ጀዋርና ቡድኑ ከመጀመሪያውም ልዩ ሴራ እንደነበረው ለመረዳት ልዩ

የሲአኤ መረጃ አያስፈልግም ነበር፡፡ ችግሩ ከነፈሰው የሚነፍስ የዲያስፖራ

ማህበረሰብ መገለባበጥና ትኩረት የሌለው የወሮበሎች አጫፋሪ መሆኑ

ነው እንጂ፡፡ ሰው ቢኖር ኖሮ ገና ድሮ ጀዋር በአሜሪካን አገር ተቀምቶ

በሚዲያ በሜጫ የሰውን አንገት እቆርጣለሁ ሲል ይህ ንግግሩ በአገሩ ሕግ

መሠረት ሊያስጠይቀው በቻለ ነበር፡፡ እኔ የአሜርካን ሕግ አላውቅም፡፡

ሆኖም እንዲህ ያሉ ንግግሮችን የሚናገር ሰው ሊያውም በሕዝብ መገናኛ

ከራሱ አልፎ ሌሎችንም ሰውን በሜጫ አንገቱን ቁረጡ የሚል አዋጅ እያወጀ

እንደሆነ ታስቦ ዛሬ አይሲስ እየተባሉ ከሚጠሩት አሸባሪዎች እንደ አንዱ

ያስጠይቀዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ እርግጥ ነው የአሜሪካ ፖሊስ አማርኛ

ወይም ኦሮምኛ ላይሰማ ይችላል፡፡ ግን እኮ መሠረቱ ኢትዮጵያ የሆነ የአሜሪካ

ፖሊስም ይኖራል፡፡ ያም ባይሆን ስንት ስለኢትዮጵያ አስባለሁ እያለ የሚደነፋ

ዲያስፖራ ባለበት እንዲህ ያሉ ግለሰቦች በሕዝብ ላይ የግድያ ዛቻ እየዛቱ ዝም

መባሉ ከሚያሳዝኑኝ ነገሮች አንዱ ነው፡፡ ጭራሽ ትልቅ ትኩረት እየሰጡት

ትልልቅ መገናኛ ብዙሀን ሳይቀሩ ተጋባዥ እንግዳ አድርገውታል፡፡ ይህ ይገርማል፡፡

ይህ ነው ስለአገር አስባለሁ ባይ ዲያስፖራ፡፡

በሌላ በኩል ሰዎች ጀዋርና ቡድኑ ከሚያስበው ውጭ ከተናገሩ ዘመቻ

ይዘመትባቸዋል፡፡ በቅርቡ ፕ/ር ኃይሌ ላሬቦ ከዚያ በፊት ታዋቂው

የጀርመን ድምጽ ጋዜጠኛ ይልማ ኃ/ሚካኤልና የጅርመን ድምጽ ራሱ

የዚሁ ጀዋር የሚመራው የሽብር ቡድን ዘመቻ ከከፈተባቸው ናቸው፡፡

በምን መለኪያና መስፈርት ነው ሰውን በሜጫ አንገቱን እቆርጣለሁ

እያለ በየመድረኩ የሚዝት ሰው እሱ ሕጋዊ ሆኖ ሕጋዊ መሠረት

ያላቸውን ባለሙያዎችና ተቋማት ይህን ያህል ለመገዳደር እድል ያገኘው;

