የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ ሊፈጸም የነበረ “መጠነ ሰፊ” ጥቃት እንዲቀር ካደረጉ በኋላ ዛሬ ሰኞ ከቴህራን ባለሥልጣናት ጋር አዲስ ንግግር እንደሚጀመር ተናግረዋል። ኢራን ግን ከአሜሪካ ጋር ምንም ዓይነት ንግግር እያካሄደች አለመሆኗን ገልጻ፣ ከኦማን ጋር በሆርሙዝ ወሽመጥ ደኅንነቱ የተጠበቀ ጉዞ እንዲደረግ የሚያስችል “ጊዜያዊ የባህር መጓጓዣ መስመር” ለመመስረት እየሰራሁ ነው ብላለች።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. 3 ነሐሴ 2026የአሜሪካ ጦር ኢራንን ለመቅጣት “ያልተለመዱ ሐሳቦች” እንዳሉት ተዘገበዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,APየአሜሪካ ጦር ኢራንን ለመቅጣት እና ጫና ለማሳደር “በፈጠራ የተሞሉ እና ያልተለመዱ” ሐሳቦችን እየተመለከተ እንደሚገኝ ሲኤንኤን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮችን ጠቅሶ ዘገበ።በአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንትኮም) አመራር የሆኑ የሲኤንኤን ምንጭ እንደጠቆሙት፤ “ኢራን ላይ ጫና ለማሳደር እና ለመቅጣት አዳዲስ መንገዶች እየተመለከትን ነው” የሚል ኢሜል ተልኳል።የአሜሪካ ጦር ስትራቴጂውን መለወጥ ስላለበት ሁሉንም ዓይነት መንገዶችን እየተመለከተ መሆኑን ሌላ የሲኤንኤን ምንጭ ጠቅሰዋል።የአሜሪካ ጦር ሐሳቦች በኢሜል እንዲላኩለት መጠየቁ የተለመደ አሠራር እንዳልሆነ ወታደራዊ ባለሥልጣን መናገራቸው በዘገባው ተጠቅሷል።የአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ ቃል አቀባይ ብራድ ኩፐር በበኩላቸው “በፈጠራ የተሞሉ መንገዶች ማሰብ እና መተግበር በጦሩ ታሪክ የተለመደ ነው” ብለዋል።“ከፍተኛ የኦፕሬሽን ውጤት ለማግኘት” በየትኛውም ወታደራዊ ማዕረግ ደረጃ ላይ ከሚገኙ ወታደሮች ሐሳብ እንደሚሰበስቡ ገልጸዋል።የሲኤንኤን ምንጭ “በስተመጨረሻ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ስምምነት ላይ መድረስ ይፈልጋሉ። ስለዚህም ጫና ማሳደሪያ እና ከዚህ ሁኔታ መውጫ መንገድ ይፈልጋሉ። አንዳንዴ የተለመደው አካሄድ ሲሟጠጥ በፈጠራ የተሞላ አስተሳሰብ ያስፈልጋል” ብለዋል።ያጋሩ, የአሜሪካ ጦር ኢራንን ለመቅጣት “ያልተለመዱ ሐሳቦች” እንዳሉት ተዘገበ
  2. 3 ነሐሴ 2026የፍርድ ሒደት እየተካሄደ ሳለ የሱዳን ጦር ባደረሰው የድሮን ጥቃት 35 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸየሱዳን ሰንደቅ አላማየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesበሰሜን ሱዳን ዳርፉር ግዛት ባህላዊ የፍርድ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ሳለ የሱዳን ጦር በፈጸመው የድሮን ጥቃት 35 ሰዎች መገደላቸውን የመብት ተሟጋች ተቋም አስታወቀ።ትናንት እሑድ ከሰዓት በተፈጸመው ጥቃት በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውን የሱዳን የመብት ተሟጋች ተቋም ገልጿል።በንጹኃን ላይ የሚፈጸም ጥቃትን የሚከታተለው ‘ዘ ኢመርጀንሲ ሎየርስ ግሩፕ’ እንዳለው የድሮን ጥቃቱ የተፈጸመው ጋህራ አል-ዛዊያ በተባለ መንደር ነው።