December 6, 2016

ኮሚቴውን በሀይል ለማስፈታት ሞክራቹዋል የተባሉት 7ቱ ወጣቶች ሙስሊሞች የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላለፈባቸው

ሙስሊሙ ላይ የሚደርሰው ግፍ ለቀቅ ከማድረግ ይልቅ እያጠነከሩት መጥተዋል፣ ኮሚቴውን በሀይል ለማስፈታት ሞክራቹዋል የተባሉት 7ቱ ወጣቶች ጥፈተኛ ናቹ ተከላከሉ ተብለዋል እነሱም ፍትህ በሌለበት አንከላከልም በማለት ወስነው የቅጣት ብይን ለማስተላለፍ ለታህሳስ24 ተቀጥሯል፣ በነገራችን ላይ በሀይል ልታስፈቷቸው ነበር የተባሉት የኮሚቴው አባል አብዛኛው ከእስር ተፈተዋል፣ አገዛዙ ሙስሊሙ ላይ የሚያደርሰው ግፍ አጠናክሮ በቀጠለበት ጊዜ ሙስሊሙ የታሰሩትንም የረሳን እስክንመስል ድረስ ዝምታ ውጦናል አላህ ይድረስልን! !!!
ዛሬ
ፍትህ ራዲዬ
በነብዩ ሲራጅ መዝገብ የተከሰሱት 7 ሙስሊሞች የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላለፈባቸው
ፍትህ ራዲዬ/ኅዳር 27/2009
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
ከአዲስ አበባ ከተማ ከተለያዩ አካባቢዎች ለእስር የተዳረጉት በነብዩ ሲራጅ የክስ መዝገብ የተከሰሱት 7 ሙስሊሞች በቀነ ቀጠሯቸው መሰረት
የጥፋተኝነት ውሳኔ የተላለፈባቸው 7ቱ ሙስሊሞች
1. ነብዩ ሲራጅ
2. ሰፋ በደዊ
3. መሃመድ ሰዒድ
4. ሰላሃዲን ከድር
5. ሙጂብ አደም እረሺድ
6. ከድር ታደለ
7. አህመድ ኡመር መሆናቸው ታውቋል፡፡
ፍርድ ቤቱም በተከሰሱበት የሽብር ወንጀል የሚጣልባቸውን የቅጣት ውሳኔ ለማስተላለፍ ለታህሳስ 24 ቀነ ቀጠሮ መስጠቱን የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