Date: Mon, Jan 9, 2017 at 1:18 AM

Subject: Re: የውይይቱ መንሥኤ፤ ለውድ ፕሮፌሰር ፍቅሬ፤ ከጌታቸው ኃይሌ

ውድ ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌና ልፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ እንዲሁም ለተከበራቸሁአንባቢዎች፣

እየተማርን ነው። ዕንቁ ታሪክ በዕንቁ አቀራረብ።

ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ የሰጡት መልስ የተጠየቁትን ጥያቄዎች የሚቋቋም ሆኖ አላየሁትም። የግሌ ግምት ሲሆን፣ የጠበኩት መልስ፣ ለያንዳንዱ ጥያቄ ማስረጃ የሆነውን “ገልጫለሁ፣ እንዲህ ብያለሁ” ሳይሆን፣ ለእንደዚህ ላለው ሥነጥበብ ጉዳይ መልስ የሚቀርብበትን መልክ የያዘ ሆኖ አላገኙሁት በሚል ድምዳሜ ነው። ይኽ አቀራረብ ደግሞ፣ ለታሪክ ምርምር ብቻ ሳይሆን፣ ለማናቸውም ሥነጥበበ ምርምርና የጥናት አቀራረብ የሚውል ስርዓትን (ደንብን) የተከተለ ስላልመሰለኝ ነው። ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ የታሪክ ምርምሩን የማሳመርና የማሳመን ግዴታ አለበት፤ ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ ታሪኩን የማረጋገጫ ምርምር ምሑርነታቸውና ሊቅነታቸው ያስገድዳቸዋል። ይህ ደግሞ የታሪክ ጥናት የሚያቀርቡ የሚገጥማቸውና የሚያልፉት ትግል ነው። ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ዶ/ር ኦፍ ፊሎሶፊ የተባለውን የትምህርት ፍጻሜ ማዕረግ ሲቀናኙ ያለፉት ውጣ ውረድ ስለሆነ፣ የተጠየቁትን በዚያው አንጻር አቅርበውት ቢሆን ኖሮ ተገቢና የሚደነቅ ነበር። የመልሱ ዝንባሌ ሌላ ግምት በሰው አዕምሮ እንዲሰፍን አድርጓል። ምናልባት ዕድሉ ያከተመ ሆኖ መታየት የለበትም። ፕ/ር ፍቅሬ ወደዚያ አዘንብለው የተጻፈውን ታሪክ ጥያቄ ሊዋጡ የሚሞክሩ ይሆናል። ዕውነቱ እስከሰፈረ ድረስ ተጠቃሚና ጠቃሚ ሊቅ ይሆኑበታል።

አንድ ምሑር፣ በጻፈው ታሪክ ውስጥ፣  የተዛባውን መረዳትና መቀበል፣ ትክክለኛውን ደግሞ ማስተማርና ማሳመን ግዴታው ነው። የታሪክ ተመራማሪው መስተካከል የሚገባውን በማስተካክልና ዕውነተኛ የታሪክ ስነ-መዝገብ ሊያበረክት ይጠቀማል ይጠቅማልም። የተመራማሪ ሰው ጥረት የተጣራ ታሪክ ለማቅረብ ስለሆነ። በዚህ መንገድ ታሪኩ በሁሉም ምሑራን ተነጻጽሮና ተገድፎ ሲቀርብ ተመራማሪው ተቀማጭና ኗሪ ታሪክ ለማበርከት ይችላል። ይህ ያለምንም ትርፍ (ሥልጣን፣ ገንዘብ፣ ታላቅ ስም) መታሰብ ያለበት የጥበብ ሰዎች ግብ ነው።