መንደሩ በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል (አርኤስኤፍ) ቁጥጥር ሥር የሚገኝ ነው። ስለተፈጸመው የድሮን ጥቃት የሱዳን ጦር አስተያየት አልሰጠም።አርኤስኤፍ አብዛኛውን የዳርፉር አካባቢ ይቆጣጠራል።ለሦስት ዓመታት በተካሄደው የእርስ በርስ ጦርነት በአሥር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተፈናቅለዋል።ኤኤፍፒ ያነጋገራቸው የዐይን እማኝ “የእሑዱ የፍርድ ሥነ ሥርዓት የማኅበረሰብ መሪዎች በተገኙበት ዛፍ ሥር እየተከናወነ ነበር” ብለዋል።አራት የጎሳ መሪዎች እና ሁለት የአርኤስኤፍ ኮማንደሮች በጥቃቱ ከተገደሉት መካከል እንደሚገኙበት የዐይን እማኙ ገልጸዋል።የግል ሚዲያ የሆነው ዳርፉር 24 ድረ ገጽ አንድ ነዋሪን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ሁለት ድሮኖች በአካባቢው በርረው “ከአራት ሚሳዔል በላይ” ተኩሰዋል።የመብት ተሟጋች ቡድኑ የድሮን ጥቃቱን አውግዞ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቋል።ንጹኃን ዜጎችን እና መሠረተ ልማትን ዒላማ ማድረግ “ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ጋር የሚጻረር” እንደሆነም ገልጿል።ያጋሩ, የፍርድ ሒደት እየተካሄደ ሳለ የሱዳን ጦር ባደረሰው የድሮን ጥቃት 35 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ
  3. 3 ነሐሴ 2026ኢራን ከአሜሪካ ጋር እየተነጋገርኩ አይደለም አለችየአሜሪካ እና የኢራን ባንዲራዎችየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesኢራን ሰኞ ዕለት ከአሜሪካ ጋር ምንም ዓይነት ንግግር እያካሄደች አለመሆኗን ገልጻ፣ ከኦማን ጋር በሆርሙዝ ወሽመጥ ደኅንነቱ የተጠበቀ ጉዞ እንዲደረግ የሚያስችል “ጊዜያዊ የባህር መጓጓዣ መስመር” ለመመስረት እየሰራሁ ነው አለች።የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኤል ባጋይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ቴህራን ከሙስካት ጋር የምታደርገው ንግግር ቁልፍ በሆነው የባሕር መስመር ላይ ጊዜያዊ የመርከቦች መንቀሳቀሻ ለመመስረት ያለመ ነው ብለዋል።ከኢራን መንግሥት ጋር ቅርበት ያለው ፋርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው ባጋይ “ከኦማን ጋር የምናደርገው የአሁኑ ውይይት በሆርሙዝ ባህር ወሽመጥ ውስጥ የመርከቦችን ደኅንነቱ የተጠበቀ ጉዞ ማረጋገጥ ላይ ያተኮረ ነው” ብለዋል።“በሆርሙዝ ባህር ወሽመጥ ውስጥ የመርከብ ጉዞ ደኅንነትን ለማረጋገጥ እንዲቻል፣ ከኦማን ጋር በመተባበር በተቻለ ፍጥነት ጊዜያዊ የመተላለፊያ መስመር ለመዘርጋት እየሰራን ነው” ሲሉም አክለዋል።ባጋይ በቴህራን እና በዋሽንግተን መካከል ንግግር እየተደረገ ነው የሚሉ ዘገባዎችን ውድቅ በማድረግ “ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ድርድር እያደረግን አይደለም” ብለዋል።የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ሰኞ ከሰዓት በኋላ ውይይት እንደሚጀመር ትናንት እሁድ ተናግረው ነበር። ትራምፕ፣ በሆርሙዝ ጉዳይ እና የኢራንን “ኒውክሌር ማስወገድ” በተመለከተ በቅርቡ ስምምነት ላይ መድረስ እንደሚቻል ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል ።ባጋይ “አሜሪካ ጥቃቷን እና ክልከላዋን እስከቀጠለች ድረስ [በሆርሙዝ ያለው ሁኔታ ላይ] የሚለወጥ ነገር አይኖርም” ብለዋል።ያጋሩ, ኢራን ከአሜሪካ ጋር እየተነጋገርኩ አይደለም አለች
