በከፍያለው Aባተ (ዶ/ር

ዝም ከምል የሚሰማኝን ላንባቢ ላካፍል ብየ Eንጂ፣ ያቀራረብና የሀሳብ Aገላለጽ ልዩነት ካልሆነ በስተቀር፣ ይህ ጽሑፍ (Eስካሁን ድረስ) ያልተነሳ Aዲስ ሀሳብም መልEክትም የለውም። Eሚያስተላልፈው ያንኑ የተለመደ የAማራን ታሪካዊ ‘በሽታ’ ነው። የሀገርና የወገን ፍቅር፣ የAንድነት ‘በሽታ’

ይህ የወገንና የሀገር ፍቅር ‘በሽታ’ በAማራው ይጠና ይሆናል ለማለት Eንጂ፣ በዚህ ‘በሽታ’ የተለከፈ ስንት (በጐሳም በግለሰብም ደረጃ Aማራ ያልሆነ) Iትዮጵያዊ Aለ። ይህ የሀገርና የወገን፣ የAንድነት ‘በሽታ’ ለረዥም ዘመናት Aማራውን ሕዝብ ለጥቃትና ለበደል ሲያጋልጠው ኑሯል። ይህ ከዘመን ዘመን፣ ከጊዜ ጊዜ Eየከረረ የመጣ፣ በAማራ ላይ ያነጣጠረ በደል፣ የAማራውን ነባር ፀባይ Eንዳያስለውጠው፣ Eጁን Eንዲሰጥ Eንዳያደርገው Eሰጋለሁ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ “Aማራውም Eንደ ሌሎቹ በጐሳ መደራጀት Aለበት” የሚለውን Aስተሳሰብ የሚያፋፍም (ቆስቋሽ) ኃይል Eየጨመረ መጥቷል። በደል Aያመጣው መዘዝ የለምና የበደል ብዛት (ብሎ ብሎ) Aማራውንም ሊያጠበው ነው። ነባር ታሪካዊ ፀባዩን ሊያስቀይረው በመዳዳት ላይ ነው

የAማራው ነባር ታሪካዊ ፀባይ (ከነፍሱ Aብልጦ) Iትዮጵያን መውደድ፣ በIትዮጵያዊነት መመካትና መኩራት፣ Iትዮጵያዊያንን በሀገር ልጅነት መውደድ፣ ከIትዮጵያዊያን ጋር መጋባትና መዋለድ፣ በየትኛውም የIትዮጵያ ምድር ሠርቶ፣ ሀብትና ንብረት Aፍርቶ ከሌላው Iትዮጵያዊ ጋር ተመሳስሎ (Aብሮ) መኖር ነው። የAማራው ነባር ፀባይ ክፉና በጎውን፣ ደስታና መከራውን ከሌሎች Iትዮጵያዊያን ጋር መካፈል፣ ከሌሎች Iትዮጵያዊያን ወገኖቹ ጋር Iትዮጵያን በግምባር ቀደምነት ከጠላት መመከትና መከላከል ነው።

የAማራ ዋናው መለያው ለIትዮጵያ ያለው ልዩ ፍቅርና ልዩ ተቆርቋሪነት ነው። Aማራው Iትዮጵያን ከራሱ ሕይወት Aብልጦ Iትዮጵያን የመውደድ Aባዜ የተጠናወተው በመሆኑ፣ “Aማራ ከሁሉ ተለይቶ Iትዮጵያ፣ Iትዮጵያ የሚለው ለምን ነው? የዚች ሀገር ልዩ ተጠቃሚ ስለሆነ Aይደለም Eንዴ?” ይላሉ (በምEራባዊያን Aገር Aሳሾች፣ በሚሲዮናዊያንና በሀገራችን ቀንደኛ ጠላቶች Eኩይ ሰበካ የተለከፉ) Aንዳንድ ሰዎች። Aማራው የIትዮጵያ ልዩ ተጠቃሚ Aለመሆኑን ለመረዳት ግን ወደ ሰሜን ሸዋ፣ ወደ ጐጃም፣ ወደ ጐንደርና ወደ ወሎ ብቅ ብሎ የሕዝቡን Aኗኗር፣ መመልከትና ከሌሎች Aካባቢዎች ጋር ማመዛዘን ይበቃል።

