የአጥንት መሳሳትን ለመከላከል
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)
1) የአልኮል መጠጥ አለመውሰድ ምክንያቱ የሰውነታችንን ካልሲየም መጠን ስለሚቀንስ
2) ሲጋራን ማጤስ ማቆም ምክንያቱ በደም ውስጥ የሚገኝን ካልሲየም መጠን እንዲሁ ስለሚቀንስ
3) ወተት እና የወተት ተዋጽኦ የሆኑ ምግቦችን ማዘውተር
4) በካልሲየም የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ ለምሳሌ፣ ቆስጣ እና አሣ የመሣሠሉትን
5) የጠዋት ፀሐይን መሞቅ ይህም ቫይታሚን ዲ እንዲመነጭና ካልሲየም በሰውነታችን እንዲወስድ ይረዳል
6) የሚወስዱትን የካፊን መጠን ይቀንሱ ምክንያቱም ካፊን ካልሲየም ከሰውነታችን እንዲወጣ ስለሚያደርግ ነው
7) ቀለል ያለ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ ይህም ሰውነትዎን ጥንካሬ እና መፍታታትን ስለሚሰጥ በቀላሉ ወድቀው ለስብራት እንዳይጋለጡ ይረዳል
8) ወደ ሐኪም በመሄድ ቅድመ ምርመራ ያድርጉ በተለይ ከ65 ዓመት ዕድሜ በላይ ያሉ ሴቶች ምርመራ ቢያደርጉ ይመከራል፡
እባክዎን ለወዳጅዎ ያካፍሉ!!
ጤና ይስጥልኝ
ይህ ቪዲዮ የአጥንት መሳሳት እንዴት እንደሚከሰት ያሳያል ይከታተሉ
http://www.honeliat.com/osteoporosis/

Three factors essential for keeping your bones healthy throughout your life are: Adequate amounts…
HONELIAT.COM