ከተማ ዋቅጅራ
ኢትዮጵያ የሶስቱ እሳቤ ሲንጣት ሲንጣት አሁን ያለነበት ግዜ ላይ ደርሰናል አሁን ያለንበት ጊዜ ጠንክረን ከሰራንበት በአጭር ግዜ ለውጥ ሊመጣ የሚችልበት ነው። ኢትዮጵያየም ለሁላችን የሚበቃ የተትረፈረፈ ሃብትና የመሬት ስፋት ያላት ናት ለውጥስ እንዴት ይምጣ ምን አይነት ለውጥ ይምጣ ኢትዮጵያንስ እንዴት በስራ እንለውጣት የሚለው የሁሉም ጥያቄ እንደሆነ እሙን ነው። ለዚህ መልሱ ከላይ በእርዕሱ ያነሳሁት ለጥቆማ ያህል በአጭሩ እገልጸዋለው አንባቢው ማሳደግና አስፍቶ መመልከት ይችላል።
አንድ የቱርክ ጋዜጠኛ ኢትዮጵያን ሊጎበኝ ይመጣል ወደ ኢትዮጳያ ሲመጣ ያለው አመለካከት የተዛባ ስለነበር የኢትዮጵያን በርሃነት እና የተጓሳቆሉ ሰዎችን ቀርጾ ዜና ለመስራት ነበር። ኢትዮጵያ መጥቶ በሁሉም አቅጣጫ ከጎበኛት በኋላ ጋዜጠኛው የጠየቀው ጥያቄ ለምን ትራባላቹሁ? ነበር ብዙ ለም መሬት ብዙ ዝም ብለው የሚፈሱ ወንዞች እያላቹሁ እንዴት ልትራቡ ቻላቹሁ? እንኳን ለራሳቹህ ለአፍሪካ በሙሉ ለመመገብ የሚችል የተፈጥሮ ሃብት ነው ያላቹሁ። እኔ እንደተረዳሁት አለ የቱርኩ ጋዜጠኛ እኔ እንደተረዳሁት የመስራት ልምድ የላቹሁም ወይም ስነፍ ናቹሁ ማለት ነውን? ብሎ ተናግሯል።
እውነት የቱርኩ ጋዜጠኛ እንደተናገረው የኢትዮጵያ ህዝብ የመስራት ልምድ የለንምን? ወይንስ ሰነፍ ነንን? መልሱ አይደለም ነው። የኢትዮጵያ ችግሯ የህዝብ ሳይሆን ግለሰቦች ወደ ስልጣን ከመጡ በሃላ የሚሰሩት ስህተት ኢትዮጵያን ችግር ውስጥ ከቷአታል ከላይ በርዕሴ እንደጠቀስኩት የሶስቱ ጎንዮሽ እሳቤ የሚለውን በጥቂቱ ለመንደርደር ያህል እንመልከት፦
የመጀመርያው ለአገር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ብለው የሚታገሉ ታጋዮች ወይንም ፖለቲከኞች
እነዚህ ግለሰቦች ከራሳቸው የግል ፍላጎትና ጥቅም የአገርና የሕዝብ ፍላጎትና ጥቅምን ለማስጠበቅ የሚሰሩ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ታጋይ ወይም ፖለተከኛ ናቸው።
ኢትዮጵያ በእንደዚህ አስተሳሰብ ባላቸው ቅን ሰዎች ብትመራ ሃገሪቷ ወደ እድገት ህዝቦቿ ወደ ተረጋጋ ሰላም ይለውጣል።
ኢትዮጵያ በእንደዚህ አይነት ቅን ሰዎች ብትመራ ስደት ርሃብ በኢትዮጵያ ውስጥ ተረት ሆነው ይቀራሉ ነበረ።
ኢትዮጵያ በእንደነዚህ አይነት ቅን ሰዎች ብትመራ አንዱ የበላይ ሌላው የበታች አንዱ ተጠቃሚ ሌላው ተጎጂ አንዱ በይ ሌላው ተራቢ ሆኖ የሚኖርባት አገር አትሆንም ነበረ።
ኢትዮጵያ በእንደዚህ አይነት ቅን ሰዎች ብትመራ በስልጣን ተጠቅሞ መባለግ፣ ግፍ መስራት፣ ህዝብን ማሰቃየት፣ ያለ አግባብ መበልጸግ፣ በኢትዮጵያ ምድር አይኖርም ነበር።
