ናዚጀርመኒ ለ20ኛው መቶ ክ/ዘመን በጀርመን ሲነፃጸር

ወያኔ/ህወሃት ለ21ኛው ክ/ዘመን በኢትዮጵያ

ወልደአብ ደንቡ

(12 ጄንዋሪ 2017)

ጀርመን የተልያዩ ዘሮች(races) ፣ቋንቋዎች ፣ባህሎች ፣እምነቶች ፣ፖለቲካዊ አስተሳሰቦች ወዘተ..የነበራቸው ስዎች እንድ አንድ ሕዝብ የሚኖሩባት አገር ነበረች ፤ ከ 1933 -1945 .ም ሂትለር የፋሺዝምና የናዚዝም የፖለቲካ ርዕዮቶችን መሥርቶና ተጠቅሞ ጀርመንን ለመግዛትና ዓለምን በቁጥጥሩ ሥር የማድረግ ሙከራ ሲጀምርመጀመርያ ያነጣጠረው የአርያን ደም(Arayan genetic make up) የላቸውም ወይም እነዚያ (the other) በሚላቸው ጀርመናውያን ላይ ነበር ።

ፋሺምና ናዚዝምየአንድ ሳንቲም ፊትና ጀርባ ናቸው ፤ ሁለቱም አክራሪ ቀኝ ክንፍ የፖለቲካ ርዕዮቶች ናቸው( they are the two extreme right wing political ideologies) :: ፋሺም ከአክራሪ የቀኝ ክንፍ ብሄርተኝነት ይፈልቃል ፤ ማለት የፋሺዝም እናት አክራሪ ብሄርተኝነት ነው ።

አክራሪ ብሄርተኝነት ሌሎችን ወይም እነዚያ (the other) የሚላቸውን ብሄር ብሄረሰብ አባሎችን ክፉኛ ይጠላል ። የሌሎችን ቋንቋ ፣ባህል ፣ታሪክ ፣ማንነትና ሕልውና ይንቃል/ይረግጣል ፣ የራሱን የማንነት እሴቶች ያሳብጣል ፤ከማንም /ከምንም በላይ ነኝ ይላል ። የአክራሪ ብሄርተኛ የፖለቲካ ድርጀት አባሎችየእነሱ ዘውግ ወይም ዘር ያልሆኑትን ሁሉ እንዲጠሉ ስለሚታነጹ የስብዕና ንቃተኅሊናና ሕዝባዊ ባህሪ ይጎላቸዋል ስለሆነም የሌሎ ችን ብሶት፣ ሃዘንና መከራ አይጋሩም ፤ የእኛ አይደለም/አይደሉም በሚሉት/ሏዋቸው የሰው ልጅ/ልጆች ላይ የሚፈጸምን ግፍ አይሰማቸውም ፤ጨቋኝና ጨካኝ ናቸው ።

በመሆኑም የጀርመን ፋሺዝምና ናዚዝምዋንኛ መርሃግብር (programme) ያተኮረው በፀረ እነዚያ በሚላቸው ብሄረስብ አባሎች ወይም ዘሮች፣ በፀረ ይሁዳዎች (አንቲ ሰሜትዝም) እና የሌሎችን አገሮች በመውረር ላይ ነበር ።

ስለሆነም የአርያን ዘር ‘በተፍጥሮ የጠራ/ንጽህ ዘር’ ነው ፤ በተፈጥሮ ከተበከሉ(polluted) ዘሮች ተለይቶና እርቆ መኖር አለበት አርያኖች በሥነፍጥረት (በባዮሎጂ) ከሌሎች ዘሮች ከሚተላለፉ ማንኛውም በሽታ ማጽዳት/መከላከል አለብን ፤ጀርመናዊ አርያን ሃያል ዘር ነው (Germanic Aryan race is master race) ስለሆነም ዓለምን መግዛት እንችላለን ወዘተ..በሚል ቅስቀሳና ፕሮፓጋ ዳ ምክንያት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ፖሊሽዎችን ፣ሩሲያዎችን፣ ዩክሬኒያዎችን፣ ስላቮችን፣ጥቁሮችን ፣ ጅፕሲዎችን፣ሰርብዎችን ፣ሮማኒያዎችን ፣አካለ ስንኩሎችን ወዘተ.. ያለፍርድ በጅምላ ጨፈጨፉ/መነጠሩ ። የሂትለር ቀኝ እጅ በነበረውበአዶልፍ ሃይክማን (Adolf Eichman) አዛዥነት 6 ምሊዮን አይሁዶችን በመርዝ ጋዝ አፍነው ሸረከሟቸው ። ድርጊቱ ሆሎኮስት (Holocaust) በአይሁዳዎች ቋንቋ ሸወአህ(Shoah) በመባል ይታወቃል ።