የጀዋርና ቡድኑ አዲሱ ዘመቻ

ሰሞኑን ቴዴ አፍሮ ዘፈኖቹን ይለቃል ሲባል ብዙ የሚያዝተዛዝቡ ነገሮች

እየተነሱ ነው፡፡ እንዳንዱም አስቂኝ ነው፡፡ ሁሉም ግን መሠረቱ ከቅናት

የተነሳ ይመስላል፡፡ የቴዲ ዘፍን ሰባኪዎችንም አነቃቅቷል፡፡ እስከዛሬ ስንቱ

ዳንኪራ ሲጨፍር ትዝ ያላላቸው ዘፋኝነት ሀጥያት ነው የሚለው የመጽሐፍ

ጥቅስ ትዝ እንዲላቸው አድርጓል፡፡ ስለ እምነት ጉዳይ ብዙ ማለት

አልፈልግም፡፡ ሁሉም የመሠለውን ይመን፡፡ ሆኖም ግን ፈላስፋውፎች

የቀደሙ አባቶች የተናገሩበትን ሁኔታ ማስተዋልን ትተን ተንኮለኞች

ለራሳቸው እንዲመች ጥቅስ ሲጠቅሱ ስናይ ያበሳጫል፡፡ ፈላስፋው

ቅዱስ ጳውሎስ በጻፈው ደብዳቤ የተጠቀሰው ዘፈን ማለት ማህበራዊና

(የሴትና የወንድን ፍቅር ዜማ ጨምሮ) አገራዊ ጉዳዮችን በሥርዓትና በወጉ

ማዜም ከሆነ ሰው ሁሉ በዘፈን ምክነያት የገሀነም እራት ሊሆን ነው፡፡

አንሸዋወድ፡፡ ብዙዎቻችን መጽሀፍ ቅዱስን የምናነበው ከእምነት መጽሀፍነቱ

አንጻር ብቻ ነው፡፡ ይህ እኛን እየጎዳ የራሳቸውን ምኞች ለማሳካት ለሚሮጡ

ግለሰቦች ትልቅ እደል ፈጥሮላቸዋል፡፡ በየትኛውም ህዝብ ዘፈን አለ፡፡ ሁሉም

እንደባህሉና ወጉ በአዘቦትም በተለያዩ ማሕበራዊና አገራዊ በዓላትም

በዘፈን በዓላቱን ደስታውንና ሀዘኑንም ይቀልጻል፡፡ ሌሎች መልዕክቶችም

ያስተላልፋል፡፡ ጌታ እና እናቱ የተገኙበት ገሊላው ቃና ሰርግ ሳይቀር በዘፈን

የደመቀ እንደነበር እናስበለን፡፡ የዚያ ሕዝብ ባህሉ እንደዛ ነውና፡፡ ይበቃኛል

ስለዚህ ጉዳይ፡፡ ይልቁንም ሰሞኑን የጀዋር ቡድን በቴዲ ላይ ስለከፈተው

ዘመቻ እንድታስተውሉ፡፡ ዘመቻውም እንደተለመደው ነው፡፡ ጀዋርና ቡድኑ

ሰውን ለመግደል በይፋ በአደባባይ መናገር በሕግ የማይጠየቁበት

መብታቸው እንደሆነ መረዳታቸው ብቻም ሳይሆን በግልጽ በሕዝብ ላይ

ግድያን ለመፈጸም መረጃ በማኅበዊ መገናኛ መለዋወጣቸው ያሳዝናል፡፡

ደግሜ  እላለሁ በያለበት ያለ ዲያስፖራ እነዚህን ግለሰቦች እንኳን በሚኖሩበት

አገር መንግስት የሚናገሩትን አደገኛ ዛቻ አሳውቆ እርምጃ ማስወሰድ

ሲችል አፍ ይካፈታል፡፡ ይሄው የቴዲ ዘፈን የጀዋርን ቡድን እንደልዩ ነገር

ነው የናደደው፡፡ እንደተለመደው የኦሮሞን ሕዝብ ፍላጎት ሁሉ የራሳቸው

ስለሚመስላቸው ኦሮሞ የተባልክ ሁሉ የቴዲን ዘፈን አትግዛ ማለት

መብታቸው ነው፡፡ ሰሚ ከአገኙ፡፡ ይሄ በራሱ አእምሮ ላለው ትልቅ

