞቱ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ከፍተኛ መጠን ያለው ርዕደ መሬት መነሳቱን ተከትሎ 13 ሰዎች ሞተዋልደቡብ ምዕራብ ጃፓን በሚገኘው ኩይሹ ግዛት ወደ 100 የሚጠጉ ውስን ርዕደ መሬቶች ተከሰቱ።ከፍተኛ መጠን ያለው ርዕደ መሬት መነሳቱን ተከትሎ 13 ሰዎች ሞተዋል። ከፍተኛውን ርዕደ መሬት ተከትሎም መጠነኛ የሆኑ 100 የመሬት መንቀጥቀጦች ተከስተዋል።በርካታ ሰዎች ድንገተኛ የደም ዝውውር መቋረጥ እንደገጠማቸው ተገልጿል።በጃፓን ከፍተኛ ሙቀት ያለ ሲሆን፤ በኩማማቶ አካባቢ በሚገኝ የወረቀት ፋብሪካ እና የመደብር ፍርስራሽ ውስጥ ከአደጋው የተረፉ ሰዎችን ለማዳን ጥረት ቀጥሏል።የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሳኔይ ታካይቺ “ከጊዜ ጋር እሽቅድምድም ላይ ነን” ሲሉ ሰዎችን በሕይወት ለማግኘት የሚደረገውን ጥረት ገልጸዋል።በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በድንገተኛ መጠለያ ውስጥ ይገኛሉ።የጃፓን ሜትሮሎጂ ተቋም ባወጣው ማስጠንቀቂያ ነዋሪዎች አነስተኛ መጠን ላላቸው ርዕደ መሬቶች (aftershocks) ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።“ለሚቀጥለው ሳምንት፣ በተለይም ለቀጣይ ሁለት እና ሦስት ቀናት እስከ 7 ማግኒትዩድ የሚደርስ የመሬት መንቀጥቀጥ ይኖራል” ሲልም አስታውቋል።ትናንት ማክሰኞ ኩማማቶ በተከሰተው ርዕደ መሬት ኤዩን የተባለ ግዙፍ መደብር ተጎድቷል።
የፎቶው ባለመብት,EPAየምስሉ መግለጫ,በኩማማቶ አካባቢ በሚገኝ የወረቀት ፋብሪካ እና የመደብር ፍርስራሽ ውስጥ ከአደጋው የተረፉ ሰዎችን ለማዳን ጥረት ቀጥሏል
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በድንገተኛ መጠለያ ውስጥ ይገኛሉያጋሩ, በጃፓን በተከሰተው ርዕደ መሬት ሳቢያ 13 ሰዎች ሞቱ - 29 ሀምሌ 2026አሜሪካ እና ሳዑዲ የኢራን አጋር የሆኑትን የኢራቅ ታጣቂዎች ሲደበድቡ በባሕረ ሰላጤው ዳግም ውግያ አገርሸ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በሳዑዲ አረቢያ ነዳጅ ማውጫ ላይ የኢራቅ ታጣቂዎች የፈጸሙት ጥቃትን የሚያሳይ የሳተላይት ምስልአሜሪካ ለሦስት ቀናት በኢራን ላይ የምትፈጽመውን ድብደባ ገትታ ከቆየች በኋላ ረቡዕ ዕለት በኢራቅ የሚገኙ እና በኢራን የሚደገፉ ታጣቂዎች ላይ ጥቃት ፈጽማለች።ዋሺንግተን እና ሪያድ ጥቃቱን የፈጸሙት በጋራ መሆኑን አሳውቀዋል።ኢራን በበኩሏ በወሽመጡ ላይ የሚንቀሳቀሱ መርከቦች እንዲሁም በዮርዳኖስ ወደሚገኝ የአሜሪካ ጦር ሠፈር ሚሳዔሎችን ማስወነጨፏን ገልጻለች።የኢራቅ ‘ፖፑላር ሞቢላይዜሽን ፎርስ’ በመባል የሚታወቀው እና በኢራን የሚደገፈው ቡድን በአሜሪካ ጥቃት ቢያንስ 20 አባላቱ እንደተገደሉበት እና 32 እንደቆሰሉበት አስታውቋል።