ክርስትና የእግ/ር ፍቃድና ህግ የሚፈፀምበት መንፈሳዊ ሀይማኖት ነው፡፡ የክርስትና አስተምሮት በመፅሐፍ ቅዱስ ቀርቦ ለዓለም እየተዳረሰ ይገኛል፡፡ ከ1054 ግ.ካ በፊት ክርስትና አንድ አምልኮ ብቻ ነበር፡፡ ማለትም አንድ መፅሐፍ ቅዱስ፣ አንድ አምልኮ፣ አንድ አጥብያ ቤተክርስቲያንና አንድ የምዕመናን ህብረት ብቻ ነበር፡፡ በ1054 ግ.ካ ክርስትና ለሁለት ተከፍሏል፡፡ ክርስትና ምስራቃዊው ኦርቶዶክስና ምዕራባዊው ካቶሊክ በመባል ተከፈለ፡፡ ወደ 16ኛው ክፍለ-ዘመን ደግሞ ፕሮቴስታንት በመባል ሁለተኛው ምዕራባዊ ክርስትና ተመስርቷል፡፡ ካቶሊክ ከኦርቶዶክስ ሲነሳ ፕሮቴስታንት ደግሞ ከካቶሊክ ተነስቷል፡፡ ከፕሮቴስታንት ደግሞ በወንጌል አለማመን ወደሚል አዲስ አቋም እየተመጣ ነው፡፡ አንዱ ከአንዱ የሚነሳበት ምክንያት የሀይማኖት መሪዎች ከአስተሳሰብና ከአቀባበል ልዩነት የተነሳ ነው፡፡ ከግል አስተሳሰብ ተነስቶ ሀይማኖት የመቀየርና የራስን ተቋም ወደ ማቋቋም ደረጃ ተኪዷል፡፡ አንዱን በማደስ ወደ ሁለተኛው ሀይማኖት እየተወራረደ ክርስትና በህዳሴ ጎዳና ተበታትኗል፡፡ ስለክርስትና እንደ መረጃ፦

ተ.ቁ የክርስትና ዓይነት የስያሜ ትርጉም የተከታዮች ቁጥር የሚከተሉት ወንጌል ቁጥር ምርመራ

1 ኦርቶዶክስ ቀጥተኛ 450 ሚሊዮን 81 ከጊዜ ወደ ጊዜ የወንጌሉ ቁጥር እየወረደ ሄዷል ተሃድሶ በሚባል ልክፍት

2 ካቶሊክ ሁሉን-አቀፍ 1 ቢሊዮን 71

3 ፕሮቴስታንት የነበረውን የሚቃወም 850 ሚሊዮን 66

4 ክረስቶስ ብቻ ወልዳዊ 50 ሚሊዮን 56

ዛሬ ላይ ደግሞ ወንጌል-0 ወይም በወንጌል አለማመን ወይም አምላክ አለ ግን ሀይማኖት የለም ወደሚባል ደረጃ ተደርሷል፡፡ ነገስ ወዴት?

ተሃድሶ ሊያመጣ የሚችለው ጣጣዎች በሌሎች ጉዳዮች ሲዳሰስ፦

1. ለፆታ እኩልነት የተደረግ አብዮት፡ ሴት እህቶቻችን በቀድሞው ዘመን መብቶቻቸው በመረገጡ ከፍተኛ ትግል አድርገው አሸናፊዎች በመሆን መብታቸውን መቆናጠጥ ችለዋል፡፡ በትግል ወቅት ከከፈሉት መሰዋትነትና በወንዶች ከደረሰባቸው በደል ለወንዶች መጥፎ አመለካከት እንዲኖራቸው አድርጓቸዋል፡፡ ከዚህም አልፎ በቀለኛና እንዲሁም ወንዶች የሚባሉ ሰዎችን አንፈልግም ወደሚባል አስከፊ ሁኔታ አምርተዋል፡፡ ለምሳሌ፦ የሴት ክርስትናና መፅሐፍ ቅዱስ፣ የሴቶች መኖሪያ ፕላኔትና ዓለም፣ የሴት ት/ት ተቋማት፣ የሴት ካምፓኒዎች፣ የሴት ሆቴሎች፣ ሴት ለሴት የተመሣሣይ ፆታ ወሲባዊ ግንኙነት…ወንዶች ፈፅሞ አያስፈልጉም ከሚል አጉል አመለካከት የተነሳ ነው ይሄ እየሆነ ያለው፡፡ ይሄም ነፃነት ለማግኘት በሚደረግ ወቅት በወንዶች ላይ በተደረገ የጥላቻ መንዣ ዘመቻ ነው፡፡ በስተመጨረሻ ለተራበ ሰው አልኮል እንደመጋበዝ ሆነ፡፡ የተፈለገው ሌላ የሆነው ሌላ እንደማለት፡፡ አንዳንድ ነባር ነገሮችን ከነችግራቸው መቀበል ሊበጅ እንደሚችል ትልቅ ማሳያ ነው፡፡

