ላለፉት ሁለት ዐሥርት ዓመታት በዘረኛው የትግሬ ነፃ አውጪ  የአገዛዝ መዳፍ ሥር የታፈነውን ሕዝባችንን ወደ ነፃነትና የዴሞክራሲ ምዕራፍ ለማሸጋገር የጋራ ትግል ለማድረግ ሲሞከር ቆይቷል።

ሆኖም በእነዚህ ዘመናት ውስጥ የተፈጠሩት የፖለቲካ ኃይሎች ትብብር፣ቅንጅት፣ኅብረት እና ውህደት አንዱም ከዳር ሳይደርስ እንዲሁ ሲሰበሰብና ሲበተን ከርሟል።እንደ አባባልም እንደ መታወሻም “ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ” የሚለው የዶ/ር መረራ ጉዲና መፈክር አንዱም ገቢራዊ ሳይሆን አብዛኞቹ  የፖለቲካ ተቋማት በአገዛዙ ጫናና በራሳቸው ደካማ አደረጃጀት ህልውናቸው እየጠፋ ለሐገር የሚተርፍና ትውልድ የሚረከበው አንድም አግባቢ የጋራ ማዕከል ሳይመሰረት በኪሳራ የታጀቡ ዓመታትን አሳልፈናል።

ትብብር የጉልበት ምንጭ ነው።ትብብር ድልን ማቅረቢያ ዘለቄታዊና ሠላማዊ ሽግግርን ማሳለጫ መሳርያ ነው።ትብብር ከሚከሰረው የሚያተረፈው የሚበዛበት የሕዝብን አብሮነት ማጠናከርያ፣ልዩነትን ማጥበቢያና የቅራኔ ማርገቢያ ጠቃሚ ዓላማ ነው።

አበው“ድር ቢያብር አንበሣ ያስር ” እንዲሉ የተበታተነን ትግል አቀናጅቶ ለውጤት በማብቃት የትብብር አስፈላጊነት ላይ ማንም ጥያቄ ባይኖረውም ይህንን ጠቃሚ መሳርያ ተጠቅሞና ኃይልን አጠናክሮ ጠላትን ለመርታት የሚያስፈልገውን ሰጥቶ የመቀበል፣የመቻቻልና የሰለጠነ ፖለቲካዊ ባህል ባለመኖሩ በተደጋጋሚ በሕዝብ ተነሳሽነት የተገኙ ወሳኝ ድሎች የተባበረ አመራር በመጥፋቱ ለቅልበሳ ሲዳረጉ ቆይተዋል።

____________________________

አምስቱ ምሁራን እና ሕወሓት …. ለመመልከት እዚህ ይጫኑ

____________________________

ባለፈው ሰሞን የተለያዩ ወገኖች በተለያየ ጽንፍ ቆመው በአወዳሽነትና በነቃፊነት በየመገናኛ ዘዴዎቹ ሲናጩ የከረሙበት የአድዋ  ድል በዓል ከአሸናፊነት የስነ ልቦና ውርስነቱና ፤ የክብር ልዕልናው ባሻገር ለዓለም ጭቁን ሕዝቦች ተምሣሌት  የሆነ የመተባበር ውጤታማነት ማሳያ መሆኑን “ የራስ ወርቅ አያደምቅ” እንዲሉ እኛ ባለቤቶቹ ልንጠቀምበት ባንችልም በደቡብ አፍሪካ ፀረ-አፓርታይድ ትግል እና በሠሜን አሜሪካ የቆዳ ቀለም {ጭቆናን} ለመሰባበር ያስቻለ ተምሣሌት ለመሆኑ የትግሉ ባለቤቶች የመሰከሩትን ማየት ብቻ በቂ ይሆን ነበር።

ይህን የመሰለ ታሪክ አባቶቻችን ዘር፣ ቀለም፣ፆታና የብሔር ማንነት ሳይገድባቸው በሐገር ውስጥ የነበራቸውን ልዩነት አቻችለው በተባበረ ኃይል የአውሮፓ ወራሪን አሳፍረው በመመለስ ያቆዩልንን ሐገርና ዝንተ ዓለም በዓለም ጭቁን ሕዝቦች ታሪክ እንዳበራ የሚኖረውን  ታሪክ ልንመራበት ቀርቶ ልንማርበት አለመቻላችን እጅጉን ያሳዝናል።