ሳዑዲ ጥቃቱ የተፈጸመው ቡድኑ የነዳጅ ማውጫዎቿን ዒላማ ካደረገ በኋላ እነደሆነ አስታውቃለች።አሜሪካ እና ሳዑዲ አረቢያ በጋራ የፈጸሙት ይህ ጥቃት በሳዑዲ የሚገኙ ሱኒዎችን በኢራቅ ከሚገኙ ሺዓዎች ጋር ጦርነት ውስጥ በመክተት አዲስ የግጭት በር የከፈተ ሆኗል።ሳዑዲ አረቢያ ከአሜሪካ ጋር በመሆን በዚህ ጦርነት ውስጥ መሳተፏን ስታሳውቅ ይህ የመጀመርያዋ ነው።ከአሜሪካ እንዲሁም ከኢራን ጋር የቅርብ ግንኙነት ያለው የኢራን አስተዳደር አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል።ዋሺንግተን ለረዥም ጊዜ ባግዳድ በኢራን በሚደገፉት ታጣቂዎች ላይ እርምጃ እንድትወስድ ስትጠይቅ የቆየች ሲሆን የኢራን አስተዳደር ይህንን ለማድረግ ሲሞክር በአካባቢው አለመረጋጋት ተከስቷል።ሳዑዲ አረቢያ በሌላ አቅጣጫ በየመን ከሚገኙት የሁቲ አማፂያን ጋር ግጭት ውስጥ ገብታለች።በኢራን የሚደገፉት ሁቲዎች የሳዑዲ መርከቦች በቀይ ባሕር እንዳያልፉ እገዳ ጥለዋል።ሳዑዲ አረቢያ እና አሜሪካ በጋራ በኢራቅ ጥቃት ከፈጸሙ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ የአሜሪካ ጦር በወታደሮቹ ላይ ኢራን የከፈተችውን ድንገተኛ ጥቃት ማክሸፉን አስታውቋል።የዮርዳኖስ ጦር ከኢራን የተወነጨፉ አምስት ሚሳዔሎችን መትቶ መጣሉን ገልጿል።በዚህ ወር በኢራን ጦርነት ከሞቱት አራት የአሜሪካ ወታደሮች መካከል ሦስቱ የተገደሉት በዮርዳኖስ ነው።የኢራን አብዮታዊ ዘብ በበኩሉ በዮርዳኖስ በሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሠፈሮች ሚሳዔሎችም ማስወንጨፉን እንዲሁም ያለ ፈቃድ በወሽመጡ ለማለፍ የሞከሩ ሦስት ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን ማጥቃቱን አስታውቋል።ያጋሩ, አሜሪካ እና ሳዑዲ የኢራን አጋር የሆኑትን የኢራቅ ታጣቂዎች ሲደበድቡ በባሕረ ሰላጤው ዳግም ውግያ አገርሸ - 29 ሀምሌ 2026አምስት የኬንያ የጸጥታ አባላት በሶማሊያ ድንበር አቅራቢያ በአልሸባብ ታጣቂዎች ተገደሉ
የፎቶው ባለመብት,Washinton Post via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የኬንያ ፖሊስ አባላትበሶማሊያ ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው ማንዴራ ክልል ውስጥ ከአል ሻባብ ታጣቂዎች ጋር በተደረገ ግጭት አምስት የኬንያ የጸጥታ ኃይል አባላት መገደላቸውን ፖሊስ ገለጸ።ታጣቂ ቡድኑ የሶማሊያን ማዕከላዊ መንግሥት ለመጣል እና በእስላማዊ ሸሪዓ ሕግ የሚመራ ሥርዓትን ለመዘርጋት ለዓመታት ሲታገል ቆይቷል።ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ “በአካባቢው ቅኝት እያደረገ የነበረ ቡድን በዋንቴይ ግድብ አካባቢ ከአል ሸባብ አማጺያን ጋር ከተገናኘ በኋላ” ጥቃቱ መፈጸሙን ፖሊስ አስታውቋል።