January 8, 2017 19:44

By ሳተናው

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ “የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ” የተሰኘ አዲሱን መጽሐፍዎትን አንብቤው ስለ አገራችን ኢትዮጵያ ያለዎትን የግል ስሜት ፣ጥልቅ ፍቅር ለህዝባችን፣ ለባህላችን እንዲሁም ለቋንቋችን ያለዎትን ክብር ሳነብ አይኔ እንባ እየቋጠረ ነበር። በተለይ አሁን ባለንበት ዘመን ሰለ አገራችን ኢትዮጵያ ፍቅር ከግለስብ መስማት ብርቅ በሆነበት ጊዜ ትልቅ ተስፋ ይሰጣል። ምክርዎት፣ ያለዎትን ሰጋት በተለይ የህዝባችንን መገነጣጠል ሊያመጣ የሚችለውን ጉዳትና እጣ ፈንታችንን በቅጡ ለአንባቢ ግልጽ አድርገው አስገንዝበዋል። ለዚህም ትልቅ ምስጋና አቀርባለሁ።

ለእምዬ ኢትዮጵያ ያለዎትን ፍቅር ለአንባቢ በፍጹም ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ ፍላጎት ስለሌለኝ የምሰጥዎት አስተያየት ውስጥ የአገር ፍቅርዎን ከጻፉት መጽሃፍ ነጥዬ ማየት እፈልጋለሁ። አገርን ማፍቀር እና የታሪክ መረጃ አለኝ ብሎ ስለ አገር ታሪክ ለትውልድ ሊተላለፍ የሚችል መጽሃፍ ለሕዝብ ማቅረብን ነጣጥለን ማየት አለብን። በመጽሃፉ አጠቃላይ ይዘት ላይ የፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌን እና የፕሮፌሰር ጳውሎስ ሚልኪያስን አስተያየት እጋራለሁ። ሁለቱም ፕሮፌሰሮች ትዝብታቸውን ሆነ በመጽሃፉ ውስጥ የሰፈሩትን—-  ሙሉውን በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