ከዚህ የተነሳ ሊያቀራርበን የሚችለውን ትተን ዘመን የሻረው አሮጌ ታሪክ ላይ ተቸክሎ ፤  ማላዘን ተቋማዊና ሕብረተሰባዊ  ባህል ወደ መሆን የደረሰ እስኪመስል ድረስ በሺህ ዘመናት ውስጥ ተገንብተው የኖሩ በጎና ተወራራሽ የጋራም የተናጥልም ፤ የድል፣የአብሮነትና የመቻቻል ታሪካችን ላይ ትኩረት ሰጥተን ያንን እንደማዳበር  ከመቶ አምስት ዕጅ በማይሞላው የንትርክ አጀንዳ ላይ ኃይላችንን በማዋላችን ለሕዝባዊ ውድቀትና ለሃገራዊ ኋላ ቀርነት ተዳርገን ቆይተናል።

ሕወሃት ባሰማራቸው ቅጥረኞ ፤ ባዶ ዝና ያናወዛቸው ዋልጌዎ  ፤ በጽንፈኛ ብሄረተኞች አቀጣጣይነት  በሶሻል ሚዲያው በኩል የሚራገበው አሳፋሪ ፤ አደገኛና ሗላቀር የጥላቻ ቅስቀሳ ተጠናክሮ ከቀጠለ ሕብረት  መፍጠር አይደለም የሰላም ተስፋም እይኖርም። ከዚህም በላይ በሃገር ውስጥ ከእለት ወደ እለት  እየተባባሰ የመጣው  ድህነትና የአገዛዝ ጫና ሕዝባችንን ተስፋ ቆርጦ ወደ ለየለት አመጽ ገብቶ ሁኔታው ከቁጥጥር ውጭ  ከሆነ በሗላ ለሕዝቡም  ሆነ ለሃገሪቷ   ልንደርስ የምንችልበት እድል በቀላሉ ስለማይኖር ፤ ቀኑ ሳይመሽ  ባለን እድል  መጠቀሙ ለሁሉም የሚበጅ ይሆናል

የልዩነትን መንገድ የሚጠርጉ ፤ የጥላቻን እንክርዳድ የሚዘሩ ጨለምተኞች ከየማዐዘኑ ሆነው የሰላሙን አውድ ሲንጡትና የትብብሩን መንገድ እሾሃማ ለማደረግ ሲሞክሩ ከርመዋል። በዚህ ባለንበት በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሰው ልጅ የእውቀትና የስልጣኔ ደረጃ በመጠቀበት ግዜ ላይ ሆነን የጥላቻ ተገዢና ፤ላሮጌ አስተሳሰቦች ምርኮኛ መሆናችን እርግማን ሆኖብናል። ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነውና የሚያሳፍረው ፤ ሃሳብ ማፍልቅ፤ አቅጣጫ ማሳየት ፤ አመራር መስጠትና ፤ ዓርኣያ መሆን የሚገባው ምሁር የሚባልው የማሕበረሰባችን ክፍል ፤ ምሕዋሩን ስቶ የጥላቻና የአሉባልታው መሪ ተዋናይ በመሆን መዝቀጡ ፤ ችግራችንን ከባድ ትግሉንም ረጅምና መራራ አድርጎታል ። ዘመኑን ከማይዋጅ ኋላቀር የድንጋይ ዘመን አሮጌ ፖለቲካ ባለመላቀቃችን ዕጃችን ላይ የወደቁትን ዕድሎች እንዳንጠቀም አድርጎናል።

በኦሮሚያ ለአመት ያህልና በአማራ ክልል ለወራት  በተካሄደው ሚሊዮኖች የተሳተፉበትና ፤ የአያሌ ዜጎች  የሕይወት ዋጋ የተከፈለበት አስደማሚ የሕዝብ ንቅናቄ መሠረታዊና ስር ነቀል ለውጥ ሳያመጣ ይዳፈናል የሚል ግምት አልነበረም።ነገር ግን ብሶት የወለደው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ አቅጣጫ የሚያሲዘው ፣ለድል እንዲበቃ በታክቲክ፣በዕቅድና ፤ በስትራቴጂ አጣጥሞ የሚመራው ማዕከላዊ የፖለቲካ አመራር ባለመኖሩ በስሜት ተነሳስቶ የተንቀሳቀሰው የሕዝብ ማዕበል መስዋዕትነቱ ፍሬ አልባ ከመሆን መታደግ ሳይቻል ቀርቷል።

____________________________

“መሬት እሠጣችኋለሁ በሚል የሕዝቡን አፍ ማዘጋት አይቻልም” – ሳዲቅ አህመድ ልዩ ትንታኔ …. ለመመልከት እዚህ ይጫኑ

____________________________

ይህ በየማዕዘኑ የተንቀሳቀሰው የሕዝብ ንቅናቄ በጽኑ አስቀምጦት ያለፈው ነገር ቢኖር ያለ ፖለቲካና የዘውግ ሃይሎች ሕብረት፤ ያለ ድርጅትና አመራር ሰጪ አካል የሕዝብ ተነሳሽነት ብቻውን የትም አለመድረሱን  በተጨባጭ አስተምሮ አልፋል።

