የመሳይ ከበደና የሬኔ ለፎርት ወግ – ታሪኩ ውብነህ ጌታሁን

December 9, 2016 20:11

ክፍል አንድ

[ማሳስቢያ፡ ይህ በክፍል አንድ የቀረበው ጽሑፍ ለማሰተማር ሳይሆን ለመማማር ታስቦ መሆኑን ለአንባቢ ማሳወቅ እወዳለሁ፤ስለኢትዮጵያ የሚጻፉትን የምችለውን ያህል እከታተላለሁ፤ነገር ግን እጅጉን ያስቸገረኝ ጸሐፊዎች ስለ አሁን አለንበት “ሁኔታ” ሲጽፉ እንደመሰላቸው ብቻ ሳይሆን የአንባቢዎቻቸዉን ችሎታ ከግንዛቤ ሲያሰገቡ መሆኑን  ጽሑፋቸው በሚገባ ያንፅባርቃል፤ለዚህም በመረጃነት የማቀርበው ከላይ የተጠቀሱት ሁለት ሊቃን አሁን ባለው የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የጻፉትን በመመልከት ነው፤ እንዲት እንደተመለከትኩት በአጭሩ ላስረዳ፤ ከአንድ ወዳጄ ጋር በቅርቡ ታትሞ ስለወጣ መጽሐፍ ስናወራ “ጸሐፊው ዝም ብሎ ነው፤ከዚህም ከዚያም አሰባስቦ መጽሐፍ ጻፍኩይላል” አለኝ፤ መጽሐፉ በሚገባ ስለተጻፈ ሁለት ግዜ አንብቤ ያደነቅሁት ጽሑፍ ነው፤ ስለዚህ ይህንን ወዳጄን መጽሐፉን ማንበቡን ጠየኩት፤መልሱ በጣም የሚያስገርም ነው፤መልሶም “ለምንድነው ከዚህም ከዚያም የተለቃቀመ ጽሑፍ የማነበው” አለኝ፤ እዚህ ላይ ስለመጻሕፋ ውይይት ቆመ፤ ምክናያቱም እኔ እንደገባኝ “ያለማውቅ እንዲት ደፋር እንደሚያደርግ” እና ሊላዉንም እንዲት ደፋር እንደሚያደርግ ስለ አስረዳኝ ነው። ይህ ወዳጄ መጽሐፉን ቢያነበው ኖሮ ተወያይተን እንማማር  ነበር፤ ማጋነን አይሁንብኝምና ይህ ወዳጄ እስክማውቀው ድረስ አንድ መጽሐፍ አንብቦ አያውቅም፤ አንብቦማ ቢሆን መጽሐፍ የሚጻፈው የተለያዩ ጽሁፎቹን አንብቦ ነው፤ የተለቃቀሙት ጽሑፎች ከብዙ መጻሕፍት ሲሁኑማ የጸሐፊው ዕውቀት በዚያው ልክ ክፍ ይላል።  ስለ ጽሑፍ መለቃቀም ታላቁ የኢትዮጵያ ፈላስፋ የጻፈዉን በማስታወስ ነው፤ ፈላስፋው ዘርዓ ያዕቆብ (ንጉሡን አይደለም) ንቧ የምታደርገዉን ተገንዝቦ እንዲህ ይላል፤ “ንቧ የተለያዩትን አበባዎችን ቀስማ ማሩን ታመርታለች፤ ማሩም ጥሩ ማዕዛ የሚስጥ መጠጥ ይሆናል፤የመጠጡም ቅሪት ጧፍ ሆኖ በጨልመ ግዜ ብርሃንን ይሰጣል” ይላል፤ ይህ ፕሮፊሰር መሳይ ከበደን ያስቆጣል፤ምክናያቱም ዘርዓ ያዕቆብን ፈላስፋ ነው ብለው አይቀበሉትም፤ የዘውግ አቀኝቃኝ ስለሆኑ አፍሪቃዌ እንደ አውሮፓውያን ፈላስፋ ይሆናል ብለው ስለሚያምኑ፤ ሆኖም ጽሑፋቸዉን በሚገባ አጥንቺአልሁ፤  የኢትዮጵያ ታሪክና የፖለቲካውን ሥርዓት አዋቂ ስለተባሉት ረኔ ለፎርት ለማወቅ ብዙ ጥረት አድርጌአለህ፤ ነገር ግን ምንም ያገኝሁት ነገር የለም፤ ስለዚህ የምሰጠው አስተያየት ሁለቱ በአደረጉት ውይይት ላይ ብቻ ይሆናል፤ የዚህ ጽሑፍ ዋናው አላማው ከአንባቢ ጋር ለመወያየትና ለመማማር ስለሆነ የጽሑፉን ይዘት ከመረጃ ጋር እንመለከታልን፤ እዚህ ላይ መጠንቀቅ የሚያስፈልገው ውይይታችንን አቅጣጫ እንዳይዝ የሚደረገዉን ጥረት መቛቛም ይኖርብናል፤ እንግዲህ ውይይታችን ረጅም የሆነ “ታሪካዌ ሂደት” ስለሆነ አስፈላጊዉን ግዜ ወስደን መወያየት አስፈላጊ ነው፤ “ከታሪክ የማይማር ውጢቱ ሞት ነው” እንደተባለው ሁሉ እኛም ያለፈዉን ስህተት እንዳንደግም አስፈላጊዉን ጥንቃቄ ማድረግ አልብን፤ አዶልፍ ሒተለርና ዱቼ ሙሶሎኒን መቋቋም ሲገባቸው ዝም ያሉ ሰዎች የደረሰባቸው ሞት ነበር፤ በእነዚህ ሁለት እብዶች ምክናያት 100 ሚሊዮን ሕይወታቸዉን አጥተዋል፤ ወያኒ ትግሪ በላይ ከአልሆነ ኢትዮጵያ የምትባል አገር አይኖርም እያለ እሱን አዝሎ እሽሩሩ ማለት መጨረሻው ሞት ነው፤ይህ ጽሑፍ በብዙ ክፍል ተከፋፍሎ ይቀርባል፤ በመጨረሻም ትንታኔ ይሰጣል፤ አንባቢን ለማዘጋጀት ያህል የምናደርገው ትንታኒ በቀረቡት ጽሑፍ ላይ ይሆናል፤ ለምሳሊ (በግእሊዘኛ content analysis on: “the outgrowth of the success of the ruling party; strong economic growth; the creation of demanding society; distribution of its benefit; Pragmatic leadership; they are obsessed with the wellbeing of Ethiopia; relied on a high economic growth and a drastic change or reform). እነዚህ ከጽሑፋቸው ላይ ቀንጠብ ተደርጎ የተወሰዱ ናቸው፤ የዘር ማጥፋት በከፍተኛ ደረጃ እየተካሀደ፤ የአገር መሪት በጅምላ እየተሽጠ፤የሰው ልጅ ሰብአዌ መብቱ ተገፎ እንደ ሰው የማይታይበት ሁኒታ ተፈጥሮ፤ይደረጋል ተብሎ የማይታሰብ ነገር እየተደረገ ወንበዲዎችና ወንጀለኞችን የሚሻሻሉብትን ዘዴ መፈልግ አጋባብ ያለመሆኑን ተረድተን በአንድ ነት አገራችንን የምናድንበትን መንገድ መከተል ይኖርብናል፤የኢትዮጵያ ሕዝብ አልፎን ሂዷል፤ የጎበዝ አለቃዉን እየምረጠ ነፃነቱን አውጇል ባሁኑ ስዓት ብሒራዌ ሽንጎ የሚመርጥበትን መንገድ ማሳየትና መንግሥቱን እንዲት እንደሚያዋቅር እርዳታ  መስጠት እንጂ ከባሕር ማዶ ሆኖ የግል አስተያየቱን ማስተጋባት ግዚው አልፎቦታል። የሚመጣው መንግሥት በሕዝብ ለሕዝብ ይሆናል። መልካም ንባብ]

እነዚህ ሁለት አንጋፋ ሊቃን ታሪክ ታሪክን ይደግማል የሚባለውን እውን መሆኑን ሊያሰረዱ የተካኑ ምሁራን ይመስላሉ፤ አንዱን በሚገባ አውቃችዋለሁ፤ ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ በሙያቸው የዘውግ ፍልስፍና [ethno-philosopher] ሊቃን ናቸው። አቶ ሬኔ ለፎርት [Rene Lefort] ማን እንደሆኑ የሰማሁት ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ በአድናቅት የኢትዮጵያን ታሪክ አዋቂና የወቅቱን የአገር አስተዳደር በሚገባ የሚያውቁ ሊቃን መሆናችዉን በጽሑፋቸው ላይ ከአነበብኩ በኃሏ ነው። እንግዲህ ይህ ከተባለ በኃሏ የራሴን ሙያ በመጠኑ ማሳወቅ ግዲታ ነው፤የታሪክና የአስተዳደር ሥነ ሥርዓት ተማሪ ነኝ። ምንም እንኳ የተጠቀሱትን ትምህርት ጨርሼ በአጠናቅቅም መማሬን አላቆምኩም፤ አሁንም እየተማርኩ ነው፤ የነዚህ ትምህርት ክፍል ሰፌ ስለሆነና ግዜዉን እየጠበቀ ስለሚለዋወጥ ማሊቂያ የለዉም። ታሪክም የፖለቲካ ሥርዓትም “ሁኒታ” ይለዉጣችዋል፤ መደበኛ ወይም አይነተኛ አቋም የላቸዉም። የሁኒታ ተገዥ ትዕይንት ናቸው። “ሁኒታ” ይፈጠራችዋል ደግሞም “ሁኒታ” መልሶ ያጠፋችዋል። ይህንን እንደመግቢያ ከአልኩ በኃሏ ወደ እርዕስቱ እገባለህ።

በመጀመረያ ከላይ የተጠቀሰው አርዕስት የተመረጠበት ምክንያት የእነዚህ ሁለት ሊቃን በኢትዮ-ሚዲያ [ethiomedaia-11/26/16 and 12/5/16] በአደረጉት ውይይት ላይ የተመሰረተ ነው። ውይይታቸው ጥሩ ነው፤ከዘያም በላይ ደገሞ የሚያሳየው መከባበርን ነው፤ከዚያም አልፎ  አንዱ የሊላዉን ዕውቀት ታላቅና ለወደፊቷ ኢትዮጵያ ለሚያደርጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ነው፤ ይህንን መልካም አስተያየት  ማንም አይቃወምም፤ ለአንድ አገር በጎ መመኞት ያስመሰግናል፤ይህንን በጎ አስተሳሰባቸወን እያመሰገንኩ ውይይታቸው የኢትዮጵያ ታሪክ አይደለም፤ አሁን ከአለውም የፖለቲካ ሥርዓት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፤ ስለዘህ ከላይ የተጠቀሰው እርዕስት “የመሳይ ከበደና የሬኔ ለፎርት ወግ” መባሉ ትክክል መሆኑን ለአንባቢ ማስረዳት ግዲታ ነው። በይበልጥ አንባቢ መረዳት ያለበት አሁን  ያለው ሥርዓት ሁለቱ ሊቃን እናዳወጉት ወግ ሳይሆን  ማየት ያለብን ታሪካዌ ሄደቱን ነው። እነሱ እንዳወጉት ወግ የፖለቲካ ሥርዓት ተሽላልሞና ተቀባብቶ ሊሻሻል የሚችል የመንግሥት መዋቅር አይደለም። የሥርዓቱ ታሪክ እንዳወጉት ወግ ሳይሆን ራሱን የቻለ የታሪክ አምድ አለው። ይህንን መላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ማወቅ ግዲታ ነው። ከታሪክ አምድ ከመጋባቴ በፊት የኢትዮጵያን ታሪክና የአገሩን የአስተዳደር መዋቅር በሚገባ ያውቃሉ የተባሉት ሊቃን ሬኔ ለፎርት ስለ ፖሮፌሰር መሳይ ከበደ ለሰጡት ምስክርነት አጠር ያለ መረጃ መስጠት አስፈላጊ ነው። ፖረፈሰሩ በአብዮቱ ዘመን አደረጉ ለተባለው መስትዋጽኦ በደርግ ግዜ በቀበሌ ሊቀ መንበርነት ማገልገላቸው የሚታወቅ ነው። ነገር ግን በኢትዮጵያ ሊቃን ዉስጥ ያደረጉት መስተዋጽኦ ቢኖር አንድ ብሒር ሊሎቹን በቅኝ ገዥነት [እሳቸው እንደሚሉት eternal colonization እያሉ መጻፋቸዉን በማስታወስ ነው፤ ይህንን አላልኩም ከአሉ እንደመሻሻል መወሰድ አለበት] ለብዙ ዘመናት አንድ ብሒር ሊሎቹን ብሒረሰቦች ጨቁኗል በማለት ታላቅ መስተዋጽኦ አድርገዋል ከሆነ ትክክል ነው፤ የታሪክ ሊቃኑ ለፎርት ለገዥው አካል ቅርበት አላቸው ስለተባለ የፖሮፌሰሩን የጎሳ/የዘውግ አቅኝቃኝነት ማወደሳቸው መሆኑን አንባቢ መረዳት ይኖርበታል።  ስለዘህ ጉዳይ በመጨረሻ አስተያየት ላይ በሰፊው ይቀርባል። አሁን ለአንባቢ የወያኒን የፖለቲካ ሥርዓት ከየት እንደመጣና ታሪካዌ ሂደቱ እንዲት እንደተመሰረተ አንባቢ ማወቅ ግዲታ ነው፤ ከዚያም አልፎ እኛ ኢትዮጵያውያን እንደ ኢትዮጵያዉነታችን የራሳችንን ታሪክ ባለቢት ሆነን ችግራችንን እንድንፈታ በማሳብ በተረጋጋ መንፈስ መወያያት ይኖርብናል። አገራችን ላይ ያለው ችግር በሁለት ሊቃን ወግ ሊፈታ አይችልም፤ ደግሞም እነሱ እንደሚሉት በቀላሉ ሊጠገን የሚችል ሥርዓት አይደለም፤ ይህንንም በአጭሩ ለማስረዳት እሞክራለህ። ይህ ከተባለ በኃላ የአሁኑ ሥርዓት ከየት እንደመጣ እንዴትስ እንደተጀመረ ማሳወቁ ምስቅልቅሉ የወጣዉን የኢትዮጵያን ፖለቲካ ሥርዓትና ታሪካዌ ሂደቱን ማወቁ ለአስተሳሰባችን አቅጣጫ ይሰጣል ብዮ እገምታለሁ። ይህንን ሰፋ ያለ ታሪካዌ ሂደት በቅጡ ይመልከቱት።