21ኛው መቶ ክ/ዘመን በኢትዮጵያ የተፈጠረው ናዚዝም ማለት የአክራሪ የቀኝ ክንፍ ብሄርተኛ ወያኔ/ህወሃት በባንዳው መለስ ዜናዊ መሪነትየፊንፍኔ ቤተገዢዮችን አምባ በቁጥጥር ሥር ካዋለ ማግስት ጀምሮ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የፈጸመው ግፍና ደባ ናዚዮች በጀርመን ሕዝብና በጀርመን ላይ ከፈጸሙት ግፍና ደባ የከፋ ነው ። እንዴት?

የግብረ ሰናይነት መተክልና የአገሮች ልዑላዊነትን ሕግ የጣስ ቢሆንም የጀርመኑ ፋሽስቶችና ናዚዮች ጀርመንን ለማስፋፋትና ለማተለቅ ተዋጉ እንጂየጀርመንን ልዑላዊነት ለማስደፈር ፣ የጀርመንን ዳር ድንበር ለመቆራረስ/ለመሸንሽን ፣የጀርመንን የባህር በር ለማስወሰድ ፣የጀርመንን ብሄራዊ ቋንቋ ለማሳነስ ፣የጀርመንን ታሪካዊ ቅርሳ ቅርስ ለማጥፋት ወዘተ.. አልተነሱም ፣አልተዋጉም ፤ፖሊሲ አላወጡም ። በዚህ ምክንያት ነው ወያኔ/ህወሃት ከጀርመን ፋሽስቶቻና ናዚዮች የከፋ ነው ያልኩት/የምለው ። አስተውሉ ከእነዚህ ግዙፍ ከናዚዮች ታሪክና ለሃያ አምስት ዓመታት ደጋግመን ከሰማነው እኮይ/መሰሪ የወያኔ ታሪክ መቀንጨብ የፈለኩበት ምክንያት ፤ ላስተላልፈው ከፈለኩትን መልዕክት ጋር ስለሚዛመድ ብቻ ነው ( for being contextual with this article`s message)

የትግራይን ግዛት ለማስፋፋት/ለማተለቅ የትግራይ አጎራባች ክ/ሃገሮችን ድንበር ጥሶ በጠመንጃ አፈሙዝ/ በሃይል ከወሎ ፣ከጎንደር ፣ከአፋር ፣ከወልቃይት ከጋምቤላ ወዘተ.. ምርጥና ለም መሬቶች ወስዶ ወደ ትግራይ አካሎዋል ። የወያኔ/የህወሃት ምሥራ ቾችና የአሁኑ ገዢዮቻችን በተግባራቸውና በሥነልቦና ፀረኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕ ዝብ ይሁኑ እንጂ በትውልድ (by birth) ኢትዮጵያውያን አይደሉም ብሎ የሚከራከር ያለ አይመስለኝም ። ወያኔ/ህወሃት ኢትዮጵያን ወረረ በማለት ስለሚነሱ ክርክሮችና አመለካከቶች ከሚመስል የወረራ መስፈርቶች ወይም ማስረጃዎችጋር አጣጥሞ መጻፍ ስለሚያስፈልግ በሌላ ግዜ እመለስበታለሁ ።

በተመሳሳይ፥ የ21ኛው መቶ ክ/ዘመን የኢትዮጵያው ፋሽስትናዚ ማለት ወያኔ/ህወሃት ከሁሉም አገራት ባንድራዎች ቀደምትነት ያለው መሆኑን የሚታወቀው ፤ቢያንስ እ..አ ከ1900 .ም ጅምሮ ማለት እ..አ ሰኔ (June) 28/1919 ከተመሰረ ተው (League of Nations) በመባል ከሚታወቀው የያኔ የዓለም መንግሥታት ድርጅት ከመመስረቱ በፊት እውቅና ያገኘው `ሰንደቅ ዓላማችንን የመቶ ዓመት ታሪክ ያለው አገር የሚወክ ል ጨርቅ በመሆኑ ወያኔ/ህወሃት ለሚገዛው ኢትዮጵያ አይወክልም በማለት በምትኩ የሰይጣናዊ መንፈስ እምነት (satanic cult) ተከታዮችን ምልክት/ሲምቦል በሆነው ባንድራ ተካው (ወያኔ/ህወሃት) ፤ ባንድራ የጣሊያን ስም መሆኑን ለሁላችንም ግልጽ ይመስለኛል ፤ እዚጋ ባንድራ ስል ወያኔ ሆኜ መናገሬ ነው ።

