አቶ ሐብታሙ አያሌው ከእስር ከተፈቱ በኋላ ሆስፒታል በሕክምና ላይ በነበሩበት ወቅት

“አንድ እስረኛ ተመርምሮ ሲመለስ መጀመሪያ የሚቀርብለት ጥያቄ ‘ተሰቅለህ ነበር ወይም አልተሰቀልክም?’ የሚል ነው የሚሉት ከእስር የተለቀቁት አቶ ሐብታሙ አያሌው ለማመን የሚከብድ ከባድ መከራዎች በእስር ቤት ውስጥ እንደሚፈፀም ይናገራሉ። አቶ ሃብታሙ አያሌው በዚህ ፕሮግራም ላይ ስለ ምርመራ ዓይነቶች በዘረዘሩበት ወቅት የሰጡት ማብራሪያ እጅግ ዘግናኝ በመሆኑ ሕጻናት ልጆች እንዳያደምጡት የወላጆችን ትብብር እንጠይቃለን። የቃለምልልሱ ሁለተኛ ክፍል ቅዳሜ ምሽት ይቀርባል።

የቀድሞው የተቃዋሚው አንድነት ፓርቲ ቃል አቀባይ በሽብር ወንጀል ተከሰው እሥር ቤት በቆዩባቸው ሁለት ዓመታት በምርመራ ሳቢያ ደረሰብኝ ያሉት ከባድ ስቃይ አሁን ለሚገኙበት የጤና ቀውስ እንደዳረጋቸው ይናገራሉ።ወህኒ ቤቶች ውስጥ የሚፈጸሙ ጭካኔ የተሞላባቸው ልዩ ልዩ የምርመራ ዓይነቶች በአብዛኞቹ እሥረኞች ላይ ሕልፈትን ጨምሮ ለተመሳሳይ የጤና ችግሮች እንደሚዳርጉም አቶ ሃብታሙ ያስረዳሉ።

አቶ ሃብታሙ አያሌው በዚህ ፕሮግራም ላይ ስለ ምርመራ ዓይነቶች በዘረዘሩበት ወቅት የሰጡት ማብራሪያ እጅግ ዘግናኝ በመሆኑ ሕጻናት ልጆች እንዳያደምጡት የወላጆችን ትብብር እንጠይቃለን። አቶ ሃብታሙ አያሌውን ያነጋገራቸው የፕሮግራሙ አዘጋጅና አቅራቢ ሰሎሞን ክፍሌ ነው።

አቶ ሃብታሙ ደረሱብኝ ያሏቸውን በደሎች በሚዘረዝሩበት ይጀምራሉ። – VOA Amharic


አቶ ሃብታሙ አያሌው በታሰሩበት ወቅት በመንግስት የቀረበባቸው ክስ“ሕጋዊውን የፖለቲካ ፓርቲ በሽፋንነት ተጠቅመው በአሸባሪነት ከተፈረጀው ግንቦት ሰባት ጋር በመገናኘት በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሽብር ተግባር ለመፈጸም አሲረዋል። ይህንንም ደርሰንበታል፤” ማለቱ አይዘነጋም።

አድማጮች የዚህ ቃለምልልስ ሁለተኛ ክፍል ቅዳሜ ምሽት ይቀርባል።