14 April 2017 (EMF) በሆላንድ ነዋሪ ኤርትራውያን መካከል በተነሳው ግጭት 128 ስደተኞች ትናንት አፕሪል 13 ቀን 2017 ማለዳ ላይ ታስረዋል። የቆሰሉ አሉ፣ ንብረትም ወድሟል።
ከ 13 እስከ 17 አፕሪል 2017 ሊካሄድ የታስበው የኤርትራን የወጣቶች ኮንፈረንስ በትላንትናው በኔዘርላንድስ፣ ፌልዶቨን ከተማ ምክር ቤት በትናንትናው እለት ማገዱን አለም አቅፍ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡት ነው።
ኮንፈረንሱ ሊታገድ የቻለው በኢሳያስ አፈወርቂ መንግስት ደጋፊዎች እና በተቃዋሚዎች መካከል በተፈጠሩ ከፍተኛ ግጭቶች ምክንያት እንደሆነ የከተምማዋ ከንቲባ ገልጸዋል።
የኤርትራውያን ፍልሚያ በሆላንድ Rob Burg
ከግጭቶቹ በኋላ የሆላንድ አድማ በታኝ ፖሊስ አካባቢውን ያጸዳ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የአካባቢው ጸጥታ ወደነበረበት ተመልሷል ተብሏል። ውጥረቱ ግን እንዳለ ነው።
ሃሙስ ማለዳ የጀመረው ይህ ብጥብጥ እና የተቃውሞ ሰልፍ የህዝብ መተላላፍያ የሆነውን ዋና መንገድ ዘግቶ ነበር። ተቃዋሚዎቹ በብዛት ሆነው መንገዱ ላይ በመተኛት ለስራ የሚንቀሳቀሱ መኪናዎችን አግደዋል።
ከፖሊስ በተገኘው መረጃ ከሆነ በግርግሩ 128 ኤርትራውያን በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል። ታሳሪዎቹ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡም በፖሊስ ተነግሯል።
የከታማዋ ከንቲባ ሚ/ር ጃክ ሚከርስ በትላንትናው እለት ኮንፈረንሱን ማገዳቸውን በመቃወም የኮንፈረንሱ አዘጋጆች ጉዳዩን ዛሬ አርብ 14 አፕሪል ወደ ፍርድ ቤት ወስደውታል።
የኤርትራ ዲፕሎማት የሆነው ሰለሞን መሃሪ መኪና ከተቃዋሚዎቹ በደረሰበት የድንጋይ ናዳ ከአደጋው ማምለጥ ቢችልም መኪናው ግን ከጥቅም ውጪ ሆናለች ተብሏል።
የኤርትራውያን ፍልሚያ በሆላንድ Pic Rob Brug
ከተቃውሞ አዘጋጆቹ አንዱ የቀድሞው የኤርትራ ምክትል ገንዘብ ሚኒስቴር የነበሩት አቶ ክብሮም አጽባይ ሲሆኑ እኝህ ሰው በ2010 ከአኤርትራ ተሰድደው እዚሕ በጥገኝነት ይኖራሉ። “የሆላንድ መንግስት ለዚህ አንባገነን መድረክ መፍቀዱ አሳፋሪ” እንደሆነ ይናገራሉ።
የአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ቀኝ እጅ የሆኑት አቶ የማነ ገብረአብ በዚህ ኮንፈረንስ ላይ የክብር እንግዳ ሆነው እንዲገኙ ጥሪ ቀርቦላቸው ነበር። በአቶ የማነ ገብረአብ ወደ ሆላንድ የመምጣት ጉዳዩ ላይ የሆላንድ ፓርላማ እና የሆላንድ ካቢኔ በስፋት ተወያይቶ አቶ የማነ ገብረአብ በኦፊሴላዊ መንገድ ሆላንድ መግባት እንደማይችሉና – በሌላ መንገድ ወደ ሃገሪቱም መግባት ቢችሉ እንኳን መንግስታዊ አቀባባል እንደማይኖራቸው አስቀድሞ ይፋ አድርጓል።
Yemane Gebreab
አቶ የማነ ገብረአብ ግን የሆላንድን አቋም ችላ በማለት የሸንገን ቭዛ ይዘው፣ መንግስታዊ ፕሮቶኮል ሳይኖራቸው፣ በሌላ ሃገር አቆራርጠው እንደ ተራ ሰው ሆላንድ ገብተዋል። ሳይጀመር የተቋረጠው ኮንፈረንስ ላይ ግን ንግግር ማድረግ አልቻሉም።
ሆላንድ 20 ሺህ ሊሚያህሉ የኤርትራ ስደተኞች ጥገኝነትን ሰጥታለች። ከነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ የኢሳያስ አፈወርቂን መንግስት የሚደግፉ እና ወርሃዊ መዋጮ የሚከፍሉ ናቸው።
አሁን በተነሳው ግርግር ሳብያ የሆላንድ መንግስት በኤርትራ ስደተኞች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ለማድረግ እንደወሰነ የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ነው። የስደተኝነት ወረቀታቸውን ካገኙ በኋላ ወደ ኤርትራ የሚሄዱ፣ ኢሳያስ አፈወርቂ መንግስት የሚሰልሉ እና መዋጮ የሚከፍሉ በሙሉ መንግስት ለሬሚታንስ የላካቸው ስለሆኑ – የመኖርያ ወረቀታቸውን ይነጠቃሉ ተብሏል። ወደ ፊት ከኤርትራ የሚገቡ ሰደተኞች ላይም ከባድ ቁጥጥር እንዲደረግ የሆላንድ ካቢኔ ውሳኔ አስተላልፏል።
ዘግይቶ በደረሰን ዜና መሰረት የሆላንድ ፍርድ ቤት ኮንፈረንሱ እንዲካሄድ ወስኗል።
በአካባቢው ችግር እንዳይከሰት ፖሊስ ጥብቅ ጥበቃ እያደረገ እንደሆነ ቢታወቅም ተቃውሞውም ይቀጥላል ተብሏል።
One Response to የኤርትራውያን ፍልሚያ በሆላንድ – የሆላንድ መንግስት አቶ የማነ ገብረአብን አልቀበልም አለ
I suspect many TPLF supporters might have involved in this conflict by Opposing Isias and his youth supporters.
April 14, 2017 at 9:06 am