በግድያ እና በእስር የሕዝብን ትግል ማስቆም አይቻልም::መፍትሄው ስልጣን መልቀቅ ብቻ ነው::

በማሰር የነጻነት እና የመብት ጥያቄዎችን ማሰር አሊያም ማስቆም አይቻልም::ከታሪክ እና ከአመጣጡ ሲለውም ውርስ ከሰጠው ደርግ መማር የማይችለው ደረቁ እና ድርቁ ወያኔ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚያደርሰው ግፍ እንደቀጠለ ነው:: የወያኔን ግፍ እና ችጋር ግድያ እና እስር ለረዥም ጊዜያት ስንናገረው ስንነጋገረው ከርመናል እናውቀዋለን::የለውጥ ሃይሉ ተባብሮ መስራት በጋራ መቆም ያለበት ብርቱ ወቅት ላይ መሆናችንን ሳንዘነጋ በግድያ እና በእስር የሕዝብን ትግል ማስቆም እንደማይቻል ለወያኔ በተግባር ልናረጋግጥለት ይገባል::በዲሞክራሲ እና በነጻነት ስም ተገዝቶ እና ምሎ ከበረሃ ከተማ የገባው ዘራፊው ወንበዴ ሕወሓት አሁንም በልማት ስም እየማለ እየተገዘተ የሕዝብን ደም በመምጠጥ ላይ ይገኛል::ይህ አገዛዝ እንደመንግስት ሳይሆን ሕዝብ ላይ እንደመጣ አደጋ አሊያም ወረርሽኝ በሽታ ስለሆነ ዛሬ ነገ ሳንል ተረባርበን ልናጠፋው ልናሶግደው ይገባል::

የወያኔ አገዛዝ ፊቱን ወደ ግድያ እና ወደ አፈና ወደ ማሰር እና ማሳደድ ስላዞረ ወደ መልካም እና ለዝጎች የሚያስብ አገዛዝ ፊቱን ያዞራል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ሲልም ሞኝነት ስለሆነ መፍትሄው ወያኔ ስልጣኑን አንዲለቅ ሕዝባዊ ትግሉ ተወጣጥሎ ከዳር ሊደርስ ይገባል::ዜጎችን በማሰር የነጻነት የመብት እና የፍትህ ጥያቄዎችን አስቆማለው ብሎ በሚያስበው ድፍን ጭንቅላቱ አደባባይ ለመብታቸው ከወጡ ዜጎች ጀምሮ እስከ ፖለቲካ መሪዎች ድረስ ቢያስር የሕዝብን የነጻነት ጥያቄ ይሁን የወያኔ ይወገድልን ትግልን ለማስቆም በፍጹም አይቻልም::ይህ ትውልድ ወያኔን ለማስወገድ ቆርጦ ተነስቷል::ይህን ፍም የሆነ የትውልድ ትግል አጠፋለሁ ብሎ መነሳት ራስን ማጥፋት ነው::ወያኔዎች ለጊዜው በመሳሪያ ሃይል አሸንፈናል በማጭበርበር ዝም እናሰኛለን ብለው አስበው ከሆነ በፍጹም እንዳይሞክሩት እንነግራቸዋለን::የፈጸሙት ግድያ እና ወንጀል ነገ ከተጠያቂነት እደማያስመልጣቸው ይወቁት::የአምባገነኖች የመጨረሻ እጣ ፈንታ ሞት ነው::የገዳዮች የመጨረሻ እጣ ፈንታ እስር ቤት እና ራሳቸው የገነቡት ማጎሪይ ቤት ነው::ስለዚህ ለነጻነታችን እና ለመብታችን የምናደርገውን ትግል አናቆምም::የለውጥ ሃይሎ አካላት ቢታሰሩ ትግሎ አልታሰረም::ትግሉ ይቀጥላል!!!

#ምንሊክሳልሳዊ