ከደረጀ ተፈራ
መጋቢት 2፣ 2009 ዓም
……………………………….

March 11, 2017 17:49

1). ዮሐንስ (ካሳ ምርጫ) አጼ ቴዎድሮስን አስገድለው ለመንገስ በነበራቸው የስልጣን ፍላጎት የተነሳ
እንግሊዝን መንገድ መርተው በማምጣት ለአጼ ቴዎድሮስ ሞት ምክንያት ሆነዋል።
2). ከአጼ ቴዎድሮስ ቀጥሎ የነገሱትን አጼ ተክለ ጊዮርጊስን (ዋግ ሹም ጎበዜ) በጦርነት ከማረኳቸው
በኋላ አስሮ ወይም በግዞት ማስቀመጥ ሲችሉ ሐይማኖት እንደሌለው አረመኔ ሁለቱንም ዓይናቸውን
በወስፌ  ጎልጉለው በማውጣት በጭካኔ አሰቃይተው ገድለዋቸዋል።

3). አጼ ዮሐንስ ቅድሚያ የሚሰጡት ለኢትዮጵያ ሳይሆን ለስልጣን፣ ለዝናና ለሃብት (ለዘረፋ) ነበር።
ለምሳሌ፦ (ሀ). አጼ ቴዎድሮስ ቢሞቱ እነግሳለሁ በማለት የባህር በር ለጠላት እንግሊዝ ክፍት በማድረግ
የሃገራችንን ሉአላዊነቷን (Sovereignty) አስደፍረዋል። (ለ). የጎጃምን ህዝብ ከብቱንና እህሉን ዘርፈዋል።
4). አጼ ዮሐንስ በሃይማኖት እኩልነት አያምኑም። ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት የሚል አዋጅ በማስነገር
የሙስሊም፣ የይሁዲና የሌሎች እምነት ተከታይ ወንድሞቻችን ዘንድ ቅሬታ በመፍጠር በኢትዮጵያ ላይ ቅሬታ
እንዲኖራቸው አድርገዋል።
5). ዮሐንስ የወሎ ሙስሊም ኢትዮጵያዊያንን በግድ እምነታችሁን ቀይሩ በማለት አዋጅ አስነግረዋል።
አንጠመቅም  ያሉትን ህፃንና ሽማግሌ ሳይለዩ በጅምላ ቁጥራቸው ከ30ሺህ በላይ የሆኑ ሙስሊም
ኢትዮጵያውያንን ቦሩ ሜዳ  ላይ በጅምላ ጨፍጭፈዋል፣ ምላሳቸውን ቆርጠዋል፣ አፍንጫቸውን ፎንነዋል፣
ከንፈር ገሽልጠዋል።
6). በኢትዮጵያ ታሪክ ስደት የተጀመረው በዮሐንስ ጊዜ ነው። አጼ ዮሐንስ “እስላም ሃገር፣ አሞራ ቤት
የለውም” የሚል አዋጅ ወሎ ላይ በማወጅ የወሎ ሙስሊም አማሮችን አሰድደዋል።
ወሎ ተጠመቅ እምቢ ካልክ ሃገር ለቀህ ውጣ በማለት አሳድደዋቸዋል።
በዮሐንስ ጭቆና የተነሳ በሩን ዘግቶ ከእናት አባቱ ሃገር በእምነቱ ብቻ በርካታ ህዝብ ከወሎ ወደ ሱዳንና ወደ
ደቡብ ኢትዮጵያ ተሰዷል።
*ዮሐንስ ከሞቱ በኋላ አፄ ምኒልክ እንደነገሱ “ሁሉም እንደ እምነቱ ይኑር” የሚል አዋጅ በማወጃቸው ተሰደደው
የነበሩ በርካታ የወሎ ሙስሊሞች ወደ ትውልድ አገራቸው ተመልሰዋል።
7). ዮሐንስ ቂመኛ፣ በቀለኛና እንደ ስማቸው “በዝብዝ ካሳ” በዝባዥ ነበሩ።
ለምሳሌ፦  የጎጃሙ ንጉስ ተ/ሃይማኖት አልታዘዘልኝም በሚል ምክንያት ቂም ቋጥረው የሚበቀልበትን
ጊዜ ሲጠባበቁ ቆይቶ በጎጃም አካባቢ ተነስቶ የነበረውን ቅባት የተባለ ሃይማኖታዊ አስተምህሮን ምክንያት
በማድረግ  ጉዳዩን ከካህናቱና ከሃይማኖቱ አባቶች ጋር መነጋገር ሲችሉ፣ በትግሬ አገር እንደዚህ ዓይነት ነገር
የለም እናንተ  ከየት አመጣችሁት በማለት ተራውን የጎጃም ህዝብ በየ መንገዱና በየእርሻው ያገኙትን ሰው
ሁሉ በጭካኔ በመግደል የጅምላ ጭፍጨፋና ፈጽመዋል። የጎጃምን ህዝብ ከብቱንና እህሉን ዘርፈው ወደ
