እንኳን ለግሪጎርያኑ የልደትና

የአዲስ ዓመት በዐላት ከቤተሰቦቻችሁና ከምትወዷቸው፣ ከምትሳሱላቸውም ጋር በጤናና በሠላምአደረሳችሁ!!

ዛሬ ሀገራችን ዉስጥ ሠላም አለ ማለት ራስን ማታለል ስለሚሆን፣ አብዛኛዎቹ የምንወዳቸውና የምንሳሳላቸው ወገኖቻችን ደግሞ ያሉት እዚያው ሀገራችን ዉስጥ በመሆኑ፣ በሠላም ደረስን ለማለት አያስደፍርም። ከምኞት በዘለለ።

እየተሰናበትነው ያለው ዐመት ግን ሀገራችን ዉስጥ ከፍተኛ የሕዝብ መነሳሳትና ትግል የተካሄደበት በመሆኑ በሁላችንም ዉስጥ ለለጣቂው ዐመት ተስፋን ሠንቀን እንድንታገል የሚያደርግ መንፈስን አስርጾብን ነው እየተሰናበተን ያለው።

ህወሓት/ኢሕአዴግ እየፈጸማቸው ያሉት በደሎችና ግፎች ሁላችንንም የሀገሪቱ ዜጎች ክፉኛ የሚያዋርዱ፣ የሚዘገንኑም በመሆናቸው፣ ከንግዴህ ልንሸከማቸው በጭራሽ አይገባም።

ሕዝቡ የጀመረውን ትግል በማገዝና በማበረታታት ከዳር ለማድረስ ሁላችንም የሚቻለንን ሁሉ ልናደርግ ይገበናል እላለሁ።

እንደ ንጉሱ አጎንብሱ ነውና ያለንባቸውን ሀገሮች መስለን በዐላቱን ከቤተሰብ ጋር፣ ተመሳስለን፣ ስናሳልፍም ቢሆን ወገናችን ያለበትን አስከፊ ሁኔታ፣ ከዐዕምችንገሸሽ ለማድረግ ባይቻለንም በሕብረተ በዓንድነት ልዑላዊነቷንና ልእልናዋ የተጠበቀ የተከበረች ኢትዮጵያ እንድትሆን እንታገል

መጪውን ዐመት የውጤታማ ትግልና የድል ዘመን ያድርግልን!

መርሻ ዮ

                                                                        http://www.ethiopanorama.com