December 4, 2016
ከጎንደር ህብረትለኢትዮጵያ አንድነት የተሰጠ መግለጫ
በሁሉም አውራጃዎች የሚገኜው የጎንደር ህዝብ የሚያደርገውን መራር ግን አኩሪ የሆነ ትግል ሁሉም ኢትዮጵያዊ በቅርብ በመከታተል የሚያውቀው ነው።
ህዝባችን በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ፣በወታደራዊ እና በማህበራዊ ኖሮ የሚደርስበትን ግፍ እና በደል ከአብራኩ የተፈጠርን ሁሉ በአካል ተገኝተን ማገዝ ባንችልም በስደት በምንገኝበት የአለም ዙሪያ ሁሉ ጎንደሬዎች ተሰባስበን በጉልበት፣ በእውቀት ትግሉን ለማገዝ በጎህ ስር ተሰባስበን የምናደርገውን እንቅስቃሴ ለማደናቅፍ በተለያዮ አቅጣጫ ወያኔያዊ የሆነ የጠላትነት ፕሮፖጋንዳ አንዳንዶች ሲነዙ ይውላሉ።
ከእነዚህም አሉባልታዎች መካከል” የጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት በተጋድሎ ላይ ባለው ህዝብ ስም የሰበሰበውን ገንዘብ ስም ጠርተው ለእከሌ ድርጂት ሰጠ ” የሚል ደረቅ ውሼት ይገኝበታል ።
ጎህ ሲመሰረት የራሱ አላማ እና ራዕይ ያለው ጠንካራ ድርጂት እንደመሆኑ በጎህ ስም የተሰበሰበ ገንዘብ ሁሉ በቀጥታ ለራሱ አላማዎች ለማስፈፀም ማለትም በኑሮ፣ በመፈናቀል እና በጦርነት ችግር ውስጥ ለሚገኜው ህዝባችን በቀጥታ እንዲዉል እያደረገ መሆኑን ለደጋፊዎቻችን አበክረን እንገልጻለን።
አንዳንድ ህልመኞች የሆኑ፣ በሰው ሀገር ተደብቆ አየተኖረ በሀገር ቤት የሚካሔደውን የጎንደር ትግል እኛ ካልመራን አይሆንም በሚል ቅዤት የሚነዙት አሉባልታ ጎህን ሊንደው ይችላል ብለው የሚያስቡ የዋሆች ብቻ ናቸው ። ጎህ በጠንካራ መሰረት ላይ ተገነባ የጎንደር ተወላጆች ህብረት ነው። ጥንካሬያችን እና ጽናታችን የህዝባችን ቆራጥ የተጋድሎ ወጤት የፈጠረው ነው። ለእኛ ለጎህ አመራር አባላት ፣ ለህይወቱ ሰይሳሳ ለነጻነቱ የሚዋደቅን ህዝብ ገንዘብ በአግባቡ ለታለመለት አላማ አለማድረስ ማለት በሰማዕታቱ የቃል ኪዳን ተጋድሎ እንደመሳለቅ ሆኖ ይሰማናል።
ድል ለነጻነት ለሚፋለመው ህዝባችን፣
Source – Gonder Hibret