የAማራው የሀገር ፍቅር በIኮኖሚና በቁሳዊ ጥቅም (ማጣት ወይም ማግኘት) Aይመዘንም። የAማራው የትዮጵያዊነት ፍቅር ከቁሳዊ ጥቅም የላቀ ነው። የኑሮ ጉስቁልና፣ የልማትና ማህበራዊ Aገልግሎት Eጦት፣ ሌላ ሌላውም (በEውቀትም ሆነ ያለEውቀት ሲደርስበት የኖረው) በደል የAማራውን የሀገር ፍቅር ቅንጣት ታህል
Aይቀንሰውም። ብዙዎቻችን ምንም የሌላትን (ቁርስም፣ ምሳም የማትሰጥ) ድሀ Eናታችን Eንደምንወድ፣ ሕይወታችንንም ልንሰዋላት ዝግጁ Eንደምንሆን ሁሉ፣ Aማራው Iትዮጵያንና Iትዮጵያዊነቱን ያን ያህል ይወዳል። ይህንን ጥልቅ የሀገር ፍቅርም በተለያዩ የታሪክ Aጋጣሚዎች በተፈጠሩ ጦር ሜዳዎች ተሰልፎ በግምባር ቀደምትነት ሕይወቱን ለመስዋEትነት በማቅረብ Aሳይቷል/Aስመስክሯል። Aማራው “Iትዮጵያ በጠላት ተወረረች” ሲሉት ቁሳዊ ጥቅሙ ሳይሆን ሰብAዊ ክብሩ የተነካ/የተዋረደ ይመስለዋል። በዚህም የተነሳ “ያገርህ ዳር ድንበር ተደፈረ” ሲሉት ተዘጋጅቶ Eንደሚጠባበቅ የሰለጠነ ጦር ምልምል፣ ያለምንም ማመንታት፣ ማቄን ጨርቄን ሳይል ወዲያውኑ ለጦርነት ይሰለፋል።

ይህ ተፈጥሯዊ/ባህላዊ የውትድርና ወኔና ጽኑ የሀገር ፍቅር፣ Aማራውን ሕዝብ በIትዮጵያ (የውጭና የውስጥ) ጠላቶች ጥርስ ውስጥ Aስገብቶታል።

ከረዥም ጊዜ ጀምሮ Iትዮጵያን ቅኝ ግዛት ለማድረግ፣ የተከፋፈለችና ደካማ የሆነች ሀገር Eንድትሆን የሚፈልጉ የIትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች፣ ከሌሎች Iትዮጵያዊያን ይልቅ ሲያነጣጥሩና ሲረባረቡ የኖሩት በAማራው ሕዝብ ላይ ነው። የሶሻሊዝምን ሥርAት ምንነት በቅጡ ያልተረዱት (Eራሴን ጨምሮ) በርካታ (ጥራዝ ነጠቅ) Iትዮጵያዊያን ምሁራንና ተማሪዎችም የIትዮጵያን ታሪካዊ ጠላቶች ፈለግ ተከትለው፣ Aማራውን ሕዝብ በጅምላ ሲኮንኑት ኑረዋል። ኩነኔውና ሰቆቃው Aሁንም Eንደቀጠለ ነው።

በትምህርት ሳይበስሉ፣ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ (በጀሮ ጠገብነት) የሰሙትን Eንደ ገደል ማሚቶ Eያስተጋቡ፣ ትምህርታቸውን Aቋርጠው ጫካ የገቡት ጮርቃና ለጋ የወያኔ ፋኖዎችም ያንኑ የጠላት ፈለግ በመከተል Aማራውን ሕዝብ (ከነባህሉና ከነAመለካከቱ) በይፋ ሲያወግዙት ኑረዋል። Aሁንም በያለበት በሰበብ ባስባቡ ቁም ስቅሉን Eያወጡት፣ Eያሳደዱትና Eየገድሉት ነው። ጥቃቱ ከምንጊዜውም ይበልጥ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የAማራው ቅስም Eንዲሰበር፣ ያለልማዱ/ያለጠባዩ በማንነቱ Eንዲያፍርና Aንገቱን Eንዲደፋ ፈርጀ-ብዙ የሆነ፣ የተቀነባበረ ሰፊ ዘመቻ Eያካሄዱበት ነው።

