ስለ ግንቦት ሰባት ሳስብ ለምን እንደምናደድ ላስረዳ
1ኛ ግንቦት ሰባት ታግሎ ከገደለው በግንቦት ሰባት ስም የተገደለው ህልቆ መሳፍር ነው
2ኛ ግንቦት ሰባት ከቦ ከያዘው በግንቦት ሰባት ስም የተያዘው ( የታሰረው ፥ የተገረፈው ፥ የተሳደደው እና የተዋረደው ) የትየ ለሌ ነው
3ኛ ግንቦት ሰባት በግንቦት ሰባት ስም ታስረው ለተገደሉት እና ለሚገደሉት ወገኖቻችን አንድም ቀን ሃላፊነት ሲወስድ ተሰምቶ አይታወቅም ! ለምን ?
5ኛ ግንቦት ሰባት በጀርመን ለድርጅቱ ባደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ የ ኮ/ል ደመቀ ፎቶን ለጨረታ አቅርቧል ። ኮ/ል ደመቀ የግንቦት ሰባት አባል አይደለም። እንደማውቀው እንደውም ኮ/ል ደመቀ ግንቦት ሰባትን የሚጠየፍ ሰው ነው ። የታገለውም የግንቦት ሰባትን ህልም ለማስፈጠም ሳይሆን የወልቃይትን ህዝብ የአማራነት ጥያቄ ለማስከበር ነው ። ግንቦት ሰባት ግን ይህንን ያለውን ወራዳ ነገር ሲያደርግ በ ኮ/ል ደመቀ ላይ የጠለቀውን ገመድ አጥብቆታል። ስለ ኮ/ል ግን ሃላፊነት ወስደን እንታገላለን ሲል አልተሰማም!!! ይልቁንስ መሪው አርበኛ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በቅርቡ ባደረገው ንግግር « የወልቃይት ህዝብ ጥያቄ ወያኔ ሲወድቅ ምላሽ ያገኛል » ነበር ያሉት ! ድብን ያለ ማድበስበስ ! ወያኔ ሲወድቅ ምላሽ እንደሚያገኝ ማን ጠፋው ? ጥያቄው የወልቃይትን ህዝብ የማንነት ጥያቄ ትደግፋለህ ወይ ነው እኮ ? እንደ ድርጅት መሪ ምን ይሰማኻል ነበር ያልነው ! አይመልስልህም ! ብርሃኑ ነዋ!
6ኛ የግንቦት ሰባት መሪዎች የአማራ እርበኞችን በገንዘብ እንረዳችዃለን በማለት ፥ በተደጋጋሚ ግንኙነት ከፈጠሩ ወዲህ ጥቂት ብሮችን እያሳዩ ፥ ተጨማሪ ብር እንድንልክላችሁ ከኛ ስር ግቡ እያሉ እንደሚያስገድዷቸው እና ተስፋ እንዲቆርጡ እያደረጓቸው እንደሆነም ስለማውቅ ! ይህንንም የምናውቅ እኛ ፥ የአማራን ህዝብ ለመርዳት የምናደርገውን እንቅስቃሴ የተለያየ እንቅፋት በመፍጠር ፥ እንዳንደርስላቸው ፥ ስም በማጥፋት ፥ አጓጉል መረጃዎችን በመልቀቅ ፥ በመፈረጅ እና መሰል ሴራዎችን በመጎንጎን ተጠምደው ፥ ይህንን ተንኮላቸውን ስናጋልጥ የጎንዮሽ ትግል አታድርጉ እያሉ ዛሬም የአማራን ገበሬ እያሳረዱ እንደሆነ ስለማውቅ ! አዎ በደንብ ስለማውቅ !
7ኛ የአባን ታሪክ ፥ ከግንቦት ሰባት ቃል የተገባላቸው 1ሚሊዮን ብር እና የተሰጣቸው 30ሺ ብር፥ አባን ለማሽመድመድ የተደረገው ሴራ እና ወዘተም ገና እፅፋለሁ !
ግንቦት ሰባት ለወያኔ የአማራ ዱላ ነው ! ዱላነቱን አምኖ ተቀብሎ ቁጭ ስላለ በግንቦት ሰባት ስም ለሚሞቱት አማራሮች ሃላፊነት ወስዶ የበቀል እርምጃ እንደሚፈጥም ሲናገርም ሆነ ሲፈጥም አላየንም ! ግንቦት ሰባት ለአማራው ህዝብ መሳደጃ ፤ ከስራ እና ከህይወት መወገጃ ምክንያት ነው የሆነን ! በራሳችን ለራሳችን እንቁም ! ወያኔ በተባበረ የአማራ ክንድ ይወድቃል ! ያለ ማንም እርዳታ እና ውለታ!
አማራ ንቃ ! አማራ ተነስ !
ኄኖክ የሺጥላ