ከዚህም አንጻር መጪው የትግል ሁኔታ ብዙ አቅምና መስራትን ይጠይቃል። የተበታተነውን ትግል ለማቀናጀት በተካረረ የዘውግና የመስመር ልዩነት ተነጣጥሎ የቆየውን በማቀራረብ በሕዝቦች መካከል የተዘራውን የጥላቻ መርዝ ነቅሎ ጤናማ ግንኙነትን ለመገንባት የሚያስችል የፖለቲካ ኃይሎች የጋራ መድረክ መፍጠር ያስፈልጋል። የህዝብ ዋይታ ፤ በሃገር ላይ የተደቀነው አደጋ የሚያሳስባችው ቅን አሳቢዎች ጥረት ድጋፍና ይሁንታ የሚቸረው ጥቂት ወገን ካገኘ ውጤታማ ለመሆን የሚያስችለው እድልም እንዳለ በቅርቡ የተመሰረተው የኢትዮጵያ ሐገራዊ ንቅናቄ ከመነሻው የታየው የሕዝብ ምላሽ እንደ አንድ በጎ ተሥፋ ሰጪ ጅምር መታየት የቻለ ነበር።

የኢትዮጵያ ሐገራዊ ንቅናቄ ከመነሻው ያስተጋባው የአብረን እንታገል ጥሪ በተገቢውና በቀና ሁኔታ ተግባራዊ ከሆነ ከሞላ ጎደል ምድር ላይ ያሉ ኃይሎችን የሚያሰባሰብ ማዕከል ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑ እሙን ነው።ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በፖለቲካ ኃይሎቻችን መካከል የተለያዩ የትብብር እንቅስቃሴዎች በተደጋጋሚ ለመመስረት ሙከራ መደረጉ አይዘነጋም።በእነዚህ ሁሉ ሙከራዎች የሚፈለገው ውጤት ባይገኝም  በግንቦት 1997 ዓ/ም ሐገር አቀፍ ምርጫ ወቅት የታየው የሕዝብ  ተነሳሽነትና ተሳታፊነት እንዲጎመራ ቅንጅትና ኅብረት ያካሄዱት የምርጫና የፖለቲካ ዕንቅስቃሴ ምንም እንኳን የቅልበሳና የትርምስ ጠባሳውን ጥሎ ቢያልፍም የተበታተኑና የተንጠባጠቡ ቡድኖች ተሰባስበው ከቆሙ ምን መፍጠር  እንደሚችሉ ጥሩ ማሳያ መሆኑ አይዘነጋም።

ሃገራችን ከምተገኝበት የህልውና ፈተና ለመዳን በእኔ እምነት የኢትዮጵያ ሐገራዊ ንቅናቄ ያለው ፋይዳ  ካለንበት  ማህበራዊ ፤ ኢኮኖሚያዊና ፤ ፖለቲካዊ ቀውስ በላይ ለህልውናዋ አደገኛ የሆነው ጠርዝ የያዘ የጎሣ ፖለቲካ ሊያስከትል የሚችለውን የብተና አደጋ በተወሰነ ደረጃ በማርገብ ረገድ ተስፋ ሰጪ ሚና ይኖረዋል የሚል ነው።   ለተራዘመ ዘመን የግንጠላ አጀንዳ እንደዋና የመታገያ መፈክር አንግበው የቆዩት የቀድሞው ኦነግ መሪዎች በንቅናቄው ውስጥ መሪ ተዋናይና በአንዲት ሉዋላዊት ሐገር ውስጥ ችግራችንን መፍታት ይቻላል በሚል ተለዋጭ አጀንዳ መሳተፋቸው በሰለጠነና ወቅቱን ባገናዘበ መንገድ ከተጠቀምንበት ሊያሰራ የሚችል ሐገራዊ ተቋም ይሆናል የሚል ስሜት አሳድሯል።

ከአደገኛው የብተና አዙሪት ወጥተን ሕልውናችንን ለማስቀጠል ከእንግዲህ እስከዛሬ ከተጓዝንበት አባጣና ጎርባጣ መንገድ ወጥተን ወደ ተሻለው የጥንካሬ መስክ ላይ ለመድረስ በጋራ ተሠባስበን ኃይላችንን ማጠናከርና አማራጭ የሌለው መፍትሄ መፈለግ ግድ ይለናል።