ወንጀል ቢሆንም ቴዲን መግደልን አዋጅ ማወጅን ግን አይተካከልም፡፡

አይሲስ በየአገሩ እኮ የሚያደርገው ይሄንኑ ነው፡፡ ከላይ ጀዋር ለዘመናት

የክርስቲያኑን አንገት በሜጫ መቀንጠስን ሀይማኖታዊ መብቱ እንደሆነ

ሲነግረን ኖረ፡፡ ዛሬ ደግሞ ሕዝብ የሚወዳቸውን ሰዎች እያደኑ መግደል

የእሱ ተከታዩች ዘመቻ እያካሄዱ ነው፡፡ ይህን ደግሞ እየተናገሩ ያሉት

በግልጽ የእስልምና እምነት ተክታዮች እንደሆኑ ልናስተውል ይገባል፡፡ ነገሩን

እንደ ተራ ነገር እየታየ እስከዛሬ ችላ የተባለበት ሂደት በራሱ በብዙ ነገር

ዋጋ አስከፍሏል፡፡ ይሄ ከቴዲ አፍሮ ጋር ብቻ የተገናኘ ጉዳይ አይደለም፡፡

ቴዴ አፍሮን የሚኒሊክ ወዳጅ በሚል ከላይ በአነሳሁት ታሪክ ጋር

አያይዘው በማጥላላት፣ ከአባቶቹ ታሪክ ጋር የተጣላውንና ዛሬ እየባዘነ

በጠላቶች የሚዘወረውን ኦሮሞ ትውልድ ድጋፍ እነዳስገኘላቸው እናውቃለን፡፡

እንኳንስ ኦሮሞ ነኝ የሚለው የዛሬው የመከነው ትውልድ ቢጠላውም ልዩ

የኦሮሞ ልጆች የስኬት ታሪክ የሰሩበትን የሚኒሊክን ታሪክ ይቅርና በእርግጥም

የኦሮሞን ሕዝብ ያለተሳተፈበት ታሪክ ቢሆን ቴዴ በግሉ ያንን ታሪክ ማድነቅ

መብቱ ነው፡፡ እነሱም ያንን ከእኛ አልፎ አፍሪካንና በዓለም ሁሉ ያሉ የነጻነት

ናፋቂዎች ሁሉ ሳይቀር ተስፋና ኩራት የሆነውን ታሪክ ለማጥላላት መብት

አግኝተው እንደልባቸው እየፈነጩ ነው፡፡

ጀዋራውያንና ወያኔ

ሌላው እንዴት ሰዎች እንደተጋረደባቸው የማይገባኝ ጀዋር በኦሮሞ ሕዝብ

ላይ የነገደው ንግድ ነው፡፡ ጀዋር ከወያኔ ጋር ግንኙነት እንዳለው ለመረዳት

የዚያን ያህል የተመሰጠረ አካሄድ የለውም፡፡ ይልቁንም አዚም እንዳለው

አላውቅም፡፡ የኦሮሞን ልጆች አደባባይ ያለምንም ስልታዊ ሁኔታ እየወጡ

ለወያኔ የጥይትና የስቃይ ሰለባ እንዲሆኑ ሁኔታዎችን ሲያመቻች ነበር፡፡

ኦሮሚያ ውስጥ ሲካሄድ የነበረውን አመጽ ወደ ራሱ ቀለበት አዙሮ ውጤት

አልባ እንዲሆን ትልቅ ሚና ተጫውቷል፡፡ ለጀዋር ሚዲያም ጥሩ ዜና ሆኖለት

ገንዘብ ማግኛ ሆኖለታል፡፡ በመጨረሻም ወያኔ አጣብቂኝ ውስጥ ስትገባ

በልዩ ሁኔታ  እየተቀጣጠለ የመጣውን ሕዝቦችን አንድነት ለማምከንና

ወያኔን በሕብረት ከተነሳባት የሕዝብ ማዕበል ለማዳን የለንደኑንና

የአትላንታውን ጉባዔ በማዘጋጀት ትልቅ ውለታ ለወያኔ የጀዋር ቡድን ሰራ፡፡