ፖሊስ ተጨማሪ ኃይል ከተላከለት በኋላ ታጣቂዎቹን መከታተል መጀመሩን እና የተቀበረ ፈንጂ መኪናው ላይ ጉዳት ማድረሱን አስታውቋል።በፈንጂው ፍንዳታ በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ጨምሮ ገልጿል።አል ሸባብ በጸጥታ ኃይሎች እና በሰላማዊ ዜጎች ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት የሚያደርስ ሲሆን በጥር ወር በጋሪሳ የአካባቢውን አስተዳደር እና አንድ መምህር ገድሏል።ያጋሩ, አምስት የኬንያ የጸጥታ አባላት በሶማሊያ ድንበር አቅራቢያ በአልሸባብ ታጣቂዎች ተገደሉ - 29 ሀምሌ 2026ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን በጋራ ለማስተዳደር አማን ያቀረበችውን ዕቅድ ውድቅ አደረገች
የፎቶው ባለመብት,APየምስሉ መግለጫ,በሆርሙዝ ወሽመጥ በኦማን ባህረ ሰላጤ ውስጥ የነዳጅ እና የጭነት መርከቦች ሲንቀሳቀሱ ይታያልኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን በጋራ ለማስተዳደር አማን ያቀረበችውን ዕቅድ የመሳካት ዕድል የለውም ስትል ውድቅ አደረገች።አንድ ከፍተኛ የአራን ባለሥልጣን ለሮይተርስ እነደተናገሩት ዕቀዱ “የመሳካት ዕድል የለውም” በማለት ወሽመጡን መቆጣጠር የኢራንን ሉዓላዊ መብቶች ማረጋገጥ አለበት ሲሉ ተናግረዋል።ባለሥልጣኑ ኢራን እና ኦማን ብቻ የሆርሙዝ ወሽመጥን በማስተዳደር ረገድ የሚጋሩት ድንበር ስላለ የመወሰን መብት እንዳላቸው በመጥቀስ የሌሎች የቀጣናው አገራትን ሚና ውድቅ አድርገዋል።ባለሥልጣኑ አሜሪካ እና ሳዑዲ አረቢያ በወሽመጡ ላይ ያላቸውን “ከእውነታው የተቃረነ ዕቅዳቸውን” ለማስፈጸም ኦማን ላይ ጫና እያደረጉ ነው ሲሉ ተናግረዋል።ኢራን እና ኦማን የሆርሙዝ ወሽመጥ ተቃራኒ የባሕር ዳርቻዎችን ይቆጣጠራሉ።ነገር ግን ቴህራን የወሽመጡ የውስጠኛ መተላለፊያ እንዲሁም በከፊል ከወሽመጡ ውጪ ያሉ አካባቢዎች በኢራን ቁጥጥር ሥር መሆን አለበት ብላ እንደምታምን ባለሥልጣኑ ጨምረው ለሮይተርስ አስረድተዋል።ያጋሩ, ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን በጋራ ለማስተዳደር አማን ያቀረበችውን ዕቅድ ውድቅ አደረገች - 29 ሀምሌ 2026ኢራን የሚሳዔል መከላከያ በቅርቡ ከቻይና ልታገኝ ነው ተባለ