የአፍሪቃና የአውሮፓው አህጉር ግንኙነት የጀመረው በ1498 አካባቢ በፖርቲጌስ [Portuuese] መንግሥት በተላከው ቫስኮ ዳጋማ [Vasco da Gama] በሚባለው መርከበኛ መሪነት ነበር፤ መርከበኛው ከአውሮፓ ተነስቶ ወደ ምስራቅ ኢሲያ ሲሂድ በአጋጣሚ ወደ ደቡብ አፍሪቃ ወደብ ደርሶ እግረ መንገዱን ወደ ምስራቅ አፍሪቃ ወደብ በመሂድ አውሮፓዉያንን ከአፍሪቃና ከሩቅ ምስራቅ ጋር የሚያገናኝዉን የባሕር መንገድ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፈተ። ይህም ለአውሮፓያን ንግድ ጥሩ አጋጣሚ ነበር፤ በግዜው የነበረው ንግድ ከአፍሪቃና ከኢስያ ጋር ስለነበር አውሮፓዉያን የዚህ ንግድ ተካፋይ ከመሆን አልፈው አካባቢዉን ለመቆጣጠር ጥሩ አጋጣሚ ስለአገኙ ጎሗ በምትባል የሕንድ ከተማ ላይ ምሽጋቸውን በማመቻቸት በምስራቅ አፍሪቃ በሚገኙት ኪ-ስዋሕሊ ተናጋሪዎችና በአረብ ነጋዴዎች ታላቅ የሆነ የንግድ ቅብብልና ውድድር ጀመሩ። ውድድሩ ከፍ ባለ ሁኔታ ስለተካሂደ ሊላ የአውሮፓ አገሮች አዲስ በተከፈተው ባሕር መስመር መምጣት ጀመሩ። ግን ፖርቱጌስ በተቀዳሚነት የምስራቅ አፍሪቃን ወደብን አልፈው  መሐል በመግባት በወርቅ ማዕድን የታወቀችዉን ሾና የምትባለዉን አገር ከሙታምፓ አገረ ገዥ ጋር ስምምነት በማድረግ የወርቁን ማዕድን ተቆጣጥረዉት ነበር፤ በ1659 ዓ ም የፖርቱጌስ መንግሥት ጠቅላላ አገሩን ለመቆጣጠር አስቦ ከፍተኛ የጥር ኃይል ልኮ ነበር፤ ግን የአገሬው ሕዝብ ከመሬው ጋር በመተባበር አገሩን አልሰጥም ስለ አለ የቅኝ ገዥነቱ ሳይሳካ ቀረ፤ ይህ በዚህ እንዳለ  የፖርቱጌስ ቅኝ ገዥነት በመንግሥት ደረጃ መሆኑ ቀርቶ ዜጎቿን ቀስ በቀስ በማስገባት በዴፕሎማሲ የአገሩን መሬዎች እንዲያግባቡ በማድረግና አንዱን መሪ ከሊላው መሪ በማጋጨት፤ መሳሪያ በማቀበልና ዚጎቿን በአባሪነት በማስተባበር የአገር መሪዎችን እንዲተባበሩ በማድረግ የወደፊቱን የቅኝ ገዥነት ዕቅዳቸዉን ከግቡ ለማድረስ ችለዋል። ምንም እንኳ ቫስኮ ዳጋማ  በደቡብና በምስራቅ አፍሪቃ  የነበረዉን የባሕር መንገድ ለአውሮፓዉያን በመጀምሪያ ቢከፍት የቅኝ ገዥነቱ እድል የደረሰው ለደች ምስራቅ [the Dutch East India Company] የንግድ ድርጅት ነበር፤ ይህ የደች ድርጅት የምስራቅ አፍሪቃን ወደብ አልፎ ወደ ደቡብ አፍሪቃ ወደብ በመድረስ “የወደፊቱ ከተማ ተስፋ በደቡብ አፍሪቃ ወደብ” [the Cape of Good Hope of South Africa] ተብሎ የሚጠራው ወደብ ላይ ምሽጉን አቋቋመ፤ ስለ ስሙ ስያሚ ብዙ አባባል አለ፤ አንደኛው ከሩቅ ምስራቅ ጋር በባሕር ጉዞ ስለአገናኘ የተሰጠው ቅጽል ስም ነው ይላሉ፤እዘህ ላይ የሚደረገው ጥረት አንባቢ የዚህን ታሪካዌ ሂደት በቅደም ተከተል ተከትሎ “ሁኔታ” በመለዋወጥ ያደረገዉን ለዉጥና ያስከተለዉን ጥፋት  ነው። ይህ ከዚህ በላይ የተጻፈው የታሪካዌ ሂደት መቅድም ነው፤ ከዚህ ቀጥሎ የአውሮፓዉያን ቅኝ ገዥነት እንዲት እንደተስፋፋ በቅደም ተከተል ስለሚቀርቡ አንባቢ በትኩረት መገንዘብ ይኖርብርታል።

1.የደች ኢስት ኢንድያ ንግድ ድርጅት የደቡብ አፍሪቃን ወደብ ከተቆጣጠረ በኋላ ቀስ በቀስ እየገፋ ወደ ማህል አገር ገብተው ሕዝቡንና አገሩን መቆጣጠር ችለዋል፤ የአገሩ ተወላጅ በተቻላቸው መጠን መዋጋተቸዉን ታሪክ ይመሰክራል፤ ነገር ግን አውሮፓዉያኖች ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ስለነበራቸው የአገሩን ለም መሪት፤ ክብት፤ ማዕድን በቁጥጥራቸው ስር በማድረግና ከዉጭ ሰራተኞች በማስመጣት የአገሪዉን ሰው በማግለል ኢኮነሚውንና አስተዳደሩን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር የአገሩ ባለቢት ሆነው ነበር፤ ለዚህም መሆን የበቁት በባብርነት ከሲሎን፤ከሕንድ፤ከኢንዶኒሽያ፤ከማልያ፤ከማዳጋስካር በመጡት ሰራተኞች ኃይል ነበር፤ያለምንም ክፍያ በጉልበታቸው ስለአገለገሉ አውሮፓዉያኖች የአገሩን ሰው ለማሽነፍ አስችሎችዋል፤ሆኖም የዙሉ፤የናታል፤የኮሕ ኮሕይ፤ሕዝብ ለነፃነታቸው ብዙ ታግለው መስዋዕት ሆነዋል፤ የደቡብ አፍሪቃ ትግል መራርና አስከፊ ቢሆንም አውሮፓዉያን የነጭ መንግሥት በማቋቋምና የተለያየ ሕግ በማውጣት አውሮፓውያን ያልሆኑትን ብሒረ ሰቦች በማግለል በአፓራታይድ ሥርዕት [Apartheid System: The Native act of 1913]. ለቡዙ ዘመን ገዝተዋል።

2.የታሪክ ሂደት የሚመዘነው “ሁኔታዉን” በፈጠረው ኃይል ነው፤ ለምሳሊ ፖርቱጌስ በቫስኮ ዳጋማ መሪነት ደቡብ አፍሪቃ ባይደርስና የሩቅ ምስራቅ የንግድ ግንኙነት ባይሆን ኖሮ ከላይ የተዘረዘሩት ታሪክዌ ሂደት አይከናወ ኑም ነበር? ሊላ ጥሩ ምሳሊ፤ አውሮፓዉያን ንግዳቸው ሰው በግልበቱ ያመረተዉን ምርት ብቻ ቢሆንና የሰው ልጅ በሰዉነቱ የተከበረ ቢሆን ዉጢቱ ምን ይመስል ነበር? ይህንን አንባቢ ተመራምረሕ ድረስበት ማለት አይቻልም፤ስለዚህ እዚህ ላይ ትንሽ ቆይታ አድርገን መወያየቱ አስፈላጊ ነው። በዚህ ሁለተኛው ታሪካዌ ሂደት ላይ የምንመለከተው ፖርቱጌስ በማወቅም ሆነ ባለማውቅ አሁን ለአለንበት ችግር ትልቁን መስተዋጽኦ አድርጓል በማለት እንወያያለን፤ በአፍሪቃ ዉስጥ የፖርቱጌስ ቅኝ ግዛቶች ስድስት ናቸው፤ አንጎላ፤ኬፕ ቨርድ፤ጊኒ ቢሳው፤ሞዛምቢክ፤ሳዎ ቶም፤ኢኳቶሪያል ጊኒ ናቸው፤ እነዚህ ተጠቃለው ሉሶፎን ይባላሉ ቋንቋቸዉ ፖርቱጊስ ስለሆነ። እነዚህን አገሮች በቅኝ ግዛት አስተዳድረው እነሱ የደሩሰብትን ስልጣኒ ለአፍሪቃዉያን ቢያክፍሉ መልካም ነበር፤ ነገር ግን የሰዉን ልጅ መሽጥና መለወጥ ስለጀመሩ ለሰው ልጅ ያተረፈው ዘላለማዌ እሮሮ ነው። ከታሪኩ ቀንጨብ አድርገን ብንመለከተው ይህንን ይመስላል፤ የአስራምስተኛው መቶ ዘመን ሲገባደድ ፖርቱጌስ የአፍሪቃን አህጉር ዙራዌን ዞረው በመጨረሽ ንግዱን ሙሉ በመሉ በቁጥጥራቸው ስር አድርገዉት ነበር፤ ከቅኝ ግዛታቻው የሚያገኙት ጥሬ ሃብት አልበቃ ብሎአቸው ጊኒ አካባቢ በምትገኝው ሳኦ በምትባል ደሲት ላይ የሱካር ማምረቻ ሁዳድ በመስራት ከአካባቢው አፍሪቃውያንን በጠመንጃና በዉስኪ በመለወጥ የነፃ አግልግሎት የሚስጥ ኃይል ከአዘጋጁ በኋላ ወደ አውሮፓ የሚላክ ስኳር ማምረት ጀመሩ፤ይህ የስኳር ምርት በጣም ተፈላጌ እየሆነ ስለመጣ ታላቅ የእስር ቤት በመገንባት ለሽያጭ የሚቀርቡትን አፍሪቃዉያንን ማከማቻ በማደረግ የሰው ልጅ እንደቃ መሽጥና መለወጥ ተጀምሮ ከአንድ መቶ ሚሊዮን በላይ አፍሪቃዉያን ለባርነት ተሽጠዋል፤ ዋልተር ሮድኒ የሚባሉ ጸሐፊ “አውሮፓ እንዲት አፍሪቃን ወደ ኋላ እንዳስቀሯት” በሚል መጽሐፋቸው ላይ እንደጻፉት ቢያንስ ከመቶ ሚሊዮን በላይ አፍሪቃዉያን ከአጠቃላይ አፍሪቃ አገሮች ለባርነት መሽጣቸዉን ከበቂ መረጃ ጋር አቅርበዋል፤ ነገር ግን የአውሮፓ ምሁራን ቁጥሩን እጅግ በማሳነስ ከ 9 እስክ 11 ሚሊዮን ሊደርስ ይችላል በማለት በታሪክ ማህደር ዉስጥ አስቀምጠዋል፤ ይህም ሆነ ያ የሰው ልጅ እንደክብት በሐራጅ የተሽጠበት ዘመን መሆኑን ሊካድ አይችልም። በዚህም ንግድ ተጠቃሚ የነብሩ አገሮች አሚሪካ፤ብራዚል፤ በአጠቃላይ የካሪቢያን ደሲቶች የስኳርና የጥጥ አምራች በመሆን ይታወቃሉ፤ ለአውሮፓ ኢንዱስትሪ መዳበርና ለቲክኖሎጂ ማደግ ትልቁን መስተዋጽኦ ያደረገ ከአፍሪቃ የመጣ የነፃ ጉልበት መሆኑን ታሪክ ሳይዘግበው መቅረቱ እጅግ በጣም አስዛኝ ነው። ይህ አልበቃ ብሎ አውሮፓ አፍሪቃን እንደቅርጫ እንዲት እንደ ከፋፈሏት  በክፍል ሁለት እንመለከታለን።

የመሳይ ከበደና የሬኔ ለፎርት ወግ [ታሪኩ ዉብነህ ጌታነህ]