  4. 3 ነሐሴ 2026ዩክሬን የሩሲያን ነዳጅ ማጣሪያ እና አየር ማረፊያ መምታቷን ስትገልጽ፤ ሞስኮ ስምንት ሰዎች መገደላቸውን አስታወቀችየዩክሬን ጥቃትየፎቶው ባለመብት,Zelenskiy / Officialዩክሬን ወደ ሩሲያ ግዛት ዘልቃ በመግባት በፈጸመቻቸው ጥቃቶች የአገሪቱን ዋነኛ የነዳጅ ማጣሪያ እና የሩሲያ ስትራቴጂካዊ አቪዬሽን የሚገኝበትን አየር ማረፊያ መምታቷን ገልጻለች።ከዩክሬን ድንበር 600 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኙት የኤንግልስ አየር ማረፊያ እና የነዳጅ ማጣሪያ መመታታቸውን የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቭሎዲሚር ዜሌንስኪ ተናግረዋል።እነዚህ መሠረተ ልማቶች የሩሲያን ጦርነት በገንዘብ ለመደገፍ እንደሚያገለግሉም ጠቅሰዋል። ፕሬዝዳንቱ ኤንግልስ አየር ማረፊያ እና ሳራቶቭ ነዳጅ ማጣሪያንም “ስትራቴጂካዊ ተቋማት” ሲሉ ገልጸዋቸዋል።ካሉጋ ግዛት ውስጥ የሚገኝ የነዳጅ ዴፖ እና በብራያንስክ ያለ የድሮን ማስወንጨፊያ ስፍራም ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል።ሩሲያ በበኩሏ ዩክሬን በፈጸመቻቸው ጥቃቶች ስምንት ሰዎች መገደላቸውን እንዲሁም 635 ድሮኖችን መምታቷን እና መጥለፏን አስታውቃለች።በተጨማሪም በሩሲያ ትልቁ የኦንላይን ችርቻሮ ንግድ ኩባንያ የሆነው ‘ዋይልድቤሪስ’ መጋዘን እንደተመታ ተገልጿል።በሌላ በኩል ሞስኮ በጥቁር ባሕር የሚገኙ የዩክሬን ወደቦች እና ሁለት መርከቦች ላይ ጥቃት መፈጸሟን ተናግራለች።ዩክሬንም በሰሜን ምሥራቅ ካርኪቭ ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ የፖስታ ተርሚናል ላይ በተፈጸመው የሩሲያ ጥቃት አንድ ሰው መገደሉን ገልጻለች።በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት የሚገኙ ሠፊ የጦር ግንባሮች እንቅስቃሴ ሳይታይባቸው ባሉበት ቢሆኑም፣ ሁለቱም ወገኖች በዋና ዋና ከተሞች፣ በኤነርጂ መሠረተ ልማቶች እና መጋዘኖች ላይ የሚፈጽሟቸውን ጥቃት አጠናክረዋል።ጦርነቱን ለመቋጨት በአሜሪካ የሚመራው የሽምግልና ሂደት እስካሁን ድረስ ውጤት አላመጣም።ያጋሩ, ዩክሬን የሩሲያን ነዳጅ ማጣሪያ እና አየር ማረፊያ መምታቷን ስትገልጽ፤ ሞስኮ ስምንት ሰዎች መገደላቸውን አስታወቀች
  5. 3 ነሐሴ 2026ትራምፕ ዛሬ ከኢራን ጋር አዲስ ንግግር እንደሚጀመር ጠቆሙየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Reutersበኢራን ላይ ሊፈጸም የነበረ “መጠነ ሰፊ” ጥቃት እንዲቀር ማድረጋቸውን ያስታወቁት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ዛሬ ሰኞ አዲስ ንግግር ለመጀመር ከቴህራን ጋር እንደሚቀመጡ ተናገሩ።ትራምፕ “ጥቃቱ ምን ያህል ሰፊ እንሚሆን ያውቁታል፤ ምክንያቱም ዐይናቸው ስር የሚሆነው እያዩ ነበር” ሲሉ እሁድ ዕለት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። “[ከቴህራን ጋር] በድርድር መልክ እያየተነጋገርን ነው። ነገ [ሰኞ] ከሰዓት በኋላ ይጀምራል።”