ይህ የተቀነባበረ የረዥም ዘመን ዘመቻ ወደ ሀገራችን Aራት ማEዘናት ተሰራጭቶ፣ ዛሬ Aማራን “ Aይንህን ላፈር” የሚለው የሌላው ጐሳ ተራ ሕዝብ** ጥቂት Aይደለም። የተጋነነ Eንዳይመስልብኝ Eንጂ፣ ዛሬ በብዙ የሀገራችን Aካባቢዎች የAማራ ሕዝብ የበዝባዥነት፣ የጨቋኝነት፣ የAድላዊነት፣ የትምክህተኝነት፣ የመሠሪነትና የተንኮለኛነት ቀለም ተለቅልቆ፣ ሳያውቁት Eሚያወግዙት፣ ሲወድ የሚጠሉት፣ ሲቀርብ የሚሸሹት ጭራቅ ሁኗል። ይህ ሁሉ የሆነው ያለምክንያት
* የሌላው ጐሳ ተራ ሕዝብ ስለAማራ ያለው ግንዛቤ የተለየ ነው። በብዙ የደቡብና ምEራብ Iትዮጵያ Aካባቢዎች፣ “Aማራ” ማለት Aማርኛ የሚናገር፣ ያካባቢው ተወላጅ ያልሆነና ያካባቢውን ቋንቋ Eማይናገር፣ በንግድ፣ በውትድርና፣ በዳኝነትና በሌላም የመንግሥት ሥራ ምክንያት የመጣ፣ መጤ ማለት ነው። ይህ ሁሉ መጤ ከየትኛውም ጐሳ ተነስቶ የመጣ ሊሆን ይችላል። በተራው ሕዝብ ላይ የሚፈጽመው ግፍና በደል ግን የAማራው ጐሳ Eንደፈጸመው ተቆጥሮ Aማራው ይወገዝበታል፣ ይጠላበታል።
Aይደለም። ለዘመናት በተካሄደበት የጥላቻ ዘመቻ ነው። ይሁን Eንጂ ያ ሁሉ በደል Aማራውን Aላጠበበውም።

Eንዲያውም (በEልህም ይሁን በልማድ) ለIትዮጵያና ለIትዮጵያዊያን ያለውን ፍቅር Eጥፍ ድርብ ያደረገው ይመስለኛል። ለዚህም በቅርብ ጊዜ ጎንደር ላይ ከተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ የተሻለ ማስረጃ የለም።

በቅርብ ጊዜ ጐንደር ላይ በወልቃይትና ጠገዴ የማንነት ጥያቄ የተነሳ በተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ፣ የመከራና የበደል ገፈታ ቀማሹ Aማራ ሕዝብ ከያዛቸው መፈክሮች መካከል Aንዳንዶቹ፣

 Aትለያዩን፣ ቅማንትና Aማራ Aንድ ነው   የOሮሞ ወንድሞቻችን ደም ደማችን ነው  በቀለ ገርባ ይፈታ

የሚሉ ነበሩ። በነዚህና በሌሎችም (በማላስታውሳቸው) መፈክሮች Aማካይነት Aማራው በደሉንና ብሶቱን ከሌሎች Iትዮጵያዊያን በደልና ብሶት ጋር በማጣመር Iትዮጵያዊ ጩኸቱን Aሰማ። በመፈክሮቹ Aማካይነት ለሌሎች Iትዮጵያዊያን ወገኖቹ ያለውን ፍቅርና ተቆርቋሪነት ገለጸ። “Aትከፋፍሉን፣ Aትለያዩን” የሚሉት መፈክሮች ብቻ የAማራውን የAንድነት ፍላጐትና ጥልቅ የሀገር ፍቅር ቁልጭ Aርገው የሚያሳዩ ናቸው። ታዲያ ይህ ሥር የሰደደ የIትዮጵያዊነት ፍቅር/ስሜት ይመስለኛል ከሌሎች ጐሳዎች በላቀ ሁኔታ Aማራውን ሕዝብ የረዥም ጊዜ የጥቃት ሰለባ Aድርጐት የሚኖረው።

በሀገር ውስጥ የሚገኘው፣ መከራ ገፊው Aማራ፣ ከራሱ መብት ጋር በማጣመር ለመላ Iትዮጵያዊያን ሰብAዊ መብት መከበር በሚጮህበትና በሚዋደቅበት ባሁኑ ወቅት፣ የባሕር ማዶ ‘ልሂቃኑ’ ግን Eንደ ሌሎቹ የጐሳ ቡድኖች ሁሉ፣ “Aማራም በAማራነቱ ተደራጅቶ ራሱን ከጥፋት ማዳን Aለበት” Eያሉ ይወተውታሉ። በሌላ Aነጋገር Aማራው “Iትዮጵያ፣ Iትዮጵያ” Eያለ ማነኛውንም Iትዮጵያዊ የሚያሳትፍ ድርጅት ለማቋቋም ከሚመኝ ይልቅ፣ የወያኔን ፈለግ ተከትሎ፣ በጠባቡ በጐሳ መደራጀት Aለበት ማለት ነው። ውትወታው በጠባቡ Eሚያስበውን በሰፊው Eንዲያስብ በማትጋት ፈንታ፣ በሰፊው Eሚያስበውን በጠባቡ Eንዲያስብ የሚያደርግ ነው።

ይህ ውትወታ የወያኔን መንግሥት በመጣል ላይ ብቻ ያነጣጠረ የትግል ስልት ነው። የወያኔን መንግሥት ከመጣል ያለፈ ራEይ ግን የለውም። “የAማራ ቡድን Eንዲፈጠር Eናድርግና የጐሳዎች ቡድኖች ባንድ ላይ ተሰልፈን ወያኔን ከስልጣን Eናስወግድ፣ ከዚያ በኋላ Eንደፍጥርጥራችን” Eንደማለት ይመስላል። ይህም ማለት Eናፍርስና (Eንደ ልማዳችን) በፍርስራሹ ላይ ጉልበት ያለው፣ በለስ የቀናው፣ የወርተረኛ የጐሳ ቡድን ሥልጣን ጨብጦ፣ ያንኑ Aሳረኛ Iትዮጵያዊ Eንደ ወያኔ ሲያተራምስ ይቆይና፣ Eድሜው ሲደርስ ለሌላ ወር-ተረኛ ይልቀቅ ማለት ነው።

በጐሳ ቡድኖች ጣምራ የሚደረግ ትግል ከዚህ የተሻለ ውጤት ሊኖረው Aይችልም። የሻቢያ፣ የOሮሞ ነፃ Aውጭ ቡድንና የወያኔ ቡድን ጣምራ ትግል፣ የደርግን መንግሥት ገልብጦ ከጣለ በኋላ፣ ጉልበተኛው ወያኔ ሥልጣን ጨብጦ Iትዮጵያዊያንን Eንዳሻሮ Eያመሰ መሆኑን ነው በመታዘብ ላይ ያለነው። የጐሳ ቡድን ጥርቅም ከቡድናዊ ንትርክና ሽኩቻ የተለየ ጠቃሚና ገምቢ ነገር ሊያስገኝ Aይችልም።

ጉልበተኛው ወያኔም የIትዮጵያን ሕዝብ በጐሳ ከፋፍሎ የሚያካሂደው Aገዛዝ፣ ለጋራ Aገራቸው Aንድ ላይ ደማቸውን ያፈሰሱትንና የሚያፈስሱትን ዜጐች፣ ተጋብተውና ተዛምደው ለረዥም ጊዜ የኖሩትን Iትዮጵያዊያን፣ በቋንቋቸውና በጐሳቸው ለይቶ በመከለሉ፣ በተፈጥሮም ሆነ ባስተዳደር የተነሳ የሚደርስባቸውን ጉዳትና በደል Aብረው Eንዳይወጡ Aድርጓቸዋል። ደስታና መከራቸውን Aብረው Eንዳይካፈሉ ሁነዋል። በጋራ የዜግነት ጉዳያቸው ላይ Aብረው Eንዳይመክሩና Eንዳይዘክሩ ተለያይተዋል። ለውጭ ጠላት ጣልቃ ገብነትም የተመቻቹ ሁነዋል። የሀገሪቱ ቀጣይነትም ሆነ የሕዝቦቿ Aንድነት ቋፍ ላይ ነው።

ታዲያ በጐሳ ድርጅቶች የጋራ ትግል መንግሥትን መገልበጥ Eንደ ወያኔ ዓይነቱን Aንድ የጐሳ ቡድን ብቻ ፈላጭ ቆራጭ ያደረገ ከሆነ፣ ከየትኛው በጐ ተመክሮ ተነስተን ነው Aማራው በጐሳ Eንዲደራጅ የምንወተውተው?

Oሮሞው በጐሳ በመደራጀቱ ያገኘው ልዩ ጥቅም ምንድን ነው? Aፋሩስ? ቤኒ ሻንጉሉስ? ደቡቡስ? ሐረሬውስ? ወ.ዘ.ተ.

Aንድ ወጥ በሆነ የዜግነት Aመለካከት በመመራት ፈንታ፣ በጠባብና በጥቃቅን (በጐሳ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ ወ.ዘ.ተ) ቡድን የምንደራጅ ከሆነ፣ ሊፈጠር የሚችለውን የቡድን ብዛት ለማሰብ Eንኳን ያዳግታል። የሚፈጠረውም ቡድን Eርስ በርሱ የሚፋተግ Eንጂ ለሕዝባችንና ለሀገራችን Aወንታዊ ውጤት ኑሮት Aያውቅም፣ ወደፊትም Aይኖረውም።

ለምሳሌ ያህል በOሮሞው ሕዝብ ስም የተፈጠረው የፓለቲካ ቡድን ስንት ነው? ትክክለኛ ቁጥሩን ባላውቀውም በርካታ መሆኑን Aውቃለሁ። በሆነ Aጋጣሚ Oሮሞው ሥልጣን ቢጨብጥ የOሮሞውን ሕዝብ Eወክላለሁ የሚለው የፖለቲካ ድርጅት ሁሉ Eርስ በርሱ ለመጠላለፍ ደባ የሚሸርብ ነው የሚሆነው። በደባ ሽረባው ሂደት ውስጥ የሚሰቃየው ግን የOሮሞው ሕዝብ ነው። Oሮሞው በጆግራፊ ክልል የሚደራጅ ቢሆን፣ የAርሲ Oሮሞ ድርጅት፣ የቦረና Oሮሞ ድርጅት፣ የወለጋ Oሮሞ ድርጅት፣ የሸዋ Oሮሞ ድርጅት፣ ወ.ዘ.ተ. Eየተባለ Eያንዳንዱ ድርጅት የየክልሉን Oሮሞ Eወክላለሁ በማለት Aንዱ ከሌላው Aካባቢ የOሮሞ ድርጅት ጋር ሲነታረክ የሚኖር ነው የሚሆነው። በሃይማኖትም መቧደን ቢጀመር Eንደዚያው ተመሳሳይ ችግር Aለ። የEስካሁኑ ተመክሯችን የሚያሳየን በጠባብ በጠባቡ ከመቧደን ተጠቃሚ የሆኑት (በሕዝቡ ስም መዋጮ የሚሰበስቡት፣ በያሉበት ተንደላቀው የሚኖሩት) የቡድን መሪዎች ብቻ ናቸው። የOሮሞም ሆነ የሌሎች ጐሳዎች ሕዝቦች ግን ከነበሩበት የኑሮ ሁኔታ ስንዝር ታህል Eንኳን ፈቀቅ Aላሉም። ፍትሕ Aላገኙም፣ መሠረታዊ ዲሞክራቲክ መብታቸውን Aላስከበሩም፣ Eንዲያውም የOሮሞም ሆነ
ሌላው በጐሳ የተደራጀ ሕዝብ ከምንጊዜውም የበለጠ (ካማራው ባላነሰ ሁኔታ) ለEስራትና ለሞት ተጋልጦ ይገኛል። ስለሆነም ለAማራው ሕዝብ በጥሩ Aርኣያነት የሚወሰዱ Aይደሉም።