የሠለጠነና ሕዝብን ማዕከል ያደረገ የፖለቲካ አቋም እናራምዳለን የሚሉ ኃይሎች ከእንግዲህ ያለምንም በቂ ሁኔታ ከሌሎች ጋር ላለመተባበርና ላለመስማማት የሚያቀርቡትን  አጀንዳ ሕዝባችን መፍቀድ አይኖርበትም። ዘመኑ ከሚዋጅ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ እና የሕብረት ትግል ሊርቁ የሚችሉበትም ምክንያት ሊኖር አይገባም።

ሕዝባችን የህይወት ዋጋ ከፍሎ ዘረኞች የገነቡትን የመለያየትና የጥላቻ ግንብ ንዶ ወገናዊነቱን በማስተጋባት ያሳየው የትግል አንድነት ማስቀጠል የምንችለው ለልዩነቶቻችን እውቅና ተሰጣጥተን በመከባበር በጋራ መቆም ስንችል ነው። ይህ ሕዝባችን ደምህ ደሜ ነው ፤ ብሶትህ ብሶቴ ነው በሚል ያሳይው ስልጡንነት ፤ በተለይ በምዕራቡ ዓለም በስደት ያለንው ሃገር ወዳድ ነን የምንል በጥንቃቄ ልናስተውለውና በስራ ልንተረጉመው የሚገባ ተምሳሌታዊ ተግባር ነው።

የኢትዮጵያ ሐገራዊ ንቅናቄም በሃገር ቤት ያስተጋባውን አንቂ ሕዝባዊ መፈክር በማንገብ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ሙከራ ማድረጉ ስብስቡ ላይ ተሥፋ እንዲጣል አድርጓል። ይህ ሐገራዊ የኃይሎች ንቅናቄ ባሳተፋቸው ድርጅቶች ቁጥር ማነስና በአንዳንዶቹ የኋላ ታሪክ ላይ ጥርጣሬ  ያለው ቢኖርም ሁኔታውን ቀረብ ብሎ ማየትና ውይይት መጀመሩ የተሻለ አማራጭ መሆኑ ይሰማኛል።

እንደ አንድ ከዚህ ንቅናቄ ጋር በታዛቢነት እንደቆየ ግለሠብ ስብስቡ ምንም እንኳን እኔ የምፈልገውን የዘውግ ኃይል በተገቢው መንገድ አካቶ ባይገኝም በንቅናቄው ውስጥ ያሉ ኃይሎች ግንኙነት ቀና ሆኖ ከቀጠለ ለወደፊቱ የሐገራችን የፖለቲካ ትግል ሂደት በጎና ገንቢ አስተዋጽኦ ሊኖረው እንደሚችል ያለኝ ተሥፋ የጎላ ነው።

እንደ እኔ ዕምነት የሐገራችንን የፖለቲካ ችግር ለመፍታት ወደድንም ጠላንም የየትኛውም ዘውግ ይሁን  ፓርቲ አባል ዕድል ፈንታና ጽዋ ተርታችን  በእጅጉ የተቆራኘ ነው።የአንዳችን ችግር ተፈትቶ የሌላችን የሚቀጥልበት ምንም አይነት ዕድል የለም።ከለማንም በጋራ ስንጠፋም በጋራ መሆኑን ማመን ትንቢት አይሆንም።ስለሆነም እንዳለፉት ረጅም አመታት  ላለመስማማት ወስነን ጠላቶቻችን በቀየሱልን የብተና ቦይ እንደፈሰስን ባክነን ለመቅረት ካልወሰንን በስተቀር ችግሮቻችንን ለመፍታት በጋራ የማንቆምበት ከጸሃይ በታች ምንም ምክንያት አይኖረንም።

እርግጥ ነው በሐገራችን የረጅም ጊዜ ሂደት ውስጥ በፖለቲካው መስመር ላይ ብዙ መቋሰሎች የፈጠረው የበደል ሸክሞች የሁሉንም ወገን ጀርባ አዝሎታል።አሮጌ የፖለቲካና የታሪክ ሸክም ባጎበጠው ትከሻችን  ላይ የብረት ቀንበሩን የጫነብን የትግራይ ነጻ አውጪ ቡድን ባርያ አድርጎ ሊያስቀረን ቁስላችን ላይ ጨው እየነሰነሰ መከራችንን እያከበደው ይገኛል።ይህንን ሴራ ለማክሸፍ የተሸከምነውን አሮጌ አጀንዳ አራግፈን ፤ የታሪክ ሂሣብ ከምናወራርድበት ሰባራ ሚዛን ወርደን በይቅርታና በወንድማማችነት መንፈስ ቆመን እንድንገኝ የደረስንበት የህልውና ፈተና ግድ ይለናል።

