….የመሸበት ማደር!

አስፋ ጫቦ

Dallas Texas USA
“እውነቱን ተናግሮ የመሸበት ማደር!” የሚል አባባል አለ። ወዳጄን ዶክተር መረራ ጉዲናን ሳስታውስ ያ አባባል ይመጣብኛል። ከዚያ የተሻለ ሊልገልጸው የሚችል አባባል ሊኖር ይችላል።አልመጣልኝም!አሁን ታሰረ!በዚያ ምክንያት ነው ይህንን የምጽፈው
መረራ ሲጽፍ፤ ሲናገር እውነቱን ፤መረራ የሚያውቀውን እውነት፣ይጽፋል፣ ይናገራልም። ለማስቀየም ወይም ለማስደሰት ፤ወይም ፖለቲካዊ ጥቅማ ጥቅም ለማግኘት ብሎ ሲናገር የሰማሁበት ጊዜ የለም። ያ በንግግሩ ፤በጽሑፍ ያነሳቸው ሌሎቹን አላስቀየመም፤አላበሳጨም አላጋለጠም ማለት አይደለም።ያ የመረራ ግቡ አይመስለኝም።ያ የተነገረው እውነት ፤የጻፈው እውነት ውጤትነው።ከዚህ የተነሳ ምሁርነቱ፤የፖለቲካ ተዋናኝ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ መረራ ለኔ “የሰፈር አስታራቂ ሽማግሌ!” መስሎ ይታየኛል። ባለ አንጣዎቹ የሽማግሌውን ምክር ሰምተው ላይታረቁ ይችላሉ።ይህ የሽማግሌው፤የመረራ ጥፋት አይመስለኝም። “እኔ ያልኩት ብቻ ካልሆነ!” ብለውፎንክች የማይሉ ተፋላሚዎቹ ጉዳይ ይመስለኛል።