ታዲያ የሌሎቹ የጐሳ ድርጅቶች በጐ ተመክሮ ያስገኙ ይመስል Aማራው በጐሳ ተደራጅቶ ራሱን Eንዲከላከል የሚደረገው ግፊት ከጊዜ ወደ ጊዜ Eየጨመረ ነው። የባሕር ማዶ የAማራ ልሂቃንም ይህንኑ ጐሰኛና ጠባብ የAማራ ድርጅት ለማቋቋም ደፋ ቀና በማለት ላይ ናቸው። ይሁን Eንጂ በሰሞኑ ጉትጐታ መሠረት Aማራውም Eንደ Oሮሞው በጐሳ ልደራጅ ቢል ፋይዳቢሶች በሆኑ Aንስተኛ ቡድኖች መሸንሸኑ Aይቀርም። የመሸንሸን ፍንጭም Eየታየ ነው። የሸዋ Aማራ Aሊያንስ፣ የጐጃም Aማራ፣ የጐንደር፣ የወሎ፣ የጐጃም Aገው፣ የላስታና ሰቆጣ Aገው፣ የቅማንት፣ ወ.ዘ.ተ. Eያሉ ብዙ ቡድን መፍጠር ይቻላል።

Aማራውን ሕዝብ ከIትዮጵያ መለስ በጐሳ ማደራጀት፣ ነባሩን የAማራ Iትዮጵያዊ ፀባይ በማይረባ Aዲስ ቀለም ለቅልቆ Eንደማበላሸት ነው። ለIትዮጵያና ለIትዮጵያዊያን መበታተን AስተዋጽO ማድረግ ነው። ለAማራው ሕዝብ፣ በጐሳ መደራጀት የሽንፈት ምልክት ነው። ራሱ በጐሳ ከተደራጀ በኋላ ሌሎችን የጐሳ ድርጅቶች በጠባብነት የሚወቅስበትና የሚተችበት የሞራል ብቃት Eንዳይኖረው ማድረግ ነው።

ትግላችን የሚሰምረው ባንዲት ሀገር ዜግነት Aንድ ላይ ስንንቀሳቀስ ነው። በጐሳ ላይ በተደራጀው ጉልበተኛ የወያኔ መንግሥት ከሸፈ Eንጂ፣ የ1997ቱ የቅንጅት ትግል Aስደናቂ ውጤት ያስገኘው ከጐሰኝነት ስሜት የጸዳ ስለነበረ ነው። የ1997ቱ የቅንጅት ድል Iትዮጵያዊያን ጐሰኝነትን/ጠባብነትን Eንደማይፈልጉ ያሳየ ጉልህ ማስረጃ ነው። ሰሞኑን ወያኔን ያሸበረውና “Aስቸኳይ ጊዜ Aዋጅ” Eንዲያውጅ ያስገደደው (ጐሰኛ የተናጠል ድርጅት ትግል ሳይሆን) ከሰሜን Eስከደቡብ፣ Iትዮጵያዊያን ባንድ መንፈስ ገንፍለው በመውጣታቸው ነው። የወያኔ ወዳጆች የሆኑትን ምEራባዊያን ሀገሮች ሳይቀር ቀልብ ስቦ፣ ወያኔ በሕዝቡ ላይ የሚያካሂደው በደል Eንዲጋለጥ፣ ወያኔ ገመናው Eንዲወጣ ያደረገው የIትዮጵያዊያን Aንድነት ነው።

ስለዚህ A ማራው ሳይታክት በEድሜ ተመክሯቸው፣ በEውቀታቸው፣ ባመለካከታቸውና በራEያቸው Iትዮጵያንና Iትዮጵያዊያንን ሊያገለግሉ ከሚችሉ፣ ከጠባብ የጐሳ ስሜት ከጸዱ Iትዮጵያዊያን ጋር ተሰልፎ፣ ወያኔንም ሆነ ሌሎች ፀረ-Aንድነት ኃይሎችን መታገል Aለበት። ይህ ነው ታሪካዊውና ነባሩ የAማራ ፀባይ።