ጀዋር በኢሳት ቀርቦ ሳያፍር ነው ትግሉ ወያኔን በአስቸኳይ እንዲጥል

አልፈለግንም ያለው፡፡ የጎንደሬዎቹ የኦሮሞ ደም የወንድሞቻችን ደም ነው

የሚለውና የእነበቀለ ገርባ ፎቶ በፋሲል አደባባዮች በክብር ማውለብለብ

ለወያኔና ጀዋራውያን እጅግ አስደንግጧቸው ነበር፡፡ ይባስ ለጎንደሬዎቹ

የወገንተኝነት አጸፋ በኦሮምያ ልዩ ልዩ ቦታ የተነሱ ሰልፎች አማራ ወንድሜ

ነው በማለት 25 ዓመት ሙሉ የታቀቡትን ወንደማማችነታቸውን

አስተጋቡት፡፡ ያኔ ነበር ጌታቸው ረዳን በድንጋጤ እንዴት አማራና ኦሮሞ

አንድ ሊሆኑ ቻሉ ብሎ በይፋ በሕዝብ መገናኛ እንዲባርቅበት የሆነው፡፡

ከዘህች ጊዜ ጀምሮ እንደገና  ይህን ሕዝብ ለመለያየት ጀዋርና ቡድኑ ከወያኔ

ጋር አብረው ሲዶልቱ ነበር፡፡ ወያኔ ጀዋርና ቡድኑ በብዙ ኦሮሞ ዘንድ

ተቀባይነት እንዳለው ስለምታውቅና እነጀዋርም የወያኔን ውለታ አሁንም

ቢሆን የሚያገኙትን ጥቅማ ጥቅም  በማሰብ ሌላ የወዳጅነት ምዕራፍ

ጀመሩ፡፡ ለንደንና አትላንታው የዚህ ውጤት ነበር፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ

የወጣው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሽብርተኛ ነህ በሚል አዋጅ ለማወጅና

በሕግ ተመስርቶ ሕዝብን ለመግደልና ለማሰቃየት መረጃ የሚሆን

ክስተትን መፍጠር ነበር ለእነጀዋራውያን የተሰጣቸው ሚና፡፡ በለንደን

ያደረጉት በትክክል ይህን ከወያኔ የተቀበሉትን ሴራ ነበር፡፡ የጀዋር

ቡድንን ብታዩት አንዳንድ ተደነባብረው በአጀብ ከተቀላቀሉት ውጭ

በብዛት ከወያኔ መንግስት ጋር ግንኙነት ያላቸው ናቸው፡፡ ራሱን ጀዋርን

ጨምሮ አብዛኞቹም ወደውጭ አገር የሄዱት በወያኔ እድል ተሰጥቷቸው

ተልከው ነው፡፡ የለንደኑን ተናጋሪ ጨምሮ ብዙዎቹ በወያኔ እድል የተሰጣቸው

በአገር ቤት ሕዝብን ሲያሰቃዩ የነበሩ ጅብ የማያውቁት አገር ሄዶ …

የተባለው አይነት ናቸው፡፡ እርግጥ ነው አዳማ ላይ ያደረጉትን

የወለጋው ኦሮሞ አያውቅም፣ ነቀምት ያደረጉትን አዳማ አሰላ

ያለ ኦሮሞ አያውቅም፡፡

መረራን ከወሮበሎች ጋር መክሰስ፡ የወያኔና ጀዋር ቁማር

ሌላው ወያኔ ጀዋር የኦሮሞ ሕዝብ ድጋፍ እንዲኖረው የምታደርገውን

ጥረት ማስተዋል ጥሩ ነው፡፡ በቅርቡ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ እየነገደ

