April 6, 2017

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፣የልደት ቀን !!! —

የተወዳጁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የልደት ቀን ፣ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ።ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የፍትህ ጋዜጣ፣ የአዲስ ታይምስና የፋክት መጽሔት ባለቤት እና አዘጋጅ በነበረበት ወቅት በጹሑፍ ሥራዎቹ፤ አክብሮትና አድናቆትን ያተረፈ ተወዳጅ ጋዜጠኛ ነው። ይሁን እንጂ ጋዜጠኛ ተመስግን ደሳለኝ ! በጋዜጠኝነት ሙያው በሚያቀርባቸው የሰላ ትችት እና አሰተያየት ለእስር የተዳረገ ጋዜጠኛ ነው።

UNESCO-Registered-World-Heritages-Ethiopia-720x592

በዝዋይ ማረሚያ ቤት የሦስት ዓመት እስራት ተፈርዶበት የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ በዚህ ማረሚያ ቤት ከታሰረ ሁለት ዓመት በላይ ያስቆጠረ ሲሆን፣በተደጋጋሚ ሕመሙ ፀንቶበት ወደ ሆስፒታል ተወስዶ እንደነበር ቤተሰቦቹ በተደጋጋሚ ሲገልጹ ተስተውሏል።አሁን ላይ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ማንም ሊጠይቀው እንደማይችል እና ከቤተሰብ ለአንድ ሰው ብቻ ተፈቅዶ እንደሚጎበኝ ለማወቅ ተችሏል።

ለእስር ከተዳረገ ለሁለተኛ ጊዜ በተከበረው የልደት ቀን ፣ወላጅ እናት ወ/ሮ ፋናዬ ይርዳው፣ ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ በተገኙበት የልደት ቀኑ የተከበረ ሲሆን ፤ በዝግጅቱ ታዳሚ የነበሩት አርቲስት ደበበ እሸቱ፣ የታሪክ ተመራማሪ እና አርታዒው ብርሃኑ ደቦጭ ፣ ደራሲ ለማየሁ ገላጋይ ፣ የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች፣ የጋዜጠኛው የሙያ ባልደረቦች ፣በዘመን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ላይ ተሳታፊ የሆኑ አርቲስቶች እና አድናቂዎቹ እንዲሁም ቤተሰቦቹ በተገኙበት የልደት ቀኑ ተከብሯል ።

በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ እና አቶ ዳንኤል ሺበሺ ከእስር ቤት ፣የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የልደት ቀን አስመልክቶ የላኩት መልእክት የተነበበ ሲሆን ፣ዳንኤል ሺበሺ ፦ ” ተሜ አንተን የወለደች ማኅፀን የተባረከች ናት፣ እንኳን ተወለድክልን ።” ያለ ሲሆን። ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ፦ ” በውድ ሀገራችን ኢትዮጽያ ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ጠንክረ ስትታገል በግፍ የታሰርከው ተሜ! እንኳን ተወለድክ ፣አይዞን የደስታ ቀን አለን ።”በማለት መልእክቱን አስተላልፉል።

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፣የልደት ቀን አስመልክቶ በስሙ የተዘጋጀውን ኬክ ፣እናት ወ/ሮ ፋናዬ ይርዳው እና አርቲስት ደበበ እሸቱ በጋራ ቆርሰዋል፣ የልደት ቀኑን አስመልክተው ንግግር አድርገዋል ። — (ይድነቃቸው ከበደ)