25 ዓመታት ዓይተነው ዓይተነው የሰለቸን ሰለሆነ ምስሉን እዚህ ጋ መለጠፈ አልፈለኩም ። Satanic cult ritual (SRA), sometimes known as ritual abuse, ritualistic abuse, organised abuse, sadistic ritual abuse and other variants) was the subject of a moral panic that originated in the United States in the 1980s; spreading throughout the country and eventually to many parts of the world by the late 1990s https://en https://en.wikipedia.org/wiki/Satanic/ ግልጽ እንግሊዝኛ ስለሆነ ወደ አማርኛ መተርጎም አልፈለኩም ።

ወያኔዎችም ጫካ እያሉ በሚሠርዋቸው ተንኮሎች ፣ በሚፈጽሟቸውን ግፎች ፣ባፈሰሱት የሰው ደም ወዘተሲሸበሩና ሲደናገጡ ለሰይጣናዊ ለ(satanic cult) እምነት የሆነው ምስል/symbol ይማጸኑ ነበር ማለት ነው ። ስለሆነም ቀንቷቸው የፖሊቲካ ስልጣን ሲጨብጡ ባንድራቸ ው አደረጉት ማለት ነው ።ይህንን አስመ ልክቶ በርካታ አተያይ/ቪዩ ማስቀመጥ የሚቻል ቢሆንም ፤ አንባቢ ላለማስልቸትና ጊዜ ከመቆጠብ አንጻር ማሳጠሩን መርጥኩ ።

በዲሞክራሲያዊ ሕገመንግሥት ሥርዓት በዜግነት ፖለቲካ ለሥልጣን መወዳደር በማይቻልባቸው ፤ በጠመንጃ አፈሙዝ የፖለቲካውን ሥልጣን በአምባገነን ንጉሣዊ (absolute monarchy) ሥርዓት ፣ ህዳጣን ብሄር /ብሄረሰቦች እና ወታደራዊ መንግ ሥት በሚፈራረቁበት እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች ከፖልቲካ ሥልጣን የተገለሉ ወይ ም እዚያ መድረስ የማይችሉ የአናሳ ብሄረሰበ አባሎች በንግድና በተራ ሥራ ዘርፍች እንድሚሠማሩ ከአንዳንድ ግራ ዘመም የፖለቲካ ሳይንስ መፅሃፍት መማር ይቻላል ።

በመሆኑም አሁን እስከ ደረስንበት 21ኛው መቶ ክ/ዘመን የጉራጌ ብሄረሰብ የጠመንጃ አፈሙዝ ተጠቅሞ ለፖለቲካ ሥልጣን ከማይወዳደሩ አናሳ ብሄረሰቦች አንዱ ለመሆኑ ምስክሩ የኢትዮጵያ ታሪክ ነው ። ምክንያቱ/መነሻው ለምን እንድሆነ ባይታወ ቅም የጉራጌ ብሄረስብ ሥራ ወዳድነት ከሌሎች የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ሁሉ የተለየ ስለመሆኑ እዚህ ጋ መግለጽ ለቀባሪ መርዶ ማርዳት ይሆንብኛል ፤ “necessity is the mother of invention” ማለት ችግር ብልሃት ያስተምራል ስለሆነ ይሆን ? “Labour created man himself” (Frederick Engels) ማለት ‘ሰውን ሰው ያደረገው ሥራው ነው’ የተሰኘው (የፌደሪክ ኤንጅልስን) ጥቅስ ወይም መርህ የሥራ ባህላቸው ያደረጉት ፈሬደሪክ ኤንግልስ ገና ሳይወለድ ነው ።

ከጫማ ጠራጊነት አንስቶ በየትኛውም ዝቅተኛ የሥራ ዘርፎች ተሠማርተው በመስራት የሥራ ክቡርነት ለኢትዮጵያ ሕዝብ አስተምረዋል ። ከተሰማሩባቸው የሥራ ዘርፎች አንዱ ነግደው የመኖር ዘርፍ ሲሆን ከሱቅበደረቴነት ንግድ እስከ አስመጪና ላኪ (exporters and importers) ለመሆን በቅቷል ። በቅድመ ወያኔ/ህወ ሃት በኢትዮጵያውያን የሃብት አሰላለፍ በርካታ ጉራጌዎች የኢትዮጵያ ብሄራዊ ከበርቴ ለመሆን በቅተው ነበር ። አሁን ግን እንኳንስ የኢትዮጵያ የአንድ መንደር ከበርቴ የሆነ ጉራጌ የለም ።