የኢትዮጵያ ሐገራዊ ንቅናቄ ተሥፋ የሚሰጥ ጅምር ነው ለማለት የሚያስደፍረኝ አጠቃቀሙን ካወቅንበት ካለፍንበት የጭለማ መንገድ ወጥተን ቢያንስ ያሉብንን ችግሮች ለይተን ለመነጋገርና የሕዝባችንን መከራና ስቃይ ያረዘመውን የዕርስ በእርስ መከፋፈልና የተነጣጠለ ትግል ዕልባት እንዲያገኝ  ወደፊት ለማየት እንድንችል የሚረዳም አጋጣሚ  ማድረግ ይቻላል። ከዚህም በላይ ይህ ንቅናቄ ሁኔታዎች ፈቅደው ከጎለበትና አብዛኛውን የዘውግና የፖለቲካ ማህበረሰብ የሚወክሉ ሃይሎች ከተካተቱበት  ወደ አንድ ሃገር አቀፍ ፓርቲነት በሂደት እንደሚለወጥ በዕቅድ መያዙ በበጎ እንዲታይ ያደርገዋል።

በታላቅ የልዩነት አዙሪት በጽንፈኛ የግንጠላ አጀንዳ አራማጆችና በአንድነቱ ጎራ በተጻራሪ ካምፕ መሽጎ ለመጠፋፋት ሲያደባ የኖረው የፖለቲካውና የዘውግ አንቀሳቃሹ ዋና ተዋናይ የሆነው ኤሊቱ ሃሳቡን አሸጋሽጎና ልዩነቱን በተወሰነ መልኩ አጥብቦ  ችግሮቹን በአንድ ሉዋላዊት ሐገር በዴሞክራሲና በእኩልነት ላይ በተመሠረተ መልኩ ለመፍታት ወስኖ ትብብር መፍጠሩ ሌላው ተሥፋ ሰጪ ጎኑ መሆኑ መዘንጋት የለበትም።

____________________________

ጀዋር መሐመድ ስለብሔር ኃይሎች እና አንድነት ኃይሎች የሰጠው ትንታኔ…. ለመመልከት እዚህ ይጫኑ

____________________________

በታሪካዊና ጂኦ ፖለቲካዊ ጠላቶች የተከበበችው ሐገራችን ከውስጧ የሚመነጭ የመለያየት አጀንዳ ኖሮ አይደለም ራሳቸው ፈጥረው ለመሰማራት የማይቦዝኑበት ሁኔታ ባለበት ፤ ሐገራዊ አንድነታችን ከመቼውም ጊዜ በላይ በተዳከመበት ወቅት የፖለቲካ ልዩነታችንን በአንድ የኢትዮጵያዊነት ሐገራዊ ማዕቀፍ ውስጥ ለመፍታት የረጅም ዘመን የግንጠላ አጀንዳቸውን ጥለው ለመጡ ወገኖች ተገቢውን ቦታ ሠጥቶ አብሮ መቆም የጥንካሬ ምንጭ እንጂ አንዳንዶች እንደሚሉትት  ስህተት  አለመሆኑ ሊሰመርበት ይገባል።

የሃገራዊው ንቅናቄ ስጋቶች

የወቅቱ የሃገራችን የፖለቲካ መሪ አጀንዳና ፤ የሃይሎች አሰላለፍ መሰረት ያደረገው በዘውግ ማንነት ላይ ለመሆኑ የሚያከራክር አይደለም። ባለፉት አመታት ከመጠን በላይ ለከፋፍለህ ግዛው አፓርታይዳዊ የወያኔ አገዛዝ እንዲመች ሆኖ የተራገበው የብሄረሰብ አጀንዳ በቀላሉ ሊቀለበስ በማይችል መልኩ ሁሉንም የሃገሪቱን ብሔሮች በአካባቢያቸው ዙሪያ እንዲሰባሰቡ አስገድዷል። ይህ አካባቢያዊ በዘውግ ማንነት ላይ ያነጣጠረ እሳቤ በማህበረሰባችን  ውስጥ በሰፊው ሰርጾ ሃገሪቷን በከባድ የተቃውሞ ማዕበል ሲያጥለቀልቃት ቆይቷል። በኦሮሚያ ከአመት በላይ በአማራ ክልል ለወራት በዋናነት የብሔር ማንነትን መሰረት አድርጎ የተነሳው ሕዝባዊ ቁጣ ለግዜው በሕወሃት ወታደራዊ ወረራ የረገብ ቢመስልም ፥ ዘውግን አስታከው የተንሱት ጥያቄዎች እስካልተምለሱ ፤ የብሄሮች እኩልነት እስካልተርጋገጥ ፥ የወልቃይት አማራነት እስካልተመለሰ ፤ ከእንግዲህ መቼም ቢሆን ሃገሪቱ ከብሄር ተኮር  አዙሪት ቀውስ እንደማትወጣ  መተነበይ ነብይ መሆን አይጠይቅም።