በዚህ Aቋምና Aመለካከት Aማራው ሕዝብ ብቻውን Aይደለም። የAማራውን Aመለካከት ሌላውም የIትዮጵያ ሕዝብ በሚገባ ይጋራዋል። በሥልጣን ላይ የተቀመጡ ቡድኖች በሕዝብ ላይ የሚያደርሱት በደል (ቢበላለጥም) ከሞላ ጐደል Aንድ ዓይነት ስለሆነ፣ የበደሉን መራራ ጽዋ የተጐነጩ ሁሉ ባንድነት ተሰልፎ ለመታገል ይፈልጋል። በጠባብ የጐሳ Aመለካከት ተደራጅተው Iፍትሃዊነትን፣ ግፍና ጭቆናን Eንታገላለን የሚሉ የIትዮጵያውያን፣ Aንድነት ደንታ
Eማይሰጣቸው፣ የሀገራችን ህልውና Eማያሳስባቸው፣ ግላዊ ወይም ቡድናዊ ጥቅም ለማግኘት ብቻ የሚራወጡ Aስመሳዮች ናቸው።

“Aማራው በጐሳ ላይ የተመሠረተ የፖለቲካ ፓርቲ Aቋቁሞ መብቱን ያስከብር” Eያሉ የሚወተውቱ ሁሉ የAማራ ወዳጅ Aይደሉም። Aማራው የIኮኖሚ ተጠቃሚ ባይሆንም በቋንቋው፣ በሃይማኖቱና ከነዚህ ጋር Aብረው በሚሄዱ ባህሎቹ Aማካይነት በIትዮጵያ ውስጥ የበላይ (dominant) ሁኗል” የሚሉ ተራ ቀናተኞች/ምቀኞች ዘይንተረፍ ናቸው።

Eነዚህ ተራ ቀናተኞች ሊረዱት የሚገባቸው Aንድ ነገር Aለ። የተለያዩ ባህሎች በተለያየ ምክንያት (በንግድ፣ በስደት፣ በጉርብትና፣ ባስተዳደር፣ ወ.ዘ.ተ.) ለረዥም ጊዜ ጐን ለጐን ሲኖሩ ይደበላለቁና የድሮ ፀባያቸውን ይለውጣሉ። ወይም Aንደኛው ጐልቶ ይወጣል። ሌላው ደግሞ Eየደበዘዘ ከዚያም Eየጠፋ ይሄዳል። ሕዝቦች Aብረው ሲኖሩ ይህ Eማይቀር ነገር ነውና ከወዲሁ ልናውቀውና ልንቀበለው ይገባል። የሚጠፉት Eንዳይረሱና የተናጋሪዎቹ ይትብህልም Aብሮ Eንዳይጠፋ ከወዲሁ በጽሑፍ Eየመዘገቡ ማስቀመጥና ለትውልድ ማቆየት/ማስተላለፍ ነው። ባጋጣሚ Eሚያድገውንና Eሚጐለብተውን ቋንቋ ደግሞ የጋራ ቋንቋ፣ በቋንቋው ውስጥ የታመቀውንም ባህል የጋራ ባህል Aርጐ መቀበል ያስፈልጋል። ይህን ለመቀበል ስንዘጋጅ ብቻ ነው የIትዮጵያዊያን Aንድነትና የሀገራችንም ቀጣይነት Aስተማማኝ Eየሆነ የሚሄደው።

ስለዚህ፣ Aማራው ያለባሕሉ ከጥቃት በማያድን የጐሳ ፖለቲካ ከሚደራጅ ይልቅ፣ ከማንኛውም ሀገር ወዳድ በሳል Iትዮጵያዊያን ጋር ትግሉን Aቀናጅቶ የራሱንም ሆነ የሌሎችን Iትዮጵያዊያን መብት ማስጠበቅ Aለበት። በIትዮሚዲያ ድህረ-ገጽ ላይ Aንድ ጽሐፊ Eንዳስነበቡን የቡድን ነገር ማቆሚያ የለውም፣ Eስከ ቤተሰብ ይደርሳል ብለዋል። ይኸው ጽሐፊ በመቀጠል፣ በጐሳ ፖለቲካ ከመቧደን ይልቅ ባስተሳሰብ፣ ባመለካከትና በራEይ ተመሳሳይነት ያለው Iትዮጵያዊ ሁሉ Eየተደራጀ ለሀገር የሚበጅ Eንቅስቃሴ ቢያደርግ ይመረጣል ብለዋል። በኔ በኩል ድንቅ ሀሳብ ይመስለኛል።

