November 18, 2016
achamyeleh-tamiru

(አቻምየለህ ታምሩ)

ይህ ጽሁፍ Vision Ethiopia October 22, 2016 አ.ም. ባዘጋጀው ጉባዔ ላይ በሰዓት እጥረት ምክንያት በከፊል ብቻ የቀረበው ጽሁፍ ሙሉ ዘገባ ወይንም ሀተታ ነው።

ይህ ጽሁፍ ወድቃ በምትገኘው ኢትዮጵያ የመጣንባቸው ያለፉት አርባ ሁለት የመከራ አመታት የት እንዳደረሱን በከፊል በመቃኝት ወደፊት እየታሰበ ባለው ሽግግር የመንግስት ለውጥ ብቻ ይሆን የስርዓትም ለውጥ ይመጣ ዘንድ ልንመሰረትባቸው የሚገቡ መሰረታውያን [fundamentals] እና ሊካተቱ የሚገባቸው ቁም ነገሮች ምን መሆን እንዳለባቸው እንደ አንድ የአማራ ድምጽ የሚሰማኝንና የሚታየኝን የገለጽኩበት ነው።

ጽሁፌ የሚጀምረው በግራ ፖለቲካ ልክፍት ተንጋደው የበቀሉት የአገራችን የዘር ፖለቲከኞችና የፕሮፓጋንዳ ጸሀፊዎች የደረቷቸውና እኛ እንደ እውነተኛ ታሪክ ቆጥረን ሳንመረምር የተቀበልናቸውን የተከደኑ የፖለቲካ ድርሰቶች [manufactured and distorted stories] ከፍቶ በማየት ፍንትው

ብሎ የሚታየውን ነባራዊ እውነታ በግልጽ ተንትኖ በማቅረብ ነው። ከዚያ በመቀጠል እነዚህ ድርሰቶች የወለዱት ፖለቲካ በተለየ መልኩ በአማራ ላይ ያስከተለውን ግፍና በደል ተተኪው ትውልድ ይፋረድበት ዘንድ የኢትዮጵያ አለት፣ ተራራ፣ አፈርና ቅጠል በታሪክ መዝገብነት ከትቦ ካስቀመጠው የዶሴ ክምር በማንካ በመጨለፍ ባለፉት ሀያ አምስት አመታት ውስጥ ብቻ በአማራ ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ፍጅት አይነትና ይዘት ለማቅረብ እሞክራለሁ። …… (Read more, pdf)