ይህን አይነት ዘውገኛ የፖለቲካ ማሕበረሰብ አሰላለፉን በማንነቱ ዙሪያ ገድቦ በሚገኝበት ወቅት የሚፈጠር ሃገራው የፖለቲካ ሃይሎች ንቅናቄ ይህንን ተጨባጭ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገባ አካሄድ መከተል ግድ ይለዋል።

ከዚህ መሠረታዊ ወቅታዊና ተጨባጭ ሃቅ ተነስተን ተስፋ ሰጪ ጅማሮ አሳይቷል በሚል ከላይ ለመግልጽ እንደተሞከረው ሁሉ የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ ሲመሰረት ጀምሮ እስካሁንም ያልተላቀቀውና ለንቅናቄው ቀጣይ ህልውና ሆነ ለጥንካሬው ሳንካ የሆንበት በተለይ የአማራው ሕዝብ አለመወከሉ ነው። የአማራውን ዘውግ አካቶ መገኘቱና አስፈላጊነቱ ላይ በአባዛኞቹ የንቅናቄው አባላት ዘንድ   ጥልቅ የጋራ መግባባት  ቢኖርም  በምስረታው  ላይ ሆነ በቀጣዮቹ ግዜያት አማራን የሚወክል አካል አለመኖሩ የፈጠረው ክፍተት ለመሙላት ከባድ ስራን የሚጠይቅ አድርጎታል።

ላለፉት ሁለት አስዕርተ አምታት የፖለቲካ ሃይሎቻችን ታላቅ ጋሬጣ ሆኖ የጋራ ትግሉን ሲጎዳው የቆየው የኦሮሞ የፖለቲካ ኤሊቶች  ተስፈንጣሪ አቋምና  በአንድንቱ ጎራ ግትርነት እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ ሳይሳካ ችግር ሆኖ ቆይቷል። በእንጻሩ ጎምቱ የኦሮሞ ፖልቲከኞች ወደ ጋራ ትግሉ መድረክ በመሪ ተዋናይነት  ሲመጡ የእማራው ኤሊት ማፈግፈጉ ወይም በትግሉ መድረክ በበቂ ተደራጅቶ አለመገኘቱ ሠፊ  ክፍተት እንዲኖር አድርጎታል። ይህ በአማራና በኦሮሞ ሃይሎች ዙሪያ የተፈጠረው የሃይል አሰላለፍ ሽግሽግና መዘባረቅ በአጭሩ ቋጭቶ ሕዝባችን በአደባባይ እንዳስተጋባው በጋራ ተባብረው እንዲቆሙ ማድርግ የሚቻልበት ሁኔታ ካልተፈጠረ ፤ የሕወሓት የእሳትና ጭድ ሴራ እንደገና አንሰራርቶ የገዳዩን አገዛዝ እድሜ እንዳያስቀጥል የሁለቱ ብሄር አባላት  በአንድ ሃገራዊ ንቅናቄ ውስጥ አካቶ መገኘት ከፊታችን የተደቀነ ፈተና ሆኗል።

እዚህ ላይ ሳልጠቅሰው የማላልፈው ቢኖር ፤ እንደ አንድ አማራ በታዛቢነት በንቅናቄው ምስረታ ላይ እንደመኖሬ አብዛኞቹ የቅናቄው አባል ድርጅቶች የአማራው በምሰረታው ላይ አለመኖር እንዳሳዘናቸው ለመመስከር እገደዳለሁ። ንቅናቄው እንዲፈጠር በማግባባትና በማደራደር ረገድ ድርሻ የነበራቸው ምሁራንም አማራን ለመወከል የሚችሉ ቡድኖችን በማፈላለግና በማነጋገር የሚችሉትን አድርገዋል።

መራራው ሃቅ ግን የዛሬ አራት ወር አይደለም ዛሬም እንኳ አማራን የሚያህል ሕዝብ የመወከል ቁመና ላይ የደረሰ አንድም የረባ ቡድን በፖለቲካው መድረክ ላይ አይታይም። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ከብዙ አቅጣጫዎች ድርጅት ነን በሚሉ የጽዋ ማህበር አቅም ያልዘለሉ ግለሰቦችን ማዕከል ያደረጉ እንዳንድ ስብስቦች ውሃ የማይቋጥር የአማራውን ባህልና ክብር በማይመጥን ተራ የመንደር ወሬና የስድብ ዘመቻዎች ሲያካሂዱ ታዝበናል።