Eስካሁን ያላነሳሁት ያማራ ብሶት Aለ። ይህም በIትዮጵያዊነት ፍቅሩና ለሀገር Aንድነት ባለው ከፍተኛ ተቆርቋሪነት የተነሳ፣ ለውጭም ለውስጥም የሀገር Aንድነት ጠላቶች ጥቃት ዓይነተኛ ሰለባ ሁኗል። ራሱን ካላደራጀ የሚደርስበትን ጥቃት Eንዴት ይከላከላል?

Eስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በAማራው ላይ የተቀነባበረ የረዥም ጊዜ የጥቃት ዘመቻ ሲካሄድበት፣ ከAማራውም ሆነ ከሌላው Iትዮጵያዊ የመመከት ሙከራ ተደርጐ Aያውቅም። Aማራው ያላግባብ በሀሰት ሲወነጀል ለማስተባበል ተሞክሮ Aያውቅም። ስለዚህ ሀሰተኛው ክስና ውንጀላ ሁሉ በAድማጭ ጆሮ Eየተንቆረቆረ ገብቶ Eንደውነት ሰፊ ተቀባይነት Aግኝቶ ኑሯል። ባሁኑ ጊዜ ግን ሁኔታው የተለየ ነው።

Aማራው ሲጠቃና ሲበደል ጥቃትና በደሉን የሚያሰማለት ሞረሽን የመሰለ Iፖለቲካዊ ድርጅት Aለ።
ሞረሽ ከተቋቋመ Aጭር ጊዜ ቢሆንም፣ በዚህ Aጭር ጊዜ ውስጥ በAማራው ሕዝብ ላይ የደረሰውንና የሚደርሰውን ቅጥ ያጣ በደል ለብዙ Aድማጭ Aድርሷል። በብዙ ሰዎች ዘንድ በAማራ ላይ የነበረውን የተዛባ ግንዛቤ ለማስተካከል ችሏል። ዛሬ ያለ ተጨባጭ ማስረጃ (Aፉ Eንዳመጣለት) በየቦታው Aማራን መኮነንና ማብጠልጠል ቀንሷል። Aማራም ተቆርቋሪና ተሟጋች Eንዳለው Eየታወቀ ስለመጣ፣ Aማራን በተመለከተ ንግግር ሲጀመር ትንሽ ጥንቃቄ ማድረግ ተጀምሯል። ከዚያም Aልፎ በAማራ መጠቃት Eሚያዝኑና Eሚቆጩ ደጋፊዎች (sympathizers) ማየት ተጀምሯል። ይህ የሞረሽ የሥራ ውጤት ነውና ሊመሰገንና የበለጠ ተጠናክሮ Eንዲንቀሳቀስ ሊደገፍ ይገባዋል። ሌሎች የሰብAዊ መብት ድርጅቶችም ካሉ ተመሳሳይ ድጋፍ ሊሰጣቸው ይገባል።

ሞረሽና መሰል ድርጅቶች (ካሉ)፣ Aሁንና ወደፊት በAማራው ላይ የሚከሰተውን Aሉባልታ፣ AድልOና ጥቃት Eየተከታተሉ ማሰማት/ማስተጋባት ብቻ ሳይሆን፣ ሆን ተብሎ Eንዲረክስና Eንዲበላሽ የተደረገውን (Aንዳንድ) ያማራ ታሪክ በማስረጃ Eያስደገፉ ለሕዝብ ማቅረብ ያስፈልጋል። ይህ ዓይነቱ Eንቅስቃሴ ጥላሸት የተቀባው የAማራ ታሪክ Eንዲጠራ ይረዳል።

በጐሳ መደራጀት ለAብሮነት፣ ለሰላምና ለEድገት ጠንቅ ስለሆነ፣ Eሚያቀራርበንና Eሚያስተሳስረን፣ ቀስ በቀስም ልዩነታችን Eያጠፋ በሚሄድ Aደረጃጀት ተደራጅተን፣ ሁላችንም የሀገራችን የጋራ ተጠቃሚ Eንድንሆን ምኞቴ ነው።