ቀን፤ ህዳር 28፣ 2008 ዲሴምበር 7፣ 2016
በሀገራችን ውስጥ የሚታየውን የግፍ አገዛዝ አስወግዶ በኢትዮጵያ አንድነት ስር የስርአት ለውጥ ለማምጣት የሚችል ሰፋ ያለ የተቃዋሚዎች ትብብር መፍጠር ጊዜ የማይሰጥ አንገብጋቢ አገር አድን ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበን፤ ለተግባራዊነቱ በጋራ ስንቀሳቀስ ቆይተናል። ሂደቱንም በሚመለከት ግልጽነትና ተጠያቂነትን ለማሳየት በተለያዩ የዜና አውታሮቻና መገናኛዎች ለቀረቡልን ቃለ መጠይቆች ማብራሪያ በመስጠት ላይ እንገኛለን።

ከዚህ በተጨማሪም ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር የሁለትዮሽ ውይይቶች በማድረግና የግብዣ ደብዳቤዎችን በመላክ ሂደቱን በጋራ በማካሄድ ጉባኤውን እንድናዘጋጅ ወይም በጉባኤው እንዲሳተፉ ጥረት ስናደርግ ቆይተናል፤ የተወሰኑትም እንደሚሳተፉ በፅሁፍ አረጋግጠዋል። በዚህ አጋጣሚ ያደረግንውን አገራዊ ጥሪ ወቅታዊነት በመገንዘብ፤ ለመሳተፍ ፍቃደኛ መሆናቸውን በደብዳቤ ምላሽ ለላኩልን ድርጅቶች በሙሉ ምስጋናችንን ማቅረብ እንወዳለን።

ከጃንዋሪ 14 እስከ 15፤ 2017 የሚካሄደውን ጉባኤ ሂደት የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ለህዝቡ በቀጥታ ስርጭት እንዲተላለፍ ይደረጋል። የጉባኤው ፕሮግራም ዝርዝርና ተያያዥ ጉዳዮችን በተከታታይ እንገልጻለን። ይህንን ጉዳይ በሚመለከት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የሚፈልግ ማንኛውም ድርጅት ከታች ከተገለፁት አድራሻዎች በአንዱ ሊያገኙን ይችላሉ፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ያሸንፋል!

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋር ትግል ሸንጎ (SHENGO) የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት (ENTC) የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ (EYNM)

ለበለጠ መረጃ፤ ENTC contact@etntc.org EYNM ethiorevolution@gmail.com SHENGO shengo.derbiaber@gmail.com

ምንጭ    _ የሸንጎ ድረ ገጽ