____________________________

የአቻምየለህ ታምሩ ትንታኔ ስለአማራ ተጋድሎ…. ለመመልከት እዚህ ይጫኑ

____________________________

በአማራው ሕዝብ የመደራጀትና የማታገል ሂደት ውስጥ ተሳትፎ በማደረግ ረጅም ግዜ እንደመቆየቴ በዚህ ምስኪን ሕዝብ ላይ የወረድውን ማዕት በቅርብ አይቻልሁ። በየቦታው ከተፈጸመበት እጅግ የከፋ ስቃይ በላይ ዝንተ ዓለም እንደተጠላ እንዲኖር በጠላቶቹ  የተካሄደበት የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ከወገኑ ተነጥሎ በዙሪያው ካሉት እንደተቋሰለ እንዲኖር የተቀምረበት ሴራ ምን ያህል አደገኛ ለመሆኑ በቅጡ የተረዳን አይመስለኝም። እንደኔእምነት ይህን አይነት ሴጣናዊ ሴራ  ለማክሸፍ የተሻለውና   የሰለጠነው አካሄድ  በተገቢው ተደራጅቶ በተንሸዋረረ እይታ የተወናብዱትን ወገኖች ቀርቦ በመነጋገርና አብሮ በመስራት አመለካከቶቻቸውን መሞረድ ይቻል ይመስለኛል። በዚህም   ወዳጅን የማብዛትና ጠላትን የመቀንስ ስልትን በማንገብ የጠላትን ሴራ አክሽፎ የትግሉን አቅም መገንባት ይቻላል።

ስልሆንም የአማራው ሕዝብ እንግልት የሃገራችን ቀጣይ እጣ የሚያሳስባቸው ሃቀኞች ተደራጅተው አማራን በሚመጥን ደረጃ ተሰልፈው ከሌሎች ኢትዮጵያውያን የዘውግና የአንድነት ሃይሎች ጋር ግንባር በመፍጠር ሃገራዊ ትግሉን በማጎልበት በሕዝባችን ላይ የተደቀንውን አደጋ ለማክሸፍ መነሳት ለብሄሩ አባላት የሚተው ታሪካዊ ድርሻ ነው።

ሌላው በዚህ አጋጣሚ ሳይነሳ መታለፍ የሌለብት መሠረታዊ ነጥብ ፤ እያደገ የመጣው የአማራ የብሄርተኝነት አጀንዳ ፤ የመደራጅት ጥያቄና የትጥቅ ትግል በአንድነት ፖለቲካ አራማጆች ዘንድ እውቅና ለመስጠት ማንገራገሩ ለሚደረገው ሃገር የማዳን ተጋድሎ እንቅፋት መሆኑ ግንዛቤ ሊያገኝ ይገባል። አፍቃሬ አንድነቶች ሊረዱት የሚገባው ሃቅ የአማራው ሕዝብ ትግል ከብዙ ትግስትና ውጣ ውረድ በሗላ ወዶ ሳይሆን ተገዶ ላይመለስ የተጀመረና በቀላሉም ሊቀለበስ የማይችል የሕልውና ትግል በመሆኑ ጥሬ ሃቁን ተቀብሎ ለሌሎች የዘውግ ሃይሎች  በሚሠጡት ደረጃ አብሮ ለመስራት ቀናና በጎ ፈቃደኝነት ግዜው ሳይረፍድ ሊይዙ ይገባል። ከዚሁ ጋር አብሮ ሊሰመርበት የሚገባው ጉዳይ ፤ በተቆርቋሪነት ሽፋን የአማራውን ተጋድሎ በመጥለፍ አሳፋሪ የስድብና የአሉባልታ ዘመቻ የሚያካሂዱ ጨለምተኞችና ጠባቦች  የአማራን ባህልና ወግ የተከተሉ ባለመሆናቸው  ያን ኩሩና ታላቅ ሕዝብ ፈጽሞ ሊወክሉ የማይችሉ በአድራጎታችውም የምናፍር መሆኑን ለኢትዮጵያውያን ወግኖቻችን ማሳውቅ እወዳለሁ ።

እግዚያብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!!!

አሜን!!!

  1. እኔን የገረመኝ አቶ ኃይለገብርኤል አያሌው ይህችን ያረጀች ፎቶ ከየት አግኝቶ ለዚህ ጽሁፍ እንደተጠቀባት ነው። አቶ ኃይለገብርኤል አያሌው በዚች ፎቶ ሊነግረን የፈለገው እኔ ሥሠራ የነበረው ከፕ/ሮሰሮች ጋር ነው ለማለት ነው?