የታሪኩ ምርምር በአልሆነ ትችት ውስብስብ እንዲጓዝ ተደርጓል። አንባቢና ታሪክ ተመራማሪ ለሆነው የጠቀመው ጉዳይ አልሆነም። የጠቀመው በሌላ ደረጃ ያለውን አንባቢ ብቻ ሆኗል፣ አንዱን አይነት ተመልካች፣ ከታች የተጠቀሰው ያመለክታል። ለቀረበው የምርምር ጥራት ጥያቄዎች የተሰጡት መልሶች፣ ለተመራማሪው አግባብ በሆነ መልክ አልቀረቡም። የደራሲው (የተመራማሪው) ሸክም አልወረደም ማለት ነው። ይኽን መገንዘብ ወይም አለመገንዘብ ይችል ይሆናል። ያደግሞ የጠበቀ መሰረተ ጥያቄን ያስከትላል። በተቻለ መጠን፣ ጠቃሚውንና አስፈላጊውን የጥበብ ምርምር ማስተናገድ ያሻል። የቀረበበትን መልክ ሳይሞረኮዝ። ለዶክተሬት እና ማስተር ጥናትን ለማጽደቅ አሉ በተባሉት ሊቆች ፊት አንድ ሰው ሲቀርብ፣ ከጠያቂው ጋር እንካ ስላንቴ አይገጥምም። ማስረዳት አለበት፣ ደግሞ፣ ደጋግሞ፣ መልሶና መላልሶ። ከልሆነ፣ ጥናቱን በድጋሜ ያካሂዳል። ጀምስ ብሩስ “ኢትዮጵያ የታላቅ ሥልጣኔ ሀገር ናት” ብሎ ያየውን ሲጽፍ፣ እንግሊዞች “ልብ ወለድ ታሪክ” እንዴት ተብሎ ከአፍሪካ ጫካ ከኛ የሚወዳደር ታሪክ ጽፈህ ታቀርባለህ ተብሎ ተወግዞና ተከድቶ የሞተ ሰው ሲሆን፣ ከሞተ ከመቶ ዓመት በኋላ ነው ልብወለዱ ዕውነተኛ ታሪክነቱ የታወቀው። በዚህ ሁናቴ የሚጠቀሱ ብዙ ታሪኮች አሉ።

ጥናትና ምርምር አዲስ ዕውቀትን ይፈጥራል። ማስረጃ ሳይኖር፣ ዕውነት ጊዜን፣ ወቅትን፡ ተመሳሳይ ታሪክን፣ በፊትና በኋላ የሆነውን በመመርመር ተዋቅሮ (deduce) ተደርጎ የጎደለው ታሪክ ወይም ገለጻ ይመሰረታል። ታምኖበት ይኖራል። ከጊዜ በኋላ፣ ጊዜው በወለደው ቴክኖሎጂ ወይም የተቀበሩ ማስረጃዎች ሲፈልቁ የተጻፈው ታሪክ እንዲወድቅ ወይም እንዲጸድቅ ያደርገዋል። ምድር የማይደብቀው ነገር ያለም። በኢትዮጵያ አያሌ ቦታዎች (ምድር) ለእጅግ ብዙ ዓመታት የተደበቁትን የሰው ቅርሶች ለማየት በቅተናል። በነዚሁ መሰረት የነበረው ታሪክ እንዲከለስ ወይም እንዲጸድቅ ተደርጓል። ቅርሳቅርሶች ድንጋይም ይሁን እንጨት ወይም ብረታብረት የታሪክ ምልክት ማሕተሞች ናቸው። በውስጣቸው የተደበቁ ብዙ ድርጊቶች ይኖራሉ። ከነሱ ተነስቶ ታሪክ ይጻፋል።