ያለው ጀዋር እየተነቃበት መሆኑን ያስተዋለችው ወያኔ ዳግም የኦሮሞ

ሕዝብን ድጋፍ እንዲያገኝ ከታላቁ የፖለቲካና (ለእኔ የኢትዮጵያ ጥቂት

ልጅ አንዱ) ምሁር መረራ ጉዲና ጋር ክስ አቅርባበታለች፡፡ እኔን ግን

ያበሳጨኝ ጃዋር የኦሮሞን ሕዝብ ቀልብ እንዲስብላት ማድረጓ ሳይሆን

እድሜ ልኩን ለሕዝብ ሲል ሲታገል ከኖረው ከመረራ ጋር እኩል

ያደረገችበት ሁኔታ ነው፡፡ ዓላማው፣ የመረራን ማንነት ለማሳነስ

የጀዋርን ማንነት ለማግዘፍ ነበር፡፡ ደግነቱ ብዙም አልተሳካም፡፡ ግን

ደግሜ አዝናለሁ ይሄ ለአገር አሳቢ ነኝ የሚል ዲያስፖራ መረራ በወያኔ

ወሮበላዎች ሲታሰር አንድም እንቅስቃሴ አላደረገም፡፡ በአብዛኛው

ዲያስፖራ (የባዘነው) የመረራ ጉዳይ የኦሮሞ ነው፡፡ ኦሮሞ ደግሞ

ለአብዛኛው ዲያስፖራ ኢትዮጵያዊነትን የሚጠላ ነው፡፡ እለት ከእለት

የሚሰማውም ይህንኑ የሚያሳዩትን እነጀዋርንና መሰሎቹን ነው፡፡

ወደድክም ጠላሕም ግን ያለ ኦሮሞ ሕዝብ ነጻነት የለም፡፡ አውቃለሁ

ወያኔ 25ዓመት በጥንቃቄ የሰራችበት የኦሮሞን አዲሱን ትውልድ

ከኢትዮጵያዊነት ማምከንና ራሱን ያጣ የባከነ በማድረግ እንደልቧ

መኆንን ነው፡፡ አማራ የተባለው 25 ዓመት ምንም መብት እንደሌለው

በሌሎች ሁሉ እንዲጠላ በማድረግ ዘመቻ ላይ ነበረች፡፡ በቃ እነዚህ ሁለቱ

አቅም ከአጡና እርስ በእርሳቸው እንደጠላት ከተያዩ ኢትዮጵያ ውስጥ

እንኳን በታነክና በመትረየስ ታግዞ በቀላሉ ወሬ ከአንዱ ወደ አንዱ በማመላለስ

ሕዝቡን  መንዳት ይቻላል፡፡   ጎንደሬዎቹን የገባቸው ይሄ ሴራ ነበር፡፡

የኢትዮጵያን ሕዝብ ወደ አንድነት የመለሰው ይህን የወያኔ ሴራ ስለነቃበት

ነበር፡፡ ዲያስፖራ በእነጀዋር አይን ነው ኦሮሞን የሚመለከተው፡፡ ድንገት

ስለኢትዮጵያ አንድነት አንድ ኦሮሞ ሲናገር ያደንቃል፡፡ ይገርማል፡፡ መሠረታዊ

የኦሮሞን ሕዝብ ታሪክ ሊያስተውል አይወድም፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ እየተባለች