2. አንግሊካን ቤ/ን፡ የእንግሊዙ አንግሊካን ቤ/ን በአለማቀፍ ደረጃ ስመ-ገናና እና ወግ-አጥባቂ ከሚባሉ ሀይማኖቶች አንዱ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ከ21ኛው ክፍለ-ዘመን ወዲህ በሀይማኖቱ መሪዎች ጫና አንዳንድ ህዳሴዎችን ለማድረግ ተገዷል፡፡ ከተሃድሶዎቹ መካከል፦ ሴት አገልጋችን ማሳተፍና የተመሣሣይ ፆታ ጋብቻን መፍቀድ ይገኝበታል፡፡ የሰው ልጅ ከፆታው ጋር ተያይዞ ባለው ተፍጥሯዊ ባህሪ የተነሳ ለአንዳንድ ኃላፊነቶች ላይመች በመቻሉ ነው ይህ የማይፈቀደው፡፡ በምዕራባዊያን ፖለቲካ ተፅዕኖ ስር የወደቀው አንግሊካን በየጊዜው በተሃድሶ እየተተረማመሰ ይገኛል፡፡ መፅሐፍ ቅዱስ የማይፈቅደውን ሁሉ በሀይማኖቱ መሪዎች በመፈቀዱ ለዘብተኛና ማህበራዊ ተቋም ሆኗል፡፡ ተከታዮቹም መንፋሳዊነቱ ስለጠፋባቸው ሀይማኖቱን ትተው ፓጋን እየሆኑ ነው፡፡ ተሃድሶ ባመጣው ጣጣ የሀይማኖቱ ህገ-ስርዓት ጭምር ተበታትኗል፡፡

ወደ አንተ ስመጣ

እኔ በግሌ በክርስትና ህይወቴ ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ከፈጠሩ ሰባኪያን መካከል ከዲያቆን ሳሙኤል ጌታቸው ቀጥሎ ክብር ይግባህና አንተ ነህ፡፡ በቤቴ ከሚገኙ የእግ/ር ቃል ከሚሰበክባቸው መንፈሳዊ ካሴቶች 90% ያንተ ናቸው፡፡ እግ/ር ለአገልግሎት መርጦህ ፀጋውን ስለሰጠህ እድለኛ ነህ፡፡ እንዲህ ሁሉ ነገርህን ሰጥተህ የተሃድሶ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው ሲሉ ሰምቼ ደነገጥኩኝ!!! እውነት ነው እንዴ? ወይስ በምናውቀው ነቀርሳ ጥላቻ ሸሽተህ ነው? እስቲ ልስማው ንገረኝ የሚባለው ውሸት መሆኑን? ኦርቶዳክስ ተዋህዶን ወደ ህዳሴ ካመጣነው ከጊዜ ወደ ጊዜ የሀይማኖቱ መንፈሳዊነት እየተመናመነ በስተመጨረሻ ማህበራዊና አለማዊ ተቋም ይሆናል፡፡ ይህን ስል ምዕመናኑን በእምነት ለማጠናከር የሚደረጉ መፅሐፍ ቅዱስና የቤ/ን ስርዓት የሚፈቅዳቸው እንቅስቃሴዎችን ለማለት ፈልጌ አይደለም፡፡ አዋቂ ነኝ ብዬ አይደለም፡፡ ደግሞም አይደለሁም፡፡ ነገር ግን ወንድማማቾች ነን ሀሳብ እንለዋወጥ ብዬ ነው፡፡ ስሜትህን ከነካው በጣም ይቅርታ፡፡ የሌቤን አምላክ ነው የሚያውቀው፡፡ እግ/ር ካንተ ጋር ይሁን፡፡

One Response