December 18, 2016 16:03

ክፍል ሁለት

[ ማሳሰቢያ፡ በሁለተኛው ክፍል የሚቀርበው አውሮፓዉያን እንዲት አድርገው አፍሪቃን እንደ ቅርጫ እንደተከፋፈሏት ነው፤ ይህም ያስፈለገበት ምክንያት እነዚህ ሁለት አንጋፋ ልሂቃን ስለ ኢትዮጵያ ያላቸው ግንዛቢ አሁን ከሚሉት ጋር ምን ያህል ግንኙነት እንዳለው ለማሳወቅ ነው፤ ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ በዘውግ ፍልስፍና ላይ የተመሰረተ በርካታ ጽሑፎቹን አቅርበዋል፤ ሬኔ ለፎርት በታሪክ በፖለቲካና በአስተዳደር ላይ ያለዉን ችግር በማስተዋል ሰፋ ያለ ጽሑፍ ለአንባቢዎች አቅርበዋል ። በክፍል አንድ ላይ በአጭሩ እንደቀረበው የሁልቱም ጽሑፍ የሚያንጽባረቀው የኢትዮጵያን ታሪካዌ ሂደት ሳይሆን የራሳቸዉን አስተያየት ከአለው “ሁኔታ” ጋር  እያስተባበሩ ነው። እንግዲህ አንባቢ ማገናዘብ ያለበት የሁለቱን ምርምር ከነባር “ሁኔታ” ጋር እያስተያየ እንዲት አድርጎ ከቀደምት “ሁኔታ” ጋር እንደተያያዘ በማመላከት ነው፤ በዚህን ግዜ የሁለቱን ልሂቃን ክብርና ሰብአዌ መብታቸዉን በሚነካ መንገድ ሳይሆን ነባር “ሁኔታ” የቀደምት “ሁኔታ” ዉጤት መሆኑን በመወያየት ነው፤ እዚህ ላይ የሚደረገው ታላቅ ጥረት የመወያየት “ሁኔታ” ለመፍጠር ነው። ይህ “ሁኔታ” እጅግ በጣም አስፈላጊ ስለሆነ ከአንባቢ ጋር በዚህ ጉዳይ ላይ ትንሽ ቆይታ ማድረግ አስፈልጊ ነው፤ የአስፈለገበትም ምክንያት በአጭሩ እንደዘህ ነው፤ ደርግን ለማሶገድ በነበረው ውይይት ላይ ሻብያና ወያኔ ኢትዮጵያ በሚል ሥም በሚደረግ ስብስብ ላይ አይካፈሉም ነበር፤ ኢትዮጵያ የቅኝ ገዥ ተብላ ስለተፈረጀች ማንም ቢሆን እዚያ ስብስብ ላይ ተግኝቶ ሊወያይ አይችልም ነበር። የነበረው “ሁኔታ” ይህ ነበር፤የነበረዉም ውይይት “የአፍሪቃ ቀንድ” ወይም “የምስራቅ አፍሪቃ” ጉባዔ እየተባለ አሁን አንዳንድ ልሂቃን እንደሚሉት የኢትዮጵያ የታሪክ አባቶች በሚባሉ አስተባባሪነት የሚካሂድ ውይይት ነበር፤ውይይቱም  ስለኢርትራ ነፃነት ያተኮረ ስለነበር ከዚያ ዉጭ ኢትዮጵያን የሚመለከት ነገር ሊኖር አይችልም ነበር። እዚህ ላይ ለአንባቢ መነገር ያለበት በመረጃ ስለነበረው “ሁኔታ” በቅጡ ያስረዳል ብዮ እገምታለህ፤ መረጃው ይህ ነው፤በአንድ ኢትዮጵያ ሥም የተዘጋጅ ስብስብ ላይ አንድ ምሑር ስለኢትዮጵያ ታላላቅ መጻሐፍት ጽሑፍ አዘጋጅቶ መናገር ሲጀምር አንድ ካድሬ ከመናገሪያው መድረክ ላይ ወጥቶ የድምጽ ማጉላያዉን በመንጠቅ “እኛ አዚህ የተሰበሰብነው ተረት ለመስማት አይደለም “ በማለት ስብሰባውን መበተኑ የነበሩ ሰዎች ያስታዉሱታል ፤ ይህም እንደጀግንነት ተቆጥሮ ነፃ አውጭዎቹ አዳስ አበባ ሲገቡ  ይህ ካድሬ የምክር ቤቱ ቃለ ጉባኢ ሆኖ መሾሙ በታሪክ መዝገብ ዉስጥ ሕያዉነት እንደሚያገኝ ጥርጥር የለውም። እዚህ ላይ የምንማማረው ያለማወቅ እንዲት ደፋር እንደሚያደርግ ነው።  ሊላ ጥሩ ምሳሌ ደግሞ አሁን በቅርቡ ታትሞ በወጣው መጽሐፍ ላይ ነው። ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ “የኦሮሞና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ ብለው በጻፉት መጻሐፍ ላይ ተመሳሳይ “ሁኔታ” ተፈጥሯል፤ ይኽውም  “መጽሐፉ ያለምንም መረጃ ታሪክ ያልሆነ ጽሑፍ ነው” ፤ ከዚያም ሊላ “ከምንም ጋር ያልተያያዘ አፈ ታሪክ ነው” የሚሉ አላማቸው ምን እንደሆነ የማይታወቅ ጸሐፌዎች አስተያየት እየሰጡበት ነው፤ ከአለፈው ጋር ተመሳሳይነቱ እንዲህ ነው፤ “ኢትዮጵያ የምትባል አገር ትላንት በምኒልክ የተፈጠረች አገር ነች፤ አንድ ብሒር ሊሎቹን ብሒረሰቦች ጨቁናል፤ በሬ ሲወልድም አይተናል” የሚሉ ልሂቃን “የኦሮሞና የአማራ ግንኙነት ልብ ወለድ ነው” ሲሉ ለሰሚው ሕሊና ያስቸግራል፤ መጽሐፉን አላነበብኩቱም፤ ነገር ግን ስለ መጽሐፉ የተጽፉትን በአትኩረት ተመልክቻለሁ፤ የዚህ መጽሐፍ ይዘት በሁለት ይከፈላል፤ አንድኛው የአንድ “አገር ንግርት” ወይም “አፈ ታሪክ” ይሆናል፤ ይህም  የዚህ አገር “ንግርት” ከትውልድ ወደ ትውልድ ተላልፎ የሚነገር “አፈ ታሪክ” ነው፤ “አፈ ታሪክ” የሊለው አገር በምንኖርበት ዓለም የለም፤ እንኳን አገር  ቀርቶ ቀበሌም ጭምር ንግርት አለው፤ ምናልባትም ፕሮፌሰሩ መጽሐፉን የጻፉት በዚህ ንግርት ተነቃቅተው ሊሆን ይሆናል፤ ይህ “አፈ ታሪክ” በመረጃ የሚደገፍ ታሪክ አይደለም፤ ጸሐፊዉንም  መረጃ እንዲያመጣ አይገደድም፤ ንግርት ስለሆነ በንግርትነቱ ይነገራል ደግሞም ይጻፋል፤ ከዚያም አልፎ ለትምህርት መማሪያ ተቀነባብሮ ይቀርባል፤ ምክንያቱም “ንግርቱ” ወይም “አፈ ታሪኩ” የአገር ቅርስ ስለሆነ እንዳይጠፋ በጽሑፍ ተጽፎ ይቀመጣል፤ ምን አልባት ይህ ጽሑፍ  በኮንቱ ሮሲኔ፤ሪቻርድ ፓንከረስት፤ዶናልድ ለቬን እና በሌሎች የታሪክ አባቶቻችን በምንላቸው ቢጻፍ ኖሮ ምን እንል ነበር? ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ኢትዮጵያዌ ስለሆኑ ይህንን መጽሐፍ ሊጽፉ አይችሉም ማለት ነው? ትልቅ ችግር ያለብን ይመስለኛል። ሁልተኛው ደግም ጽሑፉ ኦሮሞና አማራ አንድ ዘር ነው የሚለው፤ ይህንን ለማለት አውሮፓ ሄዶ የነሱን ታሪክ አጻጻፍ ዘዴ ተምሮና  ተመራምሮ  በተጨማሪ ማ እንዳስተማረው ስሙን በዋቢነት ጠቅሶ ሲጽፍ ነው የኦሮሞና የአማራነት ዘር ተቀባይነት የሚያገኝው? ይህንን ለአንባቢ መርምረህ ድረስበት ተብሎ አይተዉም፤ እዚህ ላይ ትንሽ ቆይታ ማድረግ አስፈላጊ ነው። ፕሮፌሰሩ መጽሐፋቸዉን ለሁለት ከፍለው “የኦሮሞና የአማራ ንግርትና  እውነተኛ ታሪክ” ቢሉት ጥሩ ነበር፤ ነገር ግን የራሳቸው “ራዕይ” ስለሆነ  እንደዚህ እንዲሉ ማንም ሊያስገድዳቸው አይችልም፤ ኦሮሞና አማራ በታሪክ አጋጣሚ ስለተገናኙ ዘመዳሞች ናቸው። ለዚህ ምን መረጃ ያስፈልጋል? ከአስፈለገም  ይህ ጸሐፊ በቂ መረጃ ሊስጥ ይችላል፤ መረጃውም እንደዚህ ነው፤ የአክስቲ የልጅ ልጅ ኦሮሞ ነው፤ ከጥቂት ዓመታት በፊት ለግብኝት ወደ ትውልድ አገሬ ሂጄ ነበር፤ እዘያ የሂድክበት አገር የአክስቴ የልጅ ልጅ በዳኝነት ተሾሞ ስለመጣ ሂጄ እንዳገኝው ተነግሮኝ ብሂድ “አላውቅህም “ አለኝ፤ ምንም አልተገረምኩም፤ ምክንያቱም አማራና ኦሮሞ እንደጠላት እንዲተያዩ የተፈጠረው “ሁኔታ” ስለአስገደደው ሕጻን ሆኖ አንኮኮ ያልኩት ልጅ አላውቅህም አለኝ፤  ምንም አማራጭ የለዉም፤ በዳኝንት አማራ አካባቢ የተላክው  አልገዛ ያለዉን “ጨቋኝ አማራ” ፍርድ እየስጠ ወደወሕኒ ቤት እንዲሊክ ነው፤ ይህ የአንድ ግለሰብ ዝምድና ነው፤ በዚህ ዓይነት ስንት ሊኖር እንድሚችል መገመት ይቻላል፤ ከተራ ዜጋ በላይ የአማራና የኦሮሞ ዝምድና በገዥው ክፍል ፕሮፌሰር እንዳሉት የአንድ አባትና እናት ልጆች ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም ፤ ኦሮሞነት የሊለበት ንጉሥ የለም፤ ከጥንት ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሁሉም  ጎሳ የተውጣጣ ነው [ብሔር የዘውግ አቀኝቃኞች ቋንቋ ስለሆነ ከጥቅም ዉጭ ማድረግ ግዴታ ነው]፤ በታሪካችን ለመጀመሪያ ግዜ ከአንድ ጎሳ ብቻ የተውጣጡ ግለሰቦች የመንግሥቱን አዉታር ሲቆጣጠሩ ማየት እጅግ በጣም አሳፋሪ ነው፤ አይን ያወጣ እፍረት የሊለው ስራ ነው። ይሉኝታ የሚባል የሰው ልጅ አለኝታ በቋንቋቸው ዉስጥ የሊለ ሰው የሚመስሉ አውሬዎ ች ናቸው፤ የፕሮፌሰሩ የኦሮሞና የአማራ ዝምድና በእዉነት ላይ የተመሰረተ የትውልድ ዘርፍ ነው። የዘውግ አቀኝቃኞችን ስራ አሳጥቶቻዋል።

ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ እንደ መለስ ዜና እና እንደ ኢሳይያስ አፈወርቅ “ሁኔታ” ለመፍጠር እየሞኮሩ ነው፤ ነገር ግን ነባር “ሁኔታው” በከፍተኛ ደረጃ ስለሚቀሳቀስ ኦሮሞና አማራ አንድ እንዳይሆን ወያኔ ሰማይ እየቧጠጠ ነው። 600 መቶ መጻፍና ማንበብ የማይችሉ ካድሬዎችን አሰልፎ ጥዋት ማታ በየ ድረ ገጹ ላይ የሚጻፈዉን ጸረ ወያኔ ጽሑፍ በማዋደቅና በመሳደብ የለውጥ “ሁኔታ” እንዳይፈጠር እያደረጉ ነው። ካህናቱንና መንኮሳቱን መስቀል አሽክሞ አልሞት ባይ ተጋዳዩን መሳሪያዉን እንዲያስፈቱ እየተደረገ ነው፤ የሥርዕቱ ተጠቃሚዎች በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ከአቀኝቃኝ ካህናት  ጋር በመተባበር ውጅንብር እየፈጠሩ ነው። ፕሮፌሰሩ የጀመሩት “ሁኔታ” የሚቆም አይደለም፤ አማራና ኦሮሞ ግንባር የፈጠሩ ዕለት የኢትዮጵያ ችግር ይፈታል፤ አማራና ኦሮም የኢትዮጵያ ምሶሶና ግድግዳ ናችው፤ ያለነሱ ኢትዮጵያ የምትባል አገር አትኖርም፤ ኢትዮጵያን ነፃነቷን ያጎናጸፈ የኦሮሞ ፈረሰኛ ነው፤ ጣልያንን፤ፈርንሳይን፤ጀርመንን ጠይቅ፤ ጀርመን ሚሲዮኖችን ወደወለጋ ያስገባው የኦሮሞን ጅግንነት ሚስጡሩን ለማወቅ እንጂ ክርስትናን ለማስፋፋት አይደለም። በሺህ የሚሆን አማራና ኦሮም በአድዋ ጥርነት የተዋደቀው የትግራይን ነፃነት ለማስጠበቅ ነው። አሁን ለቡዙዎቹ ትልቅ ችግር ሆኖ የታየው እንዲት አንድ የጥቅር ሕዝብ ታላቅና የሰለጠነዉን አውሮፓ ማሽነፍ ቻለ? ነው፤ ይህ የነጭን የበላይነት ስሚት ስለሚነካ የግድ ያ ምሶሶና [አማራ] ግድግዳ [ኦሮሞ] ሆኖ የቆመ ቤት መፍረስ አለበት፤ ይህንን ቤት ለማፍረስ ካድሬዎች ተክነው፤ዶክተር ተብለው ፤ፕሮፌሰር ተብለው፤ ሊቃን ተብለው ፤ተጠምቀው ፤ ዕውቀታቸዉን የሚለካ ምስክር ወረቀት ተቀበለው “ኢትዮጵያ የምትባል አገር ልብ ወለድ፤ ተረት ተረት፤ አፈ ታሪክ” ነው እያሉ የዘውግ አቀኝቃኞች  በመሆን እየተፈላሰፉባት ነው። የቤተ ክርስቲያናችን  አባቶችና ካህናት በአወዳሽነት ማህበረ ምዕመኑን ለጠላት ተገዥ እንዲሆን እያደረጉ ነው። እንግዲህ አንባቢ ለዚህ ሁሉ መሆን ዋና ምክንያቱን በአትኩረት መመልከት ግዲታ ነው፤ በዚህ በሁለተኝው ክፍል እንደዚህ ሰፋ ያለ መግለጫ የተሰጠበት ምክንያት አንባቤ አሁን ያለበትን “ሁኔታ” ከቅድመ “ሁኔታ” ጋር እያገናዘበ ለመማማር እንዲረዳ ታስቦ ነው። ለግንዛቤ ያህል በሁለቱ ልሂቃን ከተጻፉት ቀንጠብ አድርገን እንመልከት፤ “drastic change or reform” [MK] and “their obsession with the wellbeing of Ethiopia” [RL]. Really? በእኔ ግምት ለነዚህ አባባሎች ሶወስት ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላል፤ አንደኛ ጽሑፋቸዉን አንባቢ ያለምነም ጥያቄ የሚቀበላቸው እየመሰላችው፤ ሁለተኛ የገዥውና የደሕንነት ክፍሉ ጽሑፋቸዉን በበጎ ተመልክቶ ምክራቸዉን የሚቀበልና ስራ ላይ የሚያዉል መስሏቸው፤ ሶወስተኛ ነባር “ሁኔታ” ከቅድመ “ሁኔታ” ጋር ያለዉን ግንኙነት ከግንዛቤ ስለአላስገቡት ይሆናል ብዮ እገምታለሁ። ስለዚህ አንባቢ ከፍ ባለ ደረጃ ስለ አገሩ መዋያየት እንዲችል በቅድም ተከተል የተፈራረቁቱን “ሁኔታዎች” በዝርዝር እንመለከታለን፤ መልካም  ውይይት]::