መረራጊዲና ከ1992 በፊዲት አላውቀውም። በስም ግን አውቀዋለሁ። እኔ ማእእከላዊ ታስሬ የነበረ ጊዜ መረራ ከርቸሌ እስረኛ ነበር። በመኢሶንነት ነበር የታሰረው። ታዲያ በማእከላዊና በከርቼሌ መካከል ላይና ታች እስረኛ ስለሚመላለስ ከርቼሌ ወጣ ብለው ስለሚታዩት ግለስቦችና ቡዱኖች በቂ መርጃ ነበረን።እኔ ነበረኝ!!
ማእከላዊ በተለያዩ ምክንያቶች አንድ ወጥ የሆነ የሚያስቀና ትብብር ነበረን። ከርቼሌ ግን እንደዚያ ሳይሆን ውጭ ይባላ የነበረው የፖለቲካ ቡድን ያንኑ ስፍራው በሚፈቅደው መጠን ቀጥሎበት ነበር። በዚህ የተነሳ ፤መረራ መኢሶን በመሆኑ እዚያ ጫና የፈጠረው ቡድን “ገባር” ሊያደርገው ፈልጎ አልገብርም ብሎ አንገቱን ቀና አድርጎ የተፈታ መሆኑን የሚያቁት ይነገሩኝ ነበር። ካልገበር የማግለልና የመገለል ሁኔታ (oetricized)ይፈጥርበታል። ከምግም ከሌላውም የማግለለል ሁኔታ ይፈጠራል። መረራ ይህ ተፈጥሩበት ከ አቋሙ ዝንፍ ሳይል ተፈታ ይሉኛል።
መረራን መጀመሪያ ያገኘሁት በ1993-94 ይመስለኛል። ዋሽንግቶን ዲ ሲ አሁን በሕይወት የሌላውን፤እንግዳ ተቀባይና አስተና ጋጁ ሙሉጌታ ኃይሉ ቤት ነበር። እኔ ከካሊፎርኒያ መረራ ከአዲስ አበባ መጥቶ እዚያ አርፈን ከረምንም መሰለኝ። አንድ በወቅቱ የነበር ኢድሐቅ የሚባል ድርጀት ባዘጋጀው ስብሰባ ለመገኘት ነበር የመጣው። ምርጫ በየጊዜው እየተደረገ ዶክተር በየነ ጴጥሮስ ነበር የሚመረጠው ።በዚህኛው ዙር መረራ ጉዲና ተመረጠ።በየነ ጴጥሮስ አኮረፈው።መነጋገር አቆሙ!
በአሁኑ ዙር አሜሪካ የመጣ ጊዜ በስልክ አንድ ሁለት ሶስቴ አግንቸው ነበር። በጫወታችን መካካለ የበየነ ጴጥሮስን ነገር አነሳሁበትና ሌላም የሰራውንንና የሚሰራውን አነሳነው።” አስፋ እሱን እባክህ እርሳው! ጉዳት የለውም!” አለኝ። መረራ ነገር ፍቆ አልፎ መሔድ የሚችል መሆኑን አስተዋልኩ።
ከሚጻፋቸው ነገር አንዱ ትዝ የሚለኝ የኦነግ መሥራችና መሪ ስለነበረው ስለባሮ ቱምሳ በጦቢያ መጽሔት የጻፈው ነው። ባሮ የነጻ አውጭ ጦር ግንባር ለመክፈት ሐረርጌ ወርዶ እዚያ ነው የሞተው። “እገሌ…እነእገሌ አስገደሉት!” የሚል ወሬ በወቅቱ ስራዬ ተብሎ ጭምር ይናፈስ ነበር። መረራ ማስረጃና ስም ጠቅሶ “ባሮ የተገደለው አብሮትበዘመተ፣ ብዙ የሌለ ተስፋ ሰጥቶ ከወሰዳቸው፣ተስፋ ከቆረጡት ልጆች በአንዱ፤ ከአምቦ ነው መስለኝ በሔደድ ወጣት ክላንሽኒኮብ ነው “ብሎ ጻፈ። የኦነግን ነን በሚሉ ብቻ ሳይሆን በሌላው ኦሮሞ ዘንድ ሁሉ “እውነተስ ቢሆን እንዴት ታጋልጣለህ!” በሚል ክስና ውቅስ የሚያመጣ ነው። የመረራ ስራ ግን እውነቱን ተነግሮ የመሸበት ማደር ነው።
የአሁኑየመሸበት ማደር ግን ማደሪያውን ወህኒ ቤት አደረገው። የወያኔ አድሮ ውሎም የለየለት እዉር መሆኑ ይደንቀኛል! አውቀዋለህ ሆኖም ይደንቀኛል!ዶክተር መረራ ጊጉዲና እንዴት ይታሰራል? መታሰራ የሚገባቸው እዚያ ውስጣቸው እንደ አሽን ፍልተው ማለቴ ነው። ድንገት የምታሰር ሰው እጥረት ቢፈጠር እንኳን መረራ ጉዲና መታሰር የለበትም። ከኢትዮጵያ ወይም ከመረራ አንጻር ሳይሆን ከወያኔ አንጻር አይቸው ነው። መረራ ጉዲና አውሮጳ ይሁን አሜሪካ ፤አውሮጳ ፓርላማ ይሁን ካፌ ውስጥ የሚናገረው ከላይ ያልኩትን እውነት ነው። እዚያው አዲስ አበባ ወያኔ ፊት ለፊት የሚናገርውን ነበር ለ አውሮጳ ፓርላማ የተናገረው ።።እኔ እነደታዘብኩት መረራ ጊዲና ነገር መቀባባት ፤ሞቅ ሞቅ ማድረግ አያውቅበትም። እንደወረደ ነው። ታዲያ ከዚህ የተነሳ ፣መረራ ከሁሉም በላይ ለወያኔ ጠቃሚ ሕብት ነበር።”ይኸው እንደልቡ የሚናገርተቃዋሚአለንኮ!”ለማለትይጠቅማላ!
ወያኔ እባካችህ “እፍረት!” የሚባል ቃል ፈልጋችህ እፈሩ!
እና ዶክተር መረራ ጉዲናን ፍቱልን!