ፕሬዝዳንት ይህንን ከማለታቸው አስቀድሞ በትሩዝ ሶሻል ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፣ የድርድሩ “ማዕቀፎች” ላይ ስምምነት በመደረሱ ኢራን እና የመካከለኛው ምሥራቅ አጋሮች ማንኛውን ጥቃት “እንዲቆም” መጠየቃቸውን ጽፈዋል።ኢራን ለትራምፕ አስተያየት እስካሁን ምላሽ አልሰጠችም። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጦርነቱ ሊጠናቀቅ የተቃረበበት ጊዜ እንደቀረበ በተደጋጋሚ የተናገሩ ቢሆንም ጥቃት እና የአጸፋ እርምጃዎች ሲፈጸሙ ቆይተዋል።ትራምፕ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ ከቴህራን ጋር ስምምነት የሚደረስበትን የጊዜ ገደብ ከመግለጽ ተቆጥበዋል።“ሁኔታው እንዴት እንደሚሄድ እናያለን። በፈለግነው ጊዜ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነን… ሰዎችን መግደል አልፈልግም” ብለዋል።ትራምፕ አክለውም የሳዑዲ አረቢያው አልጋ ወራሽ ልዑል መሐመድ ቢን ሳልማን እንዲሁም የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ኳታር ቅዳሜና እሁድ ጥቃት እንዳይፈጸም ጥያቄ አቅርበው እንደነበር ተናግረዋል።”ሁላችንም ጥቃቱን ለመጀመር ተዘጋጅተን ነበር” ሲሉ የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ “አጋሮቻችን ጥቃቱ እንዲዘገይ የጠየቁበት ምክንያት ስምምነት እንዳለ ስለሚያስቡ ነው” ብለዋል። “በሆርሙዝ ላይ ስምምነት አለ፣ እና በኒውክሌር ላይ ስምምነት ይኖራል” ብለዋል።ትራምፕ ይህንን ይፋ ካደረጉ በኋላ ሰኞ ጠዋት በእስያ ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ቀንሷል።የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ በበርሜል በ4.5 በመቶ ቅናሽ አሳይቶ በ83.98 ዶላር ተሸጧል።ኢራን በአሜሪካ እና እስራኤል ለተከፈተባት ጦርነት ምላሽ ስትሰጥ በወሰደችው እርምጃ የሆርሙዝ ወሽመጥ በመዘጋቱ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ አስመዝግቧል።በዓለም ላይ ካለው ድፍድፍ ዘይትና ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ውስጥ 20 በመቶ የሚሆነው የሚመጣው ከባሕረ ሰላጤው አገራት ነው።የኢራን የዜና ወኪል የሆነው ሜህር፣ ቴህራን አሜሪካ ተጨማሪ ወታደራዊ እርምጃ እንዳትወስድ ጠይቃለች መባሉን አስተባብሏል። አክሎም የትራምፕ ንግግር “አዲስ ውሸት ብቻ ነው” ብሏል።የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ እሁድ ዕለት በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ ከኦማን ጋር የተደረገው ድርድር “ወደ መጠናቀቁ እየሄደ ነው” ማለታቸውን የኢራን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ንግግሩ ሰኞ ዕለት የሚካሄድበትን ቦታም ሆነ ሊሳተፉ የሚችሉ ባለሥልጣናትን እስካሁን ይፋ አላደረጉም።ያጋሩ, ትራምፕ ዛሬ ከኢራን ጋር አዲስ ንግግር እንደሚጀመር ጠቆሙ