Achamyeleh Tamiru ·Follow
አማራን ማጥፋትን የፖለቲካ እስትንፋሱና የኅልውናው መሠረት አድርጎ የተፈጠረውን፣ በዚያው ዓላማ የኖረውንና ወደፊትም በዚያው የጥፋት መንገድ የሚቀጥለውን ፋሽስት ወያኔን የአማራ የኅልውና ተጋድሎ አጋር አድርገው ለማቅረብ የሚደረገው አሳፋሪና ወንጀለኛ ሙከራ ዝም ተብሎ ወደማይታለፍበት ደረጃ ላይ ደርሷል። በየማኅበራዊ ሜዲያው እየወጡ ፋሽስት ወያኔን እንደ አማራ ‘ትግል’ አጋር እንድንቆጥርላቸው ላንቃቸው እስኪሰነጠቅ ድረስ ሲለፋደዱ የሚሰሙት አብዛኛዎቹ የፋሽስት ወያኔ ነውረኛ ድርጅት የሆነው የብአዴን ጠረናቸው ሳይለቅ፣ በአማራ የኅልውና ተጋድሎ ላይ ተጣብቀው የተቀመጡ አለቅቶች ናቸው።
እነዚህ ፋሽስት ወያኔን ለአማራ ሕዝብ ሊሸጡለት የሚሞክሩት በአማራ ሕዝብ የኅልውና ተጋድሎ ላይ የተጣበቁ የብአዴን አለቅቶች ፋሽስት ወያኔ ከተፈጠረ ጀምሮ ከኀምሳ ዓመታት በላይ በአማራ ሕዝብ ላይ በቀጥታ ሲፈጽምና በወኪሎቹ ሲያስፈጽም የኖረውን ፍጅት፣ የዘር ማጥፋት፣ እልቂት፣ መከራ፣ ግፍ፣ ማፈናቀልና ተቆጥሮ የማያልቅ ታሪካዊ በደል ዳግም በመካድ፣ በአማራ ሕዝብ ደም፣ መስዋዕትነት፣ ክብርና ታሪካዊ ትውስታ ላይ ግልጽ ክህደትና ከባድ የፖለቲካ ወንጀል እየፈጸሙ ነው።
ፋሽስት ወያኔ ትናንትናም ሆነ ዛሬ ጦር የሚሰብቀውና የሰበቀው አማራን ለማጥፋት እና አጽመ ርስቱ የሆኑትን ወልቃይትን፣ ጠገዴን፣ ጠለምንት፣ ሁመራን፣ ኮረምን፣ አላማጣ፣ ዋጃ፣ መሆኒ እና በወረራ የያዛቸውን የራያ አካባቢዎች ለመውረር እና ታላቋን ትግራይ ለመመስረት ብቻ ነው። ፋሽስት ወያኔ ከዚህ ውጭ የሚዋጋበት ምክንያት የለውም!
በአሁኑ ወቅት አማራ የሚያስፈልገው የአማራ አላማ ያለው እና በጥብቅ ዲሲፕሊን የሚገዛ አታጋይ ድርጅት እንጂ እንደ ፋሽስት ወያኔ አይነት አማራን ማጥፋትን የፖለቲካ እስትንፋሱና የኅልውናው መሠረት ያደረገ የትግል ‘አጋር’ አይደለም።
ባጭሩ እንደ ቱትሲ የዘር ማጥፋት ጦርነት የታወጀበት የአማራ ሕዝብ እንደ ሁቱዎቹ ኢንተርሃሞዮች ከኾነበት የዐቢይ አሕመድ የኦሮሙማው አረመኔ አገዛዝ የዘር ማጥፋት ጦርነት ለመትረፍ ያለው ብቸኛ አማራጭ እንደ ቱትሲዎቹ አላማ እና ዲሲፕሊን ያለው የአርበኞች ድርጅት ማቋቋምና እንደ ፖል ካጋሜ አይነት ጀግና የአርበኛ መሪ መፍጠር እንጂ ሲያጠፋው ለኖረውና ሊያጠፋው ጦር ከሚሰብቀው ፋሽስት ወያኔ ጋር አንሰላ መጋፈፍ አይደለም። የአማራ ሕዝብ እንደ ቱትሲዎቹ አላማ እና ዲሲፕሊን ያለው የአርበኞች ድርጅት ማቋቋምና ከራሱ በላይ የኾነ አላማ ያለው አታጋይ መሪ ካገኘ የፋሽስት ወያኔና መሰል ጸረ አማራ እና ጸረ ኢትዮጵያ ድርጅቶች አጋር አያስፈልገውም።
See less