መቅድም

በክፍል አንድ ላይ በአጭሩ ስለ ደቡብና ምስራቅ አፍሪቃ ተወያይተናል፤ አውሮፓዉያኖች ቀስ በቀስ የቅኝ ግዛታቸዉን ከአስፋፉ በኃሏ ወደ መካከለኛውና ወድ ምዕራብ  አፍሪቃ በማምራት ንግዱን በቁጥጥር ስር አዉለዉት ነበር፤ ይህ አልበቃ ብሎ ሕዝቡን እርስ በራሱ በማዋጋት የባርነት ንግድ እንዲስፋፋ በማድረግ በጥንታዌነት የሚታወቁቱን የጋና፤ማሌ እና ሶንጋይ ሥረወ መንግሥታትን እንዲፈርሱ ተደረገ፤ ከታሪኩ ቀንጠብ አድርገን ብንመለከት ጥንታዌት ጋና የታወቀችና ገናና እንደነበረች ታሪክ ያወሳላታል፤ የጋና ጥንታዌ ስም ዋጋዱዱ ይባል ነበር፤ ጋና ማለት ማንዴ ማለት ነው፤ ማንዴ ማለትም ጦረኛው ንጉሥ ማለት ነው፤ በ11ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የጋና  ሥረወ መንግሥት  በዋጋዱዱ ጠቅላይ ግዛት ዉስጥ ተመሰረተ፤ የጋና ንጉሠ ነገሥትም በአክባቢው ያሉትን ሕዝቦች በጦር ኃይል አንድ በማደረግ አፍሪቃ ዉስጥ አሉ ከሚባሉ ነገሥታት ዉስጥ አንዱ እንደነበር ይነገርለታል፤ ጋና በ16ኛ መቶ ክፍለ ዘመን ታዋቂና ዝነኛ መንግሥት ነበር፤ የፖለቲካና የኢኮነሚው ሥርዓት ተጠቃሎ በንጉሠ ነገሥቱ ስር እንደነበር ታሪክ ዘግቦታል፤ በወርቅ ማዕድንም ታዋቂ ስለበር ፖርቱጌስ በመጀመሪያ ንግዳቸዉን የጀመሩት በ1471 ነበር፤ በዘህም ምክንያት ጋና የወርቅ ወደብ [Gold Coast] የሚባል ስም ተሰጥዋት ነፃነቷን እስክታገኝ ድረስ መጠሪያ ስሟ ነበር፤ በመጨረሻም የኢንግሊዝ መንግሥት ጠባቂና የቅኝ ገዢ በመሆን እስክ 1952 ዓ ም ድረስ በተገዥነት ቆይታለች፤ በዚሁ አይነት የማሌና የሶንጋይ ሥረወ መንግሥት በተመሳሳይ ሁኒታ ፈርሰዋል። እዚህ የሚደረገው ጥረት የአፍሪቃን ታሪክ ለመጻፍ ሳይሆን “ሁኒታ” የአንድ አገርን “ታሪካዌ” ሂደት እንዲት መለወጥ እንደሚችል ለማሳየት ነው፤ ለምሳሌ ካንት፤ ሔግልና ቶዮንቢ [Kant, Hegel and Toynbee] የተባሉ የምዕራብ ልሂቃን የሰዉን ፍጥረት በደረጃ ይከፋፉሉቷል፤ ነገር ግን ፍጥረት አንድ ነው፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ፈላስፋ ዘርዓ ያቆብ [ንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብ አይደለም] እንዳለው “ፍጥረት አንድ ነው፤ፍጥረትም ያለ ፈጣሪ ሊኖር አይችለም” ይላል። እንግዲህ እነዚህ የምዕራብ ልሂቃን ፍጥረትን ያዩት በእውቀት ደረጃ ነው፤ የእውቀት ደረጃ  በ “ሁኔታ” ምክንያት እንደሚለያይና እንደሚለዋወጥ ልብ ብለው አልተመልክቱም፤ ለምሳሌ በአባይ ሽለቆ ይኖሩ የነበሩት አፍሪቃያኖች እርሻና የዘመን አቆጣጠር የተማሩት ፍጡራዌ ሂደትን በመመልከት ነው፤ የአባይ ወንዝ በየዓመቱ ከኢትዮጵያ ተራራ ላይ በዝናም ኃይል በሚወርደው ጥቁር አፈር መስኖ ሆኖ በሚያበቅለው ሰብል ምክንያት ነው በእርሻ መተዳደር የጀመሩት፤ የእርሻው አጀማመር  የተጀመረው የአባይ ወንዝ በፈጠረው “ሁኔታ” ነው፤ ሊላው ደግሞ የዘመን አቆጣጠር ነው፤ አባይ በየዓመቱ  መስከረም ወር በሚያመጣው ጎድፍ ነው፤ ጎድፉ ዓመቱን ጠብቆ ስለሚመጣ  መስከረምን የዘመንን መለወጫ በማድረግ በዓለማችን ለመጀመሪያ ግዜ ትክክለኛዉን የዘመነን መቅጠሪያ አግኝተናል። እንግዲህ እነዚህ ሁለቱ የፉጥራዌ ሂደት ናቸው እንጂ ሰው ሰራሽ አይደሉም፤ ዕዉቀት አንድ ነው፤ “ሁኔታ” ይፈጥረዋል ደግሞም “ሁኔታ” ያጠፈዋል፤ “ግብፅ የአባይ ስጦታ ነው” የተባለው  ግብፅ አለአባይ ሊኖር አይችልም ለማለት ነው። ይህም ማለት የኢትዮጵያን አፈር የሚገድብ “ሁኔታ” ከተፈጠረ ለግብፃዉያን መጥፋት  አመቺ  ሰው ሰራሽ “ሁኔታ” ተፈጠረ ማለት ነው። እንግዲህ አንባቢ በዚህ ጉዳይ ላይ በአንክሮ መመልከት ያለበት የአፍሪቃን ታሪካዌ ሂደት “ሁኔታ” እንዴት አድርጎ እንደለዋወጠው ነው፤ አፍሪቃ በአውሮፖዉያን ቅኝ ገዥነት ባይወደቅ ኖሮ “ታሪካዌ ሂደቱ ምን ይመስል ነበር? ይህንን ወደፊት በቅጡ እንመረምራለን።

የበርሊን ጉባኢ 1884-85 [The Berlin Conference of 1884-85-Germany]

አንድ ስለ አፍሪቃ የሚያጠና ተማሪ ሲጽፍ እንዲህ ይላል፡ የአውሮፓውያን ቅኝ ገዥዎች አፍሪቃን ሲከፋፈሉ እርስ በራሳቸው ተመካክረው እነሱን በሚጠቅም “ሁኔታ” ዳር ድንበሩን በመካለል ነው፤ ይህ ዳር ድንበር የለያየው 177 የቋንቋን፤ የባሕል፤ የጎሳ ክፍሎችን ያካትታል፤ ይህም ከዚህ በፊት የነበረዉን የኢኮኖሚ፤ ፖለቲካና ማህበሪዌ እድገት አቃውሶታል፤ ዳር ድንበሩም ጎሳዎቹንና ቋንቋዎቹን ስለከፋፈላቸው እድገትና መሻሻል ምንም ግዜ ቢሆን ሊመጣ አይችልም፤ ይህም የሆነው በአጋጣሚ ሳይሆን በጉባ ኢ ተመክሮና ተጠንቶ ለብዙ ዘመን የጥግኝነተን “ሁኔታ” በአፍሪቃዉያን አእምሮ ዉስጥ ለመፍጠር ነው። ይህንን “ሁኔታ” ለይቶ ለማየት በመጠኑ የአውሮፖውያንን ታሪካዌ ሂደት ማወቅ አስፈላጊ ነው፤ አውሮፓዉያን  ለራሳችው የፈጠሩት “ሁኔታ” በቋንቋና በጎሳ የተለያይቱን የአውሮፓ ጎሳዎች በውድም ሆነ በግድ በማስተባበርና  የየራሳቸዉን ግዛት በማስፋት ነው ፤ ከዚያም አገር ምን ማለት ነው? ሰንደቅ ዓላማ የምን ምልክት ነው? የአንድነት ጥቅሙ ምንድን ነው? የሚለዉን በዜጎጆቻቸው አእምሮ ዉስጥ በመቅረጽ ነው፤ የተባበረችው ኢንግሊዝ፤ ጀርመን፤ ፈረንሳይ፤ ኢጣሊያን እንደዚሁም ሊሎች የአውሮፖ አገሮች እንደ አፍሪቃ የጎሳ ጥርቅሞች ነበሩ፤ ነገር ግን አገር፤ ሰንደቅ ዓላማ ፤ አንድነትን ከአጠናከሩ በኃሏ አፍሪቃውያን እንደነሱ ለመጠናከር ሲጀምሩ በጉባኢ መክረው ዛሬ የአፍሪቃ አህጉርን የጎሳ ኮሮጆ እንድትሆን አደርገዋታል፤ ዉጢቱን ይመልከቱ፤ አምሳ አገር፤ እያንዳንዱ አገር ቢያንስ ሁለት ወይም ሶወስት አገሮች ያዋስናል፤ ታንዛኒያና ዛምቢያ ከስምንት አገሮች ጋር ይዋሰናል፤ ኮንጎና ሱዳን ስምንት አገሮች ያዋሱኑታል፤ አስራ አምስት አገሮች የባሕር ወድብ የላቸዉም፤ በሕዝብ ብዛት ከአፍሪቃ ሁለተኛዋ የሆነችው ኢትዮጵያ ወደብ አልባ ነች፤ በአሁኑ ስዓት በአውሮፓውያን በከለሉት ድንበር ያልተቸገረ የለም ለማለት ያስቸግራል፤ ችግሩ መፍተሄ የሊለው ለብዙ ዘመን የሚቆይ ነው፤ ዉጢቱም አፍሪቃ ለአውሮፓውያን የሚያስፈልገዉን ጥራ ጥሬ ሃብት ከማቀበል በላይ ትርጉም ያለው የፖለቲካ፤ የኢኮነሚ፤ የቴክኖሎጂ፤ የባህል እድገት ልታደርግ የማትችልበት “ሁኔታ” ላይ ነው ያለችው። ምን አልባት አንባቢ እንዲት እንደዚህ ሊሆን ቻለ? ይል ይሆናል፤ ታሪኩ እንዲህ ነው፤ አውሮፓዉያን የአፍሪቃን ነፃ የጉልበት ኃይል ለሶወስት መቶ ዓመት ከተጠቀሙ በኃሏ፤ ቲክኖሎጂያቸውና ኢንደስትሪያቸው ከዳበረ በኃሏ ይህ ንግድ መቆም አለበት በማለት ሁሉም ተስማሙ፤ ይህ የሆነበት ምክንያት ለሰው ልጅ መሽጥና መለወጥ ብሎ በማሰብ ሳይሆን የጥቁር ሕዝብ ቅጥር በምዕራብ ዉስጥ ወደፊት ሊበዛ ስለሚችል ከአሁኑ መቆም አለበት በማለት ነበር፤ በተጨማሪ ቲክኖሎጂው እየተሻሻለ በመምጣቱና የሰዉን ግልበት በመተካቱ ከአፍሪቃ ይመጣ የነበረው የሰው ኃይል አስፈላጊ ሆኖ  ስለአልተገኝ ነው፤  ነገር ግን የአፍሪቃ ጥራ ጥሬ ሃብት አሁንም አስፈላጊ ስለነበር አሕግሩን ለመከፋፈል አውሮፓዉያን ከፍተኛ የሆነ  እርስ በርስ ውድድር ዉስጥ ገቡ፤ ፈረንሳይ፤ኢንግሊዝ፤ፖርቱጌስ፤ጀርመን፤የአፍሪቃን ቅኝ ግዛታቸዉን ባሳወቁበት ግዜ የበልጂያን ንጉሥ ሊዮፖልድ ሁልተኛው ራሱን የኮንጎ ንጉሠ ነገሥት ብሎ አወጀ። በዚህን ግዜ ነው የበርሊን ጉባኢ የተጠራው፤ ምክንያቱም ንጉሡ የራሱ ምክር ቤት ኮንጎን የግሉ ቅኝ ግዛት እንድትሆን እውቅና ስለከለከለው ነው፤ በዚህ ጉባኢ ላይ የተግኙ አገሮች አውስትሪያ-ሐንጋሪ፤ቤልጃም፤ደንማርክ፤ኢንግሊዝ፤ሖላንድ፤ኢጣልያን፤ኖርዌ፤ፖርቱጌስ፤ረሺያ፤ስፔን፤ስዌድን፤ቱርክ፤አሚሪካ ናቸው። ጉዳዩም የቢልጂያን ንጉሥ ኮንጎ የግሉ ቅኝ ግዛት ለመሆኑ ዕውቅና ለመስጠትና በግዛቱ አክባቢ ለንግድ የሚተላለፉትን የአውሮፓውያን ትራፊክ ያለምንም ቅድመ “ሁኔታ” እንዲያሰተናግድ ነበረ። በተጨማሪ አውሮፓውያን በቅኝ ግዛት አድርገው የተዋሰኑትን አገር አክብረው በሰላም ጥቅማቸዉን  እንዲያከብሩ ነበር፤ ይህንን ውል ሲፈራረሙና የየአገሩን ድንበር ሲያካልሉ አፍሪቃውያኖች ምንም የሚያውቁት ነገር የለም ነበር።

በዘመኑ አንድ ም አፍሪቃዌ እንኳንስ ስለ አገሩ ጉዳይ ላይ ሊነጋገር ቀርቶ ስለራሱም ጉዳይ የመናገር መብት አልነበረውም፤ የተሰጠው መብት ራሱን በአፉ በሚወጣው ቃላት ከመስደብ በላይ አያልፍ ም ነበር፤ እንግዲህ አንባቢ በጥልቀት ሊመለከት የሚገባው እንዲት አድርገን እራሳችችንን እንደምንሰድብ ነው፤ መረጃዉም ይህንን ለመማማር የቀረበዉን ጽሑፍ በአስተያየት ገጽ ላይ የሚስጠዉን አስተያየት ማንበብ ነው፤ ይህ ጽሑፍ የተጻፈው ፕሮፌሰር መሳይ ከበደንና ሚስተር ረኔ ለፎርትን ዝቅ ወይም ክፍ ለማድረግ ሳይሆን ስለ ነባር የአገር ”ሁኔታ” ያላቸዉን አስተያየት ለማጥናትና አማራጭ “ሁኔታን” ለመፍጠር ነው፤ ምናልባትም አማራጩን “ሁኔታ” በውይይት ቅሬታን ቀርፈን ልንቀበለው እንችል ይሆናል፤ ደግሞም  በዚያው መጠን ላም አለኝ በሰማይ ሊሆንም ይችላል፤  ለግዜው እንዳንሰላች ውይይታችችን እዚህ ይቆማል፤ በሶወስተኛው  ክፍል ዉይታችን ላይ አድዋን፤ የዱቼ ሙሰሊንንና የአዶልፍ ሂትለርን ሥልጣን መውጣትና መወደቅ እንመለከታለን፤  የመለስ ዜናንና የኢሳያስ አፈወርቂን ሥነ ልቦናን እንመረምራልን፤ የወያኔን የፖለቲካ ቅዠትና የግብረ አበሮቹን ሚና በሰፊው እንወያያለን፤ ከዚያም ወደ ተነሳንበት አርዕስት ተመልሰን ቅሬታን ለማስወገድ እስክ መጨረሻው ድረስ ውይይታችን ይቀጥላል ፤ የዉይይታችን መድረሻው ስለማይታወቅ ከአስተያየት ተቆጥበን እስክመጨረሻው ብንወያዩ ለተከሰተው ችግር መፍተሔ ሊሆን ይችላል ብሎ በማሰብ ነው፤ምን ይታወቃል እስምምነትም ላይ ሊደረስ ይችል ይሆናል፤ መለስና ኢሳያስ ያፈሩስትን ቤት ምሶሶና ግድግዳ ሆነው ደምህ ደሜ ነው ያሉት  ወንድማማቾች ይሰሩታል፤ድርጅቶች በአንድነት በመሆን ድሉን ለማስገኝት ከኦሮምና  ክአማራ ተጋዳዮች በስተጅርባ መቆም ታሪካዌ ግዲታ ነው፤ ኢትዮጵያ የፈርሰው ቤቷ በልጆቿ ተመልሶ ይሰራል፤ ኢትዮጵያ የሁሉም ጎሳ እናት ነች ፤ መንግሥቷም  ተመልሶ  በልጆቿ  ይመሰረታል፤ አዲሲቱ ኢትዮጵያ  በሕዝብ ለሕዝብ በሚመረጠው ብሒራዌ ሽንጎ ይቋቋማል።