ትግራይ አግዘዋል።
8). ራስ አሉላን እንደ-መሾምና እንደ-መሸለም ለምን ያለኔ ፍቃድ ዶጋሊ ላይ ከጣሊያን ጋር ተዋጋህ በማለት
ከስልጣን መሻራቸው (የቁም እስረኛ ማድረጋቸው)።
9). አጼ ዮሐንስ የምኒልክን ሃይል ለማዳከም በማሰብ የምኒልክ ግዛት የነበረውን የወሎን ክፍል ቀምተው
ለልጃቸው ለማንገሻ ዮሐንስ መስጠታቸው።
10). አጼ ዮሐንስ 4ኛ ከእንግሊዝ ተወካይ ከሆነው ከአድሚራል ዊሊያም ሂዎት ጋር የሂዎት ውል / Hewett Treaty/ መፈራረማቸው። ይህ የሂዎት ውል በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ትልቅ ጠባሳ አስከተለ።
11). ኤርትራን እስከ መረብ ምላሽ ለጣሊያን አሳልፈው የሰጡት እራሳቸው አጼ ዮሐንስና ከሳቸውም
ቀጥሎ ልጆቻቸው
እነ መንገሻ ዮሐንስ መሆናቸው።
12). ዮሐንስ ለራሳቸውም ሆነ ለሃገራችን ደርቡሽ የሚባል የጎረቤት ጠላት አፍርተዋል።
ደርቡሾች (ሱዳኖች) መተማን በመውረር ጎንደርን ያወደሙት፣ ቤተክርስቲያን ያቃጠሉበት
ምክንያት በዮሐንስ ላይ ቂም ስለነበራቸው ነው። ምክንያታቸው አጼ ዮሐንስ በጠብ ጫሪነት
ለቀኝ ገዢዋ ለእንግሊዝ   አግዘው የሱዳንን ድንበር ጥሰውና ሉአላዊነታቸውን ደፍረው
በጀብደኝነት በመውረር ህዝቡን በመጨፍጨፋቸው የተነሳ ነበር።
ወያኔ ከአሜሪካና ከምዕራባውያን በሚያገኘው ዶላር የተነሳ መሃል ሶማሌ ድረስ ወታደሮቹን
በመላክ ህዝቡን  እንደሚጨፈጭፍ ሁሉ አጼ ዮሐንስም ለእንግሊዝ ተላላኪ በመሆን በጀብደኝነት
የደርቡሾችን ደም አፍሷል። የዮሐንስ ጣጣው ግን ለጎንደር ህዝብ ተረፈ።
13). አጼ ዮሐንስ የሱዳን የነጻነት ትግል ወደ ኋላ 72  ዓመት ጎትተዋል፣
የፓለቲካ ብስለት የሌላቸው ጀብደኛውና ጸብ ጫሪው ዮሐንስ ከእንግሊዝ ቀኝ አገዛዝ ሲታገሉ የነበሩትን
ደርቡሾች (መሃዲስት) ማገዝ ሲገባቸው በተቃራኒው በመውረራቸው ሱዳኖች ያደርጉት የነበረውን የነጻነት
ትግላቸው ላይ ቀዝቃዛ ውሃ አፍሰዋል፣ አደናቅፈዋል።
ሱዳኖች ከእንግሊዝ ነጻ የወጡት ብዙ ቆይተው በ1956 ሲሆን የሂዎት ውልን ዮሐንስ ለእንግሊዝ በመፈረም
ሱዳንን “በጀብደኝነት” የወረሩት በ1884 ነው። ስለዚህ አጼ ዮሐንስ የሱዳን ነጻነት ወደ ኋላ 72 ዓመት
ጎትተዋል ማለት ነው። በሌላ አነጋገር ዮሐንስ የሱዳን ህዝብ ለተጨማሪ 72 ዓመታት በቀኝ ገዢዋ እንግሊዝና
በተባባሪዋ ግብጽ ስር እንዲማቅቁ ያደረጉ የቀኝ ገዢዎች ተባባሪ ነበሩ።
14). አነሳሳቸው ከሽፍትነት፣ አስተዳደራቸው በዘፈቀደ፣ ውሳኔ አሰጣጣቸው የንጉስ ሳይሆን እንደ
ሽፍታ ነበር፣
እንግሊዝ ካሳ ምርጫን (ዮሐንስን) ለመንገድ መሪነት ባይመርጣቸው ኖሮ፣ ዮሐንስ እንኳን ንጉስነት
ቀርቶ ከሽፍትነትም የዘለለ ይህ ነው የሚባል ታሪክ አይኖራቸውም ነበር። ለንግስና የበቁበት አጋጣሚ
አፋር በረሃ በሽፍታነት ሲንገላወዱ ሳለ ለእንግሊዝ ወራሪ ሰራዊት የመቅደላን መንገድ በመምራት
በተሸለሙት የጦር መሳሪያ የንጹሃንን ደም አፍሰው ነው።
15). እና ሎሎችም።