December 3, 2016

ኢህአዴግ ብቻውን የማይወጣው ተግዳሮት — “እኛስ ምን አይነት ብሄራዊ የአላማ አንድነት እያቀረብን ነው?”

እኔ የኢትዮጵያ ባለ ውለታ ነኝ የሚል የጸና እምነት አለኝ። ይህን ስል ወላጆቸ፤ አያቶቸና ቅድመ አያቶቸ የተለየ ጥቅም አግኝተዋል ማለቴ አይደለም። ይህች አገር የማንነቴ መገለጫ ናት ማለቴ ነው። ሕብረ ብሄር በሆነ አገር፤ ዜጎች ከተለያዩ ብሄሮች፤ ዘሮችና ኃይማኖቶች ሊመጡ ይችላሉ። ይህ የተፈጥሮ ጸጋና መብት ሲሆን ለመለያየት መሰረት መሆን የለበትም። ከብሄርና ከኃይማኖት ባሻገር፤ ሰብሳቢ መለያቸው ግን የአንድ አገር ዜጋ መሆናቸው ነው። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ አሜሪካ ነው። ከሁሉም አገሮች የተሰበሰቡ ብሄሮች፤ የኃይማኖት ተከታዮች አገር ናት አሜሪካ። ሆኖም፤ አንድ ግለሰብ ዜግነትህ/ዜግነትሽ ከየት ነው ቢባል/ብትባል አሜሪካዊ እንጅ ጀረመናዊ ወይንም እንግሊዛዊ ወይንም ናይጀሪያዊ አይልም/አትልም። የእኛም አገር ሁኔታ ከዚህ የተለየ አይደለም። ብሄራችን፤ ኃይማኖታችን፤ መደባችን፤ አመለካከታችን ወዘተርፈ ይለያያል። ይህ ችግር አይደለም፤ እንዲያውም ጸጋ ነው። ወደ አሜሪካ ተሰደን ዜግነት ስንጠይቅ የእኔን “አማራነት፤ ትግሬነት፤ ኦሮሞነት ወዘተርፈ” ፓስፖርቴ ላይ ለጥፉልኝ ብንል እብድ እንባላለን፤ ወደመጣህበት/ወደመጣሽበት! ሳንባልም አንቀርም። ይህን አስቡት። አሜሪካዊ ለመሆን ብሄራችን የመታወቂያ መለያችን አይሆንም። ያሳደገችን ኢትዮጵያ ስትሆን ግን “እኔ መለያየ ዐማራ፤ ኦሮሞ” ወዘተርፈ እያልን እንስተጋባለን። ይህ የመለያ መርህ ለአገራችን ጥፋት ግብዐት ሆኗል። የሕዝቡን አመጽ ስኬታማ ለማድረግ አንዱ የሚጎትተን ይህ ይሆናል የሚል ግምት አለኝ።

ሙሉውን ለማንበብ በPDF እዚህ ይጫኑ

አክሎግ ቢራራ (ዶር)