የጉበት ስብ (Fatty liver)
በ ዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር

የጉበት ስብ የምንለው በጉበት ውስጥ የሚገኘው የስብ መጠን ከ 5-10 በመቶ የሚሆነውን የጉበት ክፍል ከያዘ ነው።
ጉበታችን ከሰውነታችን ክፍል ውስጥ ሁለተኛ ትልቁ አካል ሲሆን የምንመገበውንም ፣የምንጠጣውን አና መንኛውንም ለሰውነ ጠቃሚ ያልሆነ ነገረን ከደማችን ያጣራል። የጉበት ይህን የማከናወን ስራ በጉበት ስብ መብዛት ሊዛባ ይችላል።
የጉበት ስብ ይህ ነው የሚባል የራሱ የሆነ ምልክት ላያሳይ ይችላል።

የጉበት ስብን የሚያስከትሉ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?

*በአብዛኛው የጉበት ስብ የሚከሰተው አብዝተው የአልኮል መጠጥ በሚያዘውትሩ ሰዎች ላይ ነው እስካሁንም ድረ የአልኮል መጠጥ በማይወስዱ ሰዎች ላይ የሚከሰት የጉበት ስብ ምክንያቱ በውል ግልጽ አይደለም ነገር
*ከልክ ያለፍር ውፍረት
*ከፍተኛ የስብ መጠን በደም ውስጥ መኖር
*የስኳር ህመም
*ፈጣን የሆነ የክብደት መቀነስ
*የመድሃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳቶች( አስፕሪን፣ቴትራሳይክሊን)

አራት አይነት የጉበት ስብ አይነቶች ይገኛሉ

**በአልኮል መጠጥ ምክንያት የሚመጣ
ይህ የጉበት ስብ ከአልኮል መጠጥ ጋር ተያይዞ የሚመጣ በሽታ የመጀመሪያ ምልክት ተደረጎ የወሰዳል።
ከፍተኛ የአልኮል መጠጥ መጠቀም ጉበት ላይ ጉዳትን ያስከትላል ይህም ጉበት ስብን እንዲከማች ያደርገዋል የአልኮል መጠጥን በማቶም የጉበት ስብ እንዲወገድ ማድረግ ይቻላል።

** ያለ አልኮል መጠጥ የሚከሰት የጉበት ስብ
ይህ ፲% በሚሆኑ ሰዎች ላይ የሚታይ ሲሆን ጉበታችን በጤናማ ሁኔታ ስብን ማቅልውጥ ሲያቅተው በሚከማች ስብ ምክንያት ነው።

** ያለአልኮል መጠጥ የሚከሰት ስቴአቶሄፕታይተስ
የስብ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመር ምክንያት ጉበት እንዲያብጥ የሚያደርግ ነው። ይህ ህመም የጉበትን ስራ በእጅጉ ሊያውክ ይችላል። ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ ምልክቶች
– የምግብ ፍላጎት ማጣት
– ማቅለሽለሽ
– ማስመለስ
– የሆድ ህመም ስሜት
– የሰውነት ቢጫ መሆን ናቸው።

** በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የጉበት ስብ
ይህ ህይወትን አደጋ ላይ የሚጥል አይነት የጉበት ስብ ሲሆን ምልክቱ በሶስተኛው የእርግዝና ክፍለ ጊዜ መለትም ከ6-9ውራት መለው የሚከሰቱ
የሚያቋርጥ ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ
በቀኝ የሆድ ክፍል አከባቢ የህመም ስሜት
የሰውነት ቢጫ መሆን
የድካም ስሜት ናቸው ።

ለጉበት ስብ ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?
–ከልክ ያለፈ ውፍረት
–የስኳር ህመም
–የአልኮል መጠጥ አብዝቶ መጠጣት
–እርግዝና
–ከፍተኛ የኮሌስቴሮል መጠን
–ከፍተኛ የትራይግላይሴራይድ መጠን ናቸው።

የጉበት ስብ እንዴት ይታከማል?
ይህ ነው የሚባል የህክምና መድሀኒትም ሆነ ቀዶ ጥገና የሌለው የጉበት ስብ የአኗኗር ዘይቤን ማስተካከል እንደሚኖርብዎ በሀኪምዎ ይነገሮታል። እነዚህም
–የአልኮል መጠጥ አለማዘውተር
–የኮሌስቴሮል መጠንን መቆጣጠር
–ክብደትዎን መቀነስ
–የስኳር መጠንዎን መቆጣጠር ናቸው።

ጤና ይስጥልኝ
http://www.honeliat.com/fatty-liver-disease/