በልኡል አለሜ

በመሃበራዊ ግንኙነት ዙሪያ ላይ መበለጣችን ለህዝባዊ አመጽና ለስልጣን መፈረካከስ አድርሶናል በማለት በአዲስ እራይ ልሳኑ በይፋ ያወጀዉ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የተቃዉሞ ምንጭ በሚል ድምዳሜ በግንባር ቀደምትነት የፌስ ቡክ ሚዲያ ዘርፍን ለማጥቃት ዘመቻ መዉጣቱን ተንተርሶ ለቅጥረኞች የሶሻል ሚዲያ አጥቂ ሰራዊቱ የተሰጣቸዉን ግዳጅ በጥንቃቄ እንመለከተዉ ዘንድ በዘርፉ ከተሰማሩ ምንጮቻችን መረጃ ደርሶናል።Ethiopian government (TPLF) social media campaign

የሰራዊቱ ዋነኝ አላማ

  • በተቃዉሞ ዘርፍ ላይ ተሰማርተው ወያኔን በከፍተኛ ሁኔታ ከሚሞግቱት ጋር ተመሳስሎ የትግላቸዉ አካል በመሆን እና መረጃዎችን በመቀባበል ትግሉን ማጥቃት እና ማኮላሸት ህወሃትን ማዳን ።
  • አላማዉን ለማሳካት እነዚህ የሶሻል ሚዲያ ሰራዊት አባላት በተቃዋሚ ሰራዊቶች ዉስጥ ታማኝነትን በማፍራት እና ሰርገዉ በመግባት በዉስጥ መስመር የማሳመን ስራ መስራት የማህበራዊ ግንኙነት የጥምር ቡድን ስብሰባዎችን መቀላቀል ሐሳቦችን እና ሆን ተብለዉ የተጠኑ መረጃዎችን በማቀበል ሙሉ እምነት እንዲጣልበት አድርጎ ለዘርፍ ሐላፊ የብሄራዊ ደህንነት ተጠሪዎች ማሳወቅ።
  • ይህ ተግባር በተለየ መልኩ ከነጻነት ሐይሎች ጋር ቀጥታ ግንኙነት አላቸዉ የሚባሉ ተጠቃሚዎች ላይ ያነጣጠረ ሲሆን በመካከል በሚፈጠር ጠንካራ ታማኝነት ምክንያት የሚዲያ ሰራዊቱ አባላት እስከ ግንባር ድረስ እንዲዘምቱ እና የማፍረስ ስራ እንዲያከናዉኑ ይታገዛሉ።
  • አብዛኛዎቹ የህወሃት የሶሻል ሚዲያ አባላት አዲስ አካውንት ከመክፈት ይልቅ ነባር አካዉንታቸዉን ስም በመቀየር እንዲገለገሉበት ተደርገዋል።
  • የሶሻል ሚዲያ ሰራዊቱ ሆን ተብለዉ በፖለቲካ ምክንያት ከሐገር እንዲሰደዱ በማድረግ በተልይ የኮማንድ ፖስቱ ባለ ቀይ መስመር ሐገሮች ላይ እነርሱም አሜሪካ ፣ ኖርዌይ ፣ ሲዉዲን ፣ እንሊዝ ፣ ኒዘርላንድ ፣ ካናዳ ፣እንዲሁም ደቡብ አፍሪካ ፣ ኬንያና ፣ ዩጋንዳ ላይ ልዩ የጥቃት ስልት ተንድፎ ይቀርብላቸዋል።
  • የህወሃት ሰራዊት የተሳሳቱ መረጃዎችን በመስጥት ታማኝነት እንዲጠፋ መተማመን እንዳይኖር በብርቱ ይተጋሉ

አፈጻጸም

  • ጥቂትና እዉነተኛ መረጃዎን ከሁሉም ቀድሞ በማሰራጨት ታማኝነን ማዳበር
  • የተቃዋሚ ክፍል አደገኛ ተግባራቱን ማጥናትና ማቅረብ በግል ደረጃ እነማን እንደሆኑም በጾታዊ ወይም በመመሳሰል የትግል ስልት በማሳመን እና በማግባባት ማወቅ የት እና ከየትኛዉ ማህበረሰብ ከምን አይነት ቤተሰብ የወጡ ናቸዉ ? እስከሚባሉት ድረስ መሄድ..
  • ለታዋቂ የፌስ ቡክ ገጾች የተጠኑ መረጃዎችን ማቀበል ለተለያዩ ድህረ ገጾች በተለይም ዘ_ሐበሻና ኤካዴፍ ለመሳሰሉት መረጃ መስጠtና በሌሎች ዉስጥ ቦታ መያዝ።

የምርመራና ከሳሽ ዘርፍ

  • ይህ ዘርፍ በቀጥታ ከህወሃት የደህንነት ሰራተኞች ጋር በቅንጅት የሚሰራ ሲሆን ዋነኛ አላማዉ አዝማች የተቃዋሚ አጥቂ ግለሰቦችን በህግ ሽፋን ክስ ለመመስረት በሚያስችል መልኩ አሳልፎ ለመስጠት መረጃ መሰብሰብ ዋና ስራዉ ነዉ::
  • በዚህ ክፍል ዉስጥ የተሰማሩ ቅጥረኞች የተቃዋሚ ክንፍ ባለ አካዉንቶችን በዉስጥ መስመር በመልእክት ወይም በድምጽ እንዲሁም በጽሁፍ መስቀለኛ ጥያቄ መጠየቅ ሲሆን ጥያቄዎቹ . . . መዝመት እፈልጋለዉ? በየት በኩል ልጓዝ ? ከእነማን ጋር ልገናኝ ?. . . እነ እገሌን ታዉቃቸዋለህ? እነማን ሲባል (የሚጠየቁት ግለሰቦች በሽብር የተከሰሱ ሊሆኑ ይችላሉ) እና የመሳሰሉት።
  • ህወሃት ያሰማራቸዉን የሶሻል ሚዲያ ሰራዊት አባላት ከተቃዋሚ ሰራዊቶች ጋር ተመሳሳይነት ያላቸዉን ስሞች በመቅረጽ የማደናገር ተግባር መፈጸም
  • በተቃዋሚ የመረጃ ዘርፍ ዉስጥ በዘላቂነት ከርሞ አቋምን በመቀየር የማደናገር ተግባር መፈጸም።

የልማትና የስራ ዘርፍ

  • ከተራ አካዉንት እስከ ኢቢሲና የተለያዩ የህወሃት ልሳኖችን በመጠቀም ልማታዊ ክንዉኖች ቦታ እንዲይዙ የሚጥር የሚዲያ ክንፍ

ዉድና የተከበራችሁ ኢትዮጵያዊያን ይህ አንባገነኑን ህወሃት በዚህ ዘርፍ ላይ በብርቱ እያማከረች የምትገኘዉ ቻይና ስትሆን ለዚህ የሚዲያ ዘርፍ የሚዉል የግፍ ገንዘብ 1 ቢልዮን የአሜሪካ ዶላር ተመድቦለት ወደ ተግባር ተገብቷል፡

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !