19-year-old Elsa Isaias with her father at Sawa Festival

April 12, 2017

የኢሳያስ ክህደት
——
OMN ኢሳያስን ቃለ መጠይቅ ካደረገ በሗላ ብዙ እየተባለ ነው፡፡ ከአንዳንዶችም ሙገሳ እየተቸረው ይገኛል፡፡ ለመሆኑ ኢሳያስ ማን ስለሆነ ነው ሙገሳ የሚቸረው?? ኢሳያስ እኮ ሰው በላ ነው፡፡ ለሰው በላ ከሃዲ ደግሞ ሊጨበጨብለት አይገባም፡፡ ስለ አሁኑ ኢሳያስ ለማውራት የሗላ ታሪኩን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ኢሳያስና የሚመራው ሸአቢያ በትጥቅ ትግል ወቅት ምን ሰሩ የሚለው መጤን አለበት፡፡

ሸአቢያ ከጀብሃ አፈንግጦ ሲወጣ እንደ ምክንያት ያስቀመጠው ጀበሃን <<የጎሳና የሃማኖት ድርጅት ነው>> በሚል ሲሆን ራሱን ደግሞ በተራማጅነት በመፈረጅ ነበር፡፡ በኢሳያስ የሚመራው ሸአቢያ ግን ተራማጅ አደለምና በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ክህደቶችን ፈፀመ፡፡

ክህደት አንድ
—–
የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ሠራዊት (ኢሕአሠ) አስኳል ቡድን በ1965 ቀይባህርን ተሻግሮ ግርገር ከተባለው የሸአቢያ ጦር ሰፈር ሲደርስ ትጥቁን እንዲፈታ ካደረገ በሗላ <<ኤርትራ በኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት የምትገኝ ሃገር ናት፤ ሸአቢያም የሚዋጋው ኤርትራን ነፃ ለማውጣት ነው>> ብሎ የፖለቲካ እውቅና ካልሰጠ ወደ አሰበበት ትግራይ መዝለቅ እንደማይችል አስጠነቀቀ፡፡ ትጥቃቸውን አስፈትቶ በርሃብና በርዛትም ቀጣቸው፡፡ በርካታ ጀማሪ ታጋዮችም በሁኔታው ተደናግጠው እንዲሸሹ አደረገ፡፡

ክህደት ሁለት
—-
የሸአቢያን ተራማጅ መስሎ መቅረብ የሰሙ በርካታ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችና የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሳህል በረሃን አቋርጠው የሸአቢያ ካምኘ ያጥለቀልቁታል፡፡ በዚህም የሸአቢያን ተዋጊ በሶስት እጥፍ በመብለጡ እነ ኢሳያስን ስጋት ላይ ጣለ፡፡ አዲሱ መጤ ወጣት የኢትዮጵያን አንድነት፣ የብሄር ብሄረሰቦች መብት፣ ዲሞክራሲ…..ማንሳትና ማብላላት ሲጀምር በየምክንያቱ እየተገደለ ለበረሃ አሞራ ይጣል ጀመር፡፡ በዚህም ሃገር ወዳድ ፋኖዎች እንደወጡ እንዲቀሩ አደረገ፡፡

ክህደት ሶስት
——
የኤርትራ ህዝብ የራሱ የቅኝ ተገዥነት ታሪክ የነበረው ህዝብ እንደሆነ፤ ከቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የታሪክም ሆነ የባህል አንድነት እንዳልነበረው፣ እንደሌለውና እንደማይኖረው በድፍረት ልቦለዳዊ ታሪክ ፈብርኳል፡፡ ቀመሩም ሠምሮለት ዛሬ በአብዛኛው ቆለኛ ትግርኛ ተናጋሪ ኤርትራውያን እሱ በቀደደው ቦይ እየፈሰሱ ነው፡፡

ክህደት አራት

ተራማጅ ነኝ ብሎ ያወጀው ሸአቢያ ብዙም ሳይቆይ በማንኛውም የኤርትራ ክፍል አማርኛ ቋንቋ እንዳይነገር ሙዚቃም እንዳይሰማ አወጀ፡፡ ወንድማማች ህዝቦችን የመከፋፈል ስራም ከወያኔ በላይ አጠናክሮ ቀጠለ፡፡ ለነፃነታችን እንታገላለን ያሉ ወጣቶች በቋንቋቸው ምክንያት በእየበረሃው አንገታቸው ተቀነጠሰ፡፡ ኢኸው ዛሬ ስልጣን ሲይዝም የአማርኛን ጥላቻ በህግ አስደግፎ አወጀ፡፡ በዚህም አስመራ ላይ በጣሊያንኛ “ሰርቺሰርቺቺ” እያለ የሚዘፍን ነጭ ታላቅ ክብር ሲሰጠው፤ የአማርኛ ሙዚቃ የከፈተ መዝናኛ ቤት ግን 2000 ብር ይቀጣል፡፡