የመሳይ ከበደና የሬኔ ለፎርት ወግ – ታሪኩ ውብነህ ጌታነህ

December 27, 2016 22:13

ክፍልሰወስት

የአድዋ ጦርነት፤ የአፍሪቃ ሰብአዌነት፤ ለሰው ልጅ ሕሊናዌነት

[ማሳሰቢያ፡ በዚህ አርዕስት ላይ የምንወያየው የአድዋ ጦርነት ለአፍሪቃዉያን ሰብአዌንትና ለሰው ልጅ ሕሊናዌነት ያደረገዉን መስተዋጽኦ ነው። የአድዋ ጦርነት ወይም የአፂ ሚንልክ ታሪክ እዚህ ሊጻፍ እንደማይቻል ለአንባቢ በቅድሚያ ማሳወቅ ተገቢ ነው።  የአድዋ ጦርነት በውጭ አገር የታሪክ ሊሂቃን በመጠኑ ተጽፏል። ግን ታሪክ በአገሩ ሊቃን ሲጻፍ የተልየ መልክ ይሰጠዋል፤ ይህም ማለት ጸሐፊዉ ከሕብረተሰቡ አካል ስለወጣ ባህሉን፤ ዘየዉን፤ አስተሳሰቡን፤ አመለካከቱን፤  አኗኗሩን፤ በአጠቃላይ ሕሊናዉነቱን በቅጡ ያንጸብርቃል፤ ለምሳሌ እንግሊዝ የአገሩን ታሪክ የውጭ ሰው እንዲነካበት አይፈልግም፤ በዩነበርሲቲም ውስጥ ታሪክ እንዲያጠኑ የሚመለመሉ ተማሪዎች በአጠቃላይ ትምህርታቸው ከፍተኛ ዉጢት ያላቸዉን ተማሪዎች ነው። ከውጭ የመጡ ተማሪዎች የሚነገራቸው የራሳቸዉን ታሪክ እንዲማሩ እንጂ ስለ እንግሊዝ አገር ተምረው የእንግሊዝን ታሪክ እንዲጽፉ አይደረግም።  የእንግሊዝ ታሪክ እነሱ እንደሚሉት  በጣም የተከበረና የተለየ ነው፤ “የታላቁ የእንግሊዝ ታሪክ” ተብሎ በክፍተኛ ደረጃ ይቀመጣል፤ “ታላቋ ብሪታንያ” ትባላለች፤ “ፅሐይ በእንግሊዝ ግዛት አትጠልቅም”” ይላሉ። ይህም ማለት አንድ ሶወስተኛዉን የዓልም ክፍልን በቅኝ ግዛታቸው ስለአደረጉ እንግሊዝ አገር ጀምበር ስትጠልቅ ቅኝ ግዛቷ ላይ ትወጣለች። የሊላዉን አገር ታሪክ በፈለጉት ዓይነት ጽፈው ለቅኝ ተገጆቻቸው ያስተምራሉ፤ ለዚህ ነው “የታሪክ አባቶቻችን” እየተባሉ የሚጠሩት፤ ይህ አይነት አባባል እኛም አገር የተለመደ ነው፤ጥገኝነቱም  የጠበቀ ስለሆነ እነሱ ያሉትና የጻፉት ከአልሆነ  በዚህ አይነት ቢቀርብ  ተቀባይነት አይኖረዉም፤ትልቅ ያለመታደል ነው፤ ለዚህም መረጃ የሚሆነው የሚሰጠው አስተያየት ነው ። እንግዲህ እዚህ ጽሑፍ ላይ የምንመለከተው ምኒልክንና አድዋን በአንድነት አድርገን ነው። ምኒልክ ከአድዋ ተነጥሎ ሲታይ ብዙ በደል እንደሰራና ሕዝብን በኃይል አስገድዶ እንደገዛ “የታሪክ አባቶቻችን” በምንላቸው የተጻፉትን በማየት  “አድዋ የአፍሪቃ ድልና አለኝታ” የሚለዉን እንገድፈዋለን። “የከፋፍለህ ግዛ” የፖለቲካ ስልት ክግንዛቤ ስለአላስገባነው አገር፤ ሰንደቅ ዓላማ፤ አንድነት የሚለዉን ማሰሪያ አንቀጽ ተሰባብሮ እንዳለነበረ ሆኗል፤  ይህንን በተመለከተ በዚህ ጽሑፍ ዉስጥ ያስከተለዉን ጉዳት እንመለከታለን።

ይህንንም “ሁኔታ” የምንመለከተው ከታሪክ ቀንጨብ እያደረግን ነው፤ ለአደዋ ጦርነት ዋና መንስኢ የሆነው በክፍል ሁለት ላይ እነደተጻፈው የ1884-5  አፍሪቃን ለመከፋፈል በተደረገው የበርሊን ጉባኢ ነበር። በዚህ ጉባኢ ላይ ተካፋይ የነበረችው ኢጣልያን በወቅቱ ምንም የቅኝ ግዛት የሊላት አገር ስለነበረችና ግዛቷን በጋሪባልዲ አማካይነት ታላቋን ኢጣልያንን መንግሥት በ1860 ስለአስተባበረች የቅኝ ግዛት ባለቤት መሆን አስፈላጊ ከመሆኑም በላይ ሲሲልና በስተደቡብ የሚገኘዉን ሕዝብ አንድ ስላደረገች በቂ ኃይል ስለአገኘች ነበር። በወቅቱ የነበረው  የኢጣልያንን የቅኝ ግዛት ፍላጞትን እጅግ ክፍ ያደረገው የቢልጅያን ንጉሥ ሊዮፖልድ ነበር፤ አንድ ግለሰብ ከአንድ ትንሽ አገር ተነስቶ ትልቅ የቅኝ ግዛት አፍሪቃ ዉስጥ ሲመሰርት እንዲት ታላቋ ኢጣልያን የቅኝ ግዛት አይኖራትም  በማለትና ከሊሎች አውሮፓውያን አገሮች በመፎካከር ነው።  ሊላው ከፋፍለህ ግዛ [Divide et imperia] የተባለዉን የአውሮፓውያን ዕቅድ ስራ ላይ አውለው በጥንታዌነቷ ታዋቂ የነበረችዉን የሮማን ግዛት መልሶ  በተምሳሊቷ ታላቋን የኢጣሊያን ንጉሠ ነገሥት  መንግሥት ለማቋቋም ነበር። አውሮፓውያኖች የራሳቸዉን ጎሳዎች አስተባብረው አንድ አገር፤ አንድ ሰንደቅ ዓላማ ፤ በጎሳ ሊከፋፈል የማይችል ሕብረት ከፈጠሩ በኋላ [Divide and conquer”] አፍሪቃን በጎሳ ከፋፍለው ለነሱ ታላቅነት ተገዥ ለማድረግ እንደሆነ ግልጽ ነው። ይህን “ሁኔታን” የአፍሪቃ ወገኖች ግንዛቢያችው ዉስጥ ስሊለ በጎሳ መለያየቱን እንደ በጎ ስራ አድርገው ይመለከቱታል፤ የኢትዮጵያ የዘውግ አቀኝቃኞች በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ለጎሳቸው ተቆርቋሪ ሆነው የሚያካሂዱት የፖለቲካ  ትልቅ ነገር የሰሩ የሰሩ እየመሰላቸው ነው። የፕሮፌሰር መሳይ ከበደ “ወግ” ከዚህ አያልፍም፤ ፍልስፍናቸዉም “የዘውግ አመሰራረት ስር ነቀል ስለሆነ ሊቀለበስ አይችልም” ነው የሚሉት፤ ይህ የመለስና የኢሳያስ ራዕይ ነው። እንግዲህ በዚህ ውይይታችን የምንመለከተው የአፍሪቃን የጎሳ መለያየትና የአውሮፓን ሕብረት መፍጠር ይሆናል። ውይይታችን መልካም እንዲሆንና ለመማር ጥሩ “ሁኔታ” ለማመቻቸት የምንሰጠው አስተያየት በተሰጠው መልዕክት ላይ እንጂ በመልከተኛው ላይ መሆን የለበትም፤ አንባቢ አስተያየት ለመስጠት ፍጹም የሆነ መብት አለው፤ ውይይቱ  ግን አንባቢው በስጠው  አስተያየት ላይ ከአቶኮረ ዉጢት አልባ ሆነን መማማር አንችልም፤ የወያኔ ዋናው ስራው ተሽቀዳድሞ በመጀመሪያ አፍራሽ  አስተያየት መስጠት ነው። ለዚህ አፍራሽ አስተያየት አንባቢ ቦታ መስጠት የለበትም ፤ ይህ የተባለበት ምክናያት በሁለተኝው ክፍል ላይ የተሰጠዉን በማየትና በርከት ያሉ አንባቢዎች በላኩሉኝ መልእክት መሰረት ነው፤ መልካም ውይይት]።

መቅድም

ታሪክ ጸሐፊዎች እንደሚሉት የአድዋ ጦርነት የተከሰተው ኢትዮጵያና ኢጣልያን በተፈራረሙት ውሎች ምክናያት አይደለም፤ የዉሎቹ ፊርማ ሰበብ ነው እንጂ  ለጦርነቱ ምክናያት አልነበረም ፤ዉል ተፈረመ አልተፈረም ኢጣላያን የግድ ቅኝ ግዛት አፍሪቃ ዉስጥ ማግኝት ስለአለባት ጦርነቱ አይቀርም ነበር፤ ለዚህም በመረጃነት መቅረብ ያለብት  የ1884/85 በርሊን ላይ በተደረገው ጉባኢ ላይ ማን ምን ማግኝት እንዳለበት የተደረገው ስምምነት ነው። ይህ ከተባለ በኋላ ታሪኩ ቅደም ተከተሉን ይዞ ይቀርባል። የሚኒልክና የአድዋ ጦርነት ታሪክ ብዙ ቅድመ “ሁኔታዎች” ስለአሉት በአጭሩ ይጠቀሳሉ፤ እዚህ ላይ አንባቢ ታሪኩን በቅጡ እንዲመለከተው የታሪኩን አቀማመጥ በቅድሚያ ማስረዳት አስፈላጊ ነው። ታሪክ ፈጣሪ አለው፤ ያ ታሪክ ፈጣሪ አስቦበትም ሆነ ሲያስብበት፤ በአጋጣሚም ሆነ በስሊት “ሁኔታው” ሲመቻች የታሪክ ሂደቱ ይጀምራል፤ በሂደቱ እያለ ታሪክ ሊሆን አይችልም፤ መድረሽዉም ምን እንደሆነ ስለማይታወቅ ታሪካዌ ሂደቱን ሳይጨርስ ሊጻፍ አይችልም፤ ታሪክነቱ የሚታወቀው ቢያንስ ከሶወስት ትውልድ በኃሏ ነው። ለምሳሌ ዶሮዋን ተመልከት፤ እንቁሏሏን እንደጣለች ጯጩቶቻ አይፈለፈሉም፤ የሚፈለፈልበትን “ሁኔታ” ታመቻቻለች፤ ፉጡራዌ ሂደትን ተከትላ የፈለፈለችውን  እንቁላል የሚያስፈልገዉን ሙቀት በመስጠት ጯጩቹ  እንዲፈለፈሉ ታደርጋለች፤ ይህ ፉጡራዌ ሂደት ነው፤ አንባቢ በድጋሜ መመልከት ያለብት “ሁኔታን” ነው፤ ዶሮዋ የምትወልደዉን እንቁላል በየግዜው ከተበላባት ጯጩቾቻን የምታገኝበት “ሁኔታ” አይኖርም፤ “ሁኔታ” ወሳኝ ነው። በተጨማሪ አንባቢ በትኩረት ማወቅ ያለበት የታሪኩን  የአጻጻፍ ዘዴ ነው። ሁለት ዓይነት ታሪክ አለ፤ በተለምዶ የሆነ ያልሆነዉን ተጽፎ ታሪክ ሆኖ ሲቀርብ የሚያስክትለው ጥፋት ከፍ ያለ ነው፤ ታሪክ የሕብረተሱቡ ያለበትን “ሁኔታ” የአለፈዉን ስሕተት የሚያበት መስተዋት ስለሆነ ከዚህ ታሪክ ከአልሆነ ታሪክ የሚያገኝው ትምህርት ሳይሆን ጥፋትን ነው። የሁለትኛው  ታሪክ አጻጻፍ በታሪክ ጸሐፊዎች ሲጻፍ ልዩ ቦታ ይኖረዋል፤ የታሪክ ቧለሟዩም ትልቅ ኃላፊነት ስለአለበት የተከሰቱትን “ሁኔታዎች” ከነባር ቅርስ ጋር እያመሳከረ አፈ ታሪኩና ንግርትን እያገለለ ምክናያቶችን እየመረመረ የሕብረተሰቡን ሕሊናዌነት ከነባር “ሁኔታ” ጋር እያገናዘበ በጽሑፍ ይመዘግባል፤ ቅድመ “ሁኔታ” እንዲት እንደተፈጠረና ለሕብረተሰቡ ያስገኘውን ጥቅም ወይም ጉዳት በሂሳብ ተሰልቶ በሚዛን ተመዝኖ ይቀርባል፤  ለዚህ ነው “ታሪክ የሕብረተስብ መስተዋት” ነው የተባለው፤ ደግሞም “ስህተቱን ከታሪክ ያልተማረ ሕበረተሰብ መጨረሽው ጥፋት” ነው የሚባለው። እዚህ ላይ  ከፕሮፌሰር መሳይ ከበደና ከሚስተር  ሬኔ ለፎርት ጋር ትንሽ  ቆይታ ከአደረግን በኋላ ወደ ሚኒልክና አድዋ  ጦርነት እንገባለን፤ ከፕሮፌሰሩ ጋር መወያየት ያስፈለገበት ጉዳይ እሳችውና የዘውግ አቀኝቃኞች ሚኒልክን የሚመለከቱት በተለምዶ የሚነገርዉን አፈ ታሪክና ጥራት በሊለው የዘውግ ፍልስፍናን መሰረት በማድረግ ነው፤ ነገር ግን ቅድመ ሁኔታን ተወያይተን እስምምነት ላይ የማንደርስበት ምንም ምክናያት አይኖርም፤ ግን ሚስተር ለፎርትን እዚህ ውይይት ላይ ማቆየቱ አግባብ አይደለም፤ ምክናያቱም ጽሑፋቸው ከኢትዮጵያ ታሪክም ሆነ የፖለቲካ “ሁኔታ” ጋር ምንም ግንኙነት ስለሊለው ነው፤ ጽሑፋቸው ምናልባት ለብጎ አድራጊ አገሮች ወይም  ለልማት ገንዘብ አበዳሪ ባንኮችና  [ለዓለም ባንክ] ለአትራፊ ነጋዴዎች  ያለዉን “ሁኔታ” ሊያስረዳ ይችል ይሆናል፤ ስለዚህ እዚህ ላይ  ሚስተር ለፎርትን እንሰናበታቸውና ውይይታችን ከፕሮፌስሩና አክራሪ ብሕሬተሰበኞች ከሆኑ ወገኖቻችን ጋር ይሆናል፤ በተረጋጋ መንፈስና ቅን በሆነ ልቦና ከተወያየን  በኃሏ በታሪካዌ ሂደት አንድ አገር፤ አንድ ሰንደቅ ዓላማ፤ አንድ በሒር የሚባልበት “ሁኔታ” ሊፈጠር ይችላል፤ የውውይቱን መነሻና መድረሻ  ስለማናውቀው በትዕግስት እንጠብቀው። ከሁሉ አስቀድመን ለዉይይታችን ከታሪክ እየተቀነጠቡ የሚቀርቡትን ታሪካዌ “ሁኔታዎች” የሚመረምር መላ ምት እንመለከታለን፤ የመላ ምቱ መሰረት ቋንቋ ነው፤ ቋንቋው በሚገባ ስለዳበረ “ልብ ወለድ” ወይም “አፈ ታሪክ” ወይም “ንግርት” ወይም እንደ “ተረት” የሚነገሩትን ከመረጃ ጋር የሚቀርቡትን ታሪካዌ ሂደትን ለይቶ ለማየት ያስችላል፤ ለምሳሌ በዚህ ድረ ገጽ ላይ ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ እንዲት እንደገባ የሚመረምር በቋንቋ የዳበረ መላ ምት እንመልከት፤