ያማራና የኦሮሞ ሕዝብ ምንጭ አንድ ከተባለ፣ መነሻውም ‘ደሸት’ ከሆነ፣ ታሪኩ ያለ ችግር አሁን ካለበት ወደ ኋላ በማግተልተል እስከ መጣበት ዘመን መድረስ ይችላል። መጀመሪያ ‘ኦሮሞ’፣ ‘ጋላ’፣ ‘ማራ’ ወይም ‘አማራ’ የተባለውን መንስዔ የጋራ ዘርፍ ስም መሻት አለብን። ይህን ማድረግ፣ ከደሸት ተነስቶ ወደ ሌላው ምድር የተሰራጨውንና ‘ኣማራ’ ‘ጋላ ወይም ኦሮሞ’ የተሰኘበትን ታሪክ እንደርስበታለን። ሌላ አወሳሳቢ ነገር እንዳልጨምር እንጂ፣ በጀርመን ያሉ ‘ኤርያን’ የተባሉት ሕዝቦች ኢትዮጵያኖችን “አንክል ኢትዮጵያንስ” ይሉ ነበር። መሰረት ያለው አባባልና የቅርስ ጉዳይ ነው ይባላል። ይኼ ሲባል፣ በኢትዮጵያ የሰፈረው ሁሉ ከሉሲ የፈለቀ መሆኑን በመቀበል ነው። ሉሲ ከዛሪው ወሎ-ኣፋር ምድር ግማሽ የሰው አካል ይዛ የፈለቀችው፣ ልጆቿ በመጣው ችግር ወይም በአንድ አይነት ግዳጅ፣ ከአፋር ተነስተው በአሁኑ ሸዋ ብለው ቀይባህርን አቋርጠው፣ በግሪክ ከዚያም ኤሮፓ ገብተው በመዋለድና በመባዛት አሕጉሩን ያጥለቀለቁ እንደሆኑ የዘመኑ ጥናት ያስረዳል። የአማራውና ኦሮሞው ጉዳይ በጊዜ አንጻር የትናትና ታሪክ ነው ሊባል ይችላል። ስለዚህ፣ የነሱም ስርጭት በኮቴአቸውና በልዩ ልምዳቸው የገቡበትና የሄዱበት መታወቅ አለበት፣ ይኼም ይቻላል። ችግሩ የሁለቱ ዘርፎች መነሻ አንድ ግንድ ነው ከተባለ ማነው የደሸት ‘ሉሲ’? መቸም የጋራ አያት እንጂ፣ የአሁኑ ሕዝብ በሚታወቅበት ‘ኦሮሞና አማራ’ በደሸት ኖሯል ለማለት ይከብዳል። “አያታቸው አንድ ነው” ለማለት ከሆነ፣ ሌላውን፣ ጉራጌውን፣ ብሌኑን፣ አዳሉን፣ ወዘተ ምን ታሪክ የማያደርገው ይሆናል?

ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ለታሪክ የፍልስፍና ዲግሬ የሚያበቃ ጥናት ይዘው የቀረቡ ይመስላል። ይህንንም የምለው በአድንቆትና በታላቅ አክብሮት ነው። ያቀረቡት አዲስ ሀሳብ እጅግ በጣም አሳሳቢ መሆኑን ከፕ/ር ጌታቸው በላይ አርቅቆና ገላልጦ የሚያቀርበው ሌላ ምሑር ተፈልጎ የሚገኝ አይመስለኝም። ይህ የግል አስተያየቴ ሲሆን፣ እሳቸውን በብዙ አንጻር፣ በተለይ በውጩ ትምርትና ዕውቀት ላይ ከፍ ያለ ቦታ የሚሰጣቸው መሆኑና የተሟላ መሆኑን በመገንዘብ ነው። ወደር የሌላቸውን በሀገር ውስጥ ያሉትን ሊቃውንት ደግሞ ማንም የማይደርስበትን ጣራ የያዙ መሆናቸውን አጥብቄ በመገንዘብ ነው።