የምትጠራዋን አገር እኮ የገነቡት የአሮሞ አባቶች ናቸው ብለን እውነቱን

ስንናገር ሊያደንቅ ይሞክራል፡፡ ምኑ ነው የሚደነቀው፡፡ እውነት አይደለም ነው፡፡

በተቃራኒው ያንን ታሪክ የሰሩትን አባቶቻችንን ዛሬ እነጀዋራዊያን በአባቶቻችን

ታሪክ ላይ የጥላቻ አብዮት ከፍተው እንደልባቸው ሲፈነጩ ጭራሽ አሁን

አሁን ልክ ናቸው የሚለው እየበዛላቸው ነው፡፡ ወያኔ አኖሌን ሀውልት

ለመገንባት ሙክታርን የኦሮምያ ፕሬዘዳንት ማድረግ ነበረበት እንጂ

የታሪኩ እውነታነት አያስፈልግም፡፡ ዓላማው አንድና አንድ ነው፡፡ 25 ስለ

ሚኒሊክ ታሪክ ተዘመተበት ግን ከሕዝብ ልብ ሊተፋ አልቻለም፡፡ የበለጠ

ያንን ታሪክ ለማኮሰስና ለማጥላላት አኖሌ ሌላው አማራጭ እንጂ የታሪክ

እውነታነት የለውም፡፡ መረራን ጨምሮ ስለኢትዮጵያ የቀደመ ታሪክ ይህን

ታሪክ ከሚያወግዙት ናቸው፡፡ መረራንና ቡድኑን ቀለበት ውስጥ እኮ

ያስገባቸው፡፡ ኦሮሞ የኢትዮጵያ ታሪክ ባለቤት መሆኑን መናገራቸው ነው፡፡

ለመረራ ነፍጠኛ የሚለው ቃል ራሱ የአማራ ብቻ እንዳልሆነ በተደጋጋሚ

ተናግሮታል፡፡ የአማራ ነፍጠኛ እንደነበረ የኦሮሞ ነፍጠኛም ነበር ብሎ በግልጽ

ይናገረዋል፡፡ እውነት ነው፡፡ በእርግጥም በተለይ በታሪካዊውና ታላቁ መሪ

ሚኒሊክ የኦሮሞ አመራር የበላይነት መኖሩ ብቻም ሳይሆን የዚያ ታሪክ ልዩ

ስኬት ምክነያትም እንደሆኑ ስናስብ ሚኒሊክ አጠፋም አለማም የእነዚህ

አባቶቻችን ሚና የላቀ እንደነበር እናውቃለን፡፡ ያ ታሪክ ወያኔን ከምንም ነገር

በላይ ያስፈራታል፡፡ ቀን ከሌሊት በዛ ታሪክ ላይ ጉድፍ ለማወጣት ዋና ሥራዋ ነው፡፡

እነመረራ ደግሞ በአብዛኛው የዛሬው ትውልድ ዘንድ በወያኔ ከአእምሮው

እንዲመክንና ጭራሽ በጥላቻ እንዲያየው የተደረገውን የአባቶችን ስኬታማ

ታሪክ በማስታውስ ለወያኔ ችግር ሆኑባት፡፡ እስከዛሬ መረራን ብዙም

የሚከተለው አልነበረም፡፡ አሁን ብዙ ነገሮች የገባው ሕዝብ እየተፈጠረ

እሕ ማለት ጀመረ፡፡ ይሄኔ ነበር መረራና ቡድኑ ለወያኔ አደጋ የሆነባት፡፡

ይህ ነበር ሚስጢሩ፡፡ ዲያስፖራ አንዳርጋቸው ኢትዮጵያዊ ነው ብለህ

የምታምን መረራን እንዴት ዘነጋህው፡፡ አንዳርጋቸው አደለም እያልኩ

አደለም፡፡ ግን አንዳርጋቸው አማራ መረራ ኦሮሞ መሆናቸው ለዲያስፖሬው

ልዩነት እንዳመጣበትና ቢያንስ በእኩል ለማየት አለመቻሉ ነው፡፡ ለእኔ

ግን መረራ ይበልጣል፡፡ ከወገንተኝነት ሳይሆን መረራ እኮ የታሰረው አንዳች

ምክነያት ሳይኖር ነው፡፡ አንዴም ከሰላማዊ ትግል ውጭ አማራጩ አልነበረም፡፡

በአለም አቀፉም ዘንድ ስለመረራ ሰላማዊ ሰልፍ ቢወጣ ትልቅ ተሰሚነት

የሚያስገኝ ነበር፡፡ ጭራሽ ስለእሱ የሚያነሳም የለም፡፡ ከኦሮሞ አክቲቪስት ነን

ከሚሉ የጀዋር ቡድን የወያኔ የሴራ ቡድን ስለመረራ እንዲነገር ነው የምንጠብቀው;

በየፌሰቡክ ላይ የመረራን ፎቶ መለጠፍ እኮ አደለም ሙያ፡፡ ግልጽ የሆን ኮሚቴ

ተቋቁሞ መረራ የታሰረበትን ሂደት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ

ማሳያ ማደረግ በተቻለ ነበር፡፡

ሁሉም ሊያስብበት የሚገባ

ዛሬ ትልልቅ የሕዝብ ተጋድሎዎችና ጥረቶች ተራ በሆኑ ግለሰቦች እየታፈነ

ለወሮበሎች እድልና ድል እየሆነላቸው ነው፡፡ እኔ ሁሌም አጀንዳዬ የኦሮሞ

ሕዝብ ስለሆነ እዚህም ጋር የማነሳው ከዛው በተያያዘ ነው፡፡ አሁን አሁን ብዙ

የኦሮሞ ሕዝብ ልጆች ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው፡፡ ከጎናቸው ግን የሆነው

