“… በአዲስ አበባ ውስጥ ማዕከላዊ ብቻ ሳይሆን በርካታ ቪላዎች ስም የሌላቸው እስር ቤቶች ሆነው ማሰቃያ ይፈጸምባቸዋል።ሀብታሙ አያሌው የደረሰበትን ሰቆቃ ሲናገር ስሰማ በጣም አዝኜያለሁ ነገር ግን ሀብታሙም ከባህሉ ከሀይማኖቱና ለአድማጭ ጭምር በመጠንቀቁ ሙሉ ለሙሉ የተፈጸመበትን ግፍ የተናገረ አይመስለኝም ።ትላንትም እንደ ሀብታሙ ያለ እና በሀብታሙ ላይ ከደረሰውም በላይ ስም ባላቸውና በሌላቸው እስር ቤቶች ብዙ ግፎች ተፈጽመዋል ዛሬም ያ አልቆመም። ችግሩ ይሄን ሰቆቃ ለአንድ ሰሞን ሰምተን እናዝናለን እንቆጫለን ቆይተን ትኩረታችን ሌላ ነው ።እነዚህን ግፍ ፈጻሚዎች በዓለም አቀፍ የተለያዩ ቦታዎች ለመፋረድ ይቻላል ይሄን ግን ማድረግ አልቻልንም ።አሁንም ግን እነሱን ለመፋረድ ስራውን የሚሰራ ተቋም ያስፈልገናል …” የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ሀይለማሪያም ከቤልጂየም በወቅታዊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