    አቶ ኃይለገብርኤል አያሌው የጻፈውን አርቲክል ከላይ እስከታች አነበብኩ። ሃሳቡ ጥሩ ነበር። ነገር ግን አቶ ኃይለገብርኤል አያሌው ያልገባው ነገር እሱ በእንግድነትና በታዛቢነት ተገኝቶ የመሰረተውና “የኢትዮጵያ ተስፋ ነው” የሚለው የኢትዮጵያ ሐገራዊ ንቅናቄ በበላይነት የመመራውን የግንቦት 7 ተንኮል አማራውን በሚመለከት ያለውን ፀረ-አማራ የሆነ አቋሙን ወይም አያውቀም አልይም ግንቦት 7 ምን እንደሆነ አልገባው።

    አቶ ኃይለገብርኤል አያሌው አማራው ተሎ ተደራጅቶ በግንቦት 7 የሚሾፈረውን መርከብና የኢትዮጵያ ሐገራዊ ንቅናቄ የሚባለውን ድርጅት በጁኔር ፓርትነርነት እንዲቀላቀል ያሳስባል። አይ መጃጃል!!

    አቶ ኃይለገብርኤል አያሌው እስኪ የግንቦት 7 ከፍተኛ ባልስልጣን የሆነው አቶ አበበ ቦጋለ የአማራውን መደራጀት በሚመለክት ያለውን ስማ ከዚህ በታች።

    የግንቦት 7 ከፍተኛ ባልስልጣን የሆነው አቶ አበበ ቦጋለ የአማራውን መደራጀት በሚመለክት ይህን አስተያተ የሰጠው ከኢትዮትዮብ ጋር ሰሞኑን አድርጐት በነበረው ቃለ ምልልስ ላይ ነው። ቃለ ምምልሱን ከዚህ ላይ ማዳመጥ ይቻላል።

    እኔ ከዚህ ላይ አቶ ኃይለገብርኤል አያሌው እንዲያዳምጠው የምፈልገው ከ 1 ሰዓት 05 ደቂቃ ላይ ጀምሮ ያለው ነው።

    https://youtu.be/eI7ZkWy3gyo?t=4316

    ጥያቄ (ኢትዮቱብ ጋዜጠኛ ዮሴፍ)፡- ከሰሞኑ በሻለቃ ዳዊት ወልደጊወርጊስ አማካኝነት የግንቦት 7፣ የኦሮሞ፣ የአፋር እና የሲዳማ ድርጅቶች የተካተቱበት አንድ የኢትዮጵያ ሐገራዊ ንቅናቄ የሚባል ድርጅት ተቋቁሟል። በዚህ ወቅት ሻለቃ ዳዊት ወልደጊወርጊስ አምራው በንቅናቄ ውስጥ ያልተካተተበት ምክንያት ተጠይቀው ሲመልሱ በአሁን ወቅት በአማራ ስም ብዙ የተደራጁ የፖለቲካ ድርጅቶች ስላሉ ሁሉንም መጥራት ስላልቻልን ወደፊት አመራውን የሚወክል አንድ ድርጅት ወደ ጥምረቱ እናጣለን ብለው መልስ ሰጥተዋል።

    መልስ (አቶ አበበ ቦጋለ የግንቦት 7 ከፍተኛ ባልስልጣን)፡- እኔ ሻለቃ ዳዊትን ብሆን ኖሮ በስብሰባው ላይ ብኖር ኖሮ የአማራ ተደራጅቶ ወደ ንቅናቄ ይመጣልና ይቀላቀልቅል የሚሉት ትክክል አይደለም ብየ ሻለቃ ዳዊትን እከራከራው ነበር። {የአማራውን በአማራነት መደራጀት ግንቦት 7 አይቀበለውም ማለቱ ነው።}

    አቶ ኃይለገብርኤል አያሌው አየህ ግንቦት 7 የሚለው እኮ የአማራን ተደራጅቶ እራሱን ከዘረኛም የትግሬ ወያኔ የሚደረሰበትን መከላከል አንደግፍም። እኛ አማራውን የምፍልገው በግንቦት 7 ስር ሆኖ የግንቦት 7 ስብሰባዎችን እንዲያደምቅልና ገንዘብ ስጠን ስንለው እንዲሰጠን ነው። አማራ ጀግና ስለለውና ተደራጅቶ እራሱን መምራትና ስለማይችል እኛ እየመራነው እሱ የእኛ እግረኛ ወታደር ሆኖ ነጻ የምናወጣው እኛ ነን ነው የሚልህ። ገቢቶ አቶ ኃይለገብርኤል አያሌው ???

    በአሁን ሰአት የአማራ ወጣት በአማራናቱ ተደራጅቶ ወያኔን እየተፋለመ ይገኛል። አማራው ለመደራጀት የግንቦት 7ንም ሆነ የማነንም ፈቃድ አይጠይቅም።