ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ዕውቀት መለዋወጫ መረብ

የትግሬ ነፍጠኛ፣ የሸዋ ፈረሰኛ፣ የጎጃም እግረኛ፣ የአማራ ስልተኛ ከብ ይቀላው፣ ያናፋው፣ ያንደገድገው ጀመር። ከእንዝርት የቀለለ የጁየ፣ ከነብር የፈጠነ ቤጌምድሬ፣ ከቋንጣ የደረቀ ትግሬ፣ ከአሞራ የረበበ ሽዌ፣ ከንብ የባሰ ጎጃሜ እያባረረ በየጎዳናው ዘለሰው። አውሬ የነጨው ነጭ መንጋ እየመሰለ በየዱር ሆዱን ገልብጦ ወደቀና የአሞራ ቀለብ ሆነ።

መጋቢት ፲፭ ቀን ፪ ሺህ ፱ ዓ. ም.

በወለላዬና በዶክተር ተድላ ሀሳብ ላይ ተጨማሪ፥ በቅድሚያ ክብር በደምና በአጥንታቸው አንድነት ሀገር ላቆዩልን ለአድዋው ጀግኖች በሙሉ፥ ወለላዬ በስዊድን የመቶ ሃያ አንደኛው ዓመት የአድዋን ድል መዘክርና በዝግጅቱ ላይ የነበሩትን ክስተቶች ስላሳወቁን ብቻ ሳይሆን ምላሽ በመስጠትዎና ለሚመለከተውም ጥሪ በማድረግዎ ምስጋናችን የላቀ ነው። በእኛም በኩል የመቶ ሃያ አንደኛው ዓመት የአድዋን ድል በመጣጥፎች ለመዘከር ዝግጅት በምናደረግበት ጊዜ አንዳንዶቻችን የእቴጌ ጣይቱን ታላቅ አስተዋጽዖ ለብቻው ማዘጋጀት ጀምረን፥ ነጥለን የምናወጣው ታሪክ ጎደሎ ሆኖ ስላገኘነው አድዋን ከመላው ጀግኖቹ ጋር መተረኩ የተሟላ ሆኖ አግኝተነዋል።

ይህ ጽሑፍም በስዊድን የመቶ ሃያ አንደኛው ዓመት የአድዋን ድል ለመዘከር እ. ኤ. አ. ማርች አምስት (፭) ቀን (፪) ሁለት ሺህ አስራ ሰባት (፲፯) ዓ. ም. በነበረው ዝግጅት ላይ ፕሮፌሰር ተከስተ ነጋሽ ያደረጉት ንግግር፣ ስንትና ስንት ሕይወት የተከፈለበትን የአድዋን ድል በዕድል ነው የተገኘው ማለታቸው ከአንድ አፍሪካዊ የሚጠበቅ ነው? ለምንስ ንግግራቸው ከቀድሞው የደቡብ አፍሪካ መሪ ከሚስተር ታቦ ምቤኪና ከፕሮፌሰር ዮናስ ሬይሞንድ ተቃራኒ ሆነ? ፕሮፌሰር ማሞ ሙጬንና ታቦ ምቤኪን በማገናኘት የሰጡት የግል አስተያየትስ የጓደኛቸው የፕሮፌሰር ማሞን ጥልቅ የምርምር ጽሁፎችና አፍሪካዊ ስራዎች ያንጸባረቀ ትክክለኛ መረጃ ነው? መረጃቸውና ንግግራቸውስ አነጋጋሪ ሆኖ “ሶስቱንም አጣጣሉ” ተብለውስ ለምን ስማቸው እንዲነሳ አደረገ? የምኒልክን ባህርይ የሚጻረር በመናገራቸውም ‘እምዬ ምኒልክ ወላዋይ ነበሩ ወይ?’2 ብለው ወለላዬ የተባሉ ጸሐፊ በኢትዮሚድያ ድህረ ገጽ ላይ እንዲጠይቁ ስላነሳሳቸው ይህን ጥያቄ የታሪክ ባለሙያዎች በአግባቡ እንደሚመልሱት በመተማመን በዚህ ጽሑፍ ለጊዜው ከታላቁ የአፍሪካውያን ድል አንጻር ለመዳሰስ እንሞክራለን።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