ሕዝብ ሴረኞቹ ጋር ከአለው ያንሳል፡፡ የኦሮምን ሕዝብ ነጻነት እያሉ ሲገድሉትና

ሲያስገድሉት አሁነ 50ዓመት (ግማሽ ምዕተ ዓመት ነው)፡፡ ኦሮሞ ከኢትዮጵያዊነቱ

እንዲመክንና አቅም አጥቶ ማንም የሚዘውረው እንዲሆን በፖሊሲ ተነድፎ

ነው የተሰራበት፡፡ ዛሬ ላይ እንደምታዩት ማንም ተራ እየተነሳ እኔ ነኝ የአንተ

ነጻ አውጭ የሚለው ማንነቱን ስላጣ ነው፡፡ ኦሮሞ ነኝ የምትልና በእርግጥም

ስለሕዝብ የምታስብ ከሆነ ኦሮሞ እንደ ዛሬው ዘመን በታሪክ የተዋረደበት

ዘመን ለም፡፡ ቀድሞ ኦሮሞ በዳይም ተበዳይም፣ ገዥም ተገዥም ሆኗል፡፡

ዛሬ ግን እንደዛ አደለም፡፡ ዛሬ ኦሮሞም እርግጥ ሌላውም ተበዳይ ብቻ ነው፡፡

ቀድሞ መከላከያ ሲባል አየር ሀይልን ጨምሮ ብዙ የኦሮሞ አመራሮች

እንደነበሩበት በሥም የምናውቃቸው እንኳን እናስታውሳለን፡፡ ዛሬ ያ የለም፡፡

በሌላ ሥልጣንም ቢሆን ኦሮሞ ትልልቁን ቦታ መያዙን እናስታውሳለን፡፡

ዛሬ እስኪ አንድ ሰው ጥቀሱ፡፡ የዛሬው ኦሮሞ ቁቤ ትውልድ የሚያረክሰው

የታላቁ ሚኒሊክ ታሪክ ደግሞ በተለየ የኦሮሞ አመራር የበላይነት የታየበትና

በእርግጥም ታላላቅ ስኬቶች በአገሪቱ የተመሠረቱበት ነው፡፡ የዛሬዎቹ ሴረኞች

የዛን ታሪክ ኢላማ ማድረግ ዋና አላማቸውም ይህን ታሪክ ከኦሮሞ ሕዝብ

በመነጠል በኢትዮጵያ ውስጥ ታሪክ የለህም የሚለውን የውስጥ መልክታቸውን

ለማስተላለፍ ነው፡፡ ሚኒሊክ ለኦሮሞ ልጆች ሥልጣን ሲሰጡ አንዳች

አልተጠራጠሩም አልሰሰቱም፡፡ መጨረሻም ሚኒሊክ ዙፋናቸውን የሰጡት

ለኢያሱ ነው(የየጁ ኦሮሞ)፡፡ ወያኔን ይሄ ታሪክ እጅግ ያስበረግጋታል፡፡

ትጠላዋለች፡፡ ኦሮሞ በምንም መልኩ ታሪክ ያለው ሕዝብ እንደሆነ

እንዲነገር አትፈልግም፡፡ በተቃራኒው ያልተፈጠረ ታሪክ እያነሳች የኦሮሞን

ሕዝብ ልጆች ከአባቶቹ ታሪክ እንዲጣላ በፖሊሲ 25 ሰርታለች፡፡

ተላላኪዎቿንም በየቦታው አሰማርታለች፡፡ የእነ ተስፋዬ ገ/አብ ዋና

ሥራ ይሄ ነው፡፡ የሰሞኗ ጂጂ የሚሏትንም አስተውሉ፡፡ ለኦሮሞ ሕዝብ

ያላትን ንቀጥና ጥላቻን ፊትለፊት ስትናገር ድፍረቱን የሰጣት ዛሬ

ከማንነቱ መክኖ የባዘነውን ትውልድ ስላወቀቸው ነው፡፡ አሁን ላለው

የቁቤው ትውልድ ዋና ወዳጆቹ አማራን የሚጠሉለትንና በአማራ

ተገዝተህ ነበር እያሉ የበታችነቱን እየነገሩ ዛሬም የበታች ሆነህ ትኖራለህ

የሚሉትን ነው፡፡ እውነታው ኦሮሞ ገዥ እንጂ ተገዥ አልነበረም፡፡

ተገዥ የሆነው ዛሬ ነው፡፡

ይህ የገዥነትና የበላይነት መንፈስ በኦሮሞ ሕዝብ እንዳይኖር ነው ዋና