እንግዲህ  አንባቢ እስከ አሁን  ድረስ በአደረገው የውውይት ጉዞ በቂ የሆነ ታሪካዌ ግምገማና “ሁኔታን” መርማሪ [ሐታቲ] መላ ምት ስለ አዳበረ ከዚህ በላይ የተጻፈዉን “ሐተታ” [ምርምር] “ሐትቶ” [መርምሮ]  በዋቢነት የቀረበውን ጽሑፍ ክርስትና ወደኢትዮጵያ ለመግባቱ መነሻ “ታሪክ” መሆኑንና ያለመሆኑን ሊመረምር [የሐትት] በቂ “ችሎታ” ይኖረዋል ብዮ እገምታለሁ፤ ይህ ግምት ነው፤ሊሆንም ላይሆንም ይችላል፤ እዚህ ላይ ዉይይታችን ከፍ ባለ ደረጃ እንዲያድግ በማለት “ሐተተ” የሚለዉን የግዕዝ ቃል ግሥ  እርባታዉን ማሳየት ለአንባቢው ምርምር ይረደዋል፤ እንግዲህ  “ሐተተ” የሚለዉን አርእስት ወስደን የግሡን እርባታ [እርባ ግሥ] እንመልከት፤ “ሐተተ” [መረመረ] “የሐትት” [መረመረ] “ይሕትት” [ይመረምር] “ሐቲቶት” [መመርመር] “ሐታቲ” [የመረመረ] “ሐታቲያን” [የመረመሩ] “ሐታቲት” [የመረመረች]  “ሐታቲያት” [የመረመሩ] “ሕቱት” [የተመረመረ] “ሐታቲ” [መርማሪ] እያለና በገቢር በተግብሮ እያሰረ በአር ዕስት ተከፍሎ በአዕማድ ተጠቅሎ በዕቢይ በንዕስና በደቂቅ አንቀጽ እየገባ “ሁኔታን”  የሚመረምር የግሥ እርባታ ነው። ቋንቋው በሚገባ ዳብሯል፤ አገር ፤ መንግሥት ፤ ሕብረተሰብ  ትምህርት ቤት ፤ ቤኖር ከዚህ የበለጠ “ሁኔታን” መርማሪ መሳሪያ የለም። ከዚህ በላይ የተጻፉቱን “ቅድመ “ሁኔታዎች” አሉ ብለን በመጠኑ ምርምራችንን እንቀጥል፤ ክርስትና ወደኢትዮጵያ ገባ በተባለብት ዓመት [334 ዓ.ም] ነበረ የተባለዉን በዕብይ አንቀጽ እንመዝግባቸው፤  “አገር” ፤ “ወደብ”  ፤ “ቤተመንግሥት” ፤ ቤተ መጻሕፍት” ነበሩ እንበል፤ በአንጻሩ ደግሞ በንዕስ አንቀጽ ደረጃ “ነጋዴ”  “ወጣቶች”  “ሽፍቶች” ነበሩ እንበል፤ እንግዲህ በዓብይና በንዕስ አንቀጽ ያሉትን ስንመረምር “በገቢርና”  “በተገብሮ” የተደረጉትን  ያለምንም ስህተት ማግኝት እንችላለን፤ ኢትዮጵያ የሚባል አገር አለ፤ ወደብ ከአለ የግድ የባሕር ኃይል አለ ማለት ነው፤ በወደቡ ላይ የሚተላለፍ ንግድ ከአለ ፅጥታ አስካባሪ አካል አለ፤ እንግዲህ በዋነኛነት የምናየው “ቤተመንግሥቱንና” ቤተ “መጻሕፍት” ነው፤ እዚህ ላይ ጥያቄው በምን አይነት “ሁኔታ” ነው እነዚህ ሆለት የሶርያን ወጣቶች የቤተመንግሥትና የቤተ “መጻሕፍት” ሃላፊ የሆኑት? በተለይ “መጽሐፍት” ቤቱ የሚነግረን በጽሑፍ የተጻፉ ጽሑፎችን የያዘና ታላቅ የሥነ ጽሑፍን ዕውቀት የተከማቸበት ቦታ መሆኑን ነው፤ ወጣቱ ፍሬሚናጦስ [Frementius] በምን ዕውቀቱ ነው ለዚህ ስራ የተመረጠው? ቋንቋዉን አይችልም ፤ ስለ ቤተ መጻሕፍት ቤትም የሚያቀው ነገር የለም ። በምን “ሁኔታ” ነው ፍሬሚናጦስ [Frumentius] አንድ የባሕር ኃይልና ወደብ ያለው አገር የቤተ መንግሥቱ ዋና አማካሪና ደግሞም የወጣቱ ንጉሥ እንደራሴ ሊሆን የቻለው? ይህንን “ሁኔታ” ሊፈጥር የሚችል ምክናያት አይኖርም፤ በተጨማሪ ለታሪኩ መጀመሪያ እንዲሆን የተሰጠው ቀን 334 ዓ.ም የተባለው ዘመን የፈጠራ እንጂ በዕውነት በዘያ ዘመን አንድ ሃይማኖት ተቀባይነት አግኝቶ  በአንድ ዘመን ወይም ዓመት ግዜ የነበረዉን ቤተ መቅደስ በከመ ቅስፈት ቤተ ክርስቴያን ብሎ ሊለዉጥ አይችልም፤ ስለዚህ በመረጃነት የቀረበው የልብ ወለድ “ታሪክ” እንጂ “ሁኔታ” ፈቅዶ በተግባር የሆነ “ታሪክ” አይድለም። ነባር ቅርስ እያለ ምን አልባት ሳይሆን  አይቀርም በሚል መላ ምት የተጻፈ ታሪክ ነው። እዚህ ላይ ክርስትና መግባቱንና ያለመግባቱን ሳይሆን በምን አይነት ሁኔታ እንደገባ ማወቅ አስፈላጊ ነው ምክናያቱም የሕብረተሰቡ ታሪክ ስለሆነ። መነሻ ፤ መንደርደሪያ፤ መድረሻ የሊለው ታሪክ ሊሆን አይችልም፤ የሕበረተስቡንም ሕሊናዉነት ምን እንደሆነ አይገልጽም፤ ከክርስትና በፊት ለብዙ ዘመናት መቅደስ ያለው አገር፤ ሥነ  ጽሑፉ ዳብሮ በመጻሕፍት ቤት የተለያዩ ጽሑፎችን ያከማቸ ሕብረተሰብ በአንድ ሶርያን ወጣት አማካይነት ክርስትናን ተቀበለ ለማለት ያስቸግራል [ሙሉ ታሪኩን ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ይመልክቱ–የጥንታዌት ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አቅጭር ታሪክና ስነ ሥርዓት፤ ክፍል አራት  December 19, 2016]

እዚህ ላይ ሰፋ ያለ  መግለጫ የተሰጠበት ምክናያት የኢትዮጵያ ታሪክ “ተረት” ነው፤ ከመቶ ዓመት በፊት ኢትዮጳያ የምትባል አገር የለችም ነበር፤ “ሚኒልክ በኃይል የደቡቡንና የሰሚኑን ሕዝብ ቀጥቅጦ”  የፈጠራት አገር ነች በማለት ንግርትና አፈ ታሪክ እንደ ታሪክ ሆኖ የሚጻፍበትና  የሚነገርባት አገር ስለ ሆነች ነው፤ በእንደዚህ አይነት “ሁኔታ” ላይ ሆኖ ታሪክን ከነባር ቅርስ ጋር እያገናዘቡ ለመጻፍ አስቸጋሪም ቢሆንም ጢኔኛ ሆኖ ለሚወለደው ትውልድ ማሳወቅ ታሪካዌ ግዲታ ነው፤ የዘውግ አቀኝቃኞችና ጥገኛነትን አክራሪዎች የታሪካችንን መላ ምት የተለየ መለኪያ ያስፈልገዋል፤ የታሪክ አባቶቻችን አላሉትም” እያሉ እንድሚያዋዱቁት አውቀን ከባሕላችን በመነጨውና በቅጡ በዳበረው ቋንቋችን ለልጅ ልጆቻችን የታሪክ ቅርሳችንን እናስቀምጣለን። እንግዲህ የመላ ምታችንን ብቁነት ከአስተካክልን በኃላ የምኒልክንና የአድዋን ቅድመ “ሁኔታውች”  ከታሪክዌ ሂደት ላይ ቀንጠብ እየተደረገ ይቀርባል።

ምኒልክና አድዋ የቅድመ “ሁኔታዎች” ዉጢት ናቸው። የሰሎሞናዌ ሥረወ መንግሥት በዛጓው ቢተ አገዛዝ ከተወሰደ ከመቶ ዓመት በኃላ በይኩኖ አምላክ በ1270 ዓ ም  ተመልሶ ሲመሰረት የኢትዮጵያ ግዛት ከአትበራ እስክ ፑንት መሆኑን ነባር ቅርስ ይመስክራል፤ በአፈ ታሪክ የሚነገርለት ፕሬሰተር ጆን [Prester John] የሚባል ንጉሥ እንደ ነበር በሞላ አውሮፓ ይነገር ነበር፤ ነገር ግን ይህ ንጉሥ  የኢትዮጵያ ወይስ የሕንድ  ይሁን በእርግጠኝነት የሚታወቅ ነገር የለም፤ ንግርት ነው፤ ሆኖም ይኩኖ አምላክ በ1270 እስከ 1277 በአለው ግዜ ዉስጥ ከክርስቲያን ተጋዲያዎች [Crusaders] ጋር ለመገናኝት ሞክሮ እንደነበር ይነገራል፤ ከንግርት በላይ ምንም ተጨባጭ ቅርስ የለም። ነገር ግን አምደ ጽዮን [1314—44] ግዛቱን እስከ ቀይ ባሕር አስፋፍቶ በቁጡጡሩ ስር እንደነበር የሚያስረዳን በቂ መረጃው ልጁ ሰይፈ አዕራድ [1344—77] ከክርስቲያን ተጋዳዮች ግንኙነት አድርጎ ኢትዮጵያዊያኖችን በኢየሩሳሊም  በቂ ድጋፍ ለመስጠት አስፍሮ እንደነበርና ይዞታዉም በኢትዮጵያ ቅርስነት እስከ አሁን ድረስ እንዳለ መሆኑን ነው። የኢትዮጵያ ግዛትም ከንጉሥ ዳዌት እስከ ዘርዓ ያዕቆብ ድረስ ተስፋፍቶ እንደነበር ታሪክ ይነግረናል፤ ነገር ግን በልብነድንግል ዘመነ መንግሥት [1508-40] የኢትዮጵያ ግዛት ቀስ በቀስ እየቀነሰ ሂደ፤ ለዚህም ዋነኛ ምክናያቱ በዳዌትና  በልጁ ዘርዓ ያዕቆብ ግዜ የአንድ ሰንበት የሁለት ሰንበት ጥያቄ በቤተ ክርስቲያኑ ዉስጥ ለብዙ ግዜ ሲያከራክር ስለነበረና ደግሞም የኢትዮጵያ መንግሥት ከክርስታያን ተጋዳዮች ጋር መተባበርና በኢየሩሳሌም ዉስጥ ድጋፍ ሰጭ ኃይል ማስቀመጥ በመካከለኛው ምስራቅ ለሚገኙ የእስልምና እምነት አስፋፌዎች አሳሳቢ ጉዳይ ሆኖ ስለ አገኝት የኢትዮጵያን ግዛት ቀይ ባሕርን፤ ኢርትራን፤ ጂቡቲን፤ በአጠቃላይ የሕንድ ውቃያኖስ አዋሳኝ የሆኑትን ወደቦች በመያዝ እስልምና ወደ መሐል አገር እንዲገባ በማድረግ ለግራኝ መሐመድ መነሳት ትልቁን መስትዋጽኦ አድርገዋል። እዚህ ላይ ለአንባቢ ሳይጠቀስ የማይታለፍ ታሪክ ቢኖር ለእስልምና ሃይማይኖት መቋቋም ኢትዮጵያ ትልቁን ሚና መጫወቷን ነው፤ በመጀመሪያ ነቢዩ መሐመድ በሕጻንነቱ ወላጆቹ ስለሞቱ እንደ እናት ሆና ያሰደገችው ባሕርዋ የምትባል ሲት ነበረች፤ ታሪኩ እንዲህ ነው፤ በዘመኑ የአረብያን ግዛት ኢትዮጵያ ታስተዳድር ነበር፤ ነገር ግን የባሕር ወደቧና የጦር ኃይሏ በሮማን መንግሥት ኃይል እየቀነሰ ስለመጣ የግድ የአረብን ግዛት መተው ስለነበረባት ኢትዮጵያውታ ባሕርዋ ጥቂት ከቀሩት  ኢትዮጵያዉያን አንዷ ነበረች፤ በዚህ አጋጣሚ የስድስት ዓመቱን ወጣት እንደ እናት ሆና አሳድገዋለች፤ በኃሏም ለአቅመ አዳም ደርሶ ነብይ ሲሆን በኢትዮጵያ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ተደርጎለታል፤ ይህውም የየጎሳው ባላባቶች ነቢዩን በማሳደድ ላይ በነበሩበት ወቅት ኢትዮጵያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት እምነቱን በነጻነት እንዲከተል አድርጋለች፤ ነቢዩም የእስልምና ሃይማኖቱን ሲመሰርት በተነሳው ጦርነት ምክናያት በመጀምሪያ እስልምና የተቀበሉትን ለደሕንነታቸው ብሎ የላካቸው ወድ ኢትዮጵያ ነው፤ ይህ አፈ ታሪክም ንግርትም አይደል፤ እውነተኛ ታሪክ ነው፤ ለዚህም በመረጃነት ሊቀርብ የሚገባው ነቢዩ ለተከታዮቹ ኢትዮጵያ ባለውለታና ታላቅ ታሪካዌ አገር ስለሆነችና ለሰው ልጅ ሁሉ ተምሳሌት ነችና እንድትነኳት በሎ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ለስምንት መቶ ዓመት የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ኢትዮጵያን አልነኩም፤ ይህንን የማያውቅ የአስልምና ሃይማኖት አባት አይኖርም።

