https://www.youtube.com/watch?v=6wuuaJ5Bn1I

ኢሕአዴግና ሃያ አንድ ሀገር አቀፍ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቅድመ ድርድር

በኢትዮጵያ መንግሥትና ሃያ አንድ ብሔራዊ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ከሚካሄደው የቅድመ ድርድር ሂደት ትልቁ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብስብ መድረክ እራሱን አገለለ።

የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ለአሜሪካ ድምፅ ራድዮ እንዳብራሩት መድረክ በቁጥጥር ሥር የሚገኙ አመራር አባላቱ እንዲፈቱና በመሪ ተደራዳሪነት በውይይቱ ለመሳተፍ ያቀረበው ጥሪ ምላሻ ባለማግኘቱ፤ ከጠረጴዛው መነሳታቸውን ገልፀዋል።

ስድሥት ተቃዋሚ ድርጅቶች አዲስ የመሠረቱት ሌላ ጥምረትም፤ ኢሕአዴግ አደራዳሪ አልሰየመም ሲሉ ወንበራቸውን ስበው፤ ወረቀታቸውን ሰብስበው ከድርድሩ ለመነሳት ያላቸውን አዝማሚያ አስረድተዋል።

የኢህአዴግ ድርጅታዊ መሪ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፤ ድርድሩ ከተቀሩት ተቃዋሚዎች ጋር ይቀጥላል ብለዋል።

http://amharic.voanews.com/a/ruling-party-opposition-negotiation-3-29-2017/3787157.html