ልጅ ግሩም

ዶ/ር መረራ ጉዲና ላይ ያላገጡትና የተሳለቁት ኦሮሞዎች ዛሬ ምን ይሉ ይሆን? ልጅ ግሩም
ቦታው ዋሽንግተን ዲሲ ነው። የኦሮሞ ጥናት ማህበር ያዘጋጀው እና አሉ የተባሉ ምሁሮች የተገኙበት ስብሰባ ነበረ።
በአንድ ወቅት የኦሮሞዎች ነብይ እስከመባል የተሾመውና የተሸለመው ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ የስደተኛው ማስታወሻ ላይ የአድርባይነት ገጽታ የሰጣትን “ሃወኒ” የምትባለው ሴት ዶ/ር መረራ ጉዲና ናት ብሎ ሲናገር የስብስባው ታዳሚዎች ኦሮሞዎች ሳቃቸውን ለቀቁት።
ዶ/ር መረራ ጉዲና የሚታገለው ፍሬ ለሌለው ትግል መሆኑ ገብቶት ተስፋ ቆርጧል ይላል። በመጽሃፉ ላይ ሃወኒ አብረን መኖር እንችላለልን በተለይ አማሮች ወንድሞቻችን ናቸው ብላ ታምናለች ብሎ ይናገራል። ታዳሚው ይሳለቃል።
ተስፋዬ ገብረአብ በስደት ላይ ነኝ እያለ ሙሉ ህይወቱን የጎሳ ጥላቻን ለመፍጠር ብቻ ስምንት መጽሃፎችን የጻፈው ማን ደሞዝ እየከፈለው ነበር? እውነት ስደተኛ ነው?
በመጽሃፉ ላይ የጀግና ገጽታ የተሰጠው “አኖሌ” የተባለው ሰው ኤርትራ ውስጥ 25 አመት የኖረው ዳውድ ኢብሳ ነው። ይሄ ጀግንነቱ እውነት ስለመሆኑ የኦሮሞ ህዝብ ራሱ ይፍረድ!!
እስከዛሬ ለኦሮሞ ህዝብ ጠንቅ የሆነው የኦሮሞ አክቲቪስቶች ነን የሚሉት ራሳቸው የሚያግበሰብሱት አዛኝ መሳይ በመሃል እያስገቡ ዘረኝነትን የሚፈተፍቱ የውሸት ኦሮሞዎች፣ ወያኔዎች ወይም ሻዓቢያዎች ናቸው።
የዝግጅቱ አቀናባሪ ምሁር ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ጋዲሳ
Oromo Studies Association Conference, 2014 Washington DC