ኢትዮጵያ በቅን ሰዎች ብትመራ ለበዳይ ይፈረድበታል፣ ለተበዳይ ይፈረድለታል፣ ስልጣን የግል ጥቅምን ማሙያ ሳይሆን የህዝብ አስፈላጊነትን ተሸክሞ አገርና ህዝብን ወደ ተሻለ ጎዳና የሚመሩ ችሎታና እውቀቱ ባላቸው ሰዎች የምትዳኝ ህዝብ የሚሾማቸው ህዝብ የሚያወርዳቸው ለህዝብ የሚሰሩ ህዝብን የሚያገለግሉ መሪወች ይኖሩን ነበር እንደዚህ አይነቶቹ ታጋዮችና ፖለቲከኖች የኢትዮጵያ ህዝብ አጥብቆ ይናፍቃል ወደ ስልጣንም ወንበር እንዲመጣ የሚያስፈልገው እንደነዚ አይነት አመለካከት ያላቸው ቅን ልቦና እና ህዝብን አገልጋይ እንዲሆን የኢትዮጵያ ህዝብ የሁል ግዜ ሃሳቡ ነው።
ሁለተኛው የሕዝብ አጀንዳ የሚመስል ይዘው በመነሳት የግል የስልጣን ፍላጎታቸውን ለማሳካት የሚንቀሳቀሱና ህዝቡ የማይፈልገውን ሸክም በግድ ለማሸከም የሚውተረተሩ ግለሰቦች ወይንም አደገኛ ፖለቲከኞችን በጥቂቱ እናያለን
ኢትዮጵያ በእንደነዚህ አይነቶቹ ስትመራ ከህዝብ ድምጽ ይልቅ የጥቂት ግለሰቦች ሃሳብ ጎልቶ ይወጣል የህዝብ ሃሳብ ተረግጦ የጥቂቶች ሃሳብ ይሰማል የህዝብ መብት ተጥሶ የጢቂቶች መብት ይከበራል።
ኢትዮጵያ በእንደነዚህ አይነት ሰዎች ስትመራ ዳር ድንበራ በጠላት ቢደፈር ግድ አይሰጣቸውም ኢትዮጵያ ብትበታተን ለነሱ ምንም ማለት አይደለም አንዱ ዘር ከሌላው ዘር ተቦዳድኖ አንድነታችን ጠፍቶ ጦር ብንማዘዝ እና እርስ በእርስ ተጨራርሰን አገሪቷ ያውሬ መፈንጫ የጠላት መሳቅያ ብትሆንም ምንም ግድ አይሰጣቸውም።
ኢትዮጵያ በእንደነዚህ አይነት ሰዎች ብትመራ የግል ፍላጎታቸውን ለሟሟላት ድብቅ አጀንዳቸውን ለማሳካት የኢትዮጵያ ህዝብ የማይፈልገውን ሸክም በግድ ለመጫን የማያቅማሙ አንባገነኖች ናቸው።
ኢትዮጵያ በኢንደነዚህ አይነት ሰዎች ብትመራ ያልተሰራ ታሪክ እየፈጠሩ እንደተሰራ ያልተደረገ ታሪክ እየፈበረኩ እንደተደረገ በመናገር ህዝቡ እርስ በእርሱ ለማጫረስ ወደሁላ የማይሉ አደገኞች ናቸው። የእነዚህ ግለሰቦች ሃሳብ የኢትዮጵያ ህዝብ ሲበላላ በድውይ ሃሳባቸውን አንዱ ከአንዱ በጠላትነት እንዲተያይ በማድረግ ወደፊት ሊመጣ የሚችለውን አደጋ በመናፈቅ በህዝብ ጫንቃ ላይ ሆነው የራሳቸውን የስልጣን ወንበር የሚያመቻቹ የግል ሃሳባቸው እና ድብቃዊ አጀንዳቸውን ለማስፈጸም የሚታትሩ… ስልጣን ከመያዝ ውጪ አገራዊ ወይንም ህዝባዊ አጀንዳ የሌላቸው ህዝብን አጫርሰው ስልጣናቸውን የሚናፍቁ ናቸው።
እነዚህ ግለሰቦች እና የወያኔ ሰዎች እየሄዱበት ያለውን አደገኛ አካሄድ በተለየ መልኩ ማስኬድ የሚፈልጉ ለኢትዮጵያ ህዝብ ምንም የሚጠቅም ሃሳብ የሌላቸው ናቸው።
ወያኔ እና ህዝብን ከህዝብ አካባቢን ከአካባቢ ለይተው የሚመለከቱ ግለሰቦች የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ናቸው።
ሶስተኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ በአገሩ በሰላም የመኖር መብት እንዲከበርለት በአገሩ ያለምንም ተጽእኖ በሙያው እና በተሰማራበት የስራ ዘርፍ ሰርቶ የመኖር መብቱ እንዲከበርለት ያለ በደሉ የሚከሰስ ያለ ጥፋቱ የሚታሰር ዜጋ እንዳይኖር ይፈልጋል። ህዝቡ ጥያቄው ጠይቆ ጠይቆ መልስ ስላጣ እንደውም እንደዜጋ የመኖር አደጋም ስለተጋረጠበት ከዳር እስከ ዳር ወደ ትግሉ ሜዳ መግባት ጀመሩ። በሰሜን የአማራው ገበሬ እና ወጣቱ ወያኔን እየተፋለመ ያለው ግፍና በደል መሸከም አቅቷቸው ነው ትግሉ የህዝብ ትግል የሆነ በአገሩ በሰላም መስራት እና መኖር ስላቃታቸው ነው። የአማራው ትግል መብቱን እና ማንነቱን ስለተነጠቀ የተነጠቀውን ሰላም እና ነጻነት ለማስመለስ ነው ሁሉም ህዝብ ወደ ትግል ሜዳ የወረደው። በኦሮሚያም ወጣቱ እና ገበሬው ወያኔን በቃኝ ብሎ መታገል የጀመረው በቄዬህ መኖር አትችሉም ስለተባሉ ነው ጥያቀው እና ትግሉ የህዝብ ስለሆነ የመብት እና የነጻነት ጉዳይ ስለሆነ ትግሉ መራር ቢሆንም መረረ ብሎ የሚተው የህዝብ ክፍል የለም ይሉቁንም ከእለት ወደ እለት ምሬቱ እና ብሶቱ ፈንቅሎት ሁሉም በሚያስብል መልኩ በደልና ጭቆና በቃን ብሎ በመታገል የነጻነት ጥያቄው የጥቂቶች ሳይሆን የመላው ህዝብ ትግል ከሆነ ከአመት በላይ አስቆጥሯል።እዚህ ጋር ሊሰመርበት የሚገባው አማራው እና ኦሮሞው እና ሌሎችም ማህበረሰቦች የወያኔ የግፍ አገዛዝ በቃን ብለው ሲነሱ አንድ አንዶቹ እንደሚሉት እነሱ በሰሩት ስራ ሳይሆን የትግሉ ባለቤት እና የነጻነት ትግል እንቅስቃሴ አቀጣጣዮቹ እራሱ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው። ህዝባችን ለውጥ ይፈልጋል ነጻነትና ሰላም የሰፈነበት ለውጥ።
ሳጠቃልለው በእውነተኛነት ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚታገሉትን እና መሰዋእት እየከፈሉ ያሉት እና የከፈሉትን የኢትዮጵያ ህዝብ ውለታቸውን አይረሳም በታሪክ ማህደር ውስጥ ከትቦ እንደሚያኖራቸው ይታወቃል። በተቃራኒው ደግሞ ህዝብን ከህዝብ ሃይማኖትን ከሃይማኖት እየለያዩ በህዝብ እና በሃይማኖት ሽፋን ተንጠልጥለው ለስልጣን እና ለግል ጥቅማቸው የሚንቀሳቀሱትን ግለሰቦች የኢትዮጵያ ህዝብ እና የኢትዮጵያ አምላክ ይፋረዳቸዋል። በታሪክም ተወቃሽ ናቸው።
የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገው ሁሉንም በእኩል አይን አይተው እና አክብረው የሚያስተዳድረውን መሪ እንጂ አንዱን ዘር ከሌላው አንዱን ሃይማኖት ከሌላው በመለያየት ለስልጣን ጥማታቸው ማስፈጸሚያ የሚሯሯጡትን ግለሰቦች አይፈልግም። በርግጥ እነዚህ ግለሰቦች ግዜአዊ ፈተና እንጂ ዘላቂ ጠላቶች አይደሉምና ሳይረፍድባቸው ወደ ኢትዮጵያ ቤታቸው ይገቡ ዘንድ ሃሳቤን አጋራለው። አበቃው።
ከተማ ዋቅጅራ
E-mail waqjirak@yahoo.com
08.12.2016
One Response