የፎቶው ባለመብት,Reutersኢራን በሳምንታት ውስጥ 400 የሚደርሱ ትከሻ ላይ ተደርገው የሚተኮሱ የአየር መቃወሚያዎች ልትረከብ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሮይተርስ ተናገሩ።ግዢው ከ60 እስከ 70 ሚሊዮን ዶላር የተገመተ ሲሆን ከአሜሪካ ጋር ጦርነት ውስጥ የምትገኘዋን የኢራን ጦር አቅም ዳግም ያጠናክራል ተብሏል።አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጦርነት ከከፈቱ ወዲህ ቴህራን የአጭር ርቀት የአየር መከላከያ አቅሟን ስታጠናክር ይህ የመጀመርያው ነው።ቴህራን በደረሰባት ተደጋጋሚ ድብደባ የወታደራዊ ካምፖቿን እና ቁልፍ መሠረተ ልማቶቿን መከላከል ሳትችል ቀርታለች።ኢራን ከቻይና የገዛችው በሰው ኃይል የሚንቀሳቀሱ ከ300 እስከ 400 የሚሆኑ የአየር መከላከያ ሥርዓቶች ሲሆኑ ይህም ቻይና ሰራሹ ኪውደብሊው-12 (QW-12) እና ኤፍኤን-16 (FN-16) ሚሳዔሎችን እንደሚያካትት ምንጮች ለሮይተርስ ተናግረዋል።የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ ያለው ነገር ለም።የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር “እንዲህ ዓይነት ዘገባዎች ሙሉ በሙሉ መሠረተ ቢስ ናቸው። ቻይና ምን ጊዜም ሰላም እንዲሰፍን እና ግጭቱ እንዲቆም ስትሰራ ቆይታለች” ብሏል።ከአሜሪካ እና እስራኤል ጋር ለወራት የዘለቀውን ግጭት ተከትሎ የቴህራን የሚሳዔል፣ ድሮን እና የአየር መከላከያ ፕሮግራሞች ጋር የተያያዙ ተቋማት በመደብደባቸው ኢራን ወታደራዊ አቅሟን እንደገና ማጠናከር አስፈልጓታል።ያጋሩ, ኢራን የሚሳዔል መከላከያ በቅርቡ ከቻይና ልታገኝ ነው ተባለ - 29 ሀምሌ 2026ኢራን በአሜሪካ ኃይሎች ላይ ድንገተኛ ጥቃት መፈጸሟ ተገለጸ
የፎቶው ባለመብት,Handout photo by US. Navy via Getty Imagesኢራን በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኝ የአሜሪካ ወታደሮች ላይ ድንገተኛ የባሌስቲክ ሚሳዔል ጥቃት መክፈቷን የአሜሪካ ጦር አስታወቀ።ጥቃቱ ማክሰኞ ምሽት መፈጸሙን የተገለጸ ሲሆን ሁሉንም ሚሳዔሎች “ውጤታማ በሆነ መልኩ አክሽፈናል” ሲል የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ አስታውቋል።ዕዙ ጥቃቱ የተፈጸመበትን አካባቢ በግልጽ ያላስቀመጠ ሲሆን በሁለቱ አገራት መካከል ለሦስት ቀን ተቋርጦ የነበረውን ውጊያ ዳግም እንዲያገረሽ ሊያደርገው ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል።የአሜሪካ ጦር እና የሳዑዲ አረቢያ ኃይሎች በጥምረት “በኢራን የሚደገፉ አሸባሪዎች” ያሏቸው በኢራቅ የሚገኙ ታጣቂዎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ሴንቲኮም አስታውቋል።ቴህራን እስካሁን ድረስ በጉዳዩ ላይ አስተያየቷን አልሰጠችም።ኢራን ፈጸመችው የተባለው ጥቃት ሁለቱ አገራት ዳግም ለድርድር ይቀመጣሉ የሚለው ተስፋ እንዲደበዝዝ አድርጓል።የአሜሪካ ጦር እና ሳዑዲ አረቢያ በምሥራቃዊ ኢራቅ ያሉ “በርካታ የአሸባሪዎች መገኛዎች እና የጦር መሣሪያ ማከማቻዎችን” መደብደባቸውን ሴንቲኮም አስታውቋል።