እንግዲህ አንባቢ ይህ ውይይት በተሟላ ታሪክ  ላይ ሳይሆን ቀንጠብ እየተደረገ የቀረበ  የዘውግ አቀኝቃኞችንና የጽንፈኛ ብሒረተሰበኞችን ወግ ለማስተካከል  መሆኑን ማወቅ ግዲታ ነው፤ የዘውግ አቀኝቃኙን ፕሮፌሰርና አክራሪ ብሒረተሰቦኞችን አስተካክላለሁ ማለት ዘበት ነው፤ ከዚያም አልፎ በሰማይ ላይ እንዳለችው ላሟን መሆን ነው። ነገር ግን የኢትዮጵያን አንድ ሕብረተሰብ እንደ ተለያየ  ሕብረተሰበዎች አድርገው ስለበከሉት ሕዝብ ይህንን አፈ ታሪክና ተረት በታሪክ አምድ አድርገን  ለማስተዋወቅና ለማስተካከል ነው፤ ሰሚና አንባቢ ከተገኝ የሕብረተሰባችንን አንድ ነት ለማዳን የተደረገ ሙክራ ነው። ደግሞም ከዚህ በፊት እንደተጠቀሰው ምን ይታወቃል በውይይት የማይፈታ ነገር የለም፤ ምናልባት ተቀራርበን  ታሪካችን በዉጭ ኃይል እንደተጻፈው ሳይሆን እውነተኛዉን ታሪካችንን መሰረት አድርገን ቅሪታችንን  እንፈታው ይሆናል፤ እዚህ  ላይ ትልቁን ጥንቃቄን ማደረግ ያለብን አሁን ባለው ሥርዓት ተጠቃሚዎችና ጥገኝነትን በሚያጠብቁ  ልሂቃን እንዳንወናበድ ነው።  በምንባቡ እንዳንሰላች የሶወሰትኛው ክፍል እዚህ ላይ ይቆማል። ከላይ እንደተጠቀሰው የሚስተር ሬኒ ለፎርት ወግ እዚህ ላይ ስልተጠናቀቀ የአራተኝው ክፍል አርዕስት የሚሆነው “የመሳይ ከበደና የጽንፈኛ ብሒረተሰበኞች ወግ”  ይሆናል። በአራተኛው ክፍል የምንወያይበት አርስዕስት “የቀይ ባሕር መወሰድ፤ የእስልምና ሃይማኖት መስፋፋት፤ የግራኝ መሐመድ መነሳት፤ የኢትዮጵያ ግዛት መፈራረስና የልብነ ድንግል መንግሥት መዳከም፤ የዘመን መሳፍንት ዘመን፤ የሚኒልክ ዘመነ መንግሥት ይሆናል። በተጨማሪ ብዙ ክፍሎች ስለሚቀሩ አስተያየቶች ቢቆዩ ይመረጣል፤ ሆኖም እዚህ በቀረበው ላይ መስተካከል አለበት የሚሉት ከአለ ለመማር ስለሆነ ይጠቅማል ብዮ እገምታለሁ። ትምህርታዌ ውይይት እንዲሆንልን እመኛለሁ።

 [ማሳሰቢያ፡ ምኒልክና አድዋ ብዙ ቅድመ “ሁኔታዎች” ስለ አሉት ታሪኩን ቀንጠብ እያደርግን ተከስተው የነበሩትን “ሁኔታዎች” አጥብቀን መመርመር አስፈላጊ ነው፤ የታሪክ አጻጻፍ መላ ምት “ይባላል” ወይም “ሳይሆን አይቀርም” ተብሎ እንዲጻፍ አይፈቅድም፤ “በምን አልባት” እየተባለ በተለምዶ የሚጻፍ አፈ ታሪክና ንግርት ነው። የፕሮፌሰሩና የጽንፈኛ ብሒረተሰቦኞች ወግ የተመሰረተው በአፈ ታሪክና በንግርት ነው። አፈ ታሪክ የሚስተካከለው በንግርት አይደለም፤  ታሪክን ታሪክ የሚያደርገው “ሁኔታ” ተመቻችቶ በተግባር የተፈጸሙ ነገሮች በቅርስነት ሲገኙ ነው። ለምሳሌ ቀይ ባሕር የኢትዮጵያ ወደብ ነበረች፤ ይህ ወደብ የኢትዮጵያ ቅርስ ነው፤  የቱርክ ኦቶማን ኃይል ወስዶ ሕዝቡን በግድ እስልምናን እንዲቀበል ቢያደርግ የሕዝቡንና የወደቡን ኢትዮጵያዌነት አይቀረዉም፤ ምክናያቱም ቅርሱ የኢትዮጵያ ስለሆነ፤ ሆኖም ከግዜ ብዛት የሕዝብ ሥነ ልቦና ከግዞት ብዛት ስለሚለወጥ ታሪክ እንዳልሆነ ሆኖ ይነገራል፤ ይህም የሚሆንበት ምክናያት ገዥው በተገዥው ላይ በሚያሳድረው የአእምሮ ተጽኖ ነው፤ ለምሳሌ የጀርመን ናዚ ኃይል በአይሁዶች ላይ ያደረገው ተጽኖ ምን ያህል የአእምሮ ቀዉስ እንዳመጣ እንመልከት፤ በሂትለር ትዕዛዝ በእስር  ቤት ለተከማቹት አይሁዶች ምግብና መጠጥ እንዳይሰጣቸው ስለከለከለ የሰው ልጅ ሥነ ምግባራቸው ዝቅ ብሎ እንደ እንስሳ  ሆነው እንደነበረ የቅርብ ግዜ ታሪክ ነው። ወያኔ በአማራው ሕዝብ ላይ ያደረገው የአረመኔ ስራ “ አማራ የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ይሁዲ” በሚል አርዕስት ተብሎ የተጻፈዉን በዚህ ድረ ገጽ ላይ መመልከት ያለዉን  “ሁኔታ” በሚገባ ያስረዳል። ይህ “ሁኔታ” ሊከሰት የቻለው በአፈ ታሪክና በንግርት ነው፤ ደግሞም “ሁኔታው” እንዲት እንደተፈጠረ ተመልከት፤ “የኢርትራ ሕዝብ ከየት ወደ የት” “የአማራ ሕዝብ ከየት ወደ የት” ተብሎ በዘውግ አቀኝቃኞች የተጻፈ ልብ ወለድ ታሪክ ነው።  ከሁሉ በላይ የሚያስገረመው ይህን “ሁኔታ” ፈጣሪ ኃይል ማንም ልብ ብሎ የተመለከተው የለም፤  ከዚህ በላይ ንዝሕላልነት የለም፤  ለአማራም ሆነ ለኦሮም ጥፋት ዋና ተጠያቄው ለባንዳዎች አሽከር ሆነው የሚያገለጉሉት  ሆዳም አማራና ሆዳም ኦሮሞ ናቸው፤ የዘውግ አቀኝቃኞችና የኦርቶዶክስ ካድሬ ካህናትም ለወያኔ መሳሪያ በመሆን እያግለገሉ ነው፤ ይህንን “ሁኔታ” የሚቀይር ኃይል መከሰት አለበት፤ ቅድመ “ሁኔታን” የሚቀይረው አዲስ “ሁኔታ” ነው፤ እንግዲህ ጥያቄው አዲሱን “ሁኔታ” ማነው የሚቀይሰው? ይህን ለአንባቢ የሚተው ነገር አይደለም፤ የዘውግ አቀኝቃኞች፤ ጽንፈኛ ብሕረተሰቦኞች፤ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ የቤተ ክርስቲያን ምዕመን፤ አንድነት ፈጥሮ ኢትዮጵያ አገራችንን ከወንበዴዎችና ከአጋዜ ነፍሰ ገዳዮች ነጻ ማውጣት ታሪካዌ ግዲታ ነው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሙሉ በሙሉ ተነስቷል፤ በጎበዝ አለቃው የብሒራዌ ሽንጎ እየመረጠ ነው። መንግሥት የሚቋቋመው በሕዝብ ለሕዝብ በተመረጠው ሽንጎ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ክለንደን፤ ከአትላንታ፤ ከዲሲ፤ ከጀርመን ሆኖ አይቋቋምም፤ ሕዝብ ይህንን አሰራር አልፎ ስለሂደ  ለሚያደርገው ተጋድሎ  በአንድነት ሆኖ ድጋፍ እየሰጡ የምንፈልገዉን ለውጥ  ማምጣት ታሪካዌ ግዲታ ነው። በየቦታው የሚካሂዱት  ውይይቶች አዲሱን “ሁኔታ” ሊፈጥር ይችላል የሚል እምነት አለ፤ በተጨማሪ አንባቢ ለአዲሱ “ሁኔታ” መፈጠር የተሻለ መላ እንደሚያመጡ ተስፋ በማድረግ ነው፤ መልካም ውይይት}። 


መቅድም

የኢትዮጵያ ታሪክ በቅጡ ቢጠና ጥንታዌነቷን የሚስተካክል አገር አለ ለማለት ያስቸግራል፤ አፈ ታሪኩና ንግርቱ አያስፈልጋትም፤ የአባይ ሽለቆ ስልጣኔ ባለቢት ነች፤ ፊደሏ ተቀርጾ የወጣው ከምስል ከተሳሉ ምልክቶች ላይ መሆኑን ነባር ቅርስ ይመሰክራል። አቡጊዳ  ምን ይሰራል እያሉ ከሚደናቆሩ ጽንፈኝች ጋር መደናቆር ይሆናል እንጂ የፊደል አመጣጥ ከአንድ ስር ነው። ማንኛዉም ፊደል ስሩ አንድ ነው፤ ላቲን ልዩ መስሎህ እንደሆነ ተሳስተሃል፤ ጽንፈኝነትና ዘውገኛነት ጉዳቱ ድንቁርናነትን ማካበት ነው። ክዚህ አያልፍም፤ ኑሮዉም ከዘውግ ኮሮጆ ዉስጥ ነው፤ ዓለምንም  እድሜ ልኩን ስያቃትና ሳያያት ያልፋል፤ የዘውግ ፍልስፍናውም ከዘመን ዘመን ከትውልድ ትውልድ የሚተላልፍ  የተለየ በሽታ ነው። መድሐኒቱ ከዘውግ ኮሮጆ ዉስጥ መውጣት ብቻ ነው፤ ዓለም የተፈጠረችው ለሰው ልጅ ነው እንጂ ለአንድ ለተለየ ነገድ አይደለም፤ ከኮሮጆህ ወጥተህ ብታያት ግሩም ነች፤ ብዙ ዕውቀትን ታገኝባታለህ፤ ያገርህ የኢትዮጵያ ታሪክ ብዙ ነው  ሂደቷም  ከ12, 000 ዓመት በላይ ነው። ዲዮድረስ ሲስለስ [ Diodorus Siculus] የሚባለው የጥንታዌት ግሪክ ታሪክ ጸሐፊ ሲጽፍ እንዲህ ይላል፤ “ኢትዮጵያውያን ከማንኛዉም ይልቅ በፍትህ የታወቁ ስለሆኑ በሁሉም ዘንድ ተወዳጅ ናቸው፤ ይህንንም በማሰብ ታላቁ  ሊቀ ሊቃዉንት ሆመር [Homer] ሲያመሰግናቸው  እንዲህ ይላል፤ “አንኳንስ በዓለማችን ዉስጥ ያሉ ፍጡር ቀርቶ  ከጽንፈ ዓለም የምትገኝው ከጁፒተር [Jupiter] ዓለም እየመጡ ግብዣዋን ይጋበዛሉ፤ ይህንንም የሚያደርጉበት ምክናያት ኢትዮጵያ የፍትሕ አገር፤ እንግዳ ተቀባይ፤ ሰው አክባሪ፤ ለሰው ልጅ ክብር የምትሰጥ፤ ፈሪሃ እግዚአብሒር ያላት ብቸኝዋ አገር ስለሆነች ነው ይላል። “ እነዚህ የጥንታዌት ግሪክ ሊቃን ይህንን የምስክርነት ቃል የሰጡት ኢትዮጵያን ጎብኝተው አይደለም፤ ግን ምስክርነታቸው አፈ ታሪክ ወይም ንግርት አይደለም፤ ልብ ወለድም አይሆንም፤ ዝናዋን ሰምተው በአድናቆት የጻፉት ነው፤ እዚህ ላይ “ጁፒተር” የተጠቀሰው ርቀትንና አድናቆትን ለማሳየት እንጂ ከዚያ ሰው መጣ ለማለት አይደለም፤  ጁፒተር ላይ ሰው የለም፤ በቃለ አጋኖ የተነገረ ግን በድርጊት የተደረገ ታሪክ ነው።  በአንጻሩ የወያኔ ኢትዮጵያ ደግሞ የሊባ፤  የዘራፊ፤ የአጭበርብሪ፤ የዝሙትኛ፤ የነፈሰ ገዳይ፤ የጽንፈኛ ብሒረሰበኛነት፤ የዘውግ አቀኝቃኞች፤ የነፍስ ገዳዩ አጋዜና  የካድሬ ካህናት አገር ሆናለች። እንግዲህ እዚህ ላይ መመማር ያለብን ስመ ጡሩዋ አገራችን “በሁኔታ” ምክናያት እንዲት እንደተለዋወጠች ነው።

አንባቢ ይህንን በአትኩረት መመርመር አለበት፤ እነዚህ ሁለት ሊሂቃን የግድ ኢትዮጵያ ድረስ መጥተው በዝና የሰሙትን ማየት የለባቸዉም፤ አንባቢ በቀላሉ እንሱ ያሉት ሁሉ በእውነት እዚህ ሕብረተሰብ ዉስጥ መኖርና ያለመኖሩን ማረጋገጥ  ብቻ ነው፤ በዚህ ጉዳይ ላይ አንባቢ እንደ ሁለቱ ሊቃን ምስክርነት ሊስጥበት ይገባል፤ ለምሳሌ ንጉሥ ዘርዓ  ያዕቆብ ልጁን አንድ ገበሬ ያለአግባብ  ገድለሃል ብሎ የሞት ፍርድ አልፈረደበትም? እቤቱ በእንግድነት ብትሂድ እግርህን አጥቦ አልጋዉን ለቆ አላስተናገደህም? በችግር ግዜ ወደ ቤገምድር ሂደህ ገበሬው ምርቱን ወደራሱ እህል ማከማቻ ስያስገባ እህሉን ሰፍሮ ለአንተ ለወገኑ አላከፈለም? ምን አይነት ሕሊናዌንት ቢኖርህ ነው ዛሬ አጋዚ ሆነህ የጎንደርን ሕዝብ በጥይት የምትደበድበው?  ምን አይነት ሕሊናዌንት ቢኖርህ ነው የአማራዉን ወገን ከሚኖርበት እያፈናቀልክ የምትገለው? ምን ስለ አደረገ ነው ከየቦታው እየተለቀመ የሚወሰደውና የሚገደለው? በቋንቋህ ይሉንኝታ የሚባል ቃል አለ? ምን አይነት አውሬ ነህ?  ይህ ሲባል የዘውግ አቀኝቃኙ ፕሮፌሰርና ጽንፈኛ ብሒረተሰቦኝች የነበረዉን ታሪካዌ ባሕል ይቀበላሉ በማለት አይደለም፤ አክራሪም ጥገኛ የኢትዮጵያን ስልጣኔና ባሕል  ሲነግሩት የታሪክ አባቱ ስለሚቆጣው አይቀበልም፤ ይህ እውነተኛ ታሪክ የሚነገረው ጤኒኛ ሆኖ ለሚወለደው ትውልድ ነው፤ እንግዲህ ይህንን ታሪክ ከነባር ቅርስ እያሰተያየን እንመልከተው።