ሂትለር አይሁዶዎችን ከጠላበት ምክንያቶች አንዱ ሃብታም በመሆናቸው ቀንቶባቸው እንድ ነበረ ከላይ ጠቅሼአለሁ ።ወያኔ/ህወሃት ጉራጌዎች የጠላበት ምክንያቶች ሁለት ናቸው ። (1) በንግዱን ዘርፍ ቀንና ለሊት ሠርትው በሃብት ከሌሎች ብሄረሰቦች በልጠው በመገኘታቸው ቀንቶባቸው ነው ። ጉራጌዎችን በንግዱ መሥክ የነበራቸውን የበላይነት ለማዳከምና ከዚያ ለማፈናቀል ፤ ከአቅማቸው በላይ የሆኑ ግብሮች፣ ቀረጦ ችና የባንክ ወለዶች ጫነባቸው ። የማይችሉትን የቤት ክራይ በማስከፈል ለንግድ ምቹ ከሆኑ ቁልፍ ቁልፍ መናኽርያዎች አፈናቀላቸው ፤ በሱቅበደሬተነት ከቦታ ቦታ በመዘዋወር ይነግዱ የነበሩትንም እነሱን ለማባረር በተመደቡትን ፖሊሶች በየእለቱ ይደርሥባቸው በነበረው ዱላ ድብደባ ተማ ርረው ወደ ለምኖ የመኖር ሕይወት ተሰማሩ ።

ህወሃት የጉራጌ ነጋዴዎችና ቤተሰባቸው ሰብስቦ እንደ ሂትለር መርዛማ ጋዝ አሳጥኖ ባይፈጃቸውም በረሃብ ፣በድኅነትና በእነዚህ ምክንያቶች በሚመጡ በሽታዎች በቀስ በቀስ ወይም ባዝጋሚ ሞት እንዲያልቁ አደረገ ። የንግዱን ዘርፍ በህወሃት የንግድ ተቋ ም ፣የህወሃት የፕለቲካ አቅም በሚያጠናክሩ ትውልደ ትግራይ በሆኑትን ኩባኒያዎች ፣ ቡድኖች ፣ግለሰዎችና ካድሬዎች ተተካ (2) ህወሃት ጉራጌዎችን የጠላበት ሁለተኛው ምክንያት አማራን ወግነው ፀረህወሃት አቋም አላቸው በሚል ነው ። አዎን ወያኔ የኢ ትዮጵያ ሕዝብ በጎሣ ክልል ሸንሽኖ ማስተዳደርን አስመልክቶ ጉራጌዎች ቶሎ አሚን እንዳላሉትና እንደተፋለሙት በአንድ መጽሄት ተጽፎ አንብቤያለሁ ፤ “ከሰሜን የአገራ ችን ጫፍ እስከ ደቡብ የአገራችን ጫፍ ፤ ከምሥራቅ የአገራችን ጫፍ እስከ ምዕራብ የአገራችን ጫፍ ተዘዋውረን መኖርና መሥራት በትውልድ ዜግነት ያገኘነው መብታች” ነው የሚል ሙግት እንድገጠሙት ለግዜው ስሙን በረሳሁት አንድ የአማርኛ መጽሄት ውስጥ አንብቤያለሁ ።

ሂትለር የሃያላን ምዕራብ መንግሥታት አገሮች ማለት ታላቋ እንግሊዝ ፣ ፈራንሳይና የሶቭየት ኅብረትን በመውረሩና የእነዚህን አገሮችና የአሜሪካ የኢኮኖሚ ጥቅሞች ለመሻማት በመዳፈሩ ፋሽስት አሉት እንጂ ፤ ሂትለር በጀርመንና በጀርመን ሕዝብ ላይ የፈጸመው ግፍ ወያኔ/ህወሃት በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ከፈጸመው ግፍ በልጦ አይደለም ። ወያኔ/ህወሃት በእነዚህ ሃያላን መንግሥታት ጫማ ሥር በመውደቁ ና ለእነሱ ጥቅም የሚገለባበጥ በመሆኑ መቶውኑ ምሊዮን የኢትዮጵያ ሕዝብ ቢግል/ቢጨፈጭፍ ፋሽስት አይሉትም ።

ወልደአብ ደንቡ

http://www.ethiopanorama.com