ከላይ እንዳልኩት፣ ፕ/ር ፍቅሬ ትልቅ ጥናት አቅርበዋል። ዕውነት ይሁን ፍልስፍና ምርምሩ ተጀምሯል። ፕ/ር ፍቅሬ ያለመታከት፣ ያለመበሳጨትና ያለማማረር የሚሰነዘሩትን ጥያቄዎች ማስተናገድ ይገባቸዋል። ምክንያቱም አዲስ ታሪክ አቅርበዋል። ጥያቄው በፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ ብቻ የሚያቆም ሳይሆን የሚቀጥል ይመስላል። ይኽ ደግሞ ለፕ/ር ፍቅሬ እጅግ በጣም ጥሩ ነው። መጽሐፉ በብዙ ሰው እጅ ይገባል። ሲያነጋግርና ሲያወያይ መልካም ነው። ሲጣል መጥፎ ነው። ፕ/ር ጌታቸው ከባድ ግዳጅ አለባቸው፣ ታሪኩና ጥናቱ ሰምሮና መስሎ ቢያገኙት፣ ያለምንም ጥርጥር በታላቅ ኩራት ያጸድቁት ነበር። ጠይቀዋል ለዚያ መልስ መስጠት ወይም መግባባት ካልታየ ዘለቄታው አዳጋች ነው። አቶ ቴዎድሮስ ጸጋየ የተባለ ጋዜጠኛ በአደረገው ጥያቄ መልስ የተለያየ አስተያየት ተሰጥቶበታል። አቶ ቴዎድሮስን ታዳጊ ጋዜጠኛ መሆኑንና የሙያ ቅመሞቹን በአንደበቱ ችሎታው ብል ይሻላል አይቻለሁ። ሌላውን በመተው አድንቄአለሁ። የፕ/ር ፍቅሬን ትግስትና የገለጻ ሙከራ አይቸ ታላቅ አክብሮቴን ሰጥቻለሁ፣ መልሼም ለመስጠት እወዳለሁ።

በመደምደሚያየ ላይ የምገልጸው ፕ/ር ጌታቸው የገለጹት ምሑር ቃል ነው። ኦሮሞና አማራ፣ አሁን ደግሞ ራያንና ቆቦን ወያኔ ከወሎ ወደ ትግራይ ካስገባው በኋላ፣ ትግሬና ኦሮሞ የተዳቀለ ሕዝብ ነው። ይኽ ማለት፣ ማንም ምድር በኢትዮጵያ የኦሮሞና አማራ ሌላው ሕዝብ ስብጥርነት እጅግ የተሟላ ስለሆነ፣ መጽሐፉ ኦሮሞንና አማራውን ያዛምዳል ለዚያ ስንል እንኳን እንቀበለው የሚል መድኃኒት ፍለጋ የገባ ሰውን ያመለክታል። በዚያ በኩል የጎደለው ይስጋና የደም ወይም ያንጥት ሳይሆን የከሃዲዎች መፈልፈሊያ የሆነው የገንዘብ ምንጭ ነው። ገንዘብ ወገንንና ሀገርን መካጃ ዋና መሳሪያ ሆኗል። መጀመሪያ ማድኽየት፣ ቀጥሎ ሊንቀው የማይችለውን መታለያ ገንዝብ እየነሱ ማሳየት ወይም እያሳዩ መንሳት። ቀጥሎ ከሃዲ (ባንዳው) ምን ላገልግል ብሎ ሰላቶውን ይጠይቃል። እንዳይርቅ እናይቀር አድርገህ ገንዘብ ስጠው። አበል እየፈለገ እንዲመላለስ አድርገው። ጌታየ እንዲል አንዲትም ነገር በራሱ ሂሳብ እንዳይሰራ እንደ መለስ ዘናዊ እንዳይጠግብና እንዳይሽከረከር አድረገው ነው መተዳደሪያው። ይህን ማንሳቴ ፕ/ር ጌታቸው እንዳሉት የተባለው አዕምሮን የሚጠመዝዝ አይሆንም። ፕ/ር ጊታቸው ያሉትን ከዚህ በታች አቅርቤዋለሁ።

’ዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳ ጂግሳ ዓላማው አማሮችና ኦሮሞች በአንድ ሀገር ውስጥ በወንድማማችነትና በሰላም እንዲኖሩ ምክንያት ለመስጠት ስለሆነ በምንም ዘዴ (ዋሽቶም ቢሆን) ቢጠቀም ክፋት አናይበትምየሚሉ አሉ። እንዳፋቸው ያድርግላቸው። ግን ይህ የሐሰት ታሪክ የኢትዮጵያ አንድነት በሚያንሰፈስፋቸው ኢትዮጵያውያን ስሜት ከመቀለድና ከመጠቀም አልፎ በክልልና በጎሳ ፖለቲካ የሚያምን አንድ የኦነግ ሰው ነፍስ አይማርክም

በአክብሮት

ዘውገ ፋንታ