የቀይ ባሕር ወደብ

የእስልምና እምነት ተከታዮች ኢትዮጵያን ነቢዩ መሐመድ እንዳላቸው ውለታዋን በማስታወስ ከሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን እስክ እስክ አስራ ስድስተኛ መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ በሰላምና በመከባበር ኖረዋል። የዚህም ታሪክ በአጭሩ እንደዚህ ነው፤ በአንድ ዘመን ኢትዮጵያ ደቡብ አረብን ታስተታድር ነበር፤ ግን የሮማን ባሕር ኃይል ስለአገኝና የኢትዮጵያ ባሕር እየተዳከመ ስለመጣ የግድ ደቡብን አረብን  ለቃ መዉጣት ነበረባት፤ በዚያን ግዜ ወደኋላ ከቀሩት ኢትዮጵያን ዉስጥ ባሕሯ የምትባል ሴት ወጣቱን መሐመድን ወላጆቹ በስድስት ዓመቱ ስለሞቱበት እንድ እናት ሆና አሳድገዋለች፤ ወጣቱም ለአቅመ አዳም ደርሶ ነቢይ ከሆነ በኋላ የየጎሳው ባላባቶች ሃይማኖቱን እንዳይከተል አስቸግረዉት ኢትዮጵያ ድጋፍ በማስጠት እምነቱን ያለምንም ተጽኖ እንዲያምን አድርጋለች፤ ከዚያም በመጀመሪያ ሃይማኖቱን የተቀበሉትን ነቢዩ ወደ ኢትዮጵያ እንዲሂዱና ከለላ እንዲያግኙ ስለነገራቸው ኢትዮጵያ ተቀብላ ከለላ በመስጠት አስተናግዳለች፤ እንደዚህ አይነት ባለዉልታ ስለነበረች ነቢዩ መሐመድ ተከታዮቹን በምንም አይነት መንገድ ኢትዮጵያንና ዜጎቻን እንዳትነኩ ብሎ በሰጣቸው ቃል መሰረት እስክ አስራ ስድስተኛው መቶ ክፍል ዘመን ድረስ በሰላም ኖሮዋል፤ ከዚያም በኋል ክርስቲያንና እስላም በኢትዮጵያ ዉስጥ የሚኖሩት ፍጹም በሆነ ፍቅርና ሰላም ነው። ይህ የትም እስላም አገር ውስጥ የለም፤ ተረት አይደለም እውነት ነው።

ግን የቱርክ ኦቶማን የእስልምናን ሃይማኖት ለማስፋፋት  ባለው ዕቅድ መሰረት የኢትዮጵያን ቀይ ባሕር ወደብ በ 1557 ዓ.ም በቅጡጡር ሰር በማደርግ ሕዝቡን ሃይማኖቱን እንዲቀበሉ ከማድረጉም በላይ የኢትዮጵያን ወድብ እስክ ሕንድ ውቃያኖስ ያለዉን ወደብና አገር ስለተቆጣጠሩት የአክራሪ እስላም ኃይል ዳብሮ ያን ያስተናገድዉንና ፍትሕ ያለዉን ሕሊናዉነት ሊያጠፋው ተነሳ፤ የዘውግ አወጠኝጣኙ ፕሮፌሰርና የጽንፈኛ ብሒረተሰበኞች ወግ የሚለው በቅኝ ገዥ ላይ ቅኝ ገዥ መጣ ነው፤ ግን ዲዮደረስ ሲስልና ሆመር ይህንን ቢያዩ ምን ይሉ ይሆን? እንግዲህ አንባቢ ማየት ያለበት እነዚህ ወገኖቻችን ምን ቢሆኑ  ነው በበጎ ስራ ዝናን ያተረፈችዉን አገራቸዉን የጠሉት? ይህንን በጥሞና መመልከት አለባቸው፤ የሰው አገር ምንም ግዜ ቢሆን አገር አይሆንም፤ አገር አቀፍ ጥሪ አድርገው ቅሪታን መቅረፍ ያለው ስልጣን እነሱ ጋር ነው፤ መለስና አጋዜ ያፈረስቱን ቤት ምሶሶና ግድግዳ ሆነው መስራት ያለባቸው ደምህ ደሜ ነው ብለው የተነሱ የኦሮሞና የአማራ ወጣቶች ናቸው፤ ቤቱም እንደሚሰራ አትጠራጠር።

ከታሪኩ ቀንጠብ አድርገን ብናየውና ብንመረምረው ታሪካዌ ሂደቱ ይህን ይመስላል፤  ልብነ ድንግል [1508—44] ስልጣኑን እንደያዘ የኢትዮጵያ ዳር ድንበር መፈራረስ ጀመረ። በመካከለኛው ምስራቅ የተነሳው የእስላም አክራሪ ኃይል ቀስ በቀስ በምጽዋ አድርጎ ወደ ምዕራብ ኢትዮጵያ ስለ ገባና በቂ ኃይል ስለአገኝ ኢማም  አሕመድ ኢብን ኢብራሂም ስልጣን ይዞ መላ ኢትዮጵያን እስላም ለማድረግ ጦሩን ይዞ ከሐረር ተነሳ፤ በቅጽል ስሙ የሚታወቀው ግራኝ መሐመድ “ጂሃድ” ብሎ የተነሳው አንድ ጎሳን እንደ አጋዜ ለማጥፋት ሳይሆን ባጠቃላይ ክርስቲያኑን እስላም ለማደረግ ነበር፤ ሽዋን በከፊል፤ ወሎን ሙሉ በሙሉ፤ ጎጃምና በጌምድርን በከፊል የእስልምና ሃይማኖትን በግድ እንዲቀበሉ አድርጓል፤ አቢያተ ክርስቲያናት ከነ መጽሕፍታቸው ጋር አቃጥሏል፤ እስልምና አንቀበልም ያሉትን በስይፍ አንግታቸውን ቀልቷል፤ ልብነ ድንግል መንግሥቱን ከሸዋ አሽሽቶ ጎንደር ላይ በማደረግ ለመከላከል ሞክሮ ነበር፤ ግን የኢትዮጵያን አንድነት መልሶ አንድ ለማድረግ አልቻለም ። በመጨረሻም የፖርቱጌስ መንግሥት በላከው የጦር ኃይል በምዕራብ ጎንደር በሚገኝው ወይና አደጋ በሚባል ስፍራ በተደረገው ጦርነት ግራኝ መሐመድ ስለ ተገደለ የእስልምና ሃይማኖት መስፋፋቱ ቆመ፤ ነገር ግን ሐረር ሙሉ በሙሉ፤ አርሲ፤ ጉራጌ፤ አፋር፤ አዳል፤  ከምባታ፤ ኢርትራ በከፊል እስልምና በግድ እንዲቀበሉ ተደርጎ የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲከፋፈል ተደርጓል። የቦታዎች ስም ተለዋውጦ በመካከኛው ምስራቅ ስም መጠራት የጀመረው በዚሁ ዘመን ነው፤ ለምሳሌ በሽዋ  ክፍለ አገር ኩታ ገጠም የሆኑ ስፍራዎች  ስማቸው “ምንጃር” “ቡልጋ” “ጅሩ” “ዶባ” ሸኖ” “ሰነዳፋ” “አሊልቱ” “ሰበታ”  “ቢሾፍቱ”  “አዳማ” “ሆለታ” “አምቦ” “ወሎንኮሜ” እይተባሉ መጠራት የጀመሩት ከግራኝ መሐመድ በኃሏ ነው፤ ከዚያ በፊት ሊላ መጠሪያ ስም እንደነበራችው ይነገራል፤ ለምሳሌ “ምን ታምር” “ወይራአምባ”  “ወይናምባ” “ቡላ ሜዳ” “ሾላ ሜዳ” የሚባል ስም እንደነበራቸው ይነገራል፤ ግን ንግርት ስለ ሆነ ይህ ስፍራ በፊት ሊላ ስም ነበረው ብሎ  ታሪክ ሊጻፍ አይችልም። በሽዋም ሆነ  በሊሎች  ክፍለ አገሮች ዉስጥ ኦሮምኛ ተናጋሪዎች በቋንቋ እንጂ በጎሳ አይደለም፤ ይህ በትከረት መጠናት ያለበት ጉዳይ ነው።

ዘመነ መሳፍንት

ለዘውግ አቀኝቃኙና ለጽንፈኛ ብሒረተሰበኞች “ዘመነ መሳፍንት” ማለት ስፍር ቁጥር ለሊለው የአፍሪቃ ብሒረሰቦች ታሪክ መጀመሪያ ማለት ነው። አፍሪቃ በትንሹ 3000 ቋንቋዎች የሚነገሩባት  አገር ነች። እንግዲህ  እዚህ ላይ ያለው ችግር በእኛ አካባቢ ያለዉን አገር ምን ብለን እንጥራው፤ ኢትዮጵያ  እንዳንል  በዘመነ መሳፍንት ግዜ የለችም ይሉናል። ለፕሮፌሰሩና ለጽንፈኞቹ የሚቀርበው ጥያቄ የዘመነ መሳፍንቱ ታሪክ ከየት መጣ? ፕሮፌሰሩ እንኳን ታሪክ ቀርት ፍልስፍናውንም በጥራት አላያዙትም፤ ጽንፈኞቹ ተቀጣሪ ውጅንብር ፈጣሪዎች ስለሆኑ ሙያቸው ያለዉን የለም፤ የሊለዉን አለ እያሉ  የመተዳደሪያ  ሙያ  አድርገው ይዘዉታል። ስለዚህ ምርጫችን  እነዚህ  ሕዝብን የሚያወክሉና ሕዝብ ያልመረጣቸው ተቀጣሪ  በጣት የሚቆጥሩ አቀኝቃኞን ወደ ጎን  አድርገን የአገራችንን ታሪክ በቅጡ ብናጠናው ይመረጣል፤ ክታሪኩ ቀንጠብ አድርገን እንመልከተው።

ዘመነ መሳፍንት በአንድ ግዜ የተከናወነ ሂደት አይደልም፤ “ሁኔታው” ቀስ በቀስ ነው የዳበረው፤ ለዚህም  መከናወን  ቢያንስ ከመቶ ዓመት በላይ ወስዶብታል፤ ከዳዌት [1380-1412] እስክ ዘርዓ ያዕቆብ [1434—68] የክርስትናን እምነት ተከታዮች መሃል የነበረው የአንድ ሰንበት ሁለት  የሰንበት ውዝግብ በአንድ በኩል፤ በመካከለኛው ምስራቅ የስልምና መስፋፋት ንቅናቄ፤ የአምደ ጽዮንና የሰይፈ አር ዕድ ከመስቀለኛ [crusaders] ጦሮኝች ጋር ያደረጉት ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት መፈራረስ ትልቁን መስትዋስጽኦ አድርጓል። “ሁኔታው” በሚገባ ስለዳበረ  በ1529  አሕመድ  ኢብን  ኢብራሂም  ከሐረር  ጠቅላይ ተነስቶ  የቀረቱን  አስተባብሮ   የልብነ ድንግልን መንግሥትን ኃይል ደምስሶ ያደረሰዉን ጥፋት እላይ በአጭሩ ተጠቅሷል። አሁን እዚህ ላይ የምንመለከተው ኢትዮጵያ እንዴት በጎሳ እንደተከፋፋለች ነው።

ልብነ ድንግል ወደ ጎንደር ቤተመንግሥቱን ሲያዛውር ሸዋ የመሐመድን ጦር ተቋቁሞ ግብሩን ባለማቋረጥ ወደ ልብነ ድንግል ይልክ ነበር፤ ከዚያም በኋላ ለ322 ዓመታት ባለማቋረጥ የማዕክላዩን መንግሥት በመደገፍ ጎንደር ለነበረው መንግሥት ግብሩን ይከፍል ነበር። ሆኖም የጎንደር ቤተ መንግሥት ምንም ዓይነት ኃይል በሊሎቹ ጠቅላይ ግዛት ዉስጥ ሲያኖረው ያ በዝና ትታወቅ የነበረችው ኢትዮጵያ በሰፈር አምባ አገነኖች ለሶወስት መቶ ዓመት ስትታመስ ኖራለች። እንግዲህ  የጽንፈኛ ብሒርተሰበኞች ነጻ አገሮች የሚሏቸው “ጎጃም”፤ “ወለጋ”፤ “ትግሬ”፤ “ከፋ”፤ “ወለጋ”፤ “ከምባታ”፤ “አርሲ”፤ “ሐረር፤ “አዳል”፤ “ኢርትራ” ናቸው። እንግዲህ አንባቢ የታሪክን ሂደት ማየት ያለበት ከመጀመሪያው እንጂ ቅዠተኞች ከፋፈሉት አገሮች መሆን የለበትም፤ ኢትዮጵያ ለ 80 የሚሆኑ ጎሳዎች እናት ነች፤ አንድን ካንዱ ማስብለጥ የላባትም። ጽንፈኞቹ እንዲት አድርገው የአስር ነጻ የሆኑ ብሒረሰቦች አገር እንዳደረጉ ማስረዳት አለባቸው።

ይህ ውይይታችን አቅጣጭ እንዲይዝና ወደ ትክክለኛው ታሪካችን እንድንገባ በተረጋጋ መንፈስ መዋያየት አለብን፤ ምናልባት ለመጀምሪያ ግዜ በጽኑ ልቦና ለመወያየት ፈቃድኝነቱ የመጣ ይመስላል፤ ታሪክ ታሪክን ይደግማል እንደሚባለው አሁን ወደ “ዘመነ መሳፍንት” እንድንሂድ የሚገፋፋ ኃይል መኖሩን ማወቅ ግዴታ ነው፤ ኢትዮጵያ የመቶ ዓመት ተረት ነች እያሉ በተከታታይ በጽሑፍ አስነብበውና አስምነው ሊከፋፉሉን ነው፤ ይህንን ለማስቆም አንባቢና ጸሐፊ በማያቋርጥ ጥረት ማድረግ ነው፤ ለዚህ ጥረት ወያኔ የሚያደርገዉን እንቅፋት ማለፍ ይኖርብናል፤ እውነተኛ ታሪካችን እንዳይነገር ሰምተናል በቃ የሚሉ አዘናጋዮች አሉ፤ ማን እንደሆኑ ማወቅ ታሪካዌ ግዲታ ነው፤ እነሱ ኢትዮጵያ የለችም እያሉ ቱል ቱላቸዉን ለ 60 ዓመት ሲነፉ ሕዝቡን እያወከቡና “አንተ ታሪክን አታቅም “ እያሉ ነው። አሁንም ተንስተዋል፤ እነዚህን ካድሬዋች መቋቋም አለብን፤  ከፍል አምስት የኢትዮጵያን  ግዛት አንድ ያደረገዉን የኢትዮጵያን ጅግና  “የእምዮ ምኒልክን” ፤ ለኢትዮጵያ ቤት ጊድግዳ የሆነዉን ለዓለም ሕዝብ  የአድዋን ድል ያስገኝዉን ታልቁን ጀግና የኦሮሞን ፈረሰኛ ታሪክ ቀንጠብ እያደረግን እንወያያለን፤ እዚህ ላይ የዘውግ አቀኝቃኙ ፕሮፌስርና የጽንፈኛ ብሒረተሰቦኞች  ወግ ይደመደማል፤ ወጉ ይቀርና እውነተኛዉን ታሪክ እንወያያለን፤  ቸርነቱ የሚያልቀበት አምላክ ኢትዮጵያን ከወያኔ ካደሬዎችና ከነፈሰ ገዳዩ አጋዜ ያድንልን።

Source    –      Zehabesha