«ኢትዮጵያ አውቶ ኦፍ ኦሮሚያ» በሚለው «ፌመስ» ጥቅሱ የማውቀው ጃዋር ፥ የአማራን ተጋድሎ በተመለከተ የብዙ የዋህ አማሮችን ልብ የሚነካ ንግግር አድርጓል ። ጃዋርን ባላውቀው ኖሮ ሃሳቡን እጋራ ( ሼር) አደርገው ነበር።
እርግጥ መልዕክቱንም በደንብ ካጤነው ፥ የአማራ ትግልን እሱ ለሚያስበው የፅንፈኛ ብሄርተኝነት ፖለቲካ ማሳኪያነት እንደ ግብዓት ለመጠቀም የከጀለም ነው የመሰለኝ። ምናልባት የአማራ ንቅናቄ መንስዔው ለዘመናት በራሱ በጃዋር ሃገር ልጆች እና የኦነግ አባላት በሆኑት ና በወያኔ ትግሬዎች በአማራ ላይ የደረሰው የዘር ማጥፋት ይቁም የሚል ሲሆን ፥ ቀጥሎም በዋነኝነት ወልቃይት ጠገዴ አማራ ነው የሚል አንኳር ፅንሰ ሃሳብ የያዘ መልዕክት ነው ያስተላለፍነው ።
እንደማየው ግን ጃዋር በዚህ አጋጣሚ ግንቦት ሰባትን ለመምታት ስላስቻለው ፥ የአማራ ልጆች ( ምሳሌ እኔ ራሴ ) ከግንቦት ሰባት ጋ ላይታረቁ ተፋትተዋል ብሎም በማሰቡ ፥ የአማራ ተቆርቋሪ ሆኖ ብቅ ብሏል ። ከግንቦት ሰባት ጋር አለመስማማታችን ያንተ ወዳጅ እንዴት ያደርገናል ! እንድንስማማ እና እንድንሰማህ ከፈለግህ ባልኖርክበት ትናንት የምትኮንነው የአማራ ገበሬ መኮነን አቁም ያለበለዚያ ኦቦ ጃዋር ሆይ አንተን መስሚያችንን ጥጥ ነው! ምክንያት ••• ተኩላ ሊበላን ነበር ብለን ለ ጅብ ስለማናመለክት!!!
ድል•••. አንተ ራስህ ገዳይ እና ጨካኝ ላልከው ለሚኒሊክ ዘር ፥ ለመይሳው ዘር ፥ ለአማራ ህዝብ ይሁን!
ኄኖክ የሺጥላ
Source – SATENAW