የአሜሪካ ጦር ይህ ድብደባ “ባለፉት 72 ሰዓታት ውስጥ በኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ (አይአርጂሲ) የተመሩ ከ30 በላይ የአየር ላይ ድሮን ጥቃቶች ላይ የተወሰደ ጠንካራ ምላሽ” መሆኑን ገልጿል።ሴንቲኮም የኢራን ጦር “እና የሽብር ወኪሎቹ ተጨማሪ የአሜሪካ ወታደራዊ ምላሽ ለማስቀረት ሲሉ እነዚህን ጥቃቶች ማቆም አለባቸው” ሲል አስጠንቅቋል።ማክሰኞ ዕለት ሳዑዲ አረቢያ ጦሯ በአገሪቱ ምሥራቃዊ ክፍል የሚገኙ የፔትሮሎየም ተቋማትን ዒላማ ያደረጉ ሚሳዔሎችን ማክሸፉን አስታውቃለች።የጦሩ ቃል አቀባይ ሜጀር ጄነራል ቱርኪ አል ማሊኪ የድሮን ጥቃቶቹ የተከፈቱት በኢራቅ ውስጥ የሚገኙ እና ከኢራን ጋር ግንኙነት ባላቸው ቡድኖች ነው ብለዋል።በሁለቱ አገራት መካከል ዳግም ግጭት ያገረሸው የአሜሪካው ፕሬዚዳት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር “በጣም ወዳጅነት የተሞላበት ድርድር” እያደረጉ መሆኑን ከተናገሩ በኋላ ነው።ሁለቱ አገራት የሚያደርጉትን ውጊያ ጋብ ያደረጉት፣ ለሁለት ሳምንት ገደማ አንዳቸው በሌላኛቸው ይዞታ ላይ ጥቃት ሲያደርሱ ከቆዩ በኋላ ነው። ውጊያው ማገርሸቱም ሰኔ ላይ የተፈረመውን ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት አደጋ ውስጥ ከትቶታል።ያጋሩ, ኢራን በአሜሪካ ኃይሎች ላይ ድንገተኛ ጥቃት መፈጸሟ ተገለጸ - 28 ሀምሌ 2026የአሜሪካ ጦር በቅርቡ ኢራን ላይ ለፈጸመው ድብደባ የእስራኤልን ጦር ሠፈር መጠቀሙ ተገለጸ
የፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር በቅርቡ የአሜሪካ ጦር በኢራን ላይ ለፈጸመው ድብደባ የእስራኤልን ጦር ሠፈር መጠቀሙን ገለፁ።እዝራኤል ካትዝ የኢራን ባለሥልጣናት ይህንን እንደሚያውቁ ተናግረው ነገር ግን የአጸፋ ጥቃት አለመፈጸማቸውን ተናግረዋል።“እውነታው ኢራን የቀጣናው አገራት ላይ በሙሉ ጥቃት ስትፈጽም እስራኤል ላይ ግን ምንም እርምጃ አልወሰደችም። ምንም እንኳ ያ በሰዓት ውስጥ የሚቀየር ቢሆንም” ሲሉ ለእስራኤሉ መገናኛ ብዙኃን ቻናል 14 ተናግረዋል።የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ በዋይት ሐውስ ተገናኝተው ይወያያሉ።የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ኢራን በእስራኤል ላይ ጥቃት ለመፈጸም ብትሞክር “በሙሉ ኃይላችን” ምላሽ እንሰጣለን ሲሉ ዝተዋል።“እኔ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ እስራኤል ላይ ጥቃት ከተፈጸመ በሙሉ ኃይላችን ምላሽ ለመስጠት ተነጋግረናል” ሲሉ ጨምረው አብራርተዋል።ያጋሩ, የአሜሪካ ጦር በቅርቡ ኢራን ላይ ለፈጸመው ድብደባ የእስራኤልን ጦር ሠፈር መጠቀሙ ተገለጸ