ጥረቱ፡፡ ተስፋዬ ለኦሮሞ የጻፈው ተገዥነቱን ነው፡፡ አማራ የተባለው

ሕዝብ እንዴት እንደገዛው ነው፡፡ ታሪክ ግን ይህን አይናገርም፡፡

አባ በሀሬን መጀመሪያ ከጻፉለት ታሪኩ ጀምረን እኳን ብናይ አንድም ቦታ

ኦሮሞ ተገዥ አልነበረም፡፡ ሥርዓቶች ለሕዝብ ሊመቹም ላይመቹም ይችላሉ፡፡

ሥልጣኑ ላይ ግን ኦሮሞም ተሳትፎ ነበረው፡፡ ተሳትፎም ብቻ አደለም

በበላይነት ነው ሲመራ የነበረው፡፡ ከፋሲል ጀምሮ እስከሚኒሊክ፡፡

25 ዓመት የኦሮሞን ሕዝብ የበታች ለማድረግ ከአባቶቹ አገር ድርሻ

ለማራቅ ብዙ ተሴሯል፡፡ ኦሮሞ ሆንክ ሌላ ያለዚህ ሕዝብ ሙሉ ኢትዮጵያዊ

ወኔ ነጻነት የለህም፡፡ ችግሩ ኦሮሞ መሆን አለመሆን አደለም፡፡ በዚህ ሕዝብ

ምክነያት እየመጣብን ያለው ችግር የሁላችንም ችግር መሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ

የዚህን ሕዝብ ጉዳይ የሌላ አድርጎ ማየት ይቁም፡፡ በተቃራኒው በኦሮሞ

ሕዝብ ላይ ጥላቻና ንቀት ያዳበሩ ግለሰቦች እንደልባቸው ሲጨፍሩ እድል

አትስጥ፡፡ ሕዝብን በጸያፍ ስድብ የሚሳደቡ ግለሰቦች ወና የኦሮሞ ጉዳይ

ውይይት ታዳሚ ሆነው ስናይ ምንም አላልንም፡፡ መስፍን በተባለ የአባቶቹን

ታሪክ እያስታወሰ ዛሬ የአባቶቹን ታሪክ ለወገኖቹ እየነገረ ያለውን በልዩ

ስጦታው ከዘመናት ጀምሮ ለሕዝብ ብዙ በጎ ሲያደርግ የኖረውን ሰው

ጂጂ ጸያፍ ስድብ ስትሳደብ ከግለሰቡ ጋር በተያያዘ አልነበረም፡፡ የወያኔዋ

ጂጂ የኦሮሞን ህዝብ በንቀት ጸያፍ ስድብ አንድን የኦሮሞ ልጅ አስታካ

መሳደቧ የነጀዋር የክብር ታዳሚ ሲያደርጋት ታዝበናል፡፡ የኃይሌ ላሬቦ

ታሪካዊ ምሁራዊ ትንታን ታላቅ ጩኸት ፈጥሮ ብዙ ጫጫታ እንዲፈጠር

የሆነበትን ከወያኔዋ ጂጂ ንግግር ጋር አወዳድሩት፡፡  የኦሮሞ ሕዝብ ትግል

እንዲህ ባሉ ተራ ቁማሮች ወዴት እያመራን እንደሆን ለማስተዋል እንዲረዳ

ነው፡፡ በመጨረሻም ሁልህንም የኦሮሞ የዛሬው ጉዳይ ይመለከትሀል፡፡

አትሳሳት፡፡ አያገባችሁም የኦሮሞ ጉዳይ የእኛ ነው የሚሉት ለራሳቸው ሴራ

እንጂ አንዴም የኦሮሞ ሕዝብ ስቃይና መከራ ትዝ ብሏቸው አያውቅም፡፡

ያደረጉት ነገር ቢኖር ኦሮሞን ከማንነቱ በማምክንና ከሌሎች ሕዝብም ጋር

አብሮ የመኖር እሴቱን ሁሉ በማጥፋት ለእነሱ ሴራ እንዲመች ነው፡፡

 

እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን

 

ልዑል እግዚአብሔር አገራችንንና ሕዝቦቿን ይጠብቅ! አሜን

 

ሰርጸ ደስታ